2 hours ago
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ጪሮ በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ እስራኤል መግባታቸውን አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ በእስራኤሉ አቻቸው አይዛክ ኸርዞግ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸውም ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ጪሮ ባወጡት ይፋዊ መግለጫ የሶማሊላንድ ህዝብ ላለፉት 35 ዓመታት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ጠንካራ ሀገር መገንባቱን አስታውሰዋል። "ዓለምን 'ታዩናላችሁ ወይ?' ብለን ጠየቅን፤ ለእዚህ ጥያቄያችን የመጀመሪያዋ መላሽ እስራኤል ነች" በማለት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችበትን ታሪካዊ ክስተት አድንቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህ ጉብኝት በሶማሊላንድ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን አብራርተዋል።
ለመላው የሶማሊላንድ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት የህዝባቸውን ተስፋ እና ምኞት ሰንቀው እንደተጓዙ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ በርካታ ትውልዶች ሀገሪቱን ወደዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ለማድረስ ከፍተኛ ትግል እና መስዋዕትነት መክፈላቸውን አውስተዋል። አክለውም፣ "ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በልበ ሙሉነት፣ በጥበብ እና በቁርጠኝነት እንጠቀምበታለን፤ ሁሌም ቢሆን መመሪያችን የህዝባችን እና የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ነው" ብለዋል።
ሶማሊላንድ ከእስራኤል ጋር በጓደኝነት፣ በትብብር እና በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ የጋራ የወደፊት ተስፋን ለመገንባት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል። "ዛሬ አዲስ ታሪክ እየተጻፈ ነው" ሲሉም መልዕክታቸውን አጠቃልለዋል።
ይህ የፕሬዝዳንት አብዲራህማን ጪሮ የእስራኤል ጉብኝት፣ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ይበልጥ ሊለውጠው እና ሊያጦፈው የሚችል ከባድ ክስተት ነው። እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷ እና የሀገሪቱን መሪ በይፋዊ የስራ ጉብኝት ደረጃ መቀበሏ፣ ሱማሊላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ለማግኘት ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ነው።
በአንጻሩ የሶማሊያ መንግስት ሶማሊላንድን እንደራሱ አካል አድርጎ ስለሚቆጥር እና እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና "በታሪካችን ከታዩት የጨለማ ቀናት አንዱ ነው" በማለት አጥብቆ በማውገዝ ላይ በመሆኑ፣ ይህ ጉብኝት የሞቃዲሾን ቁጣ በእጅጉ የሚቀሰቅስ እና የቀጣናውን የፖለቲካ አሰላለፍ በአዲስ መልክ የሚቀርጽ ታሪካዊ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።

3 hours ago
በቆጂ ከተማ የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫን በስኬት አጠናቀቀች
#fastmereja I ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደውን 12 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ የቦቆጂ ሩጫ በስኬት ተጠናቀቀ።
በቦቆጂ ስታድየም መነሻና መድረሻውን ባደረገው የዛሬው ውድድር በወንዶች የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን አትሌት የሆነው ማሞ ሐጫሉ ቀዳሚ ሲሆን፣ አማን ቃዲ እና አልዬ ቃሲም 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል። በሴቶች ደግሞ የአሰላ አትሌቲክስ ክለብ ተወዳዳሪዋ ማህሌት ካሳሁን ስታሸንፍ፣ ኪያ ፍስሃ እና ድርቤ ኢርኮ ተከታትለው በመግባት የ2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ተቆጣጥረዋል።
የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ’ ተከታታይ ውድድር አካል በሆነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የ15 ዓመት በታች የታዳጊዎች ሻምፕዮናም የተካሄደ ሲሆን፣ በተጨማሪም የ11 ዓመት በታች እና የህጻናት ውድድሮች ተካሂደዋል።
ከ2500 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ከአዲስ አበባ የተጓዙ ከ70 በላይ ሯጮች የተሳተፉበት ይህ ውድድር በአርሲ አባቶች ምርቃት እና በብሔራዊ መዝሙር ተጀምሯል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ ሙሐመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ቢያ፣ የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር እና የቦቆጂ ከተማ ከንቲባን ብርሃነ ነገሰ ጨምሮ በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቦታው ተገኝተዋል።

5 hours ago
በቆጂ : አትሌት ማሞ ሐጫሉ እና ማህሌት ካሳሁን የድል አክሊል ደፉ
#ethiopia | ለአምስተኛ ጊዜ መነሻና መድረሻውን በቆጂ ስታዲየም ባደረገው የ12 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወንዶች ዘርፍ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ክለብ ተወካይ የሆነው ማሞ ሐጫሉ አንደኛ በመሆን አሸንፏል።
በዚሁ ምድብ አማን ቃዲ እና አልዬ ቃሲም ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶች ምድብ በተደረገው ፉክክር የአሰላ አትሌቲክስ ክለብ አትሌት ማህሌት ካሳሁን ቀዳሚነቱን ስትይዝ፤ ኪያ ፍስሃ እና ድርቤ ኢርኮ በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።
የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር አካል በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ ዕድሜያቸው ከ11 እና ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በሁለቱም ጾታ ያደረጉት ተሳትፎ ለውድድሩ የተለየ ድምቀት ሰጥቶት አርፍዷል።
በስፍራው ተገኝተው የክብር እንግዳ የነበሩት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ ሙሐመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ ዶክተር፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ እና የበቆጂ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ብርሃኔ ነገሰ ሲሆኑ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችም ታድመውታል።
በስድስት ከተሞች ላይ የሚካሄደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር ቀጣይ መርሃ ግብሩን ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ የሚያደርግ ሲሆን የፍጻሜው ውድድር ደግሞ ሐምሌ 12 ቀን በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
#bekoji #athletics #ethiotelecom #greatethiopianrun #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

23 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የካርሎ አንቸሎቲ የጋዜጣዊ መግለጫ ሊጠናቀቅ ሲል.. ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ሁሌም በሚታወቁበት የሰከነ እና ጥልቅ በሆነ መንገድ ማንም ሊያነሳው ያልደፈረውን ጉዳይ አንስተው መናገር ጀመሩ። በግንቦት ወር መገባደጃ ላይ ብራዚል ከፓናማ ጋር ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አስቀድሞ፣ አዲሱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አንቸሎቲ እንዲህ አሉ፡...
"ሰዎች አሁን ላይ ብራዚል ኮከብ ተጫዋች የላትም ሲሉ እሰማለሁ። ምናልባት እውነት ሊሆን ይችላል። እንደ ፔሌ፣ ሮማሪዮ ወይም ሮናልዶ አይነት ተጫዋች ላይኖረን ይችላል፤ ነገር ግን የጋራ ኃላፊነት ስሜት ሊኖረን ይችላል፣ ያ ደግሞ እጅግ ኃይለኛ መሳሪያ ነው።"
ይህ የአንቸሎቲ ንግግር የብዙዎችን ቀልብ የሳበው፣ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ቪኒሽየስ ጁኒየር እስካሁን ድረስ የብሔራዊ ቡድኑ የማይነካ መሪ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ... በተግባር ግን ያ ባለመሆኑ ነው። በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በክሮኤሺያ በመለያ ምት ተሸንፈው ከወጡ ከአራት ዓመታት በኋላም.... በ25 ዓመቱ አጥቂ ላይ አሁንም በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ይህ ጥርጣሬ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ለማሳየት... በመጋቢት ወር ብራዚል በፈረንሳይ 2ለ1 መሸነፏን ተከትሎ፣ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ "ቪኒሽየስ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ መካተት ይገባዋል ወይ?" የሚል የከረረ ክርክር እስከመክፈት ደርሷል። በክለብ ደረጃ ለቪኒሽየስ እጅግ ስኬታማ ጊዜያትን ያመጣው እና ትልቅ ተጽዕኖ የፈጠረው አንቸሎቲ ብሔራዊ ቡድኑን ቢረከብም፣ "ቪኒሽየስ በሪያል ማድሪድ የሚያሳየውን ድንቅ አቋም ለምን በብሔራዊ ቡድን መድገም አቃተው?" የሚለው ጥያቄ አሁንም እንደ ጥላ እየተከተለው ነው።
በእርግጥም ቪኒሽየስ በዚህ የዓለም ዋንጫ ዑደት ውስጥ በብሔራዊ ቡድኑ ብዙ የግብ ተሳትፎ ያደረገ ተጫዋች ነው፤ ሆኖም በ28 ጨዋታዎች 7 ግቦችን እና 6 አሲስቶችን ብቻ ማስመዝገቡ ለሱ ደረጃ አነስተኛ ነው። በ2018 እና 2022 የዓለም ዋንጫዎች የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ክሌበር ዣቪየር ይህንን ሲያብራራ "በክለብ ደረጃ የምታሳየውን አቋም በብሔራዊ ቡድን መድገም እጅግ ከባድ ነው። ክለብ ውስጥ የተለየ ልምምድ፣ የተለየ የጨዋታ መንገድ እና የዕለት ተዕለት ቆይታ አለ። ግልጹ ምሳሌ የሜሲ እና የአርጀንቲና ጉዳይ ነው። ሜሲ ሁሌም ይተች ነበር፣ ሊሳካለት የቻለው በ2022 ነው። ምክንያቱም አርጀንቲና ቡድን መገንባት ስለቻለች ነው። ለተጫዋች ተገቢውን መዋቅር መፍጠር ወሳኝ ነው" ይላል።
ቪኒሽየስም ይህንን እውነታ አይክድም። በቅርቡ ለካዜ ቲቪ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ፣ "በክለብ ውስጥ በየሶስት ቀኑ አዲስ ዕድል አለ። ከ10 ጨዋታዎች ሁለቱን መጥፎ ብጫወት ማንም ብዙ አያወራም። በብሔራዊ ቡድን ግን በአንድ ጨዋታ እና በሌላኛው መካከል ያለው ጊዜ ረጅም ነው፤ ጫናውም ሁልጊዜ ከፍተኛ ነው። ሰዎች ሁሌም በምርጥ አቋሜ ላይ እንድገኝ ይጠብቃሉ። ነገር ግን ወደ ዓለም ዋንጫ ሄጄ አራት ወይም አምስት ግቦችን አግብቼ ሻምፒዮን ብንሆን፣ ታሪኩ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። ያኔ መጥፎ በተጫወትኩባቸው ጨዋታዎች ላይ እንኳን ለዓለም ዋንጫ እየተዘጋጀሁ እንደነበር አድርገው ያወራሉ" ብሏል።
ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን መጫወት ለቪኒሽየስ ቀላል ሆኖ አያውቅም። አንድ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንዳሉት፣ የ2024 የባሎን ዶር ሁለተኛ ደረጃን የያዘው ቪኒሽየስ፣ "ሁሌም ዋናው ተዋናይ የመሆን ከፍተኛ ጉጉት" ያጠቃዋል። ቪኒሽየስ በሙያ ዘመኑ ሁሉ የለመደውም ይሄንኑ የዋና ተዋናይነት ቦታ ነው።
ወደ ሁለተኛው የዓለም ዋንጫው ሲያቀና... ቪኒሽየስ 14 የንግድ ስምምነቶች ያሉት ሲሆን፣ ይህ ከማንኛውም ብራዚላዊ ተጫዋች የላቀ ነው። ከሜዳ ውጪ ይህ ሁሉ ስኬት ቢኖረውም፣ አሁንም ድረስ ኔማር ከብራዚል እግር ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ጋር ያለውን አይነት ጥልቅ ስሜታዊ ቁርኝት እና ፍቅር ማግኘት አልቻለም። ይህ ሁኔታ እጅግ አስገራሚ ነው፤ አንደኛው (ኔማር) ኮከብነቱ እያለፈ ቢሆንም አሁንም በህዝቡ ልብ ውስጥ አለ፤ ሌላኛው (ቪኒሽየስ) ደግሞ በብቃቱ ጣሪያ ላይ ቢሆንም ያንን የህዝብ ፍቅር አላገኘም።
የግብይት ባለሙያ እና የቀድሞው የኔማር አማካሪ ኤድዋርዶ ሙሳ ይህንን ሲያብራራ፣ "ቪኒሽየስ በብራዚል ደጋፊዎች ይወደዳል፤ ነገር ግን እንደ ኔማር አይደለም። ኔማር አስቀድሞ በብሔራዊ ቡድኑ ግልጽ የሆነ ታሪክ (Legacy) ሰርቷል፤ የዘመናት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ቪኒሽየስ ግን በሪያል ማድሪድ ያሳየውን ብቃት በብሔራዊ ቡድን ገና አላሳየም። ሌላው ነጥብ፣ ኔማር በሳንቶስ ቆይታው ብራዚላውያን በየሳምንቱ አስደናቂ ብቃቱን ይመለከቱ ነበር። ቪኒሽየስ ግን በፍላሜንጎ ቋሚ ተሰላፊ እንኳ ሳይሆን ነው በልጅነቱ ሀገር ለቆ የወጣው" ይላል።
ዳታፎልሃ የተሰኘው የብራዚል የምርምር ተቋም ባወጣው መረጃ፣ አሁንም 53 በመቶ የሚሆኑ ደጋፊዎች አንጋፋው ኔማር በዓለም ዋንጫው ስኳድ ውስጥ መካተቱን ይደግፋሉ።
"አሁን ሁሉም የሚያወራው ስለእኔ ነው"
የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቪኒሽየስን የብሔራዊ ቡድኑ ማዕከል ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርጓል። ባለፈው መጋቢት ወር ሮድሪጎ በጉዳት ከዓለም ዋንጫው ውጪ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ዝነኛዋን ቁጥር 10 ማልያ ለቪኒሽየስ ሰጥተውት ነበር። ዓላማው ግልጽ ነበር... ቪኒሽየስ የብራዚል ፊት እንዲሆን ማድረግ። ነገር ግን ኔማር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ሲመለስ፣ የ34 ዓመቱ የሳንቶስ አጥቂ ዳግም የቁጥር 10 ማልያውን ተረክቧል።
ምንም እንኳን ኔማር ማልያውን ቢወስድም፣...በቅርብ ጊዜያት እያስተናገደው ያለው ተደጋጋሚ የአካል ብቃት ችግር ቀድሞ ይጣልበት የነበረውን ተስፋ አደብዝዞታል። አሁን የብዙዎች አይን ያረፈው ቪኒሽየስ ላይ ነው። ብራዚል 6ኛዋን የዓለም ዋንጫ ለማንሳት በምታደርገው ጉዞ ላይ ቪኒሽየስ የጥርጣሬ ደመናን ገፎ ደምቆ መውጣት ይኖርበታል።
ቪኒሽየስም ለዚህ የትኩረት ማዕከልነት ዝግጁ መሆኑን ይናገራል። "አሁን ሁሉም የሚያወራው ስለእኔ ነው፤ ምክንያቱም በሪያል ማድሪድ አምስት ወይም ስድስት ምርጥ የውድድር ዘመናትን አሳልፌያለሁ፣ ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች ተርታም ተሰልፌያለሁ። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ተጨማሪ ኃላፊነት ያመጣል። እኔም የምፈልገው ይሄንኑ ኃላፊነት ነው። አቅሜ የት ድረስ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ምክንያቱም የኔ ጣሪያ ሁሌም በጣም ከፍተኛ ነው" በማለት ቆራጥነቱን አሳይቷል። ይህ የዓለም ዋንጫ ቪኒሽየስ የብራዚል ደጋፊዎችን ልብ ሙሉ በሙሉ የሚያሸንፍበት ይሆን? ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል።

Sponsored by
Surafel
1 day ago
ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ወሰን አቅራቢያ የሚገኘውን የግብፅ የጦር ሰፈር እንዲዘጋ አደረገች
#ethiopia | ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር በሚገናኘው የበላይኛው ናይል ክፍለ ሀገር ፓጋክ በተባለ ስፍራ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የግብፅ ወታደራዊ ማዕከል እንዲዘጋ ወስነች።
ይህ የጦር ሰፈር ግብፅ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያላትን ጥቅምና ፍላጎት ለመጠበቅ ስትጠቀምበት የነበረ ስትራቴጂያዊ የክትትል ቦታ እንደነበር ተመልክቷል።
ይህ የጁባ ውሳኔ በቀጠናው የፖለቲካና የኃይል ሚዛን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የገለጹት የፖለቲካ ምሁራን፣ ደቡብ ሱዳን በሱዳን ጦርነት ምክንያት የተስተጓጎለባትን የነዳጅ ንግድ ለመተካት ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችውን የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ የያዘችውን አቋም የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በፓጋክ ይንቀሳቀስ በነበረው በዚህ የግብፅ ወታደራዊ ጣቢያ ውስጥ የቴክኒክና የሎጂስቲክስ ባለሙያዎችን ጨምሮ ወደ 260 የሚጠጉ የግብፅ ዜጎች ይገኙበት እንደነበር ተገልጿል።
ባለፉት ሳምንታት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር አሳይቶ የነበረ ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳን የአሁኑ እርምጃ በምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ አሰላለፍ ላይ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
#southsudan #egypt #gerd #grandethiopianrenaissancedam #pagak #eastafrica #politics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ዛሬ ቀኑ ነው‼️
🎂 ዛሬ የእሱ ቀን ነው፦
በኦሊምፒክ 3 ወርቅ እና 1 ብር ሜዳሊያ
በአለም ሻምፒዮና 5 ወርቅ እና 1 ነሃስ ሜዳሊያ
በአለም ሀገር አቋራጭ 11 ወርቅ እና 1 ብር ሜዳሊያ
በአለም ሜጀር ማራቶን 2 ወርቅ 2 ብር እና 2 ነሀስ ሜዳሊያ
🎂 ዛሬ የጀግናው ቀን ነው፦
የ2004/5 የአለም የአመቱ ምርጥ አትሌት
የ2004/5 የትራክና ፊልድ ኒውስ የአመቱ ምርጥ አትሌት
የየኢኤስፒኤን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቁጥር አንድ አትሌት
ከስድስት በላይ የአለም ክብረወሰኖችን የሰበረ አትሌት
🎂 ዛሬ እለቱ ነው፦
ሱሉልታ ላይ ዘመናዊ ትራክ ያለው
አዲስ አበባ፣ ሱሉልታና አሰላ ላይ የሆቴሎች ባለቤት
ሱሉልታ ለአካባቢው ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የከፈተ
በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን ያሰራ
በበጎ አድራጎት ተግባራት ቀድሞ የሚገኝ
ታዳጊ አትሌቶችን በገንዘብና በትጥቅ የሚደግፍ
🎂 ዛሬ የእሱ ቅዳሜ ነው፦
ከቤተሰቡ 6 ፍሬዎች መካከል 2ኛ ልጅ የሆነ
3 ወንድምና 2 እህቶች ያሉት
ከባለቤቱ ዳናዊት ገ/እግዚአብሔር 2 ሴት እና 1 ወንድ ልጅ ያፈራ
🎂 ዛሬ የዝምተኛው ገዳይ ቀን ነው፦
በ27 አመታት የሩጫ አለም ቆይታው ከ200 በላይ ውድድሮችን ያደረገ፥ ብሄራዊ መዝሙራችንን በአለም ፊት ደጋግሞ ያዘመረ፥ ሰንደቃችንን ከፍ አድርጎ ያሰቀለ፥ ከአርሲ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት የተቀበለ፥ በአዲስ ስፖርት ፓርክ የክብር ሃውልት የቆመለት፥ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪክ የሰራ
🎂 ዛሬ የቀነኒ ኬኛ እለት ነው
የትዕግስት፣ የቁጭት፣ የፅናት፣ የጥረት፣ የተስፋ፣ የእልህ፣ የልፋት ከዛ የስኬት ተምሳሌት ኢትዮጵያዊው ጀግና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 6/2018 ልደቱ ነው
44 አመት ሞላው🎂
ቀነኒ ኬኛ ለኢትዮጵያ እንኳን ተወለድክላት! መልካም ልደት!
Via: ታምሩ ዓለሙ

