Logo
Getu Temesgen
የእናንተም ሳቅ ይመለስ! ...

ድምፃዊ መቅደስ ኃይሉ ከቤልጅየም 🇧🇪

ሰይፉ ፋንታሁን፦
«እሳይ ስለ አንቺ... ከሞት የተረፍሽበት አጋጣሚ አለ። የቀዶ ጥገና በጉሮሮሽ ላይ ተደርጓል?»

​መቅደስ ኃይሉ፦
«አድርጌያለሁ... አዎ። ምንድነው መሰለህ... በህይወት ውስጥ አንዳንድ ፈተናዎች ሲመጡ—ለአብነት ያህል አብዝቶ ሰውን ማመን፣ ከዛ እዚያ ላይ የሚመጣ ክህደት ወይም ደግሞ የማይጠበቅ ነገር በህይወቴ ውስጥ አጋጥሞኝ ያውቃል። እና ያ አሰናካይ ነገር... ሳቄን፣ ምቾቴን ያጣሁበት፣ ብዙ ዋጋ አስከፍሎኛል።

​በቃ እንደዚያ ዓይነት ኮንዲሽን (ሁኔታ) ላይ ሆኜ ነው ሰርጀሪ (ቀዶ ጥገና) ያደረግኩት። ሰርጀሪው ደግሞ እጅግ ለሞት የሚያደርስ ነበረ... ይሄ የጉሮሮ ኢንፌክሽን ማለት ነው።
​እና እንደዚያ ሁሉ ተደራርበው ቀኑ ያበቃ የመሰለኝ ጊዜ ነበረ። በትክክል እግዚአብሔርን ነበር የጠየቅኩት ያ ቀን እንዲያልፍ። እና በእርግጥ ለውጦኛል።

አንዳንድ ቻሌንጆች (ፈተናዎች) ለበጎ ነው የሚመጡት። ህይወትን ገጽታ ይቀይሩታል። ስለ ህይወት እንዲገባህ፣ ሁሉም ነገር እንደሚያልፍ እና እምነትህን በደንብ እግዚአብሔር ላይ እንድትጠባበቅ...

​ሁለተኛ ቻንስ እንደተሰጠኝ ሆስፒታል ውስጥ ሆኜ ነው ያመንኩት። እና ያ ሁሉ ነገር ሲያልፍ ደግሞ አምላኬን ማመስገን ፈለግኩ። በቃ ሁሉም አለፈ፣ ለበጎ ነው... እና ሳቄ ተመለሰ። ከባድ ከባድ ሰዓቶች ስለነበሩ ማለት ነው።»

​ሰይፉ ፋንታሁን፦
«የእናንተም ሳቅ ይመለስ እንግዲህ! ይሄ ሁሉ... እ?» (ለተመልካች)

https://youtu.be/C9FN3C3MZ...

6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.