የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቅርቡ ምክረ ሐሳቦችን በማጠናቀር ለተግባሪ አካላት ያስተላልፋል - ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
***********************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአሁኑ ወቅት ከ4 ሺህ ተሳታፊዎች ጋር እየተካሄደ ያለው የምክክር ምዕራፍ በቀጣዮቹ አንድ እና ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ በወቅታዊ የምክክር ሂደቱ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳመላከቱት የዚህ ምዕራፍ መጠናቀቅን ተከትሎ ኮሚሽኑ ወደ ሌላ ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ይሸጋገራል።
በዚህም መሠረት ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ ተሳታፊዎች የተሰበሰቡትን ምክረ ሐሳቦች በሚገባ በማጠናቀር አቅጣጫዎችን ለሚተገብሩ የሕግ አስፈጻሚ፣ አውጪ፣ ተርጓሚ እንዲሁም ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሃይማኖት ተቋማት በይፋ እንደሚተላለፍ አስታውቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ኮሚሽኑ ምክረ ሐሳቦቹን አጠናቅሮ ከመላክ ባለፈ የሚመለከታቸው አካላት ውሳኔዎቹን በትክክል መተግበር እና አለመተግበራቸውን በየደረጃው ጥብቅ ክትትል በማድረግ ለሕዝብ የማሳወቅ ሥራ በስፋት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ የሀገራዊ ምክክር ሂደት የረጅም ጊዜ ሥራን የሚጠይቅ እንጂ በአንድ ጊዜ ተጀምሮ እንደ ማግስቱ የሚያልቅ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚህም ምክንያት ሁሉም አጀንዳዎች በአሁኑ መድረክ ሙሉ ለሙሉ እልባት ላያገኙ እንደሚችሉ እና የተወሰኑት ጊዜ ሊወስዱ ወይም በሌላ አፈታት ሊፈቱ የሚችሉበት አግባብ እንዳለም ፕሮፌሰር መስፍን አብራርተዋል።
በጥቂት ቀናት ውስጥ ይበልጥ ተስፋ ሰጪ በሆኑ ምክረ ሐሳቦች ላይ በመድረስ ለሕዝብ ለማብሰር ኮሚሽኑ እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በለሚ ታደሰ
#ebc #ethiopia #nationaldialogue #endc

4 hours ago