2 days ago
ከሞት አፋፍ የተመለሰው የአለም ዋንጫው የመክፈቻ ጨዋታ የሜክሲኮ ጀግና ራኡል ሂሚኔዝ
#ethiopia | ሜክሲኳዊው ኢንተርናሽናል ከስድስት አመት በፊት በህዳር ወር 2020 በጭንቅላቱ ላይ ከባድ የሚባል አደጋን በጨዋታ ላይ አስተናግዶ ነበር።
የ35 አመቱ አጥቂ ከስድስት አመት በኋላ በአለም ዋንጫው የመክፈቻ ጨዋታ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል። የቀድሞ የዎልቭስ አጥቂ በፉልሀም ቤት ስኬታማ ቆይታን ካደረገ በኋላ የኮንትራት ውል ቆይታው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ሻምፒየን ሺፕ የወረደውን የቀድሞ ክለቡ ተቀላቅሏል።
ሂሚኔዝ ደቡብ አፍሪካ ላይ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል በ125 የብሄራዊ ቡድኑ ጨዋታ 46ኛው ነች። ከቀድሞ የማንችስትር ዩናይትድ አጥቂ ሀቪዬር ሄርናንዴዝ 52 በመቀጠል የምንግዜውም የሀገሩ ከፍተኛ አስቆጣሪነት ቦታ ላይ ተቀምጧል።
በአለም ዋንጫው በ2014 አንድ 2018 ሁለት እና 2018 ሶስት ጊዜ ከተጠባባቂ ወንበር ሲጀመር በ2026 ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረኩ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ መጀመር ችሏል።
የእግር ኳስ ህይወቱን የቀየረው አጋጣሚ
ለሜክሲኮው ክለብ አሜሪካ ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ቤንፊካ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ በውሰት ውል በ2018-19 ዎልቭስን ተቀላቅሎ ቡድኑ ሰባተኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ቦታን ይዞ ባጠናቀቀበት አመት 13 የፕሪምየር ሊግ ጎሎችን አስቆጠረ።
በ2019-20 17 ጎሎችን አስቆጠረ። ይህን ተከትሎም ዎልቭስ 30 ሚሊየን ፓውንድ የክለቡን ሪከርድ የዝውውር ዋጋ በማውጣት በቋሚነት አስፈረመው።
ህይወቱን የቀየረው አጋጣሚ በህዳር 29 2020 ተፈጠረ። ከአርሰናል ጋር በኤምሬትስ በነበረ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ከዴቪድ ልዊዝ ጋር መጋጨቱን ተከትሎ ሂሚኔዝ ራሱን ስቶ ወደቀ።
ለደቂቃዎች የቡድን አጋሮቹ አሰልጣኙ እና ቤተሰቦቹ በህይወት አለ ወይ ? የሚለው ጉዳይ አስጨንቋቸው ሲመለከቱ ነበር። ሜዳ ላይ ኦክስጅን ተደርጎለት መትረፍ ቻለ።
የማገገም ሂደቱ አዝጋሚ ነበር።ለስድስት ወራት ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን ለስምንት ወራት ደግሞ ጨዋታን ማድረግ አልቻለም።በመስከረም ወር ከጉዳቱ በኋላ የመጀመሪያ ጎሉን ዎልቭስ ተጋጣሚው ሳውዛምፕተንን አንድ ለዜሮ ሲረታ ማስቆጠር ቻለ።
እንደ ኤን ቢ ሲ ዘገባ በ2023 ፉልሀምን ተቀላቅሎ የሶስት አመት ቆይታን በማርኮስ ሲልቫ ቡድን ውስጥ አድርጓል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በምርምር እና በስትራቴጂያዊ ትንተና የተደገፈ “የተከዜ ፖለቲካ፤ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ።
የመጽሐፉ ደራሲ ዶክተር ቹቹ አለባቸው ሲሆኑ፣ ደራሲው በአማራና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ትንታኔዎችን በማቅረብ የሚታወቁ ነባር ፖለቲከኛ ናቸው፡፡
ዶክተር ቹቹ በአዲሱ ሥራቸው በተከዜ ተፋሰስ እና በወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምት ቀጠና ዙሪያ የሚታዩ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ፣ ማኅበራዊ እና የደኅንነት ጉዳዮችን በምሁራዊ መንገድ የሚተነትን መሆኑ ተጠቁሟል።
ደራሲው እንደሚገልጹት፣ የተከዜ ተፋሰስ የውኃ ምንጭ ወይም የተፈጥሮ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ከቀጠናዊ የኃይል ሚዛን፣ ከሕዝቦች ማንነት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ስትራቴጂያዊ ቀጠና ነው። መጽሐፉም ይህንን አቀራረብ በመነሻ በማድረግ የአካባቢውን ፖለቲካዊ እውነታ በጂኦ-ፖለቲካ፣ በኃይል፣ በማንነት እና በብሔራዊ ደኅንነት ማዕቀፎች አንጻር ይመረምራል።
መጽሐፉ በተለይ በ2013 ዓ.ም. በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት እንደ መነሻ በመውሰድ፣ የተከዜ ተፋሰስ በሀገሪቱ የደኅንነት አወቃቀር ውስጥ ያለውን ስልታዊ ሚና በዝርዝር ያስረዳል። ደራሲው እንደሚገልጹት፣ የተፋሰሱን ይዞታ መቆጣጠር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት፣ በውኃ ሀብት አስተዳደር እና በቀጠናዊ ግንኙነቶች ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ ያሳድራል።
በአጠቃላይ 20 ምዕራፎችን ያካተተው መጽሐፉ በአራት ዋና ክፍሎች ተዋቅሯል።
የመጀመሪያው ክፍል በጂኦ-ፖለቲካ ላይ ያተኩራል፤ የተከዜ ተፋሰስ ከኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ከዓባይ ተፋሰስ ፖለቲካ እና ከቀጠናዊ የኃይል አሰላለፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ይተነትናል።
ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይልን እንደ ፖለቲካዊ መሣሪያ በመመልከት፣ አካባቢውን መቆጣጠር ለባለቤቱ የሚሰጠውን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ተምሳሌታዊ ጥቅሞች ያብራራል። እንደ መጽሐፉ ገለጻ፣ ተከዜ ተራ የመሬት ክፍል ሳይሆን የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የሚገናኙበት የኃይል መድረክ ነው።
ሦስተኛው ክፍል በማንነት ፖለቲካ ላይ ያተኩራል። በዚህ ክፍል የብሔር ፌዴራሊዝም፣ የሥነ-ሕዝብ ለውጦች፣ የነባር እና የመጤ ትርክቶች እንዲሁም የማንነት ጥያቄዎች በታሪካዊ እና በንድፈ-ሐሳባዊ መሠረቶች ይመረመራሉ።
ደራሲው በወልቃይት፣ በጠገዴ እና በጠለምት አካባቢዎች የተፈጠሩ የማንነት ግጭቶችን እና የሕዝብ አወቃቀር ለውጦችን በሕጋዊ እና በታሪካዊ ማስረጃዎች ተደግፈው መቅረባቸውን ያስረዳሉ።
አራተኛው እና የመጨረሻው ክፍል የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮችን ያዳስሳል። ይህ ክፍል የውኃ ደኅንነት፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት፣ የውጭ ስጋቶች፣ የፌዴራላዊ አንድነት ተግዳሮቶች እና የሰላም ግንባታ አማራጮችን በስፋት ይተነትናል።
በመጨረሻም ለፖሊሲ አውጪዎች እና ለውሳኔ ሰጪዎች የሚጠቅሙ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን ያቀርባል።ከይዘቱ ባሻገር መጽሐፉ የተለያዩ የአገር ውስጥ፣ የቀጠና እና የዓለም አቀፍ ተዋናዮችን ሚና በጥልቀት የሚያብራራ መሆኑ ተገልጿል። የፌዴራል መንግሥት፣ የክልል ፖለቲካ ኃይሎች፣ ጎረቤት አገራት እና በቀጠናው ፍላጎት ያላቸው ዓለም አቀፍ ኃይሎች በተከዜ ፖለቲካ ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ በተለየ ትኩረት ቀርቧል።
ደራሲው መጽሐፉ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለታሪክ ተመራማሪዎች፣ ለደኅንነት ባለሙያዎች፣ ለዲፕሎማቶች እና ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጠቃሚ የማጣቀሻ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል።
የመጽሐፉ ዋና ዓላማም በተከዜ ተፋሰስ ዙሪያ ያሉ ውስብስብ ጉዳዮችን በምሁራዊ እይታ በማቅረብ፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ለአገራዊ አንድነት እና ለጋራ ልማት የሚረዱ የፖሊሲ አማራጮችን ማበርከት መሆኑ ተጠቅሷል።
መጽሐፉ በከፍተኛ የቋንቋ ደረጃ እና በምሁራዊ ጥልቀት የተጻፈ ነው የተባለለት ሲሆን፤ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትንተናዎች ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር ይበልጥ የተሰናሰሉ፣ መሆኑ ሥራው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ዶክተር ቹቹ አለባቸው እንዳረጋገጡት፣ “የተከዜ ፖለቲካ፤ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” የተሰኘው መጽሐፋቸው የፊታችን ዕረቡ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በገበያ ላይ ይውላል፡፡

3 days ago
የዓለም ዋንጫ እና አርሲ ሱዴ
ሰዓቱ ምሽት ነው። አየሩ በአርሲ ሱዴ ቀዝቃዛ ንፋስ ታጅቦ በናፍቆት ይሞቃል። ዛሬ ዓለም በሜክሲኮ፣ አሜሪካ እና ካናዳ አስተናጋጅነት ለሚጀመረው የዓለም ዋንጫ በዝግጅት ላይ ሳለች፣ የእኔ ትውስታ ግን ከሃያ ዓመታት በፊት ወደ ነበረችው ኩላ ከተማ ያንገላታኛል።
ያ ዘመን... ቴሌቪዥን በየቤቱ አልነበረም። የኢቲቪ እሁድ መዝናኛን ለመመልከት 50 ሳንቲም በእጅ ይዞ፣ በአንድ ትልቅ ስክሪን ፊት ለፊት ተሰባስቦ የመታየት ጣፋጭ ድካም የነበረበት ዘመን ነበር።
ኩላ፣ ያቺ ትንሽዬ የወረዳ ከተማ፤ ከመኪና ወርደህ "የእከሌ ቤት የት ነው?" ብለህ ብትጠይቅ፣ ከመንገድ ዳር የሚጫወቱት ህፃናት "እኔ ላሳይህ!" ብለው የሚሻሙልህ፣ እያንዳንዱ ነዋሪ የአንዳችንን ማንነት የሚያውቅባት የሞቀች ከተማ። በዚያን ዘመን መብራት የሚባል ነገር አልነበረም። ጨለማውን የሚገፈው የአፍወርቅ እና የዲደዓ ቪዲዮ ቤቶች ጄኔሬተር ድምፅ ብቻ ነበር። ማታ ማታ የውጪ ፊልሞችን፣ በዓል ሲመጣም የኢቲቪን ፕሮግራሞች በነጻም እያስከፈሉ ያሳዩን ነበር። በተለይ የስቅለት ለሊት ቪዲዮ... ያ ድባብ ዛሬም ድረስ በአይኔ ይደቀናል።
የሩጫ ውድድር፣ ዓለም ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ሲመጣ ደግሞ ከተማዋ ትናወጣለች! የአፍወርቅ እና የዲደዓ ቪዲዮ ቤቶች በሰው ተጨናንቀው የትንፋሽ እስራት ይፈጠራል። በስሜት መጮህ፣ በጎል መዝለል፣ በሽንፈት ማዘን... ያ ሁሉ ስሜት የጋራ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የተመልካቹ ብዛት ሲበዛ፣ የወረዳው መስተዳደር ጽ/ቤት ጄኔሬተር በማንሳት የራሱን በር ለህዝቡ ይከፍት ነበር። ያኔ፣ በአንድ ስክሪን ፊት የተሰባሰበው የኩላ ወጣት እና ታዳጊ፣ እንደ አንድ ቤተሰብ ነበር የሚሰማው።
ዛሬ ግን ዘመኑ ተቀይሯል። ዓለም ዋንጫው በቴክኖሎጂው ዓለም ተውቦ፣ በእጅ ስልክ ስክሪን እየተመለከትን ነው። ርቀቶች ተሰርዘዋል።
የዛሬይቱ ኩላ ምን ትመስል ይሆን? በየቪዲዮ ቤቱ ትከሻ ለትከሻ ተያይዘን የዓለም ዋንጫን ስንመለከት የነበርን ታዳጊዎች ዛሬ የት ደረስን? ምናልባት አንዳንዶቻችን በአሰላ፣ በአዳማ፣ በአዲስ አበባ፣ አንዳችን በውጪ አገር፣ አንዳችንም በኩላ የልጅነት ትዝታችንን እየናፈቅን በየስልካችን ስንመለከት ይሆን?
ወይ ጊዜ! ያ የጋራ ትዝታ፣ ያ የተሰባሰበ ደስታ ዛሬም በልቤ ውስጥ የከበረ ቦታ አለው። ዛሬ ዓለም ዋንጫ ሲጀመር፣ ከሁሉም በላይ የናፈቀኝ ያ በኩላ ከተማ የነበረው የቡድን መንፈስ እና ያ የዋህ የልጅነት ደስታ ነው።
የት ናችሁ የልጅነት ጓደኞቼ? ያ የኩላ ምሽት፣ ያ የዓለም ዋንጫ ወኔ ዛሬም ትዝ ይላችሁ ይሆን?

7 days ago
ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ የተባለውን ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ለመቀጠል ካይሮ ገቡ
የኔታ ሚዲያ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ወደ ግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አቅንተዋል።
ይህ ጉዞ ግብፅ እና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በኢትዮጵያ ላይ የጀመሩትን የዲፕሎማሲ እና የደህንነት ከበባ ይበልጥ ለማጥበቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹት ይገኛሉ።
የኤርትራ ማዕከላዊ መረጃ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በካይሮ ቆይታቸው ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ ጋር የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ትብብር በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ።
ይሁን እንጂ የሁለቱ መሪዎች የውይይት ማዕከል የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ የሱዳን ቀውስ እና የቀይ ባህር ደህንነት መሆናቸው ተገልጿል።
ይህም ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና ለማገዝ እና ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችውን የባህር በር የማግኘት ህጋዊ ጥረት በጋራ ለመቃወም የተወጠነ ስልታዊ ሴራ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው።
ካይሮ እና አስመራ ከዚህ ቀደም ከሞቃዲሾ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ የሶስትዮሽ ጥምረት መፍጠራቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ስብሰባም ይሄንኑ የኃይል አሰላለፍ ለማጠናከር ያለመ ነው።
በተለይም "የቀይ ባህር ደህንነት ጥበቃ የባህር ዳርቻው ባለቤት ለሆኑ ሀገራት ብቻ የተተወ መሆን አለበት" በሚል የሚያነሱት አቋም የኢትዮጵያን ስልታዊ ጥቅም እና የቀጣናውን የጋራ ተጠቃሚነት ያላገናዘበ ይልቁንም ለአካባቢው አለመረጋጋት በር የሚከፍት አካሄድ መሆኑን ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ።

9 days ago
ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
Federal Democratic Republic of Ethiopia
OFFICE OF THE PRIME MINISTER
ጋዜጣዊ መግለጫ
ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
#ethiopia | ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ አራት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበው ነበር። ይህ ቁጥር ከአንዳንድ ሀገሮች አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በላይ ነው። ይህ ምርጫ እውነተኛ ስለመሆኑ ጥያቄ ለሚያነሣ ለማንኛውም አካል ግልጽ እና የማያሻማ ምላሽ ሰጥቷል!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ52,000 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ከ50,188 በላይ የሚሆኑት በሰዓቱ ተከፍተው ቀኑን ሙሉ መራጮችን ሲያስተናግዱ እንደነበር አረጋግጧል። ከ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከ10,438 በላይ ዕጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል። ይህ በማንኛውም ሊለካ በሚችል መሥፈርት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ እና በውሳኔ አሰጣጥም ሆነ በአስተዳደራዊ ረገድ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የታየበት ኩነት ነበር።
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውን “ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሰፊው በሚደግፍ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ” ሲል ገምግሞታል።
በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት፤ በታዘቡባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የምርጫ ሳጥኖች በትክክል የታሸጉ መሆናቸውን፣ የፓርቲ ወኪሎች በሂደቱ በሙሉ መገኘታቸውን እንዲሁም ምርጫው አስደናቂ ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያሳየ መሆናቸውን አረጋግጧል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ይህንን ምርጫ “የበርካታ አዳዲስ ምዕራፎች ምርጫ” ሲል ሰይሞታል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድምፅ መስጠት ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልተመለከተ አረጋግጧል። የሲቪክ ማኅበረሰብ ታዛቢዎች ጥምረት በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ከተሰጧቸው 55 ድርጅቶች 65,299 ታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ያሠማራ ሲሆን፤ 99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያለምንም ዕንቅፋት የመታዘብ ዕድል ማግኘቱን አረጋግጧል። እነዚህ ተዓማኒነት ያላቸው ሀገራዊ እና አኅጉራዊ ተቋማት ያደረጓቸው ግምገማዎችና የሰጧቸው እውነተኛ ፍርዶች ናቸው። እነዚህ ለአፍሪካ ጥላቻ ካላቸው ወይም የአፍሪካን ዴሞክራሲ በውጫዊ መሥፈርቶች ከሚለኩ ተቋማት የተደመጡ ድምፆች አይደሉም።
አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ይህንን ምርጫ እንደ ንግሥና በዓል አድርገው ያቆሸሹት ሲሆን ውጤቱም አስቀድሞ የተወሰነ ድራማ እንደነበር አድርገው ሊያቀርቡት ሞክረዋል። እነዚህን መግለጫዎች ከአውነታው የራቁ፣ በጥናትና ትንተና ላይ ያልተመሠረቱ እንዲሁም ነፃና የታሰበበት ዲሞክራሲያዊ ምርጫቸውን በኩራት ላደረጉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክብር የማይሰጡ በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ የማይቀበላቸው መሆኑን ያረግጣል። አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ቢኖር ኖሮ፤ ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ገለልተኛ ታዛቢዎችን፣ 65,299 የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎችን ወይም 1,100 ዕውቅና የተሰጣቸውን የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችን መጋበዝ ባላስፈለገ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሀገራዊ ምርጫ ለተሳተፉ የኢትዮጵያ ዜጎች፤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ላሠማራቸው ከ350,000 በላይ ኃላፊዎች፤ ሂደቱን ለመጠበቅ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ግንባታ መጎልበት እና ለሂደቱ መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት ላረጋገጡት የአፍሪካ እና ቀጠናዊ የታዛቢ ቡድኖች ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።
ስለ ኢትዮጵያ ልማት
ኢትዮጵያውያን ግንቦት 24 2018 ዓ.ም ውሳኔያቸውን ሲያስቀምጡ፤ ሀገራቸውን በፍጹም የዲሞክራሲ ባህል ውስጥ ለማንበር ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ባላት ጸጋ ልክ የሚያስፈልጋትን ሁለንተናዊ ልማት በፍጥነት እውን የማድረግ ባህል እንዲቀጥል ሕዝባችን ተናግሯል።
ባለፉት ዓመታት የታየው እውነት እንደሚያሳየን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት የተስፋ ቃል መንግሥት አልነበረም፤ ይልቁንም በተጨባጭ የሚታዩ ውጤቶች የተመዘገቡበት ውጤት ተኮር መንግሥት ሲሆን፤ እነዚህም ውጤቶች በግልጽ የሚታዩ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን፤ ይህም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ዕድገቱ መነቃቃትን መሠረት በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ዕድገቱ ግብርናን፣ ኢንዱስትሪንና የአገልግሎት ዘርፎችን በከፍተኛ ደረጃ ያካተተ ሰፊ መሠረት ያለው ቢሆንም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ኢንዱስትሪው ለዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየመጣ ይገኛል። ይህም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭማሪና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት ያሳያል።
እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ናቸው። አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ይህም ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ አሳይቷል።
የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይህም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው። ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ጨምሮ፤ ውጫዊ ጫናዎች በነበሩበት ወቅት ነው።
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፤ ይህም የሀገሪቱን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል። ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለንግድ ተቋማትና ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመነጨ ይገኛል። ይህ ግድብ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የተደገፈ፣ በኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች የተገነባ እና ቀጣይነት የነበረውን ውጫዊ
ጫናዎችን ተቋቁሞ የተጠናቀቀ ነው። ከሃይድሮ ፓወር ጎን ለጎን፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኘውን የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና በአርሲ ዞን የሚገኘውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ በመሳሰሉ ሥራዎች ታዳሽ ኃይል አቅርቦቷን እያሰፋች ሲሆን፤ ይህም የቀጣናዊ ኢነርጂ ትብብርን እያሳደገ የብሔራዊ ኃይል አቅርቦት መረቡን የመቋቋም ዐቅም ያጠናክራል። በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ትልቁ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት አንዱ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው ተጀምሯል። እነዚህ ምኞቶች አይደሉም፤ ተጨባጭ ሐቆች ናቸው።
ግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ
በግብርናው ዘርፍ፤ የመንግሥት የምግብ ሉዓላዊነት አጀንዳ ወቅታዊ ለውጦችን ሳይሆን መዋቅራዊ ውጤቶችን እያስገኘ ቀጥሏል። በሶማሌ ክልል የጎዴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት ከአሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የተፈረመው አጋርነት የዘመኑ ጉልህ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ማረጋገጫ ነው። ፋብሪካው በዓመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያን በዓለም ትላልቅ ማዳበሪያ አምራች ሀገራት ተርታ ያሰልፋታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፤ “ይህ ፕሮጀክት በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢንዱስትሪ ዕድገትና በኢኮኖሚ ራስን መቻል ላይ የተደረገ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ነው” ብለዋል። አስተማማኝ ባልሆነና ውድ በሆነ የማዳበሪያ አቅርቦት ለረጅም ጊዜ ለተገደቡት ኢትዮጵያውያን አምራቾች የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ ፈጣንና ተጨባጭ ነው።
ከዚህ ምርጫ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት ላይ ሲገኑ የታየው ተምሳሌትነት ለቦረና ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ነበረው። ይህ ዞን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅበት ስም የሀገርን አንገት ያስደፋ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን፤ እርሱም ድርቅ ነው።
ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዝናብ መጥፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶችን የገደለ፣ ቤተሰቦች ለውኃ ፍለጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን እንዲጓዙ ያስገደደ፣ እንዲሁም በእነዚህ የግጦሽ መሬቶች ላይ ለዘመናት ራሳቸውን ችለው የኖሩ ማኅበረሰቦችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እጅ እንዲዘረጉ አድርጎ ነበር። ዓለም የሚያውቃት ቦረና እርሷ ነበረች።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንቦት ወር ጉብኝት ግን የተለየ ታሪክ አሳይቷል።
አሁን ላይ ለአርብቶ አደር ማኅበረሰቦችና ለከብቶቻቸው ንጹሕ ውኃ እያቀረቡ ያሉትን የውኃና የመስኖ መሠረተ ልማቶችን የገመገሙ ሲሆን፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት አቧራ ብቻ በነበረው መሬት ላይ የክላስተር እርሻዎችን ጎብኝተዋል፤ በያቤሎ የባህል ማዕከል መርቀዋል፤ እንዲሁም በአየር ንብረት ሁኔታዎች ምክንያት ቀድሞ ተገልሎ ለነበረው ቀጣና ዓመቱን ሙሉ ትስስር የሚፈጥር አውሮፕላን ማረፊያ መርቀው ከፍተዋል።
የአምራች ዘርፉም ተመሳሳይ የለውጥ ታሪክ አለው። በግንቦት 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ፤ መንግሥት ለአራት ዓመታት የተመዘገበውን ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ውጤቶች አቅርቧል። የአምራች ዘርፉ የግብአት አቅርቦት በዓመት 9 ሚሊዮን ቶን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል። የምርት አቅም አጠቃቀም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ማደጉን፣ እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው ፋይናንስ ከ8.1 ቢሊዮን ብር ወደ 50 ቢሊዮን ብር ማደጉን ያሳያል።
እነዚህ ስኬቶች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ኤክስፖው በተጠናቀቀ በሃያ ቀናት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ከ80 በመቶ በላይ ጥሬ ዕቃውን ከሀገር ውስጥ የሚያገኘውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት «ግራንዲዩር የሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ» ፋብሪካን በሞጆ ከተማ መርቀዋል። ቀደም ሲል በገቢ የሴራሚክ ምርቶች ላይ ጥገኛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሴራሚክ ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ሙሉ በሙሉ ለማቆምና ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ትገኛለች።
በቴክኖሎጂው ዘርፍም፤ ዘመናዊ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ በዳታ፣ በፈጠራና በዲጂታል ሥርዓቶች የሚወሰን መሆኑን በመገንዘብ፤ መንግሥት ኢትዮጵያን ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የኢንዱስትሪ 5.0 ማሕቀፎችን ቀድመው ከተገበሩ ሀገራት ተርታ እያሰለፋት ይገኛል።
የጽንፈኝነትን ፖለቲካ ውድቅ ማድረግ
በኦነግ ሸኔ ዐማጽያን በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ዒላማ ተደርገው የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከተሎ፤ የቤተሰብ እና የወዳጆቻቸውን ሕይወት ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና የቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአርሲ ዞን ለሚገኙ ወገኖቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻሉ።
እነዚህ ጥቃቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ዕድገት ለማደናቀፍ ከሚሹ አካላት፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ አማፂ ቡድኖች እና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጥላቻ ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በጥምረት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ ዓላማቸውም በኢትዮጵያ አለመረጋጋትንና የምርጫ መስተጓጎልን ለመፍጠር ሲደረግ የነበረ የጥፋት ውጥን ተከታይ ነው።
መንግሥት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ፍትሐዊና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀ ልዩ ትኩረትና ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል። በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሎች ከባዕዳን ጋር 'ፅምዶ' የሚል ቁርኝት በመፍጠር ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሰፊ የጥፋት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል፣ ሀገራዊ ምርጫው እንዳይከናወን ሰፊ ርብርብ አድርገዋል። በተጨባጭም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የዜጎችን የመምረጥ መብትና ነጻነት ለመጋፋትና ለማደናቀፍ አለን የሚሉትን የጥፋት እጅ ዘርግተዋል።
እነዚህ የጠላት ኃይሎች በመደጋገፍና በመናበብ ዐመፅና ሁከት ለማነሳሳት፣ ከተሞችን በሽብር ጥቃት ለማወክ፣ በመንገዶች የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ዒላማ አድርገው ነጥሎ ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል። እንደ ማሳያ የጦር መሣሪያ፣ ተተኳሾችንና ሌሎች ሎጀስቲክሶችን በድጋፍ በማቅረብ በደቡባዊ ትግራይ በሚገኙ አዋሳኝ የአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትንኮሳ ፈጽመዋል፣ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ወልድያ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና ሲቪሎች ላይ ዒላማ በማድረግ ያካሄደው የሽብር እንቅስቃሴና ዝግጅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ባደራጃቸው የኅቡዕ ሴሎች አማካኝነት በተመረጡ አከባቢዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም ይሄን የጥፋት ሴራ እና ድርጊት እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ሽብር ቡድን ከጽንፈኛው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር በመናበብ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴ ለማስቆምና ለማስተጓጎል ፍላጎት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተጠናከረ እርምጃ ፍላጎቱን ማሳካት አልቻለም። ቡድኑ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ እና ፍላጎቱን ማሳካት ባለመቻሉ ስስ ዒላማዎች ላይ ያተኮረ ርምጃ በመውሰድ የሃይማኖት እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማለም በአርሲ ዞን አሰኮ እና አካባቢው ጥቃት በመፈጸም ሁሉን አይነት የጥፋት ርብርብ ያደረገ ቢሆንም ሁኔታውን በመቆጣጠር ፀጥታ ኃይላችን በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
መንግሥት መሰል ሥጋቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ሲሆን፣ በምርጫው ወቅትም በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀነባበሩ ተመሳሳይ ዕቅዶችን በስኬት ማክሸፍ ችሏል። በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፤ ፍርሃትና ክፍፍልን ከሚያጎሉ የሚዲያ ዘመቻዎች ጋር በማስተሣሠር የተቀነባበረው ይህ እኩይ ተግባር፤ በመንግሥት የደኅንነት መዋቅርና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስተጓጎል ተደርጓል። ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍልን ለመዝራት የኃይል ጥቃትን እና ውድመትን እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙ አካላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ ሊወገዙ ይገባል። መሰል ተግባሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወደፊት ዕድል እንደሌላቸው ለማሳየት የተቀናጀ ብሔራዊ ምላሽ በመስጠት ወሳኝ ርምጃዎችን ይቀጥላል።
በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጸሙ አካላት፣ ድርጊታቸውን ምክንያታዊ ለማስመሰል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር ቢጠቀሙ፤ ወሳኝ ዓላማን እያሳኩ ሳይሆን ወንጀል እየፈጸሙ ነው። የፖለቲካ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደት እና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ እና ሊያገኙ የሚገባቸው ናቸው።
ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም::
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

14 days ago
የአርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ህልም በፍጹም ቅጣት ምት መክሸፍ እና አጨቃጫቂው የምሽቱ ጨዋታ
#ethiopia | በለንደን የሚገኙት አለባቸው ደሳለኝ አበሻ እንደዘገቡት የፒኤስጂ እና የአርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ፍልሚያ በዳኝነት ውሳኔዎች ታጅቦ እጅግ አነጋጋሪ በሆነ መልኩ ተጠናቋል።
በውድድር ዘመኑ በሻምፒዮንስ ሊጉ ምንም ሳይሸነፍ ለፍጻሜ የደረሰው አርሰናል መደበኛውና ተጨማሪው ሰዓት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት 4 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል። ይህ ምሽት ለአርሰናል ደጋፊዎች እጅግ ልብ ሰባሪ ነበር።
ስለ ጨዋታው የስፖርት ተንታኞችና ጋዜጠኞች የሰጧቸውን ዋና ዋና አስተያየቶች ከመመልከታችን በፊት የጨዋታውን አጠቃላይ ገጽታ በወፍ በረር እንቃኝ።
የአርሰናል የመከላከል ጥበብ እና የኮከቦች መዛል
ጨዋታው ከተጀመረበት ደቂቃ አንስቶ እስከ ፍጹም ቅጣት ምት ድረስ የአርሰናል የመከላከል ብቃት ፍጹም ሊደነቅ የሚገባው ነበር። ፒኤስጂ በዚህ የውድድር ዘመን እንደፈለገ ጎል እያዘነበ የመጣ ፈጣንና ጠንካራ የፊት መስመር ጥቃት ያለው ክለብ መሆኑ ይታወቃል።
አርሰናል ግን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ በከፍተኛ ዲሲፕሊን ተቆልፎ የፒኤስጂን አስፈሪ የማጥቃት ኃይል አምክኖ የዋለበት መንገድ ቡድኑ ምን ያህል ጠንካራ መዋቅር እንዳለው ያሳየበት ምሽት ነበር። ነገር ግን የኳስ ጨካኝነት እዚህ ላይ ነው 120 ደቂቃ ሙሉ በጥንካሬ ተከላክለህ በመጨረሻው የዕድል ፈተና በፍጹም ቅጣት ምት ዋንጫውን ማጣት በእውነትም ያማል።
በርካታ ተንታኞች በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የአሰላለፍ ውሳኔ ላይ ትኩረት አድርገዋል። በተለይም ቶማስ ፓርቴይን ወይም የተለመዱ ተከላካዮችን ከመጠቀም ይልቅ ክሪስቲያን ሞስኬራን በቀኝ ተከላካይነት መሰለፉ ስህተት እንደነበር አንስተው ተችተዋል። ፒኤስጂ በሁለተኛው አጋማሽ በክቪቻ ኳራፅኬሊያ በኩል ጫና ሲፈጥር ሞስኬራ ፍጹም ቅጣት ምት የተሰጠበትን ጥፋት በመስራቱ የጨዋታውን አቅጣጫ ቀይሮታል ብለዋል።
አርሰናል ጨዋታውን በካይ ሀቨርትዝ ቀደመ ግብ ድንቅ አጀማመር ቢያደርግም በሁለተኛው አጋማሽ እና በትርፍ ሰዓት ላይ ቡድኑ በከፍተኛ ሁኔታ መዛሉ ታይቷል። ፒኤስጂ 72 በመቶ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት የነበረው ሲሆን አርሰናል ሙሉ ጨዋታውን በመከላከል ማሳለፉ ለፍጹም ቅጣት ምት ሲደርሱ ተጫዋቾቹ ላይ የትኩረት ማጣት እንዲከሰትና የአርሰናል አስደናቂ ጥንካሬ እንዲዝል አድርጎታል።
የዳኝነት ውሳኔዎች እና የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውዝግብ
የዳኝነት ውሳኔው በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በኤክስ እና በፌስቡክ ላይ በደጋፊዎችና በስፖርት ተንታኞች መካከል እጅግ ሞቅ ያለና የአርሰናልን ደጋፊዎች ያስቆጣ አጀንዳ ሆኗል። ዳኛው አድላዊ ነበሩ በሚል ማህበራዊ ሚዲያውን እያነጋገሩ ያሉት 3 ዋና ዋና አጨቃጫቂ ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው።
በኖኒ ማዱዌኬ ላይ የተፈጸመው ጥፋት እና የቪዲዮ ረዳት ዳኛ ዝምታ ጉዳይ በትክክል ፍጹም ቅጣት ምት መሆን ነበረበት ተብሏል። የፒኤስጂው ተከላካይ ኑኖ ሜንዴስ በሳጥን ውስጥ ማዱዌኬን በግልጽ ሲገፋውና ሲያንገላታው ቢታይም የቪዲዮ ረዳት ዳኛው ዋናውን ዳኛ ሄዶ በስክሪን እንኳ እንዲያይ አለመጋበዙ ግልጽ አድሎ ነው በሚል የአርሰናል ደጋፊዎች ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። ገለልተኛ ተንታኞችም የግፊው ኃይል ለፍጹም ቅጣት ምት በቂ ባይሆን እንኳ ጉዳዩ ቢያንስ በቪዲዮ ረዳት ዳኛ መታየት እንደነበረበት ይስማማሉ።
የእርምጃዎች ድርብ መስፈርት በሁለተኛው አጋማሽ ክሪስቲያን ሞስኬራ በክቪቻ ኳራፅኬሊያ ላይ በሰራው ጥፋት ፒኤስጂ በቀላሉ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል። ብዙዎች ኳራፅኬሊያ በቀላሉ ነው የወደቀው ዳኛው ግን ለፒኤስጂ የነበራቸው አዝማሚያ ለስላሳ ስለነበር ወዲያውኑ ፍጹም ቅጣት ምት ሰጡ በማለት ይተቻሉ። በተመሳሳይ ጥፋት በአርሰናል በኩል የቀረቡት ጥያቄዎች ውድቅ መደረጋቸው የዳኛውን ሚዛናዊነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
የሰዓት ማጥፋት እርምጃዎች መዘግየትን በተመለከተ የፒኤስጂ ተጫዋቾች ሆን ብለው ሰዓት ሲያጠፉ እና ጨዋታውን ሲያደናቅፉ ዳኛው ጥብቅ እርምጃ አለመውሰዳቸው ሌላው ቅሬታ ነው። በተቃራኒው በአርሰናል ተጫዋቾች ላይ የተሰጡት የቅጣት ውሳኔዎች ፍጹም ጥብቅ እና ቡድኑን የተጫኑ ነበሩ ተብሏል።
የአርሰናል የቀድሞ ኮከብ አለን ስሚዝ ጨምሮ በርካታ ተንታኞች እንደሚስማሙት ዳኛው በጨዋታው ላይ የተጠቀሙት ድርብ መስፈርት አርሰናል ዋንጫውን እንዲያጣ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሯል።
የስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት የፍጹም ቅጣት ምት ሁሌም የዕድል ጉዳይ ነው።
በጨዋታው ላይ ኤበሬቺ ኤዜ ሳይጠቀምበት የቀረውን ኳስ ዴቪድ ራያ የኑኖ ሜንዴስን መቅጫ ምት በማዳን ተስፋ ቢመልስም በመጨረሻው ወሳኝ ምት ተከላካዩ ጋብሬል ማጋልሃሽ ኳሱን ወደ ላይ መስቀሉ ጨካኝ የሆነ የውጤት መደምደሚያ ነበር። ሆኖም ጋብሬል በጨዋታው ላይ የነበረው ድንቅ የመከላከል ብቃት ሳይዘነጋ ይህ ስህተት እሱን ብቻ ተጠያቂ ሊያደርገው እንደማይገባ ተንታኞች ይሟገታሉ።
የሳካ እና ኦዴጋርድ መቀየር ስህተት ነበር?
ሚኬል አርቴታ ቡካዮ ሳካንና ማርቲን ኦዴጋርድን በማስወጣቱ ለሽንፈቱ ምክንያት ሆኗል ለሚለው ጥያቄ ተንታኞች ሁለት ዋና ዋና እይታዎችን እያነሱ ነው።
በአንድ በኩል ሳካ እና ኦዴጋርድ የቡድኑ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በፍጹም ቅጣት ምት ወቅት እጅግ አስተማማኝ የተረጋጉና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ናቸው። እነሱ በሌሉበት ሜዳ ላይ የቀሩት ወጣት ወይም የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች እንደ ጋብሬል ማጋልሃሽ የፍጹም ቅጣት ምት የመምታት ከባድ ጫና እንዲወድቅባቸው አድርጓል። በተጨማሪም ሁለቱ ኮከቦች ሲወጡ አርሰናል ኳስን መስርቶ ማጥቃትና ፒኤስጂን ወደ ኋላ ማስጨነቅ ሙሉ በሙሉ አቆመ።
ይህም ፒኤስጂዎች ያለ ምንም ስጋት ሙሉ ኃይላቸውን ወደ አርሰናል ሳጥን እንዲልኩና በአርሰናል ተከላካዮች ላይ ከፍተኛ የአእምሮና የሰውነት ድካም እንዲፈጠር አድርጓል ይላሉ።
በሌላ በኩል ጨዋታው ወደ ትርፍ ሰዓት ሲያመራ ሳካ እና ኦዴጋርድ በፒኤስጂ ተጫዋቾች ከፍተኛ ክትትልና ጫና ስለነበረባቸው በከፍተኛ ሁኔታ ዝለው ነበር።
አርቴታ እነሱን የቀየረው የጡንቻ ጉዳት እንዳይገጥማቸውና ትኩስ ጉልበት ያላቸውን ተጫዋቾች ለምሳሌ ማዱዌኬን በማስገባት የፒኤስጂን መስመር ለመስበር በማሰብ ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ።
ሆኖም አርቴታ ጨዋታውን በ120 ደቂቃ ውስጥ ለመጨረስ ወይም በመከላከል ለመጨረስ አስቦ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ጨዋታው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ማምራቱ የማይቀር መሆኑን እያወቀ ሁለቱን ምርጥ የቅጣት ምት መቺዎቹን እና የቡድኑን የልብ ትርታዎች ቀይሮ ማስወጣቱ በታክቲክ ደረጃ ትልቅ ስህተት እንደነበር ይነገራል።
ይህ የሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት ለአርሰናል እና ለደጋፊዎቹ እጅግ መራራ ምሽት ቢሆንም ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በማንሳቱ ትልቅ ስኬት ማስመዝገቡ አይዘነጋም።
ቡድኑ ካሳየው አስደናቂ ጥንካሬ እና መዋቅር አንፃር በቀጣይ ዓመታት ይበልጥ ጠንክሮ እና ተምሮበት እንደሚመለስ የስፖርት ተንታኞች ትልቅ ተስፋ ጥለውበታል።
አለባቸው ደሳለኝ ለንደን 🇬🇧
#arsenal #psg #championsleague #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ፔዤ ዳግም ሻምፒዮን
መድፉ በክብር ተሸንፏል ! OHO BIG GABI ...
እግር ኳስ ከቡዳፔስት በስሜት ሀዘንና ደስታ ቅፅበታዊ ልውውጦች መሃል ! Champions League Classic .
በኤፍሬም የማነ
#ethiopia | በእነዛ ሽርፍራፊ ሰከንዶች የፔናሊቲ ድራማ ራያ ኤዜን አዳነ ። ራያ አርሰናል አዳነ ። መድፉ ሞቶ ተነሳ ። የፔናሊቲው ድራማ ከቡዳፔስት ቀጠለ ። ከሜንዴዝ መሳት በኋላ ፔዤ ብልጫውን ወሰደ ። የመድፉ ለ120 ደቂቃ የዘለቀ የጀግንነት ተጋድሎ በBig Gabi አምስተኛዋ ወሳኝ ፔናሊቲ ላይ ተወሰነ ። መድፈኞቹ ተጨነቁ ። ዓለም በስሜት ከፍ ዝቅ አለ ። የመድፉ የድል አባት አርሴን ቬንገር ከማጋሊሽ ወሳኝ ፔናሊቲ ጋር በጭንቅ ታጥፈው ታዩ ። ንጉስ ኦነሪ በCBS ስቱዱዮ አርሰናል ከተባለ እናት ሀገሩ ጋር በስሜት ተንቆራጠጠ ። ማጋሊሽ በቀጥታ ፔናሊቲ ተመቶበት ካላዳነው የፔዤው በረኛ ሳፋኖቭ ተፈጠጠ ። ፀንቶ ለአርሰናል ድል ሲዋደቅ የዋለው ብራዚላዊ የመድፉ ግድግዳ ወሳኝ ፔናሊቲ በዛች አጋጣሚ ከቡዳፔስት ሰማይ ስር በረረች ። ፔዤ ሻምፒዮን ሆነ ። አርሰናል በጀግንነት ተዋድቆ ተሸነፈ ። እግር ኳስ ከቡዳፔስት በስሜት ሀዘንና ደስታ ቅፅበታዊ ልውውጦች ተሞላች ። የፀናው የመድፉ የድል ምኞት ትጋት በመጨረሻ ከብቃት ባሻገር እንደ ሎተሪም በሆነው ፔናሊቲ ታጠፈ ። አርሰናል ሁለት ወደ ፎሪና ሰማይ በለቀቃቸው ፔናሊቲዎች አማካኝነት የህይወት ዘመን ወደር አልባው የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ህልሙን ሳያሳካ ቀረ ። መድፉ በክብር ተሸነፈ ። መድፉ በክብር ተዋድቆ ተረታ ። ከፑሽካሽ አሬና እግር ኳስ በሁለቱ ኋያላን ፍጥጫ ለ120 ደቂቃ ዘልቆ ለፔናሊቲ በተዳረገ የህይወት ገፅ ተመሠለ ። ስሜት ከፍ አለ ። ተስፋ ነገሰ ። መውጣት መውረድ መውደቅ መነሳት ፀፀት ደስታ ቁጭት እንባ ከቡዳፔስት ተፈራረቁ ። ማግኘት ማጣት መሳት ማዳን በሚሊዮኖች ላይ በእነዛ የፔናሊቲ ቅፅበቶች ተፈራረቁ ። በመጨረሻም 120 ደቂቃዎች ተሻግሮ ለፔናሊቲ የደረሰው ድራማ ፓሬዚያኑን ዳግም አነገሰ ። አርሰናል በክብር እጅ የሰጠው አሳዛኙ ተሸናፊ ሆነ ። እግር ኳስ ኳስ ይዞ መሽከርከር ብቻ እንዳልሆነ መድፉ በፀና ተደናቂ የመከላከል ቅርፁ አረጋገጠ ።
በላቀ የጨዋታ ዝግጅነት የዳበረው በታክቲክ የታጠረው ትንቅንቅ የዘመናዊው እግር ኳስ ሁለት የእግር ኳስ ቀለሞችን አሳየ ። እግር ኳስ በመድፉ የመከላከል ከፍታ ውስጥ የፔዤ የማጥቃት አቅምን አፈዘዘ ። ፓሬዚያኑ ከመድፉ ካቴና ፊት ተቆልፈው ዋሉ ። ድራማ ከቡዳፔስት ክዋክብቶቹ ከሜዳው ለድል ተዋደቁ ። ከመድፉ ግድግዳ ፊት እንደወትሮው እንደልቡ መንፈላሰስ ለፓሬዚያኑ ብርቅም ሆነ ። የመድፉ ባስ ከፓሬዚያኑ ፊት ፀንቶ ቆመ ። አርቴታ ከመጀመሪያ ቋሚ አሰላለፉ አንስቶ የመረጠው የጨዋታ ስትራቴጂው በአግባቡ ሲያዋጣው ታየ ። የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን አውራ ጆዜን መሰለ ። አርሰናል የጣሊያንን አዙሪ ካቴናን አስናቀ ። ፔዤ እንደወትሮው መንቀሳቀስ ተሳነው ። ፓሬዚያኑ የአቻ ጎል ለማግኘት ያውም በፔናሊቲ 65 ደቂቃ ታተሩ ። የመድፉ የደረጀ የመከላከል ቅርፅ የፔዤ የማጥቃት ጥራትን ለአፋልጉኝ ማስታወቂያ አበቃ ። የመድፉ ካቴና ጀገነ ። የመጫወቺያ ቦታ የተነፈጉት የፔዤ ኮኮቦች እንደ ወትሮው ማንፀባረቅ ተሳናቸው ። ዘንድሮ ብቻ በቻምፒዮንስ ሊጉ 44 ጎል አዝንቦ ለቡዳፔስት ፍፃሜ የደረሰው ፔዤ ከመድፉ ግድግዳ ፊት ህይወት ከበደው ። ተጋጣሚዎቹ ላይ እንደ ልቡ በጎሎቹ የሚዘንጠው ፔዤ የአቻዋን ጎል በዴምቤሌ ፔናሊቲ አገኘ ። ፔዤ 75 በመቶ ኳስ ተቆጣጥሮ በዘለቀው ጨዋታ የመድፉ የዳበረ አጥርን መጣስም ተሳነው ። ለጨዋታው ቀልብ ገዢ ፉክክር የሚያዋጣውን የጨዋታ ቅኝት በቡድኑ ዓመቱን ሙሉ በነበረ ጥንካሬ ላይ ተመርኩዞ ተግባራዊ ያደረገው አርቴታ የፓሬዚያኑ የተለመደ ህበረ ትርዒትን አከሰመ ። ፔዤ 21 ወደ ጎል ሞክሮ 4 ብቻ ታርጌታቸውን የጠበቁ ሆኑ ። የመድፉ የፀና የLow Block ኮንክሪትን ጥሶ ማለፍ ለእነ ክቫራ ዴምቤሌ ዱዌ ብርቅ ሆነ ። ተቀይሮ የገባው ብራኮላ የተሻለ ራያን ቀረበ ። ያለ ኳስ ቁጥጥር ተጋጣሚው አርሰናል በጨዋታ መሃል ያለውን ጥንካሬ ከጨዋታው በፊትም የመሰከረው ሉዊስ ኤኔሪኬ ምርጡ ስብስቡ ከመድፉ ኮንክሪት ፊት ከመቼውም ግዜ በላይ የማጥቃት ሀሳቦች ተፋልሰው ታዩ ።
የተፈራው ክቫራ በማስኬራ ተቆለፈ ። ዱዌ ዴምቤሌ ፈዘዙ ። የፔዤ ፍሬ አልባ የኳስ ቁጥጥር ፉርሽ ሆነ ። መከላከል ጀገነ ። አርሰናል ፔዤን አሰረ ። ከሰሜን ለንደን ቡዳፔስት የደረሰው የመድፉ አውቶብስም በjose park the Bus ስታይል ሉዊስ ኤኔሪኬን አቁነጠነጠ ። የመድፉ እንደ አለት የጠነከሩ የፀኑ አጥሮች የሆኑት ማጋሊሽና ሳሊባ በራይስ እና ስኬሊ ሽፋን ለፓሬዚያኑ ፈተና ሆነ ። ጉዳት ያጋጠመው ሄንካፔ ቅያሪ ቀድሞ በጨረሰው አርቴታ እስከመጨረሻው በጀግንነት ተሰዋ ። እንደ ጨዋታ ዕቅዱ ጥሩ አጀማመሩ የመጨረሻዎቹ የጨዋታ ሂደቶች ላይ ጠንቃቃው አርቴታ በቁልፍ የጨዋታው ቅያሪ ውሳኔዎቹ ተፈተነ ። አርቴታ ከ120 ደቂቃ በኋላ ተጋድሎ በኋላ ከመጨረሻው የፔናሊቲ መቺ ምርጫ ውሳኔዎቹ የመዱፉ የክብር ሽንፈት አይረሴው ቁጭት ሆኑ ። ከፔናሊቲው ድራማ በፊት በተጨማሪው 30 ደቂቃ ዴክላን ራይስን ጨርቅ ያስጣለች ማይክ አርቴታን ያሳበደች የሜንዴዝ ማዱኬ ፋወል ከVAR የዳኛው ዕይታ መታለፍ ጋር ሌላው አነጋጋሪም ነበር ። ይህ የመድፉ አርሰናል ወርቃማው የውድድር ዓመት መልክ ነው ። ይህ የፓሬዚያኑ እንደ ልብ ከኳስ ጋር የሚፈነጩ ክዋክብቶችን ከጎሉ ፊት ቆልፎ የዋለው የመድፉ ካቴና ታላቁ ተጋድሎ ነው ። ይህ አርሰናል ወደ ፎሪ እና ወደ ሰማይ በላካቸው ሁለት ፔናሊቲዎች ፀፀት ታጅቦ በጀግንነት እስከ መጨረሻው ተዋድቆ እጅ የሰጠበት የመድፉ የህይወት ከፍታ ጉዞ አሳዛኙ ሌላኛው የቻምፒየንስ ሊግ ምሽት የክብር ገፁ ነው ። ፔዤ ሻምፒዮን ። ናስር አልከሊፋ የፔዤው ቢሊየነር አባት ሉዊስ ኤኔሪኬ ቀምሞ ባወቀረው ቡድናቸው እንደፎከሩት ሁለተኛውን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በተከታታይ ድል ነስተዋል ። የፈረንሳይ ሊግም ምስጋና ለፓሬዚያኑ እያለ በድጋሜ በትልቁ የክዋክብቶች መድረክ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ላይ ዳግም ነግሷል ።

