4 hours ago
በአቶ ግርማ ዋቄ የሚመራው የኡጋንዳ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር የ982 ሚሊዮን ዶላር ግዙፍ ስምምነት አደረገ
#ethiopia | የኡጋንዳ ብሔራዊ አየር መንገድ 10 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችለውንና 982 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ታሪካዊ የጋራ ስምምነት ከታዋቂው የቦይንግ ኩባንያ ጋር መፈራረሙ ታውቋል።
ይህ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበት ግዢ አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2019 አገልግሎቱን በድጋሚ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የፈጸመው ትልቁ የአውሮፕላን ኢንቨስትመንት ተብሎ ተመዝግቧል።
የስምምነቱ ማጠናቀቂያ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በኢንቴቤ ቤተ መንግሥት የተከናወነ ሲሆን፣ የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በክብር ታዛቢነት ተገኝተዋል።
ይህንን ታላቅ ውል በኡጋንዳ አየር መንገድ ስም የፈረሙት ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ግርማ ዋቄ ሲሆኑ፣ በቦይንግ ኩባንያ በኩል ደግሞ የአፍሪካ የሽያጭ ኃላፊው አቶ አንበሴ ይትባረክ ውሉን አጽድቀዋል።
በገንዘብ ሲሰላ በግምት 3 ነጥብ 7 ትሪሊዮን የኡጋንዳ ሺሊንግ የሚያወጣው ይህ የ10 አውሮፕላኖች ግዢ ጥቅል አራት የቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር እና አራት የቦይንግ 737 ማክስ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ያካተተ ነው።
በተጨማሪም አንድ ወደ ጭነት አገልግሎት የተቀየረ ቦይንግ 767 እንዲሁም ሌላ አንድ ወደ ጭነት አጓጓዥነት የተቀየረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በስምምነቱ ውስጥ ተካተዋል።
ይህ የተወሰደው ስትራቴጂካዊ እርምጃ አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች በረራውን በከፍተኛ ደረጃ ለማስፋፋት ከመጣር ባለፈ፣ በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍም ጠንካራና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት ያለውን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ ነው።
በያፌት ገብረሕይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ugandaairlines #boeing #aviationnews #girmawake #business #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments