Logo
SeledaPost
ከ2010 በኋላ የወጡ አብዛኛዎቹ አዋጆች በችኮላ የተዘጋጁ በመሆናቸው በተደጋጋሚ እንዲሸሻሉ መደረጋቸው በጥናት ተመላከተ

ከ2010 ዓ.ም. በኋላ የወጡ አብዛኛዎቹ አዋጆች በችኮላ የተዘጋጁ በመሆናቸው ለተደጋጋሚ ማሻሻያ መጋለጣቸውንና ከአዋጆቹ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጩ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲወጡ ምክንያት መሆናቸውን የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ጥናት አመላከተ።

ኢንስቲትዩቱ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ባካሄዳቸው አምስት ጥናቶች ላይ ባደረገው የማጽደቂያ ዓውደ ጥናት ግኝቶቹን አቅርቧል።

ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ ሁሉንም አዋጆች የሸፈነ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መረጋጋትን የሚመለከት የተለየ ፖሊሲ እንደሌለ ጠቁሟል።

ለአብነትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣው አዋጅ በተመሳሳይ ዓመት በሌላ አዋጅ መሻሻሉንና ከሁለት ዓመት በኋላም በ2015 ዓ.ም. እንደገና መሻሻሉን ጥናቱ አመላክቷል።

በተጨማሪም አንዳንድ አዋጆች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች እንዳሏቸው ጥናቱ ጠቁሟል።

በሕገ መንግሥቱ ውስጥም አሻሚ ቃላት፣ ግልጽነት የጎደላቸው አንቀጾችና አንዳንድ የሚጋጩ መርሆዎች መኖራቸውን ጥናቱ አመላክቶ፣ የሕገ መንግሥቱ ትርጓሜ ጉዳይ በጥናት እንዲታይ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

ደንቦችና መመሪያዎች በየጊዜው ሲሻሻሉም በቂ ጥናትና ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ጥናቱ አሳስቧል።ዘገባው የሪፖርተር ነው።

Seledadotio
Seledadotio
11 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.