26 days ago
የዋንጫው ባለቤት ዛሬ ይታወቃል ወይስ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤት የሚሆነውን ክለብ ሊወስን የሚችለው የቦርንማውዝ እና ማንቼስተር ሲቲ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የምሽቱን ጨዋታ አቻ ካጠናቀቀ ወይም ሽንፈት ካስተናገደ አርሰናል አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2025/26 ሻምፒዮን መሆኑን ዛሬ ምሽት ያረጋግጣል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የዋንጫ ተስፋውን እስከ መጨረሻው ሳምንት ለማስቀጠል የምሽቱን ጨዋታ የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብቷል፡፡
በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሲቲ ጋር እንደሚለያዩ የሚጠበቁት ፔፕ ጋርዲዮላ በምሽቱ ጨዋታ የሚጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል፡፡
ጂያንሉጂ ዶናሩማ፣ ማቲያስ ኑኔዝ፣ ኩሳኖቭ፣ ማርክ ጉሂ፣ ኒኮ ኦ'ሬሊ፣ ሮድሪ፣ ኮቫቺች፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ሴሜንዮ፣ ዶኩ እና ሀላንድ በቋሚነት ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡
ባለሜዳው ክለብ በርንማውዝ ፔትሮቪች፣ ትሩፌርት፣ ሴኔሲ፣ ስኮት፣ ኢቫኒልሰን፣ አዳምስ፣ ስሚዝ፣ ታቨርኔር፣ ክሩፒ ጁኒየር፣ ሂል እና ራያንን በቋሚ አሰላለፍ ይጠቀማል፡፡
ጨዋታው ምሽት 3 ሰዓት ከ30 የሚጀመር ሲሆን፥ የ47 ዓመቱ አንቶኒ ቴይለር በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡
በሌላ ጨዋታ በለንደን ደርቢ ቼልሲ በሊጉ ለመቆየት 1 ነጥብ የሚፈልገውን ቶተንሃም ሆትስፐር ምሽት 4 ሰዓት ከ15 በስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል፡፡

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ የሆኑት የባህር ኃይል አድሚራል ብራድ ኩፐር፣ አሜሪካ በየካቲት ወር መገባደጃ ላይ የጀመረችው "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ" የተሰኘው ወታደራዊ ዘመቻ የኢራንን ወታደራዊ አቅም እና በቀጠናው ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ሙሉ በሙሉ ማዳከሙን አስታወቁ። አዛዡ ይህንን የተናገሩት በዋሽንግተን ዲሲ ለሴኔቱ የጦር ኃይሎች ኮሚቴ ስለ 2027 የበጀት ዓመት ጥያቄ እና በቀጠናው ስላለው ወታደራዊ አሰላለፍ ምስክርነት በሰጡበት ወቅት ነው።
አዛዡ በምስክርነታቸው እንዳብራሩት፣ የአሜሪካ ኃይሎች ከ40 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወታደራዊ ግባቸውን በማሳካት የኢራንን የመከላከል አቅም ክፉኛ መትተዋል። በተለይም ባለፈው ዓመት ሚያዝያ እና ጥቅምት ወራት በእስራኤል ላይ ታይቶ የማያውቅ የጅምላ ሚሳኤል ጥቃት የፈጸመችው ኢራን፣ አሁን ላይ ይህን መሰል ጥቃት የመፈጸም አቅሟ በአሜሪካ ኃይሎች ተወግዷል። አድሚራል ኩፐር አክለውም፣ የኢራን የድሮን፣ የሚሳኤል እና የባህር ኃይል መከላከያ ኢንዱስትሪ በ90 በመቶ መውደሙን እና ቀሪ አቅሟ 10 በመቶ ብቻ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኢራን የባህር ኃይል ይህንን ከባድ ውድመት ተቋቁሞ አቅሙን መልሶ ለመገንባት ከ5 እስከ 10 ዓመታት ሊወስድበት እንደሚችልም ወታደራዊ ግምገማቸውን አቅርበዋል።
ይህ ወታደራዊ እርምጃ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን መቼም ቢሆን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት ያስቀመጡትን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ከዚህም ባሻገር ኢራን በቀጠናው ለሚገኙ አሸባሪ ቡድኖች ስታደርግ የነበረው ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ ክፉኛ ተመቷል። ለዓመታት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እና የጦር መሣሪያ ሲቀርብላቸው የነበሩት እንደ ሐማስ፣ ሕዝቦላህ እና ሁቲ ያሉ የተኪ ተዋጊ (Proxy) ቡድኖች፣ በዘመቻው ምክንያት ከኢራን የሚያገኙት ማንኛውም ዓይነት ትጥቅም ሆነ ሃብት መቋረጡን አዛዡ አብራርተዋል። ይህ ድል በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ለወራት የተደረገ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ እና የዓመታት ልምድ ውጤት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
"ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ" የአሜሪካን ወታደራዊ የበላይነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ካሉ አጋር አገራት ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩ ተገልጿል። አድሚራል ኩፐር እንደገለጹት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ባህሬን፣ ኩዌት፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር ጎን ለጎን በመቆም ራሳቸውንም ሆነ አሜሪካውያንን በመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በተጨማሪም ይህ ግዙፍ ወታደራዊ ስኬት ያለ ዮርዳኖስ እና እስራኤል የጠበቀ አጋርነት ሊሳካ እንደማይችል በመግለጽ፣ ዘመቻው በቀጠናው ያለውን የጸጥታ ትብብር ምን ያህል እንዳጠናከረው መስክረዋል።

የመደመር መንግሥት መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም በነገው ዕለት ይመረቃል
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው ‘የመደመር መንግሥት’ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም በነገው ዕለት በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ ይመረቃል።
በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) እንዳሉት፤ መጽሐፉ በዋነኛነት በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ሁሉም ዓረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት፣ ሕዝቦች እና መንግሥታት በመደመር እሳቤ የምትመራዋን ኢትዮጵያን በጥልቀት የማስተዋወቅ ዓላማ አለው።
መጽሐፉ በዓረቡ ዓለም የኢትዮጵያን ፍላጎቶች እና ብሔራዊ ጥቅሞች የበለጠ ለማስጠበቅ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ አድማሷን ለማስፋት የምትጠቀምበትን የጂኦ-ስትራቴጂክ እና የጂኦ-ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ሚዛኑ የተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ካላት ፍላጎት አንጻር መጽሐፉ መተርጎሙን አስረድተዋል።
የመደመርን ፍልስፍና ይበልጥ ለቀጣናው ሀገራት ቅርብ በሆነ ቋንቋ ይዞ መምጣት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ዕይታ እንደሚያሳይ ጠቁመዋል።
በመጽሐፉ ምረቃ መርሐ ግብር ላይ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ንጉሣዊ ቤተሰቦች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች እንደሚገኙ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ጠቁሟል።
FBC

የዲያቆን ዘካርያስ ሸዋረጋን ሕይወት ለመታደግ የቀረበ አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ
#ethiopia | በአሰላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዲያቆንነት ሲያገለግል የቆየው ብርቱው ወጣት ዘካርያስ ሸዋረጋ በድንገተኛ የኩላሊት ህመም ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርጓል።
በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ኩላሊቶቹ ሥራ በማቆማቸው ሕይወቱን ለማዳን ብቸኛው መፍትሔ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ መሆኑ በሕክምና ተረጋግጧል።
ይህንን የአገልጋይ ወንድማችንን ሕይወት ለመታደግና ወደ ቀደመ አገልግሎቱ እንዲመለስ ለማድረግ ከግንቦት 5 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ተዘጋጅቷል።
በእነዚህ ቀናት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ አንጋፋና ተተኪ መዘምራን በሚሳተፉበት የቲክቶክ የቀጥታ ሥርጭት (TikTok Live) የዝማሬና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ይካሄዳል።
በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያንና ክርስቲያኖች በዚህ መንፈሳዊ ጥሪ ላይ በመገኘት የበኩላችሁን የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉ በታላቅ ትህትና ተጠይቃችኋል።
ከመርኃ ግብሩ በፊትም ቢሆን ከታች በተጠቀሱት የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ድጋፋችሁን መላክ ትችላላችሁ።
የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች (በዘካርያስ ሸዋረጋ ስም የተከፈቱ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000375284603
ቴሌብር 0913071985
አዋሽ ባንክ 013201754987100
አቢሲኒያ ባንክ 114747726
ዳሽን ባንክ 5532308128011
#health #charity #orthodoxtewahedo #support #asella #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

"እማዬ የሁሉ እናት" በእናቶች ቀን እማዬን እናስታውስ
#fastmereja I የደጋግ እጆች መገለጫ፣ የመልካምነት ተምሳሌት፣ የአገር ወዳድነት አብነት፣ የሴቶች መቻል ማመሳከሪያ፣ የመልካም እናትነት ውል፣ የማሕበረሰብ ማስተሳሰሪያ ገመድ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ሞዴል አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ (ሴንተራል)።
የሆሳዕናው ሚካዔል በአክናፉ አጅቦ፣ ከፈጣሪ የተለገሰችውን አንዲት ሕፃን "እንካችሁ! ብሎ ለዝህች ቅድስት አገር አስረከበ፡፡ በሀድያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ፣ በራሱ ስም በተሰየመለት አባባቢ (ሚካዔል ሰፈር)፣ በሰኔ 21 (ዕለተ-ማርያም) 1948 ዓ.ም. የበረከት ምሳሌ ናት፤ ሴት ስትወለድ፣ የፀጋ ማሳያናት፤ እንስት በቤተሰብ ስትበቅል። የኃላፊነት ቁነጮ ናት፤ እናት በማሕበረሰብ ውስጥ ስትገኝ። ይህንን ደስታ፣ ይንን ፍስሃ፣ ይህን ሃሴት፣ ሴትን የወለደ፣ ያሳደገ፣ አብሮ የኖረ፣ ጣዕሟን የተረዳ ያውቀዋል። በዚህ ቤተሰብ፣ በዚህ ቀዬ፣ በዚህ መንደር፣ አማረች የተባለች ሕፃን ስትወለድ የሆነውም ይህ እውነት፣ ይህ ደስታ፣ ይህ ፍንደቃ ነው። ማን ያውቃል፤ የህፃኗ መዳረሻ መልካም ገዶች ተገልፆላቸውስ ቢሆን!
ማንም ልጅ ሲወልድ ተስፋ ያደርጋል፤ ማንም ፍሬ ሲያገኝ ፈጣሪውን ያመሰግናል፤ ፍሬው በእግዚአብሔር መንገድ ሲፀድቅለት ደግሞ የበለጠ ልቡን በሀሴት ይሞላል። አድጎ ተመንድጎ፣ ተምሮ ሰርቶ፣ አግብቶ ወልዶ፣ የልፋት ጥሪቱን በሃብት፣ የሰው መሆን በረከቱን በልጅና ልጅ ልጆች፣ የሕዝብ ፍቅርን፣ ባለው ደግነትና ተግባቦት ሲታገዝ ምርጥ የቢዝነስ ፈጣሪ ደግሞ፣ ከሰውነት አልፎ አንድ ግለሰብ አገር ይሆናል፡፡ ባለታሪኳ በግል ተናጠል ከማውሳት ይልቅ፣ በአገርነት ቢነገርላቸው የሚያንስባቸው እንጂ፣ አይበዛባቸውም።
እኝህ የአገርነት ተምሳሌት የሆኑት እናት የሀዋሳዋ ወ/ሮ አማረች ሴንትራል ናቸው፡፡
በተወለዱበት ሆሳዕና ከተማ አድገው፣ መደበኛ ትምህርታቸውን በዛው ከተማ ተከታትለዋል፡፡ በለጋ እድሜ፣ ገና 14 ዓመት ሲሆናቸው፣ ትዳርን “ሀ” ብለው የሚቋደሱበትን ዕድል ሕይወት አዘጋጀችላቸው፡፡ በዚሁም፣ ነፍሳቸውን ፈጣሪ በአፀደ-ገነት ያቆይልንና፣ ለሻለቃ ወልደሰንበት ዘበርጋ ማሩ ለተባሉ ኩሩ ወታደር፣ በ1962 ዓ.ም. ተዳሩ፣ ፈጣሪም ትዳራቸውን ባርኮ፣ ኑሯቸውን ጎብኝቶ፣ የፍቅራቸውን ማሰሪያ አራት ወንድና አንድ ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡
የሰው ልጅ ቋሚ እግር እንጂ፣ ቋሚ አገር የለውም፤” እንደሚባለው፣ ከትዳር ምስረታ በኋላ፣ ከባለቤታቸው ሻምበል ወልደሰንበት ዘበርጋ በርካታ ክፍላተ-አገር ውስጥ ለመኖር ተገደዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሻምበል ወልደሰንበት አገራቸውን የሚጠብቁ ቋሚ ቦታ ያልተወሰነላቸው ጀግና ወታደር በመሆናቸው ነው። በመሆኑም፣ በአዲስ አበባ፣ በአርሲ (አሰላ እና ጢቾ)፣ በጠረፍ አገር ሞያሌ፣ በመጨረሻም በሃዋሳ ከተማ በማድረግ አሳርገዋል።
ባላቤታቸው በግዳጅ ወደ ሰሜን ዕዝ በተላኩበት ግዜ፣ ወ/ሮ አማረች ቀደም ሲል ከእርሳቸው ጋር ሲኖሩ ከነበሩበት የፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ፣ ወደ ከፍተኛ 2 (በአሁኑ ሀይቅ ዳር ከ/ከተማ)፣ ቀበሌ 05 (አሁን ጉዱማሌ ቀበሌ) በመዛወር፣ በተሰጣቸው የቀበሌ ቤት ውስጥ በወር 24 ብር እየከፈሉ መኖር ጀመሩ።
በወታደራዊ ግዳጅ ላይ የነበሩት ጀግና ባለቤታቸው ሻምበል ወልደሰንበት ዘበርጋ በግንባር መሰዋታቸውን የተረዱት በዚሁ መኖሪያቸው ነበር። ከዚህ በኋላ፣ ልጆችን ለብቻ ማሳደግ፣ እነሱ የሰው እጅ እንዳያዩ ማድረግ፣ ጤንነታቸውን መንከባከብ፣ ማስተማርና ማብቃት የሚለው መራር እውነት እንደተጋፈጠባቸው ሲያረጋግጡ፤ ፈታኙን ሕይወት ፊት ለፊት ለመግጠም አልሰነፉም፤ ቆርጠው ተነሱ።
ይህንን ሕይወት መጋፈጥ በወቅቱ በቂ ዝግጅት ላላደረገች እንስት ምንያህል ፈታኝ እንደሚሆን መገንዘብ አይከብድም፤ በሆነው ከማዘን ይልቅ፣ የተሰበረን ልብ የሚጠግንና የሟችንም ሕልም የሚያሻግረው መፅናናት፣ መበርታት ጠንክሮ መስራት መሆኑን ያመኑት ወ/ሮ አማረች፣ በቀጥታ ያደረጉት እጃቸው ላይ ያለውን ጥበብ በመጠቀም ወደኑሮ መለወጥ ነበር።
ብዙዎች የወ/ሮ አማረችን ስም ሲጠሩ የወላጅ አባታቸውን ያህል የሚያስከትሉት መጠሪያ ነው "እሜዬ የሁሉ እናት" ይህ ልዩ መገለጫ የተሰጣቸው ልዩ በሆነ ስብዕናቸው ነው ። ያለ አንዳች ልዩነት፣ የሩቅ ሰው፣ የቅርብ ሳይሉ ሁሉንም እንደ እናት ስለሚወዱና ለሰው ያላቸው እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡
ወ/ሮ አማረች በየዓመቱ 10 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዘመዶቻቸውን እና ሌሎች ሰዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ወጪ ችለው ያስተምራሉ፡፡ እስካሁን ከ300 በላይ ተማሪዎች ተመርቀው ወደ ስራ ተሰማርተዋል።
ወ/ሮ አማረች በየአመቱ የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና ህብረተሰብ የትምህርት ቁሳቁስ ወጪ ይሸፍናሉ።
በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ 5 ትምህርት ቤቶች በየአመቱ የተለያዩ በዓላትን በሚያከብሩበት ወቅት የመስተንግዶ ወጪ ይሸፍኑ ነበር።
ወላጅ አልባ ህፃናትን እና አረጋውያንን የመንከባከብ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ድጋፍ ያደርጉ ነበር።
ይህ የተጠቀሰው ከብዙው በጥቂቱ ነው ። ወ/ሮ አማረች "እማዬ የሁሉ እናት" የተባሉበት መገለጫቸው ከዚህም በላይ ነው።

