(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለ17 ዓመታት ኢትዮጵያን ያስተዳድር ለነበረው የደርግ ሥርዓት በሰላይነት ይሠራ የነበረና፣ እሱ በሰጠው ጥቆማ ሰዎች ታስረው ድብደባና ስቃይ እንደደረሰባቸው ያመነው ግለሰብ በካናዳ የመቆየት ተጨማሪ የሕግ ዕድል አገኘ።
የ54 ዓመቱ አቶ ማስረሻ ዘውዴ ከ22 ዓመታት በፊት በስደተኝነት ወደ ካናዳ ያቀና ሲሆን፣ በሰኔ 2008 (እ.ኤ.አ) ከኢህአዴግ መንግሥት ሊደርስብኝ ከሚችል ጥቃት በሚል የጥገኝነት መብት አግኝቶ ነበር። ነገር ግን ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለመጠየቅ በሂደት ላይ እያለ፣ በሚያዝያ 2017 የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ከደርግ ሥርዓት ጋር በነበረው ግንኙነት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ተሳትፎ ምክንያት በካናዳ መኖር እንደማይችል በመወሰን ከሀገር እንዲባረር ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር።
የቶሮንቶ ፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ጆን ኖሪስ በቅርቡ ባሳለፉት የፍርድ ውሳኔ ላይ እንደተገለጸው፣ ግለሰቡ በሰኔ 1989 (እ.ኤ.አ) በ17 ዓመቱ በአዲስ አበባ ውስጥ ለአካባቢው ቀበሌ እንዲሠራ በግዴታ ተመልምሎ ነበር። ለሁለት ዓመታት ያህል የኢህአዴግ (EPRDF) እና የኤርትራ ህዝብ ነጻነት ግንባር (EPLF) አባላት ናቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦች መረጃ በመሰብሰብ ለሥርዓቱ አሳልፎ ሰጥቷል። ውሳኔው አክሎም "እሱ በጠቆመባቸው ሰዎች ላይ እስራት፣ ድብደባ እና ስቃይ ደርሶባቸዋል" ብሏል።
ኢህአዴግ በግንቦት 1991 ደርግን ከገለበጠ በኋላ፣ አቶ ማስረሻ ታስሮ ለአንድ ወር ያህል በማረፊያ ቤት ከቆየ በኋላ አምልጦ ወደ ካናዳ መግባቱ ተገልጿል።
ከካናዳ እንዲባረር ከተወሰነበት በኋላ አቶ መስረሻ በሰብዓዊነት እና ርህራሄ ምክንያቶች ውሳኔው እንዲነሳለት ጠይቆ ነበር። ለዚህም በካናዳ ያሳለፈውን መልካም ማህበራዊ ሕይወት፣ በአሜሪካ የምትገኘውን ልጁን ጥቅም፣ እንዲሁም ይህ ድርጊት የተፈጸመው በወጣትነቱ በግዴታ በተመለመለበት ወቅት መሆኑን በምክንያትነት አቅርቧል።
ሆኖም የካናዳ ኢሚግሬሽን፣ ስደተኞች እና ዜግነት (IRCC) ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ግለሰቡ ለሰራው ወንጀል ፀፀት አላሳየም፤ ይልቁንም "ምርጫ አልነበረኝም" በማለት ድርጊቱን ተከላክሏል በሚል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎት ነበር።
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከቱት ዳኛ ኖሪስ ግን የኢሚግሬሽን ኃላፊው ያሳለፈው ውሳኔ "ምክንያታዊነት የጎደለው" ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል። ዳኛው እንዳብራሩት፣ አቶ ማስረሻ ድርጊቱን ትክክል ነው ብሎ አላጸደቀም፤ የደርግ ሥርዓትም ሆነ የእሱ ድርጊት ስህተት መሆኑን አምኖ፣ ነገር ግን በወቅቱ በነበረበት የዕድሜ ክልል ምክንያት ሌላ አማራጭ እንዳልነበረው ነው ያስረዳው።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የኢሚግሬሽን ውሳኔ ሰጪው አካል የግለሰቡን መከራከሪያ በተሳሳተ መንገድ ተረድቶታል በማለት፣ አቶ መስረሻ አዳዲስ ማስረጃዎችን አቅርቦ ጉዳዩ በሌላ አዲስ የውሳኔ ሰጪ አካል በድጋሚ እንዲታይለት በማዘዝ በካናዳ የመቆየት ተጨማሪ ዕድል ሰጥቶታል።

6 hours ago