የመድፈኞቹ የዋንጫ ጉዞ ..
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ባደረገው ተጠባቂ ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።
የውድድር ዘመኑ ማጠቃለያ ላይ መደረሱ ጨዋታውን ለሁለቱም ክለቦች እጅግ ወሳኝና ስህተት የማይታገስ አድርጎት አልፏል።
አርሰናል ለዋንጫ በሚያደርገው ብርቱ ፉክክር ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ የዛሬውን ጨዋታ የገጠመበት የአሰላለፍ ምርጫና በጨዋታው ወቅት ያደረጋቸው ፈጣን ቅያሬዎች ካለፉት ስህተቶቹ መማሩን ያሳየበት ሆኗል።
መድፈኞቹ እንደ ቡድን ከሜዳ ውጪ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ለማምጣት ከሚፈጠር ጫና ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጭንቀት ተቆጣጥሮ መጫወት መቻላቸው ትልቅ መሻሻል የታየበት ነው።
ባለሜዳዎቹ ዌስትሃሞች ጠንካራ የመከላከል መዋቅር ይዘው ቢገቡም የአርሰናል የፈጠራ ብቃት በተለይም ማርቲን ኦዴጋርድ ተቀይሮ ከገባ በኋላ ያንን አጥር ሰብሮ ለመውጣት ያደረገው ጥረት የሚደነቅ ነበር።
ምንም እንኳን ዌስትሃሞች በመልሶ ማጥቃት አደገኛ ለመሆን ቢሞክሩም የአርሰናል የተከላካይ መስመር ግን በንቃት ሲከላከል ውሏል።
መድፈኞቹ የተጋጣሚያቸውን ዝቅ ብሎ የመከላከል ታክቲክ ለመስበር የተጠቀሙባቸው የኳስ ፍሰቶችና የተጫዋቾች የቦታ መቀያየር በጨዋታው ላይ የበላይነት እንዲኖራቸው ረድቷቸዋል።
ይህ ጨዋታ ለአርሰናል የዋንጫ ተስፋውን ያለመለመ ሲሆን ለዌስትሃም ደግሞ በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ ለሚያደርጉት ጥረት ፈታኝ ሆኖባቸዋል።
አርሰናል ዋንጫውን ለማንሳት የዛሬው ጨዋታ ቁልፍ ነጥብ በመሆኑ ፍልሚያው እጅግ አስጨናቂና ብርቱ ፉክክር የታየበት ቢሆንም ሊያንድሮ ትሮሳርድ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ መድፈኞቹ የድል መንገዳቸውን ቀጥለዋል።
አለባቸው ደሳለኝ
ከለንደን 🇬🇧
#አርሰናል #የእንግሊዝ_ፕሪሚየር_ሊግ #ስፖርት #እግር_ኳስ #ለንደን #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ፓርቲው ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ቀጣናውን ለማተራመስ እየሰራ ነው" ሲል ያወጣውን መግለጫ መሠረተ-ቢስ፣ ኃላፊነት የጎደለው እና የሀሰት መረጃ ስርጭት አካል ነው ሲል ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ውድቅ አደረገ።
ድርጅቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ፣ ቀጣናው መረጋጋት በሚሻበት በአሁኑ ወቅት እንዲህ ያሉ ውንጀላዎች ውጥረትን ከማባባስ ባለፈ እውነተኛ የሰላም ጥረቶችን የሚያደናቅፉ ናቸው ብሏል። ህወሓት ቀጣናዊ መረጋጋትን ከሚያደፈርስ ማንኛውም ድርጊት ነፃ መሆኑንም አረጋግጧል። በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ከፍተኛ የጦርነት ጊዜ፣ የሱዳን ህዝብ እና መንግስት ለተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች ሰብአዊ እርዳታ እና መጠለያ መስጠታቸውን ያስታወሰው መግለጫው፣ ይህን ሰብአዊ ድርጊት አዛብቶ ለፖለቲካ ትርፍ ማዋል ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝቧል።
የትግራይ ህዝብ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት (CoHA) ሙሉ እና ታማኝ ትግበራ በትዕግስት እየጠበቀ መሆኑን የጠቆመው ህወሓት፣ በተለይም የተፈናቀሉ ዜጎችን በሰላማዊ፣ በፈቃደኝነት እና በክብር ወደ ቀያቸው የመመለስ ሂደት ላይ ትኩረት ማድረጉን አመልክቷል። በምዕራብ ትግራይ የሚገኙትን ጨምሮ የድርጅቱ ኃይሎች የተፈናቃዮች ምላሽ በሰላማዊ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲከናወን የበኩላቸውን ሚና ለመጫወት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አክሏል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያን እና ቀጣናውን ዳግም ወደ ጦርነት ሊያስገቡ የሚችሉ ትንኮሳዎች፣ የውጭ ጣልቃ ገብነቶች እና አጋጣሚን ጠባቂ የፖለቲካ አሰላለፎች በእጅጉ እንደሚያሳስቡት ፓርቲው ገልጿል። እነዚህ አጭር እይታ ያላቸው ስሌቶች ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ከማሻከር ባለፈ ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ሰላም አደጋ መሆናቸውን አስጠንቅቋል። የትግራይ ህዝብ ለሰላም ሲል እጅግ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሉን ያነሳው ህወሓት፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉን አሳታፊ እና አሳማኝ በሆነ የውይይት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
የሚመለከታቸው አካላት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀስቃሽ ትርክቶችን በማውገዝ፣ ተጠያቂነትን በማስፈን እና የስምምነቱን ሙሉ ትግበራ በመደገፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል። ዘላቂ ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው በውይይት እና በኃላፊነት ስሜት እንጂ በፕሮፓጋንዳ እና ግጭትን በማባባስ አለመሆኑን መግለጫው በአጽንዖት አስምሮበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት ያከናወኗቸው ተግባራት
በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳይንሳዊ የምርምር ልህቀት፣ በከተማ ልማት፣ በኢኮኖሚ ሪፎርም እና በቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።
• የፕሮጀክቶች ምረቃ እና የሥራ ጅማሮ
የመጋቢት ወር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ውስጥ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀዋል። ይህ ማዕከል 40 የላብራቶሪ ክፍሎችን እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮ-ኢኩቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን ያካተተ ነው።
በከተማ ልማት ዘርፍ፣ የሚያዝያ ወር በአገልግሎት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ግንባታ ረገድ ጉልህ እመርታ የታየበት ወር ነበር። የአራዳ ፓርክ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ገጽታ ለውጥ የታየበት ሲሆን፤ ቀደም ሲል ችላ ተብለውና ለአደጋ ተጋልጠው የነበሩ ቤቶች የሚገኙበትን 40 ሄክታር መሬት ወደ ዘመናዊ ሁለገብ መዳረሻነት ቀይሮታል። ይህ የተቀናጀ የመሠረተ-ልማት እና የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት የታየበት ፕሮጀክት፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ700 በላይ ነባር ቤቶችን የማደስ ስራን አካቷል።
ከዚህም በተጨማሪ በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና የኦሊምፒክ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መሠረተ-ልማቶችን፣ የ15 የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዎችን ሃውልት እና ለተነሺ ነዋሪዎች ተብለው የተገነቡ 105 የንግድ ሱቆችን የያዘው የአዲስ ስፖርት ፓርክ በዚሁ ወር ተመርቋል።
የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት አቅም ለማሳደግ የ100 ሜጋ ዋት የአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተመርቋል። በተጨማሪም በሀዋሳ የቶዮ ምዕራፍ 2፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል። እነዚህ ፋብሪካዎች ከአዲሱ የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ፋብሪካ ጋር በመሆን በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹህ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቱሪዝም ዘርፍ፦ በገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር የተገነባው የሀሮ ደንዲ ሎጅ በይፋ ተመርቋል። በመጨረሻም፣ እንደ መታወቂያ ምዝገባ እና የሥራ ፈቃድ ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የታለመው የመሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት ስራ ጀምሯል።
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ ኅብረት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ጤና መሪ ሆነው የተሾሙት በያዝነው የሚያዝያ ነው።
ይህ ኃላፊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአካታች ዕድገት ቁልፍ መሣሪያ የሆኑትን የፈጠራ ሥራዎችን እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማሳደግ ረገድ እያሳዩት ያለውን የአመራር ጥበብ እውቅና የሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንቁ አመራር ሰጪነት በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ያስመዘገበችውን ጉልህ ስራ የሚያሳይ ነው።
• የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአፈጻጸም ግምገማ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሦስተኛውን የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም እና የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ግምገማ መርተዋል። በዚህም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት 9.2 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ወደ 10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል። ሪፖርቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ የተመዘገበውን ስኬታማ ሽግግር በዝርዝር ያሳየ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ያስመዘግቡ የነበሩ ተቋማት በአሁኑ ወቅት 2.1 ትሪሊዮን ብር ገቢ ወደ ማስገባት ተሸጋግረዋል። ለዚህ ውጤት መገኘት ቁልፍ የሆነው የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገቱ ዋና መሪ እንዲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው የሪፎርም አጀንዳ ነው።
ይህም እንደ ካፒታል ገበያ ባሉ አዳዲስ የፋይናንስ ሥርዓቶች እና እያደገ በመጣው የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት እየተደገፈ ይገኛል።
• የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማጠናከር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) እና ሮቦቲክስን በመጠቀም ወደ ቺፕስ እና ዳታ (ኢንዱስትሪ 4.0) መሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ የውጭ ምርቶችን መተካት የቻለው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የይዞታ መጠን ወደ 88 በመቶ ማድረሱን በስኬትነቱ ጠቅሰዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ሰላማዊ የባሕር በር ማግኘት የሀገር የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዳትሆን ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ እንደሚጨምርባት አስገንዝበዋል።
• ማህበራዊ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ አመራር፦
“ማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በተሰኘው እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክክር መድረክ ላይ፣ መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ19.8 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን እና ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ሥርዓተ-ትምህርት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።
በጤናው ዘርፍም በቅደመ መከላከል እና አክሞ ማዳን፤ መካከል የተሻለ ሚዛን ለመፍጠር ለ30 ዓመታት ያገለገለው ፖሊሲ እንዲሻሻል ተደርጓል። በአካባቢ ጥበቃ ረገድም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የኮፕ32 (COP32) ጉባኤን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት የጀመረች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዝግጅቱ ከሀገራዊው የአረንጓዴ ልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴውን ሰብስበው አቅጣጫ ተሰጥተዋል።
• ዲፕሎማሲ እና ቀጣናዊ ትስስር፦
ኢትዮጵያ የብሩንዲ፣ የላይቤሪያ፣ የደቡብ ሱዳን እና የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንቶችን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያስተናገደች ሲሆን፤ ይህም በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ በርካታ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አስችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር፣ ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት (Afrexim) ባንክ ፕሬዝዳንት፣ እንዲሁም ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጅቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትርን በመቀበል በሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፤ ከአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ጋር ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ጤና ረገድ የተሰጣቸውን ሚና ጨምሮ ሰፋ ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በሀገር ውስጥ ጉዳይ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በመገናኘት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ የፕሬዝዳንቱን የሥራ ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት በይፋ አራዝመዋል።
የሚያዝ ወር የትንሳኤ በዓል የተከበረበት በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በማዘጋጀትና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ በማጋራት ተጠናቋል።
#ethiopiadelivers #pmoethiopia

በኦርዌል "1984" እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምንና ምን ናቸው?
(ቃልኪዳን ኃይሉ)
ጆርጅ ኦርዌል ማነው?
#ethiopia | ጆርጅ ኦርዌል (ትክክለኛ ስሙ ኤሪክ አርተር ብሌየር) እ.ኤ.አ. በ1903 ሕንድ ውስጥ ተወለደ። ጆርጅ ኦርዌክ በሕይወቱ ለጽሑፎቹ ትልቅ ግብዓት የሆኑ ሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ነበሩት፦ እነሱም የፖሊስነት ተሞክሮ፣ በአውሮፓ የነበረው የድህነት ኑሮ እና የስፔን የእርስ በርስ ጦርነት፡ በፋሺዝም ላይ ለመዋጋት ወደ ስፔን ሄዶ በጦርነቱ መሳተፉ አስተሳሰቡን እና መጻሕፍቱን በዚያ ልምድና ተሞክሮው ላይ እንዲያጠነጥን አድርጎታል።
ኦርዌል በተለይ በሁለት ዝነኛ መጻሕፍቱ ይበልጥ ይታወቃል፦Animal Farm (የእንስሳት እርሻ) እና 1984 ነው።
Animal Farm የራሺያን አብዮት መነሻ በማድረግ የተጻፈ ተምሳሌታዊ (Allegory) ድርሰት ነው። "ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው፤ ነገር ግን አንዳንዶቹ ከሌሎቹ ይበልጥ እኩል ናቸው" የሚለው ዝነኛ ጥቅሱ ሥልጣን እንዴት አብዮተኞችን ወደ ጨቋኝነታቸው እንደሚቀይር ያሳያል።
ሌላው 1984 ይህ ደግሞ የግለሰብ ነፃነት ሙሉ በሙሉ በጠፋበት ዓለም ውስጥ የሚኖርን ሰው ሕይወት የሚተነብይ የ"ዳይስቶፒያ" (Dystopia) ልብ-ወለድ ነው።
የመከራከሪያ ነጥቦቹ (Core Ideas)
ኦርዌል በሥራዎቹ ውስጥ ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን በጽኑ ይቃወማል፦
1.የእውነት መጥፋት (The Erosion of Truth)፦ ኦርዌል በጣም የሚፈራው "እውነት" የሚባል ነገር ጠፍቶ፣ ገዢዎች የሚሉትን ብቻ ሕዝቡ እንዲያምን የሚደረግበትን ሥርዓት ነው። "በሁለንተናዊ የማታለል ዘመን እውነትን መናገር አብዮታዊ ተግባር ነው" የሚል እምነት ነበረው።
2.የቋንቋ መበላሸት (Corruption of Language)፦ ፖለቲከኞች መጥፎ ተግባራቸውን ለመሸፈን ቋንቋን እንደሚጠቀሙ ይከራከራል። ለምሳሌ "ሰላም ማስከበር" የሚለው ቃል ጦርነትን ለመሸፈን፣ "ማስተካከል" የሚለው ቃል ደግሞ ግድያን ለመሸፈን ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ያሳያል።
3. የግለሰብ ነፃነት (Individual Autonomy)፦ ሥልጣን የሰውን ልጅ አካል ብቻ ሳይሆን አእምሮውንና ትውስታውን ጭምር እንዲቆጣጠር ኦርዌል አይፈልግም።
"ኦርዌሊያን" (Orwellian) የሚለው ቃል
በአሁኑ ጊዜ ይህ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ቅጽል ጥቅም ላይ ይውላል። አንድን ሁኔታ "ኦርዌሊያን" ስንለው፣ ያ ሁኔታ መንግሥት የሰዎችን የግል ሕይወት የሚቆጣጠርበት፣ መረጃን የሚያዛባበትና ዜጎችን በውሸት ፕሮፓጋንዳ የሚያደነዝዝበት መሆኑን ለመግለጽ ነው።
1984 Vs ኢትይጵያ
"1984" እስካሁን ድረስ ጸንቶ የቆየው እንደ ተራ የአምባገነንነት ማስጠንቀቂያ ሳይሆን፣ ሥልጣን ከተራ የተግባር ቁጥጥር ባለፈ የአረዳድ (Perception) የበላይነትን ለመያዝ በሚሻበት ጊዜ እንዴት እንደሚሠራ የሚያሳይ ጥቁር ትንታኔ በመሆኑ ነው።
በጥልቅ ሲታይ፣ ሥርዓቱ በእውቀት ቁጥጥር (Epistemic Control)፣ በቋንቋ ምህንድስና እና በሥነ-ልቦናዊ ተገዥነት ላይ የተገነባ መሆኑን እንረዳለን።
1. ሥልጣን እንደ እውነት የማምረቻ መሣሪያ
የኦርዌል ዋነኛ መከራከሪያ ፍጹም ፖለቲካዊ ሥልጣን የሚገኘው እውነታን የመተርጎም አቅም ላይ ነው የሚል ነው። "ፓርቲው" ነባራዊ እውነታዎች ለፖለቲካዊ ፍላጎት ተገዥ መሆን አለባቸው ብሎ መሟገቱ እንዲሁ ለንግግር ያህል የመጣ ሳይሆን መዋቅራዊ መርህ ነው። የሚጋጩ እውነታዎችን በግዴታ አምኖ መቀበል (Doublethink) ዜጎችን የማላመጃ ዘዴ ሲሆን፣ በእውነትና በሥልጣን መካከል ያለውን ድንበር ያጠፋዋል።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውድድር በዋነኝነት የሚካሄደው በትርክት ግንባታ (Narrative Construction) ነው።
የመንግሥት ተቋማት፣ የተቃዋሚ ንቅናቄዎች እና የሚዲያ ተዋናዮች ስለ ግጭት፣ ስለ ሪፎርም እና ስለ ቅቡልነት የተራራቁ ትርክቶችን ያቀርባሉ። እዚህ ላይ ችግሩ የፕሮፓጋንዳ መኖር ብቻ ሳይሆን፣ "ትክክለኛውን የታሪክ ስሪት" የማጽደቅ ፍልሚያ ነው። የጋራ የሆነ የእውነታ መሠረት በሌለበት ሁኔታ፣ ፖለቲካዊ ፍርድ በቀላሉ የሚለዋወጥና ለማጭበርበር የተጋለጠ ይሆናል።
2. የቋንቋ ቅነሳና ፖለቲካዊ ቅርጻ (Linguistic Compression and Framing)
"ኒውስፒክ" (Newspeak) ቋንቋ የሐሳብ መሠረት (Infrastructure) መሆኑን በሚገባ የተረዳ ስልት ነው። የቃላት ግምጃ ቤትን በዘዴ በመቀነስ፣ ፓርቲው ተቃውሞን ለማሰብ የሚያስፈልጉ የግንዛቤ መሣሪያዎችን ያጠፋል።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ ምንም እንኳ አተገባበሩ እንደ መጽሐፉ የተማከለ ባይሆንም፣ ውጤቱ ግን ተመሳሳይ ነው። ከማንነት፣ ከፌዴራሊዝም፣ ከሉዓላዊነትና ከደኅንነት ጋር የተያያዙ ቃላት በጽንፍ በተራራቁ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ትንታኔዎች በታፔላዎች (Labels) ይተካሉ። ውስብስብ የሆኑ ነባራዊ ሁኔታዎች በስሜት ወደተሞሉ ምድቦች ይጠቅለላሉ። ይህ ሐሳብን ባያጠፋውም እንኳ፣ አስቀድሞ ወደ ተወሰኑ የፖለቲካ አሰላለፎች እንዲፈስ ያደርገዋል። ውጤቱም ውይይቶች ገና ሳይጀመሩ በቋንቋ አጠቃቀም ብቻ ውጤታቸው እንዲወሰን ያደርጋል።
3. የታሪክ ትርክትና የማስታወስ ፖለቲካ
ፓርቲው ያለፈውን ታሪክ በመቆጣጠር፣ ከሥርዓቱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ነፃ የማጣቀሻ ነጥብ እንዳይኖር ያደርጋል። ታሪክ ለወቅታዊው ሥልጣን ቅቡልነት ሲባል በየጊዜው የሚስተካከል ተለዋዋጭ ነገር ይሆናል።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ በኢትዮጵያም እርስ በርሳቸው የሚጋጩ የታሪክ ትርክቶች ለወቅታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ድጋፍ እንዲሆኑ ተደርገው ይቀርባሉ።
ስለ ሀገር ምስረታ፣ ስለ ማንነትና ስለ ታሪካዊ በደሎች የሚደረጉ ክርክሮች የትምህርት ዘርፍ ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ መሣሪያዎች ናቸው። በታሪክ ትርጓሜ ላይ ስምምነት አለመኖሩ፣ ለጋራ ሀገራዊ ትርክት መፈጠር እንቅፋት ከመሆኑም በላይ ተጠያቂነትንና እርቅን የማምጣት ሂደትን ያወሳስበዋል።
4. ቁጥጥር፣ ራስን መገደብና የሕዝብ ውይይት
"ቴሌስክሪን" (Telescreen) የማያቋርጥ ክትትልን ያመለክታል፤ ሆኖም ዋናው ተግባሩ ግለሰቡ "እየታየሁ ነው" የሚለውን ስሜት ውስጣዊ አድርጎ ራሱን እንዲቆጣጠር ማድረግ ነው።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ ክትትል በተቋማዊ፣ በዲጂታልና በማኅበራዊ መዋቅሮች አማካኝነት ይከናወናል። ምንም እንኳ ቁጥጥሩ ፍጹም ባይሆንም፣ ዜጎች የሚናገሩትን ነገር እንዲመጥኑ (Calibrate) እና ራሳዊ ቅድም ምርመራ (Self censorship) ያደርጋል።
የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ተንታኞችና ተራ ዜጎች በሕግ፣ በፖለቲካዊ ተጋላጭነትና በማኅበራዊ ጫናዎች የሚወሰኑ ድንበሮችን እያጤኑ ይንቀሳቀሳሉ
(Self censorship)። ውጤቱም ፍጹም ዝምታ ሳይሆን፣ ያልተባለው ነገር ከተባለው እኩል ትርጉም የሚሰጥበት "ስልታዊ የሐሳብ ልውውጥ" (Strategic Communication) መፈጠሩ ነው።
5. ማስገደድና የውዴታ ግዴታን ማምረት (Coercion and Consent)
በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኘው የኦብራይን (O'Brien) ገጸ-ባህሪ ዓላማው ተቃውሞን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን፣ የሰውን እምነትና አስተሳሰብ ጭምር እንደ አዲስ መቅረጽ ነው።
በኢትዮጵያ ሁኔታ፡ የፖለቲካው ምኅዳር የተለያየና ብዙ ተዋናዮች የሚሳተፉበት በመሆኑ፣ ጫናው እንደ ኦርዌል ዓለም ወጥና ፍጹም አይደለም። ይሁን እንጂ የሕዝብን ድጋፍ በትርክት የማምረት ፍላጎት ማዕከላዊ ነው። የሚዲያ ሥነ-ምህዳሩ (መደበኛም ሆነ ማኅበራዊ) የተወሰኑ ትርክቶችን በማግነንና ሌሎችን በማዳከም ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
ትግሉ አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብን ከመጫን ይልቅ፣ በተሰባበረ የመረጃ አውድ ውስጥ የትርክት የበላይነትን (Narrative Dominance) የመያዝ ትግል ነው።
ማጠቃለያ
የ"1984" ፋይዳ ያለው በፅንሰ-ሐሳብ ግልጽነቱ ላይ ነው። ሥልጣን ግንዛቤን፣ ቋንቋንና ትውስታን በመቆጣጠር ራሱን እንዴት እንደሚያደላድል ነጥሎ ያሳየናል።
ኢትዮጵያ የኦርዌልን ዝግ የአምባገነንነት፣ የፖለቲካው ሜዳ ተለዋዋጭና የተለያየ ተፅዕኖ ያላቸው ኃይሎች የሚጋጩበት ነው።
ኦርዌል የለያቸው መሠረታዊ መዋቅሮች መልክ ቀይረው ይታያሉ። መረጃን መቆጣጠር፣ ቋንቋን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀምና ታሪክን ፖለቲካዊ ማድረግ እስካሁንም የሥልጣን ትግሉ ማዕከል ናቸው።

በሚስቱ የተቆረጠው የወንድ ብልት በስፌት ተቀጠለ
በአርሲ ዞን በትዳር አጋራቸው ጥቃት ደርሶባቸው ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ የወደቀው የ42 ዓመት ጎልማሳ ብልት፣ በአሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በተደረገ የ3 ሰዓታት ስኬታማ ቀዶ ህክምና ተመልሶ መገጠሙ ተነገረ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ከአንድ ወር በፊት ሲሆን፣ በግለሰቡና በባለቤታቸው መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ባለቤታቸው እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ላይ በስለት ሙሉ በሙሉ በመቁረጥ መሬት ላይ ጥለውታል። የ6 ልጆች አባት የሆኑት ተጎጂው፣ የተቆረጠውን ብልታቸውን በፌስታል ጠቅልለው በመያዝ በራሳቸው ጥረት በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መድረሳቸው ታውቋል።
የኩላሊትና የሽንት ቧንቧ ስፔሻሊስት ዶ/ር ፍቃዱ ሀብታሙ እንደገለጹት፣ ህክምናው የተከናወነው ጉዳቱ በደረሰ በ3 ሰዓት ውስጥ ግለሰቡ ሆስፒታል በመድረሳቸው ነው። በጥንቃቄ ለ3 ሰዓታት በተደረገ ስፌት ብልቱ ወደ ቦታው የተመለሰ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ተጎጂው በሽንት ቧንቧቸው በኩል መሽናት መጀመራቸውንና የጤና ሁኔታቸው በመሻሻል ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል።
እንዲህ ዓይነት ጉዳት ሲያጋጥም በ6 እና በ8 ሰዓታት ውስጥ ሆስፒታል መድረስ ለስኬታማነቱ ወሳኝ ነው ተብሏል። ብልቱ የመቆም እና የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የመፈጸም እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም፣ እንደ ቀድሞው ሙሉ ጥንካሬ ላይኖረው እንደሚችል ተገልጿል።
የተቆረጠው አካል በንጹህ ፌስታል ተጠቅልሎ ሳይቆሽሽ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መወሰድ አለበት።
ተጎጂው በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል ክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ለደህንነታቸውና ለግል ሚስጥራቸው ሲባል ማንነታቸውና ዝርዝር አድራሻቸው እንዳይገለጽ ተደርጓል ሲል ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘግቧል።
ምስል ኤአይ
seledadotio

#fastmereja I በአርሲ ዞን በትዳር አጋራቸው ጥቃት ደርሶባቸው ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ የወደቀው የ42 ዓመት ጎልማሳ ብልት፣ በአሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በተደረገ የ3 ሰዓታት ስኬታማ ቀዶ ህክምና ተመልሶ መገጠሙ ተነገረ።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ፣ በ1990ዎቹ ክለቡን በማሰልጠን ስኬታማ ጊዜያትን ያሳለፉትን ትውልደ ሰርቢያዊ አሰልጣኝ ስሎቦዳን ሚቾን ዳግም ወደ ኢትዮጵያ አስመጥቷል።
ፈረሰኞቹ በፕሪሚየር ሊጉ ከውጤት ርቀው መቆየታቸው፣ በተለይም ባለፈው ሳምንት በነበረው ተጠባቂው የሸገር ደርቢ በባላንጣቸው ኢትዮጵያ ቡና የ3 ለ 1 ያልተጠበቀ ሽንፈት ማስተናገዳቸው የክለቡን አመራሮች አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ አስገድዷቸዋል። ይህንን የደርቢ ሽንፈት ተከትሎም፣ የቀድሞ አሰልጣኙን በፍጥነት ወደ አዲስ አበባ የማምጣቱ ሂደት እንደተፈጸመ ታውቋል።
አሰልጣኝ ሚቾ ዛሬ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ ከክለቡ ተጫዋቾች እና አሁን ካለው የአሰልጣኝ ስታፍ ጋር ትውውቅ አድርገዋል። ነገ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገውን ጨዋታም በመከታተል የቡድኑን ወቅታዊ አቋም በቅርበት ይገመግማሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኙ ዛሬ በነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአርባምንጭ ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ላይ፣ በስታዲየም ተገኝተው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ እና ምክትል አሰልጣኝ መሀል ተቀምጠው ጨዋታውን ሲከታተሉ ታይተዋል።
በቀጣይ ቀሪ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ልምምድ፣ የአጨዋወት ፍልስፍና እና የተጫዋቾች አሰላለፍ ምርጫ ሙሉ በሙሉ በአሰልጣኝ ሚቾ የሚመራ ይሆናል። ይሁን እንጂ አሰልጣኙ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እስካሁን ህጋዊ ምዝገባ ያላደረጉ በመሆናቸው፣ በጨዋታ ቀናት ከፊት ለፊት (በሜዳው ዳር) ወጥተው መመሪያ ከመስጠት ይልቅ፣ ከጀርባ ሆነው የክለቡን ስራዎች በበላይነት እንደሚመሩ ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
ይህ የፈረሰኞቹ ያልተጠበቀ እርምጃ ክለቡን ወደ ቀድሞ የድል መንገዱ ይመልሰው ይሆን? የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ ጨዋታዎች የሚመልሱት ይሆናል።

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ በበርዮት ሚዲያ ላይ ቀርበው በሰጡት ቀጥተኛና ጠንካራ ቃለ-ምልልስ፣ በክልሉ እየታየ ባለው የፖለቲካ ሽኩቻና "የድሮውን ምክር ቤት መልሰናል" በሚለው የደብረጽዮን ገብረሚካኤል ሕወሐት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ስጋት ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህ አካሄድ "አጥፊና ትግራይን ችግር ውስጥ የሚከት ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።
ጄነራል ታደሰ "የድሮ ምክር ቤት መልሰናል" በሚል እየተደረገ ያለው የአንድ ወገን እንቅስቃሴ የትግራይን ሕዝብ ወደ ሌላ ጦርነትና ግጭት ሊወስድ የሚችል "የእብደት አካሄድ" ነው ብለውታል። "ከዚህ ግርግር ይልቅ በተለያየ አሰላለፍ አኩርፎ የተቀመጠውን ትግራዋይ ሰብስበን፣ ክልሉን ወደተሻለ ምዕራፍ ስለማሸጋገር መጨነቅ አለብን" ሲሉ አሳስበዋል።
በክልሉ ነገሮች እየተካረሩ ቢሄዱም፣ የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ የማቅረብ ፍላጎት እንደሌላቸው ፕሬዝዳንቱ በግልጽ ተናግረዋል። "እንደዛ የማድረግ መብት እንዳለኝ ባውቅም እኔ ግን አላደርገውም፤ የሚሆነውን እናያለን" ብለዋል። በተጨማሪም፣ "መረካከብ" የሚባል አርቲፊሻል ጨዋታ ውስጥ እንደማይገቡና የሚያስረክቡትም ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ "የለም በዛ መንገድ እንሄዳለን ካሉ ግን እንደፈለጉ ያድርጉ" ሲሉ ተደምጠዋል።
"ትግራይ ላይ እያንዣበበ ካለው አደጋ አንጻር የኔ በፕሬዝዳንትነት መቀጠል አጀንዳ አይደለም" ያሉት ጄነራል ታደሰ፣ ዋነኛው ፍላጎታቸው ሕዝቡ ከጊዜያዊ አስተዳደር ወጥቶ በራሱ በመረጠው ቋሚ መንግስት ሲተዳደር ማየት መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ያለውን አጋጣሚ ለግርግር ሳይሆን ለመልካም ዕድል መጠቀም እንደሚገባም መክረዋል።
ይህ የጄነራል ታደሰ ወረደ ንግግር በክልሉ አስተዳደርና በህወሃት አመራሮች መካከል ያለው ውጥረት እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች እየገመገሙት ይገኛል።

ከመቃብር በላይ የሚውል መልካም ስም
በአሰላ የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ!
#ethiopia | ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አንድ ታሪካዊ ክስተት ተከናውኗል።
በሀገርና በቤተክርስቲያን ዘንድ እጅግ የሚከበሩትና "መጋቤ በረከት" የሚል ማዕረግ የተሰጣቸው የታላቁ አባት የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ የመታሰቢያ ህንፃ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
የልጆች ስጦታ፦
እኚህ ታላቅ አባት ካረፉ አንድ ዓመት ሲሞላቸው ልጆቻቸው ከአባታቸው የተረከቡትን በጎነት ለታሪክ እንዲተርፍ ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን ባለ ሁለት ወለል ሙዚየም ገንብተው ለምረቃ አብቅተዋል።
"ጊዳድ" መጽሐፍ፦
የአባታቸውን የህይወት ጉዞ፣ የንግድ ስኬትና የቤተሰብ አመራር ጥበብ የሚዳስሰው "ጊዳድ" የተሰኘው መጽሐፍ በጸሐፊ ሌሊሳ ኢድሪስ ተዘጋጅቶ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ለንባብ በቅቷል።
ታሪካዊ ምስክርነት፦
ሙዚየሙ የአባቱን መልካም ስራዎች የሚገልጹ ፎቶግራፎች፣ ቁሳቁሶችና መረጃዎችን የያዘ ሲሆን፤ አዳራሽና ቢሮዎችንም ያካተተ ዘመናዊ ህንፃ ነው።
መጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ (1949 - 2017 ዓ.ም)
በአርሲ ዞን ተወልደው በንግዱ ዓለም ስኬታማ የነበሩ ሲሆን፤ አምስት ልጆችን በስነ-ምግባር አሳድገው ለሀገር ያበቁ ታላቅ አባት ናቸው።
በቤተክርስቲያን ግንባታ፣ በማህበራዊ ልማትና በሽምግልና ስራቸው "የቱሩፋት አበጋዝ" ተብለው ይወደሳሉ።
እውነትን በመናገርና ችግረኞችን በመርዳት የሚታወቁት እኚህ አባት፣ በ68 ዓመታቸው ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ማረፋቸው ይታወሳል።
ሀብት ለራስ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ለታሪክና ለወገን ሲተርፍ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። የመጋቤ በረከት ግርማ ልጆች ለአባታቸው ያደረጉት ይህ ተግባር፣ ማንኛውም ሰው በህይወት ዘመኑ የሚዘራው በጎነት እንዲህ በክብር እንደሚታጨድ ማሳያ ነው። አሰላ ዛሬ የአንድ ብርቱ አባት ታሪክ ህያው ሆኖ ሲታደስ ውላለች!
መልካም ስራ ከመቃብር በላይ ይውላል!
#getu #megabebereketgirma #asella #legacy #gidatbook #ethiopianhistory #ethiopianorthodox #arsi #inspiration #መጋቤበረከትግርማ #አሰላ #ታሪክ #ጊዳድ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago
ዋሽንግተን በኢራን ላይ ወታደራዊ ግፊት እንድታደርግ ሳዑዲ መጠየቋ ተሰማ
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት እያየለ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ሳዑዲ አረቢያ አሜሪካ በቴህራን ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ጫና አጠናክራ እንድትቀጥል መጠየቋ ተዘግቧል። ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው፣ የሳዑዲው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወስዱ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።
የአጋር አገራት ዝርዝር ይፋ ሊደረግ ነው
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አሜሪካ ከኢራን ጋር ሊኖር በሚችል ማንኛውም ወታደራዊ ግጭት አብረዋት የሚሰለፉ አገራትን ዝርዝር በቅርቡ ይፋ እንደምታደርግ አስታውቃለች። ይህ እርምጃ ዋሽንግተን በክልሉ ያላትን ወታደራዊ ዝግጁነት እና የጥምረት ጥንካሬ ለማሳየት የታለመ መሆኑ ተመልክቷል።
የከፍተኛ መሪዎቹ ሚና
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የትራምፕ አስተዳደር በመካከለኛው ምስራቅ ለሚከተለው ጥብቅ ፖሊሲ ከስተጀርባ የሳዑዲ እና የእስራኤል መሪዎች ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። በተለይም፦
* መሐመድ ቢን ሳልማን፦ የኢራንን ቀጠናዊ ተጽዕኖ ለመግታት የአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ያምናሉ።
* ቤንያሚን ኔታንያሁ፦ የቴህራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለማሰናከል ዋሽንግተን ቆራጥ እርምጃ እንድትወስድ ይፈልጋሉ።
ይህ የኃይል አሰላለፍ በቀጣይ በክልሉ ሰላምና ደህንነት ላይ ምን ዓይነት ለውጥ እንደሚያመጣ በቅርበት የሚጠበቅ ጉዳይ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አሜሪካ #ኢራን #ሳዑዲአረቢያ #እስራኤል #መካከለኛውምስራቅ #ዜና #ትራምፕ

የከተማ ይዞታን ለማስመለስ ክስ በይርጋ ይታገዳል?
(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰባት ዳኞች በተሰጠ የህግ ትርጉም የተሰጠ የህግ ትንታኔ)
#ethiopia | በጠበቃና የህግ አማካሪ አልማው ወሌ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም ? በሚለው አከራካሪ የህግ ነጥብ ላይ ሰበር ችሎቱ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ
የተከበሩ ጠበቃ እናመሠግናለን መልካም ንባብ
ኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ 1
ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና የሥነ-ሥርዓት ዳራ 1
ክፍል ሁለት፡ የሦስቱ ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎች አጠቃላይ ትንታኔ 1
ክፍል አራት፡ የሰባት ዳኞች ችሎት አዲሱ የሕግ ትርጉም 3
ክፍል አምስት፡ ተግባራዊ የተደረጉት የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ትንታኔ 4
ክፍል ስድስት፡ ስለ አዲሱ ትርጉም ጥንካሬዎች 4
ክፍል ሰባት፡ የውሳኔው ማጠቃለያ እና ቀጣይ አንድምታዎች 4
7.1 አዲሱን ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለመተግበር ትክክለኛነት፡ የሽግግር ድንጋጌዎችን በጥብቅ መከተል 5
7.2 የአመሳስሎሽ ትርጓሜ ችግር፡ የሕግ ክፍተትን ለመሙላት በተመረጠው ምንጭ ላይ የታየ የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መዛባት 6
7.3 የክፍል 7 ጥማቂ 8
ክፍል ስምንት፡ አጠቃላይ ግምገማ 9
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ.ቁጥር 244308 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ የቀረበ አጭር ትንታኔ
ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና የሥነ-ሥርዓት ዳራ
ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የሰጠው ይህ ውሳኔ በመ/ቁጥር 210477 ላይ ተሰጥቶ የነበረውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በመለወጥ ተሰጠው (Overruling) ውሳኔ ሲሆን በአገሪቱ የንብረት ሕግ ስነ ህግ እድገት እና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም ስርዓት ላይ የራሱ የሆነ አንድምታ ያለው መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ አዲስ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለውጥ በችሎቱ የተሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26(1) ድንጋጌ እና በሰበር ስነ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አንቀፅ 14(2) በተዘረጋው ስርዓት ሲሆን ችሎቱ የተሰየመበትም ዋነኛ ምክንያትም የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ይታገዳል ወይስ አይታገድም ? በሚለው አከራካሪ የህግ ነጥብ ላይ ሰበር ችሎቱ ቀደም ሲል በሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች መካከል ሊታረቅ የማይችል ተቃርኖ በመፈጠሩ ነው፡፡ የጉዳዩ ምንጭ አቶ ጅላሎ ኩመል ሼህረዲ (አመልካች/ተከሳሽ) እና አቶ ታምራት መርከቡ ፍልቾ (ተጠሪ/ከሳሽ) በአዲስ አበባ ከተማ (ለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ፣ ወረዳ 08፣ ፊጋ ሰፈር በሚባል አካባቢ) በሚገኝ 2,000 ካሬ ሜትር የከተማ ቦታ ላይ ያደረጉት ክርክር ነው፡፡ ጉዳዩ ለሰባት ዳኞች ችሎት መመራቱ ሥነ-ሥርዓታዊ ሂደት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ መሠረታዊ የሕግ ይዘት ያለው ጉዳይ ሲሆን ችሎቱም በሕግ አተገባበር ላይ ወጥነት እና ተገማችነትን የማረጋገጥ ኃላፊነቱን ለመውጣት በተጠቃሽ ውሳኔዎቹ መካከል የታየውን ተቃርኖ አስታራቂ እና ግልጽ አቋም ሊያዝበት የሚገባ መሆኑን በግልጽ አስፍሯል፡፡ ይህ እርስ በእርሱ የሚቃረኑ አስገዳጅ ውሳኔዎች ሥርዓታዊ የሆነ ችግር እንዳያስከትሉ ችሎቱ ራሱን በራሱ በማረም የወሰደው ዕርምጃ በኢትዮጵያ የአስገዳጅ የህግ ትርጉም ሥርዓት ውስጥ ያለውን ተቋማዊ ብስለት የሚያሳይ ነው ተብሎ ሊወሰድ የሚገባው ነው፡፡
ክፍል ሁለት፡ የሦስቱ ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎች አጠቃላይ ትንታኔ
በመጀመሪያ ደረጃ በሰበር መዝገብ ቁጥር 43600 ጥር 05 ቀን 2002 ዓ.ም. የተወሰነውንና በቅጽ 10 የታተመውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በአጭሩ ስንመለከት ጉዳዩ አቶ ዳዊት መስፍን ከተጠሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ጋር ያደረጉት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ዳዊት በአዲስ አበባ ከተማ (የቀድሞ ወረዳ 118፣ ቀበሌ 05) የሚገኝ መኖሪያ ቤት የባለቤትነት መብትን መሠረት በማድረግ ቤቱ እንዲለቀቅላቸው ክስ አቅርበው ነበር፡፡ ለዚህም በጥቅምት 23 ቀን 1985 ዓ.ም. የተሰጠ የከተማ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አቅርበዋል፡፡ ተጠሪው (ኤጀንሲው) በበኩሉ፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845ን ማለትም የ10 ዓመቱን የውል ግዴታዎች ይርጋ ድንጋጌ በመጥቀስ የይርጋ መቃወሚያ አቅርቦ ነበር፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይርጋ መቃወሚያውን በመቀበል ክሱን ውድቅ አድርገውት ነበር፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የሰበር ችሎት ግን የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት አግባብ መኖር አለመኖሩን ጭብጥ አድርጎ በመያዝ ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቷል፡፡ የሰበር ችሎቱ ትንታኔውን የጀመረው ማናቸውም ኢትዮጵያዊ የንብረት ባለቤት መሆኑ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(1) የተረጋገጠ መሆኑን በማንሳት ሲሆን፣ በመቀጠልም የፍትሐብሔር ሕጉን የንብረት ድንጋጌዎች ማለትም አንቀጽ 1126፣ 1168፣ 1184፣ እና 1186 ደንጋጌዎችን እንዲሁም በፍ/ህ/ቁጥር 1188 እስከ 1192 ድረስ ያሉትን ድንጋጌዎችን ሙሉ ይዘትና መንፈስ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ ችሎቱ ወሳኝ ብሎ ያነሳው ነጥብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1192 "ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን" ብሎ ያስቀመጠው ለሚንቀሳቀስ ንብረት ብቻ መሆኑን እና ስለ ማይንቀሳቀስ ንብረት በዝምታ ማለፉን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአንቀጽ 1206 ሥር የተደነገገው የመፋለም ክስ የባለቤትነት መብት ከሁሉ የሰፋ መብት መገለጫ መሆኑን፣ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ዘላቂነት (Perpetuity) ያለው መብት በመሆኑ በይርጋ ቀሪ እንዳይሆን የሕግ አውጪው ፍላጎት መሆኑን አብራርቷል፡፡ በዚህም መሠረት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ድንጋጌን ተፈፃሚ ማድረግ የሕጉን አወቃቀርና መንፈስ የሚያፋልስ መሆኑን በመግለጽ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም መብት ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም ወደሚል ድምዳሜ ደርሷል፡፡ ይህ ውሳኔ በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ ጠንካራ ቢሆንም፣ ዋነኛ ክፍተቱ ትንታኔው ሙሉ በሙሉ ታሳቢ ያደረገው "የግል ባለቤትነት መብት" (Private Ownership) መኖርን መሆኑ ነው፡፡ ጉዳዩ መኖሪያ ቤትን የሚመለከት ስለነበር ይህ አካሄድ ትክክል ቢሆንም፣ የባለቤትነት መብት በሕገ-መንግሥት በተከለከለበት መሬት ላይ ትንታኔው እንዴት ሊተገበር ይችላል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ሆኖም ትርጉም በሌሎች ልዩ ህጎች ያሉትን የይርጋ ድንጋጌዎችን የማይነካ መሆኑ በማሳሳብ አልፏል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ በሰ/መ/ቁጥ 69302 ታህሳስ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ስንመለከት፦ ጉዳዩ በአመልካች አቶ ሸለማ ነገሰ እና በተጠሪ አቶ ፋይሣ መንግስቱ መካከል በኦሮሚያ ክልል፣ ኖኖ ቤንጃ ወረዳ በሚገኝ የገጠር እርሻ መሬት ላይ የተደረገ ክርክር ነው፡፡ ተጠሪ አባቴ በሞት ከተለየበትמ 1985 ዓ.ም.
ጀምሮ አመልካች መሬቱን አላግባብ ስለያዘብኝ ይልቀቅልኝ ሲል ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካች በበኩሉ መሬቱን ለ18 ዓመታት መያዙን በመግለጽ ተከራክሯል፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች መሬቱ እንዲለቀቅ የወሰኑ ቢሆንም የሰበር ችሎቱ ግን አርሶ አደሮች የእርሻ መሬት የማግኘትና ያለመፈናቀል መብት እንዳላቸው ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 40(4) መሠረት ማረጋገጡን ጠቅሶ፣ ይሁን እንጂ መሬቱን በሌላ ሰው የተነጠቀ አርሶ አደር ክስ ማቅረብ ስላለበት የጊዜ ገደብ የገጠር መሬት አዋጆች በግልጽ አለመደንገጋቸውን በማንሳት የሕግ ክፍተት መኖሩን አሳይቷል፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉ የሁከት ይወገድልኝ ክስ የ2 ዓመት ይርጋን (አንቀጽ 1149(2)) መተግበር የአርሶ አደሩን ሕገ-መንግሥታዊ መብት አጥብቦ የሚገድብ በመሆኑ ውድቅ በማድረግ፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(1) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እንደ ድልድይ በዋቢነት በመጥቀስ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ ምንም እንኳን ከመዝገብ ቁጥር 43600 ፈጽሞ የተለየ አቀራረብ ይዞ የመሬት ይዞታን ከባለቤትነት መብት ነጥሎ በማየት የ10 ዓመት ይርጋ ተግባራዊ ያደረገ ቢሆንም፣ የውል ድንጋጌ የሆነውን የፍ/ህ/ቁ 1845 ድንጋጌን በቀጥታ መሬት ላይ ለመተግበር የሄደበት መንገድ በበቂ ሁኔታ ያልተብራራ መሆኑ እንደ ሂሳዊ ድክመት ሊነሳበት ይችላል፡፡
በሦስተኛ ደረጃ በሰ/መ/ቁ 210477 ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የተወሰነውንና አሁን የተሻረውን ስንመለከት፣ ጉዳዩ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ-ከተማ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ይዞታን በተመለከተ በአመልካቾች (የአቶ ነጋሳ ዱቤ ወራሾች) እና በተጠሪዎች (ወ/ሮ ጸሐይ ቹቾ እና ወ/ሮ ሴደሬ ንጉሴ) መካከል የተደረገ ክርክር ነበር፡፡ ተጠሪዎች ቦታውን ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለ19 ዓመታት መያዛቸውን በመግለጽ የይርጋ መቃወሚያ አቅርበው የስር ፍርድ ቤቶችም መቃወሚያውን ተቀብለውት ነበር፡፡ ሆኖም የሰበር ችሎቱ ይህንን ውሳኔ በመሻር፣ የቀረበው ክስ "የመፋለም ክስ" መሆኑን በመግለጽ የቤትን ባለቤትነት የተመለከተውን የሰ/መ/ቁ 43600 አመክንዮ በቀጥታ በመዋስ "የከተማ መሬት ይዞታን በተመለከተ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ አይታገድም" የሚል አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቶ ነበር፡፡ የዚህ ውሳኔ ዋነኛ ስህተት የባለቤትነት መብትን (Ownership) እና የይዞታ መብትን (Holding rights) አንድ አድርጎ ማየት መቻሉ ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 40(3) መሠረት ግለሰቦች በመሬት ላይ የባለቤትነት መብት እንደሌላቸው እየደነገገ፣ በሰ/መ/ቁ 210477 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ግን የባለቤትነት መብት ጥበቃን (ከይርጋ ነፃ መሆንን) በመሬት ይዞታ መብት ላይ በመተግበሩ መሠረታዊ የሆነ የፅንሰ-ሐሳብ እና የሕግ ስህተት ተፈጽሞበት የነበረ ጉዳይ ነው፡፡
ክፍል ሦስት፡ በውሳኔዎቹ መካከል የነበረው ተቃርኖ እና የሕግ ማዕቀፎች
በእነዚህ ሦስት ውሳኔዎች መካከል የተፈጠረው ተቃርኖ እጅግ የጎላ እንደነበር በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአንድ በኩል መዝገብ ቁጥር 43600 በቤት ባለቤትነት ላይ የመፋለም ክስ ይርጋ የለውም ሲል፣ በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁ 69302 በገጠር መሬት ይዞታ ላይ የ10 ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ አድርጓል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በሰ/መ/ቁ 210477 የከተማ መሬት ይዞታን አስመልክቶ የቀረበን ክርክር የባለቤትነት ጉዳይ ከሆነው ከሰ/መ/ቁ 43600 ጋር በማመሳሰል የከተማ መሬት ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት ወስኗል፡፡ ይህ ሁኔታ በመሬት ይዞታዎች (በገጠር እና በከተማ) ላይ የተለያየ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የይርጋ አተገባበር እንዲፈጠር አድርጎ የነበረ መሆኑ ከውሳኔዎቹ በግልፅ ይታያል፡፡
ይህንን ተቃርኖ ለመፍታት የሰባት ዳኞች ችሎት በርካታ ሕጎችን አንድ ላይ መመርመር ነበረበት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) ስለ መሬት የመንግስትና የሕዝብ ንብረትነት፣ አንቀጽ 40(4) ስለ አርሶ አደሮች መብት፣ እና አንቀጽ 40(7) በጉልበትና በገንዘብ ስለሚፈራ ንብረት ያካተቱት ድንጋጌዎች ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1192፣ አንቀጽ 1206 (ስለ መፋለም ክስ)፣ አንቀጽ 1149(2) (የሁከት ክስ ይርጋ)፣ እንዲሁም አንቀጽ 1677(2) እና 1845 ድንጋጌዎች ሙሉ ይዘታቸው ተፈትሸዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪም የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004፣ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818/2006 እና የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አግባብነት ያላቸው የሕግ ማዕቀፎች በመሆናቸው በችሎቱ ታሳቢ ተደርገዋል፡፡
ክፍል አራት፡ የሰባት ዳኞች ችሎት አዲሱ የሕግ ትርጉም
ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ይህንን የተወሳሰበ የሕግ ጥያቄ ለመፍታት የተጠቀሱትን ቀደምት አስገዳጅ ውሳኔዎችን በመመርመር ለእያንዳንዳቸው ተገቢ ነው ያለውን ማብራሪ ሰጥቶባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉምን አልሻረውም፤ ይልቁንም ጉዳዩ መኖሪያ ቤትን የሚመለከት በመሆኑና መኖሪያ ቤት ላይ የባለቤትነት መብት ስላለ፣ ትንታኔው ከዚህ መዝገብ ጋር በቀጥታ እንደማይገናኝ በማስረዳት የጉዳዩን ልዩነት (Distinguishing) በማሳየት ትርጉሙ እንዲፀና አድርጎታል፡፡ በመቀጠልም በሰ/መ/ቁጥር 69302 ለገጠር መሬት የተሰጠውን የ10 ዓመት ይርጋ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ትክክለኛነት የተቀበለ ቢሆንም፣ ይህንን የገጠር መሬት ቀደመት አስገዳጅ ትርጉም በቀጥታ በከተማ መሬት ላይ መተግበሩ ስህተት መሆኑን በማሳየት የስር ፍርድ ቤትን አካሄድ ነቅፏል፡፡ በመጨረሻም በሰ/መ/ቁጥር 210477 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሻረው ሲሆን ለውሳው ምሶሶ ያደረጋቸው አበይት ምክንያቶቹም የቀደመው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የባለቤትነት መብትን እና የይዞታ መብትን በማምታታት፣ በመሬት ይዞታ መብት ላይ ሊቀርብ የማይችለውን የመፋለም ክስ የይርጋ መቃወሚያ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም የሚሉት መሆናቸውን አዲሱ ትርጉም በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ችሎቱ አዲሱን የሕግ ትርጉም ለመስጠትና ለመተንተን የተከተለው አመክንዮ አራት ደረጃዎችን ያካተተ ነበር፡፡ አንደኛ ትንታኔውን በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(3) ላይ በማስረፅ መሬት የግለሰብ ባለቤትነት ሊኖርበት የማይችል መሆኑን እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 የመፋለም ክስ መሬት ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን አረጋግጧል፡፡ ሁለተኛ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ የሚኖረው መብት (በሊዝም ሆነ በነባር) በነገር ላይ ያለ (In rem) ተጨባጭ የንብረት መብት እንጂ ተራ የኪራይ ውል ግንኙነት አለመሆኑን በማብራራት የመብቱን ህልውና ገልጿል፡፡ ሦስተኛ የሲቪል ሎው (Civil Law) የመፋለም ክስ ፅንሰ-ሐሳብ እና የኮመን ሎው (Common Law) የማስለቀቅ ክስ (Action of ejectment) ፅንሰ-ሐሳቦችን በማነፃፀር፣ ምንም እንኳን ይህ የኮመን ሎው አሠራር ለሕግ ሥርዓታችን እንግዳ ቢሆንም፣ በሕግ የታወቀ መብት እስካለ ድረስ ስያሜው ክሱን ለማስተናገድ እክል እንደማይሆን አብራርቷል፡፡ አራተኛ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት (Gap-filling) የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) ድንጋጌን ድልድይ በማድረግ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ሥር የተቀመጠውን አጠቃላይ የ10 ዓመት ይርጋ በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም መሠረት
የከተማ መሬት ይዞታን አላግባብ ከያዘ ሰው ላይ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በአስር ዓመት ይርጋ ይታገዳል የሚል አዲስ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡
ክፍል አምስት፡ ተግባራዊ የተደረጉት የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች ትንታኔ
በዚህ ውሳኔ ተግባራዊ የተደረገው የፍ/ህ/ቁ 1845 "በውል ስለሚመነጩ ግዴታዎች" ሥር የሚገኝ ሲሆን፣ ውልን ስለመፈፀም፣ ባለመፈፀም እና ውልን ስለማፍረስ የሚቀርቡ ክሶች በአስር ዓመት ይርጋ እንደሚታገዱ የሚደነግግ ነው፡፡ የመሬት ይዞታ ክርክር ደግሞ በባህሪው ከውል የሚመነጭ ሳይሆን ከሕገ-ወጥ ይዞታ ወይም ንጥቂያ የሚመነጭ ነው፡፡ ሆኖም ችሎቱ ይህንን ክፍተት ያገናኘው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የውል ደንቦች ከውል ውጭ በሆኑ ግዴታዎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሕገ-ወጥ የመሬት ያዥ ያለበት "ግዴታ" ምን ዓይነት እንደሆነ (ከሕገ-ወጥ ድርጊት ወይስ ያለአግባብ ከመበልፀግ የመነጨ መሆኑን) ችሎቱ በግልጽ አላብራራም፡፡ እንዲሁም በፍ/ህ/ቁ 1846 መሠረት የይርጋው መቆጠር መነሻ ጊዜ ከመቼ እንደሚጀምር፣ በአንቀጽ 1851 መሠረት የይርጋ መቋረጥ እንዴት እንደሚስተናገድ፣ እና በፍ/ህ/ቁጥር 1854 መሠረት መጥፎ ልቦና (Bad faith) ያለው ሰው እንኳን በይርጋው መጠቀም የሚችል መሆኑ በመሬት ንጥቂያ ላይ የሚያመጣው ህጋዊ ውጤት/ ተፅዕኖ መኖር ያለመኖሩን በችሎቱ ትንታኔ ሥር በሰፊው ያልተዳሰሱ ግን መሰረታዊ የሆኑ የህግ ጥያቄዎች ሆነው አልፈዋል፡፡
ክፍል ስድስት፡ ስለ አዲሱ ትርጉም ጥንካሬዎች
የሰባት ዳኞች ችሎት የሰጠው ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ የንብረት ሕግ ስነ ህግ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው በርካታ ጥንካሬዎችን ይዟል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ችሎቱ የፍትሐብሔር ሕጉን እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥትን የመሬት መብት ስሪት በአግባቡ በማዋሃድ የግል ባለቤትነትን እና የመሬት ይዞታ መብትን በጥልቀት ለመለየት መቻሉ ሊደነቅ የሚገባው ሕገ-መንግሥታዊ ትንታኔ ነው፡፡ በተጨማሪም በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉምን ሙሉ በሙሉ ከመሻር ይልቅ በሚገባው የሕግ አውድ (በቤት ባለቤትነት ላይ) ብቻ እንዲወሰን በማድረግ ትክክለኛ የአስገዳጅ የህግ ትርጉም አስተዳደር/አተገባበርን ለማሳየት ችሏል፡፡ እንዲሁም የባለቤትነትን እና የይዞታ መብትን ማምታታት በሰ/መ/ቁጥር 210477 የተሰጠውን መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በአግባቡ በማረም ለአስገዳጅ የሕግ ትርጉም ስርዓት ጥራት እና ታዓማኒነት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ችሎቱ የከተማ መሬት መብቶችን ተራ የውል ግንኙነት ሳያደርግ ከሁሉም ሰዎች ልንጠይቃቸው የምንችላቸው ተጨባጭ መብቶች (In rem) መሆናቸውን ማረጋገጡ እና ጉዳዩን በ7 ዳኞች በማየት ተቋማዊ ቅቡልነትነን (Institutional Legitimacy) ማጠናከሩ የውሳኔው ዐበይት ጥንካሬዎች ናቸው፡፡
ክፍል ሰባት፡ አዲሱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ እና አዋጅ ቁጥር 1324/2016፡ የሕግ በጊዜ አተገባበር እና የአመሳስሎሽ ትርጓሜ መነጽር የተደረገ ዳሰሳ
7.1 መግቢያ
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ ቁልፍ ትርጉሙ (Ratio decidendi)፤ የከተማ መሬት ይዞታን ሕገ-ወጥ ከሆነ መንገድ ከያዘው ሰው ላይ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዳል የሚለው ሲሆን ፣ "የሕግ በጊዜ አተገባበር" (Intertemporal law፤ ሕጎች በጊዜ ሂደት ያላቸውን ተፈፃሚነት የሚገዛ መርህ) እና "የአመሳስሎሽ ትርጓሜ" (Analogical reasoning) ተቀራራቢ የሕግ ድንጋጌዎችን በመጠቀም የሕግ ክፍተትን የመሙላት ሥነ-ዘዴ) በሚሉት ሁለት መነጽሮች ሲመረመር እጅግ አሳማኝ የሆኑ አካዳሚያዊ እና ተግባራዊ ጥያቄዎችን ሊስነሳ የሚችል ነው፡፡ ይህ አዲስ አስገዳጅ ውሳኔ እና ከእርሱ በፊት ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም የወጣው የፌዴራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016. መገጣጠም፣ የችሎቱን ሥነ-ሥርዓታዊ ትክክለኛነት እና የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) ምርጫዎች ለየብቻ እና በሂሳዊ መንገድ እንድንገመግም ሰፊ የትንታኔ መደላድል የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡ በዚህ ረገድ ሊደረግ የሚችለው ትንታኔ የጉዳዩን ፍሬ-ነገሮች፣ የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 ድንጋጌ አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች (በተለይም የይርጋ እና የሽግግር ድንጋጌዎችን)፣ እና የፍትሐብሔር ሕጉን የይርጋ ማዕቀፍ መሠረት በማድረግ ሊከናወን የሚችል ነው፡፡
በሌላ በኩል ውሳኔው አንዳንድ ድክመቶች እና ቀጣይ ማብራሪያ የሚሹ ክፍተቶችም የሚታዩበት መሆኑን የግል ምልክታ አድርጌአለሁ፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ በከተማ መሬት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የተሰጠው ትንታኔ አጠር ያለ እና ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሻ ነው፡፡ ይህንን ይርጋ ተግባራዊ ማድረግ በተለይም ከአገር ውጭ በነበሩ ወይም በተለያዩ አቅም በሚያሳጡ ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ከፖሊሲ አኳያ አልተገመገመም፡፡ እንዲሁም በሰ/መ/ቁጥር 43600 የተሰጠውን የህግ ትርጉምን በተመለከተ "ተፈፃሚ ለማድረግም ሆነ ተቃርኖ አለው ለማለት አልተቻለም" የሚለው የችሎቱ አገላለጽ የተወሰነ ብዥታን የሚፈጥርና ይበልጥ ግልጽ ቢደረግ ይመረጥ የነበረ ነው፡፡ በዚሁ አስገዳጅ ውሳኔ ውስጥ በሌሎች ልዩ ህጎች የተመለከቱትን የይርጋ ድንጋጌዎችን በሚመለከት የተቀመጠውን አገላለፅ መጠቀም ያልተቻለበትን አግባብ ውሳኔው አያሳይም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመፋለም ክስ ከመሬት ጋር እንደማይሄድ ከተገለጸ በኋላ፣ በትክክል ክሱ በምን ዓይነት የክስ ምክንያት (Cause of action) መቅረብ እንዳለበት ግልጽ አቅጣጫ አለመቀመጡ ለባለሙያዎች ክፍተት ትቷል፡፡ ከገጠር መሬት አዋጅ ድንጋጌዎች ጋር በማነፃፀር ለከተማ መሬት ተመሳስሎሽ ትንታኔ (Analogical reasoning) ያልተጠቀመበትን አግባብም መኖሩን ውሳኔው ማሳየቱን ችሎቱ እንዲህ አይነት የህግ ትርጉም ስልት ተግባር ላይ ለማዋል/ለመውሰድ የነበረውን መልካም አጋጣሚ ማምከኑን የሚያሳይ ነው፡፡ እንዲሁም ቅን ልቦ የሌለው ወይም መጥፎ ልቦና (Bad faith) ያለው የመሬት ነጣቂ የ10 ዓመት ይርጋን ተገን አድርጎ መብት ሊያገኝ የሚችልበትን የፍ/ህ/ቁጥር 1854 ድንጋጌ አንድምታ ችሎቱ አለመመርመሩ እንደ ውሳኔው ድክመቶች ሊነሱ የሚችሉ ነጥቦች ይመስሉኛል፡፡
7.2 አዲሱን ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያለመተግበር ትክክለኛነት፡ የሽግግር ድንጋጌዎችን በጥብቅ መከተል
ከላይ እንደተጠቀሰው በፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥርዓት እና በሕግ ትርጓሜ መሠረታዊ መርሆች መሠረት፣ አዲስ የወጣ መሰረታዊ ሕግ (Substantive law) የሕግ አውጪው በግልጽ ካልደነገገ በስተቀር ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም፡፡ ይህ ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አለመሥራት መርህ (lex prospicit, non respicit) የሕግ ተገማችነት (Legal certainty) የጀርባ አጥንት ሲሆን፣ የተከራካሪ ወገኖች መብት እና ግዴታ የሚገዛው ድርጊቱ በተፈጸመበት ወይም ቢያንስ ክርክሩ በፍርድ ቤት በተጀመረበት ጊዜ በነበረው ሕግ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አሁን በተያዘው ጉዳይ ይህ መርህ እጅግ ግልጽ በሆነ መንገድ ይሠራል፡፡ ተጠሪ (ከሳሽ) ክሳቸውን ያቀረቡት ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.
ሲሆን፣ የክሱ መነሻ (ሕገ-ወጥ የመሬት ይዞታ ንጥቂያ) ተከሰተ የተባለው ደግሞ በ2011 ዓ.ም. (ወይም አመልካች እንደሚሉት በ1980 ዓ.ም.) ነው፡፡ በአንፃሩ አዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 ፀድቆ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ የወጣው በነሐሴ 08 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው፡፡ ይህም ማለት ክርክሩ ከተጀመረና በተለያዩ የፍርድ ቤት እርከኖች ሲንከባለል ከቆየ ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አዋጁ ራሱ ይህንኑ ሁኔታ የሚገዛ ግልጽ የሽግግር ድንጋጌ (Transitional provision) የያዘ መሆኑ ነው፡፡ የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 65(1) በማያሻማ ቋንቋ እንዲህ ይደነግጋል፡- "የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች ይህ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት… ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር እየተደረገባቸው ባሉ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም"፡፡ ይህ ድንጋጌ አዲሱ ሕግ፤ በአዋጁ የተካተቱ ማናቸውንም የይርጋ ጊዜያት ጨምሮ፣ ወደፊት ብቻ የሚሠራ እንጂ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩ ጉዳዮችን ወደኋላ ተመልሶ እንደማያካትት የሕግ አውጪው የሰጠው ግልጽ መመሪያ ነው፡፡
ይህ የሽግግር ድንጋጌ በቀጥታ አግባብነት ያለው፣ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 64(2) ለመሬት ማስለቀቅ ክስ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ስለሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ለዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት ቢኖረው ኖሮ ውጤቱን ሊቀይረው ይችል ነበር፡- ማለትም ፍርድ ቤቱ በተገበረው የ10 ዓመት ይርጋ ታግዷል የተባለው የተጠሪ ክስ፣ የይርጋው መቆጠር መነሻ ጊዜ አሰላል ታይቶ በ15 ዓመቱ የይርጋ ጊዜ ሥር ሊድን (ሊቀጥል) ይችል ነበር፡፡ ሆኖም ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ይህንን አዲስ የ15 ዓመት የይርጋ ጊዜ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ባለ ጉዳይ ላይ ተግባራዊ አለማድረጉ ፍፁም ትክክል ነው ሊባል የሚችል ነው፡፡ እንዲያውም በሥነ-ሥርዓት ደረጃ ሲታይም አስገዳጅነት የነበረው ተግባር ነው፡፡ ይህን አድርጎ ቢሆን ኖሮ፣ አጠቃላይ የሆነውን ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አለመሥራት መርህን እና የአንቀጽ 65(1)ን የተለየ የሽግግር መመሪያ በጣሰ ነበር፡፡
ስለሆነም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የተከተለው አካሄድ መገምገም ያለበት ክሱ በቀረበበት ጊዜ (በ2013 ዓ.ም.) በነበረው የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ ነው፡፡ በዚያን ወቅት፣ የከተማ መሬት ይዞታን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን በተመለከተ የተለየ የይርጋ ጊዜ ባለመኖሩ የተፈጠረውን የሕግ ክፍተት ለመሙላት በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የነበሩት አማራጮች፣ የፍትሐብሔር ሕጉ (በተለይም አንቀጽ 1677 እና 1845)፣ ወይም ደግሞ ቀድሞ የነበረው የገጠር መሬት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 456/1997) ብቻ ነበሩ (የኋለኛው አዋጅም ቢሆን በሰበር መ/ቁ 69302 እንደተረጋገጠው ለዚህ ክስ የሚሆን ግልጽ የይርጋ ጊዜ አላስቀመጠም ነበር)፡፡ ችሎቱ ክፍተቱን ለመሙላት የፍ/ህ/ቁ 1677(2) እና 1845ን (ጠቅላላ የ10 ዓመት ይርጋን) የመረጠ ሲሆን፣ ይህ ምርጫ የተደረገው በወቅቱ በነበረው የሕግ ሥርዓት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ ለገጠር መሬት ክሶች የተለየ እና የረዘመ የይርጋ ጊዜ ማውጣቱ የችሎቱን ውሳኔ ወደኋላ ተመልሶ ሕገ-ወጥ አያደርገውም፡፡ ይልቁንም፣ ፍርድ ቤቱ ገና ላልወጣ ሕግ እውቅና ሰጥቶ ወደኋላ ተግባራዊ አለማድረጉ የዳኝነት ሥልጣን ያለበትን የጊዜ ገደብ መረዳቱን እና የሕግ አውጪውንና የሕግ ተርጓሚውን የሥልጣን ክፍፍል ማክበሩን ያሳያል፡፡ በመሆኑም ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የሕግን በጊዜ አተገባበር (Intertemporal law) መርህ የተገበረበት መንገድ ጉድለት የለሽ ነው፡፡ ችሎቱ አግባብነት ያለውን የጊዜ ማዕቀፍ በትክክል ለይቷል፤ ክሱ በቀረበበት ጊዜ የነበረውን ሕግ ተግብሯል፤ እንዲሁም ከዓመታት በኋላ የሚወጣን ሕግ አስቀድሞ ከመገመትና ከመተግበር ታቅቧል ለማለት ያስደፍራል፡፡
7.3 የአመሳስሎሽ ትርጓሜ ችግር፡ የሕግ ክፍተትን ለመሙላት በተመረጠው ምንጭ ላይ የታየ የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መዛባት
ምንም እንኳን ችሎቱ የሕግን በጊዜ አተገባበር መርሆችን የተከተለበት መንገድ ተገቢነት ያለው ቢሆንም፣ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ (Analogical) ድልድይ ግን ቀጣይነት ያለው አካዳሚያዊ ክርክር የሚሻ ከባድ የሕግ ፍልስፍና ጥያቄን ማስነሳቱ አይቀሬ መስሎ ታይቶኛል፡፡የዚህ ሂሳዊ ግምገማዬ መነሻም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት (Gap-filling) ጥረት ማድረጉ አይደለም፤ ለከተማ መሬት ክስ የተለየ ይርጋ ባለመኖሩ ይህን ማድረጉ ተገቢና አስፈላጊ ነበር፣ ነገር ግን ትችቱ የሚያነጣጥረው በአመሳስሎሽ የወሰደውን የይርጋ ጊዜ ባመጣበት የተለየ ምንጭ ላይ በማተኮር ነው፡፡ ችሎቱ የከተማ መሬት ይዞታ ክርክርን የሚገዛ የይርጋ ጊዜ በሕግ አለመኖሩን ሲገነዘብ፣ ከፍትሐብሔር ሕጉ ሦስተኛ መጽሐፍ (ስለ ንብረት ሕግ) በመውጣት፣ ወደ አራተኛው መጽሐፍ (ስለ ግዴታዎች) ተሻገረ። በዚያም የውል ሕግ ደንቦች ከውል ውጭ በሆኑ ግዴታዎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ የሚደነግገውን አንቀጽ 1677(2) ድንጋጌን እንደ ማሻገሪያ ድልድይ በመጠቀም በፅሑፍ አቀማመጡ ውልን ለመፈፀም፣ ላለመፈፀም ወይም ለማፍረስ ለሚቀርቡ ክሶች የተዘጋጀውን በቁጥር 1845 ድንጋጌ ሥር የሚገኘውን አጠቃላይ የ10 ዓመት ይርጋ ተግባራዊ አድርጎታል። ይህ አካሄድ ከዚህ ቀደም ለገጠር መሬት ክርክሮች በሰበር መ/ቁ 69302 ከተወሰደው የትንታኔ መንገድ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው፡፡
ሆኖም የሕግ አውጪው በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/2016 የገጠር መሬትን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስን የይርጋ ጊዜ በተመለከተ በራሱ ጊዜ ምላሽ ሲሰጥ፣ በአንቀጽ 64(2) ሥር ያስቀመጠው ገደብ 15 ዓመት እንጂ 10 ዓመት አልነበረም፡፡ ይህ የሕግ አውጪው ምርጫ በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ለመሬት ማስለቀቅ ክሶች ተገቢ ነው ብሎ ያሰበው የጊዜ አድማስ ፍርድ ቤቱ በአመሳስሎሽ ከመረጠው የጊዜ ገደብ በእጅጉ የተለየ መሆኑን ያሳያልና፡፡ ከዚህም በላይ፣ የሕግ አውጪው የ15 ዓመትን ጊዜ መምረጡ የዘፈቀደ አልነበረም፡፡ ይህ ጊዜ በፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1168 ሥር የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተከታታይ ይዞታ እና ግብር በመክፈል (Adverse possession) ባለሀብት ለመሆን ከሚያስፈልገው የ15 ዓመት ጊዜ ጋር በትክክል ይገጠማል፡፡ ይህ መመሳሰል በግልጽ የሚያሳየው፣ የሕግ አውጪው የመሬት ማስለቀቅ ክስ ይርጋን ከንብረት ሕጉ የይዞታ መብት አሰጣጥ ጋር በማዛመድ (Calibrating) በንብረት መብት ማዕቀፍ ውስጥ ውስጣዊ ወጥነትን መፍጠሩን ነው፡፡
ይህ ምልከታ አንድ መሠረታዊ የስነ-ዘዴ (Methodological) ጥያቄን ቁልጭ አድርጎ ያጋልጣል፡፡ ይኸውም ችሎቱ የከተማ መሬት ማስለቀቅ ክስን (ወደ አንቀጽ 1168 የ15 ዓመት ይርጋ ከሚያመላክተው) የንብረት ሕግ አሠራር ይልቅ፣ (በአንቀጽ 1845 ወደ 10 ዓመት የሚያወርደው) የውል ግዴታ ጋር ማመሳሰል ለምን መረጠ? ጥያቄው አካዳሚያዊ ብቻ አይመስለኝም፡፡ በሲቪል ሎው የሕግ ሥነ-ዘዴ መሠረት፣ አንድ ፍርድ ቤት በአመሳስሎሽ ትርጓሜ የሕግ ክፍተትን ሲሞላ፣ አመሳስሎሹ መወሰድ ያለበት በጣም የጠበቀ የቅርብ ዝምድና ካለው የሕግ ማዕቀፍ (Nearest cognate legal regime)፣ ማለትም በውስጣዊ መርሆች፣ ዓላማዎች እና መዋቅር ከዋናው ጉዳይ ጋር እጅግ ከሚቀራረበው የሕግ
አካል ሊሆን እንደሚገባው ይታወቃል፡፡ የመሬት ይዞታ መብት (Holding rights)፣ የሰባት ዳኞች ችሎት ራሱ እንዳመነው፣ ተጨባጭ፣ የሚመዘገቡ፣ የሚተላለፉ እና መያዣ ሊሆኑ የሚችሉ፣ ከሁሉም ስዎች ልንጠይቃቸው የምንችላቸው (In rem) የንብረት መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች ከግለሰቦች ጋር ብቻ ከሚያያዙ (Personal, inter partes) እና ፍጹም የተለየ መርህ ካላቸው የውል ግዴታዎች ጋር በመደባቸው አይገናኙም፡፡ አንድ ሕገ-ወጥ የመሬት ያዥ መሬቱን የመመለስ ግዴታ ያለበት፣ በነገር ላይ ያለን (In rem) መብት በመጣሱ እንጂ የውል ቃልን በማፍረሱ (Breach of contractual promise) አይደለም፡፡
ይህ የሕግ ባህሪ ታሳቢ ሲደረግ፣ ይበልጥ ፅንሰ-ሐሳባዊ ወጥነት (Doctrinal coherence) ያለው የአመሳስሎሽ ምንጭ ሊሆን የሚገባው የፍትሐብሔር ሕጉ የንብረት ድንጋጌዎች፤ በተለይም በአንቀጽ 1168 ሥር ያለው የ15 ዓመት ማዕቀፍ እንጂ የአራተኛው መጽሐፍ የውል ግዴታዎች ክፍል አልነበረም፡፡ የፍ/ህ/ቁ 1168 ድንጋጌ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለ15 ዓመት ከነግብሩ የያዘ ሰው የንብረቱ ባለቤት እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው በኩል ያለውን አመክንዮ ስናይ (ከመብቱ ለተነጠቀው ሰው አኳያ)፣ ንብረቱን በሕገ-ወጥ መንገድ የተነጠቀ ሰው መብቱን ለማስመለስ የሚችለውም በተመሳሳይ የ15 ዓመት ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሳል፡፡ ይህ ሚዛናዊ የሆነን ማዕቀፍ ይፈጥራል፡፡ በሌላ አገላለፅ ሕገ-ወጥ ያዡ መብት ለማግኘት 15 ዓመት ያስፈልገዋል፤ መብቱ የተነጠቀው ሰው ደግሞ መብቱን ለማስመለስ 15 ዓመት አለው ማለት ነው፡፡ በአንፃሩ ሰበር ችሎቱ የ10 ዓመቱን የውል ይርጋ መተግበሩ መዋቅራዊ አለመመጣጠንን (Asymmetry) የሚፈጥር ነው፡፡ ምክንያቱም ሕገ-ወጥ ያዡ ባለመብት ለመሆን አሁንም በአንቀጽ 1168 መሠረት 15 ዓመት ሲያስፈልገው፣ መብት የተነጠቀው ሰው ግን ከንብረት ሕጉ መዋቅር ጋር ምንም ዓይነት መዋቅራዊ ዝምድና በሌለው ሕግ መብቱን በ10 ዓመት ብቻ ያጣል የሚል መልዕክት አለው ማለት ነው፡፡
የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋ ማውጣቱ፣ ከላይ ለተነሳው ሂሳዊ ትንታኔ ከፍ ያለ ዋጋ ያለውን የማጠናከሪያ ድጋፍ የሚሰጥ ሁኖ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን ችሎቱ የሕግ አውጪውን ቀጣይ ውሳኔ አስቀድሞ ማወቅ ባይችልም፣ የሕግ አውጪው የወሰደው ምርጫ ግን ለመሬት ማስለቀቅ ክርክሮች ትክክለኛው የፅንሰ-ሐሳብ (የዶክትሪን) መሠረት የፍ/ህ/ቁጥር 1168 ድንጋጌ የንብረት ሕግ አመክዮ እንጂ የቁጥር 1845 ድንጋጌ የውል ሎጂክ አለመሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የሕግ አውጪው የይርጋ ሥርዓቱን ከውል ይልቅ ከንብረት ሕግ ማዕቀፍ ጋር ማጣመሩ የሚያሳየው፣ የችሎቱ የአመሳስሎሽ ድልድይ በፅሑፋዊ ትርጓሜ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን (Doctrinally suboptimal) ነው፡፡
በመሆኑም አዲሱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ (ለከተማ መሬት ክስ የ10 ዓመት ይርጋን ማስቀመጡ) እና ከእርሱ በፊት የወጣው አዋጅ ቁጥር 1324/2016 (በአንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉ) መገጣጠም፣ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግና የአስገዳጅ የህግ ትርጉም ላይ ያልታሰበ እና ከፍተኛ አንድምታ ያለው የይርጋ ጊዜ መከፈል (Bifurcation of limitation periods) ይዞ ተከስቷል፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን በተጨባጭ ባለው ነባራዊ የሕግ ማዕቀፍ መሠረት፡-የይዞታ መብቱ በሕገ-ወጥ ያዥ የተጣሰበት የገጠር መሬት ባለይዞታ፣ መብቱን ለማስመለስ የሚያስችል የ15 ዓመት ጊዜ አለው (በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) መሠረት) ሲኖረው ፍጹም ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ የከተማ መሬት ባለይዞታ ግን በአዲሱ የሰበር ውሳኔ እና በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677(2) እና 1845 ደንጋጌዎች መሠረት የ10 ዓመት ጊዜ ብቻ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
ይህን ልዩነት በጠንካራ መርህ ላይ ተመሥርቶ ለማስረዳትና አሳማኝ ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ ምክንያቱም የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ይዞታ መብቶች የሚመነጩት ከአንድ ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት፤ ማለትም መሬት (የገጠርም ሆነ የከተማ) የመንግስትና የሕዝብ ንብረት መሆኑን ከሚያውጀውና የግል ባለቤትነትን ከሚከለክለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(3) ነውና፡፡ የመብቱ ባህሪ (ከባለቤትነት ያነሰ ነገር ግን በነገር ላይ ያለ ከሁሉም ሰዎች ልንጠይቀው የምንችለው (In rem) ተጨባጭ የንብረት መብት መሆኑ) መሬቱ የሚገኘው በከተማ ክልል ውስጥ ሆነም በገጠር፣ በተጠቃሹ ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ዕይታ አንድ ዓይነት ነው፡፡
የሕገ-መንግሥታዊ መሠረቱ አንድ ዓይነት ከሆነ፣ ለባለይዞታዎች የሚሰጠው የሕግ ከለላም በመርህ ደረጃ አንድ ዓይነት ሊሆን ይገባል፡፡ ለገጠር መሬት ባለይዞታ 15 ዓመት እየተሰጠ የከተማውን ባለይዞታ በ10 ዓመት መገደብ ምክንያታዊ የሆነ የፖሊሲ መሠረት (Rational policy basis) የሌለው ልዩነትን መፍጠር ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ሰባት ዳኞች የተሰየሙበት ችሎት የተቃረኑ ውሳኔዎችን በማረም ሊያመጣው የፈለገውን የሕግ ወጥነት (Doctrinal consistency) የሚሸረሽር ነው፡፡
አንድ ሰው የከተማ እና የገጠር መሬት የተለያዩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች እንዳላቸው፣ በተለያዩ የቁጥጥር ሥርዓቶች እንደሚመሩ፣ እና የክርክሮቹም ተጨባጭ ሁኔታዎች እንደሚለያዩ በማንሳት፣ ይህ ልዩነት የተለያየ የይርጋ ጊዜን ተገባራዊ ማድረግ እንደሚችል ይሞግት ይሆን ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ መከራከሪያ፣ የከተማ መሬት የይዞታ ሥርዓት ከገጠሩ ይበልጥ መደበኛ፣ በሰነድ የተደገፈ፣ እና በአስተዳደር ሥርዓት የተደራጀ ነው የሚለውን መደበኛ አስተሳሰብ ወደ ጎን ትቶ፣ የከተማ ባለይዞታ መብቱን ለመጠየቅ ከገጠሩ ባለይዞታ ያነሰ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባው ለምንድን ነው? የሚለውን አሳማኝ በሆነ መንገድ ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እንዲያውም፣ በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ያለው ሰፊ ኢ-መደበኛነት እና የሰነድ አያያዝ ክፍተት፣ መረጃዎች በገጠሩ አካባቢ ቶሎ ስለሚጠፉ፣ ለገጠር መሬት ክስ ከከተማው ያጠረ (ያልረዘመ) የይርጋ ጊዜ ሊያስፈልግ ይችላል ወደሚል ንድፈ-ሐሳባዊ መከራከሪያ ሊያመራን ይችላል፡፡ አሁን በህጉና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም የተወለደው ዥንጉርጉር ሥርዓት ማለትም ገጠር 15 ዓመት፣ የከተማ 10 ዓመት ይርጋ ጊዜ እንዲሆን የተደረገበት ኩነት ይህንን ሎጂክ/አመክንዮ/ የተገላቢጦሽ ያደርገዋል፡፡
7.4 የክፍል 7 ጥማቂ
የሰባት ዳኞች ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ የሕግን በጊዜ አተገባበር (Intertemporal law) ያስተናገደበት መንገድ እንከን የለሽ (Flawless) ነው ሊባል የሚችል ቢሆንም ችሎቱ ክሱ በቀረበበት ጊዜ (በ2013 ዓ.ም.) የነበረውን የሕግ ማዕቀፍ በመተግበር፣ የሕግ ክፍተቱን በወቅቱ በነበሩ የፍትሐብሔር ሕግ ድንጋጌዎች በመሙላት፣ እና ገና ፀድቆ ላልወጣ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1324/2016) ወደኋላ ተመልሶ የሚሠራ የተፈፃሚነት ኃይል ላለመስጠት መወሰኑ በሥነ-ሥርዓትም ሆነ በመሰረታዊ ህግ ይዘት ችግር የለውም፡፡ በወቅቱ ላልነበረ ሕግ አልተገበርክም ተብሎ ችሎቱን መተቸት የሚቻልበት የህግ አግባብ የለም፡፡ እንዲሁም የአዋጅ ቁጥር 1324/2016 የአንቀጽ 65(1)
የሽግግር ድንጋጌ ራሱ አዲሱ ሕግ በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ እንደማይሠራ በማረጋገጥ ይህንን ያጠናክረዋል፡፡ ሆኖም ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ ድልድይ፤ ማለትም ከአራተኛው መጽሐፍ (የግዴታዎች ሕግ) የተወሰደው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ፣ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉን ስናይ በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ የጎላ ክፍተት ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ የሕግ አውጪው የገጠር መሬት ይርጋን የ15 ዓመት የይዞታ (Adverse possession) ሥርዓት ከሚደነግገው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1168 ጋር ማጣመሩ፣ ለመሬት ማስለቀቅ ክሶች ተፈጥሯዊ እና ፅንሰ-ሐሳባዊ ወጥነት ያለው የአመሳስሎሽ ምንጭ የሚገኘው በንብረት ሕጉ ማዕቀፍ ውስጥ እንጂ በውል ግዴታዎች ማዕቀፍ ውስጥ አለመሆኑን የሚያስገነዝብ ሁኖ ይገኛል ችሎቱ ከፍ/ህ/ቁጥር 1168 ይልቅ አንቀጽ 1845 ድንጋጌን መምረጡ በፅሑፋዊ ትርጓሜ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ ውስጥ ሁለት የተምታታ እና የሚጋጭ ሥርዓት (Dual and conflicting regime) ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ምንም እንኳን ሕገ-መንግሥታዊ መሠረታቸው እና የመብታቸው የሕግ ባህሪ አንድ ዓይነት ቢሆንም፣ የከተማ መሬት ክስ በ10 ዓመት፣ የገጠር መሬት ክስ ደግሞ በ15 ዓመት እንዲታገድ ማድረግ የህግ ባለሙያውንም ሆነ ሌላውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያሳምን ሊሆን አይችልም፡፡
ይህ ሥርዓታዊ አለመጣጣም ከሁለት በአንዱ መንገድ ዕልባት እስካላገኘ ድረስ የኢትዮጵያን የንብረት ሕግ ስነ ህግ እድገና የአስገዳጅ ህግ ትርጉም ወጥነት ግብ በፅኑ መፈተኑን የሚይቀጥል መሆኑ ይገመታል፡፡ ስለሆነም ባለሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት ለከተማ መሬት የሰጠውን አስገዳጅ ትርጉም ከፍ/ህ/ቁጥር 1168 መሰረተ ሃሳብና ከተገቢው የህግ አተረጓጎም ስልት አንፃር በድጋሚ በመገምገም በቅርብ ጊዜ በወጣው የገጠር መሬት ህግ ውስጥ ከተደነገገው የ15 ዓመት ማዕቀፍ ጋር ያጣጥመዋል፣ አለበለዚያ ደግሞ የሕግ አውጪው (ፓርላማው) ከገጠር መሬት ሥርዓት ጋር የተናበበ የይርጋ ድንጋጌን ያካተተ አጠቃላይ የከተማ መሬት አስተዳደር አዋጅ ያወጣል፡፡ ከፍ ሲል ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከላይ ከተጠቀሰው ህገ መንግስቱ ጥበቃ አንፃር አይቶ ህገ መንግስታዊ ትርጉም ሊሰጠበት ይችላል፡፡ ይህ የእርምት እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ለአንድ ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ መብት፤ በከተማ 10 ዓመት፣ በገጠር 15 ዓመት ሊሆን ይገባል ተብሎ የተከፋፈለው የይርጋ ጊዜ በኢትዮጵያ የመሬት ሕግ እና በአስገዳጅ የህግ ትርጉም ስርዓት ላይ ያልተፈታ ፅንሰ-ሐሳባዊ መዛባት (Doctrinal anomaly) ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በችሎቱ ውሳኔ እንደድክመት ሊነሳ የሚችል ተገቢ ምልክታ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡
ክፍል ስምንት፡ አጠቃላይ ማጠቃለያ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰባት ዳኞች ሰበር ችሎት የሰጠው ይህ ውሳኔ ተቃርኖ ያለባቸውን አስገዳጅ የህግ ትርጉሞችን ከማረቅና የስርዓቱን ወጥነትና ተገማችነት ከማስፈን አንፃ እጅግ መሠረታዊ እና አስፈላጊ ቢሆንም በአገሪቱ የንብረት እና የመሬት ሕግ ስነ ህግ ላይ ህገ መንግስታዊ መሰረትን ባልተጎናፀፈ አመክንዮ ተመሳሳይ ጥበቃ ያለውን የባለይዞታነት መብት በተለያዩ የይርጋ ጊዜያት እንዲገዙ ስርዓት ያበጀ በመሆኑ አከራካሪነቱ አይቀሬ ይመስለኛል፡፡ ውሳኔው በቀድሞ አስገዳጅ ውሳኔዎች መካከል የነበረውን ጥልቅ ተቃርኖ ሕገ-መንግሥታዊ መሠረትን እና የፍትሐብሔር ሕግን አግባብነት ያላቸውን መርሆች በሚገባ በመመርመር ተገቢውን የዳኝነት ጥበብ በመጠቀም ለመፈታት የተቻለበት መሆኑ ይታመናል፡፡ በተለይም የባለቤትነት መብትን (Ownership) ከይዞታ መብት (Holding rights) በሚገባ በመለየት፣ ለባለቤትነት የተፈጠሩ የሕግ ማዕቀፎችን የግል የመሬት ባለቤትነት በማይፈቅድ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ በቀጥታ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ የሕግ ትርጉም በኢትዮጵያ የከተማ መሬት ይዞታ ክርክሮች ላይ ፅንሰ-ሐሳባዊ ጥራትን፣ ሥርዓታዊ ወጥነትን እና ተገማችነትን በማምጣት ወደፊት ለሚነሱ የንብረት ሕግ ክርክሮች ጠንካራ መሠረት የሚጥል አንፀባራቂ የዳኝነት አሻራ ነው ተብሎ ቢውሰድ ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ሆኖም ከላይ በክፍል 7 ስር በሰፊው እንደተብራራው ችሎቱ የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት የመረጠው የአመሳስሎሽ ድልድይ፤ ማለትም ከአራተኛው መጽሐፍ (የግዴታዎች ሕግ) የተወሰደው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የ10 ዓመት ይርጋ፣ የሕግ አውጪው ከጊዜ በኋላ በአዋጅ 1324/2016 አንቀጽ 64(2) ለገጠር መሬት ክስ የ15 ዓመት ይርጋን መደንገጉን ስናይ በፅንሰ-ሐሳብ (በዶክትሪን) ደረጃ የጎላ ክፍተት ያለበት ሆኖ ይታያል፡፡ ስለሆነም ችሎቱ በራሱ አነሳሽነት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይስ የፌዴፌሬሽን ምክር ቤት? ትክክለኛውን መስመስር ይለዩ ይሆን? በዚህ ነጥብ ላይ ሁላችንንም ሊያስተምር የሚችል የምርምር ስራ ወይም የውሳኔ ትችት እይታ በዘርፉ በበቁ በአወቁ የአገራችን ምሁራን ሊከናወን እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
አበቃ!!
ተፃፈ በአልማው ወሌ
መጋቢት 04 ቀን 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ማስታወሻ፦ ፅሁፉ ጥብቅ የምርምር ዘዴ በመከተል ያልተከናወነ መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅሁ ለወደፊቱ ግን በዚሁ አርዕስትና ተያያዥ የህግ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪ አምላክ ፍቃዱ ከሆነ ሙያዊ እና አካዳሚያዊ ደረጃውን የጠበቀ ስራ ይዠ ለመቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ማናቸውም ስህተቶች የራሴው መሆናቸው እንዲታወቅልኝም እፈልጋለሁ፡፡
https://www.facebook.com/s...

Comments