2 months ago
የተስፋው ቀለም፦ የኢትዮጵያ አዲስ የብልጽግና ስትራቴጂ
**********************
( የዕለቱ መልዕክት)
የአንድ ሀገር መልክዓ-ምድር ሲቀየር፣ ከምድር ገፅታው ጀርባ ያለው የምጣኔ ሀብት የደም ስርም አብሮ ይመታል። ለዘመናት በድርቅ፣ በአፈር መሸርሸርና በተራቆቱ ተራሮች ስትፈተን የኖረችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ታሪኳን በለመለመ አረንጓዴ ቀለም አዲስ ምዕራፍ እየፃፈችው ትገኛለች።
ይህ በአገራችን ምድር ላይ በክንድና በጉልበት እየታየ ያለው አረንጓዴ ማዕበል ተራ የአይን ማረፊያ ወይም የውበት ጉዳይ አይደለም፤ ይልቁንም የሀገራችንን የማክሮ-ኢኮኖሚ መዋቅር ከስር መሰረቱ እያደሰ እና ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነቷን ወደ ላቀ ከፍታ እያሻገረ ያለ ታላቅ ሀገራዊ ተግባር ነው።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከስነ-ምህዳር ጥበቃነቱ እጅግ በላቀ ሁኔታ "ከጥላ ማግኘት ወደ ኪስ ማዳበር" የተሸጋገረ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ሞተር ነው።
ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ አገራዊ የተቀናጁ ሥራዎች የሀገሪቱን የደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ለዚህ እውነታ ህያው ምስክር ነው።
ይህ ስኬት በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብና የሌሎች የኃይል ማመንጫዎቻችን ተፋሰሶች በደን እንዲጠበቁ በማድረግ፣ የደለል አደጋን በከፍተኛ ደረጃ ቀንስቷል፤ የውሃና የኃይል ዋስትናችንንም በዘላቂነት አረጋግጧል።
በሌላ በኩል ቀደም ሲል ወደ ውጭ ይላክ የነበረውን 230 ሺህ ቶን የቡና ምርት በአረንጓዴ አሻራ በተሰራ ጠንካራ ስራ ወደ 475 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉና እንደ አቮካዶ ያሉ ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ያላቸው ፍራፍሬዎች በጥራት ወደ አውሮፓ ህብረት ገበያ መላክ መጀመራቸው ለአገራችን አዲስና አስተማማኝ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ፈጥሯል።
ንቅናቄው እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ አረንጓዴ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የተቀናጁ የግብርና-ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በጥሬ ዕቃ በመመገብ የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ብሔራዊ ንቅናቄን በጽኑ መሠረት ላይ እየደገፈው ይገኛል።
የዚህ ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ፋይዳ ከምጣኔ ሀብት አድማስ አልፎ በዓለም አቀፍ መድረክም አዲስ የፖሊሲ መደራደሪያና የተሰሚነት አቅም ፈጥሯል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት "አረንጓዴነትን" ዋነኛ መመዘኛ ባደረገበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ያሳየችው ቁርጠኝነት በዲፕሎማሲው ረገድ ውጤታማ ፍሬዎችን እያፈራላት ነው።
አገራችን ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤና የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤን ጨምሮ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በስኬት ማስተናገዷ ብሔራዊ ተሰሚነታችን ማደጉን ያሳያል።
የዚሁ ዲፕሎማሲያዊ እምርታ ታላቅ ማሳያ ደግሞ ከ75 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበትን ታላቁን ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) እንድታዘጋጅ ኢትዮጵያ መመረጧ ነው።
ወደ 50 ቢሊዮን ችግኞች የምናደርገው ጉዞም የምስራቅ አፍሪካን መራቆት የመቀልበስ ግብ የሰነቀ ሲሆን፣ ይህም ለአካባቢ ጥበቃ የሚውል አዲስ የ"ችግኝ ዲፕሎማሲ" ስትራቴጂ ወልዷል።
ይህ አካሄድ ከጎረቤት አገራት ጋር የችግኝ ስጦታዎችንና የጋራ ተከላዎችን በማከናወን ቀጣናዊ ትስስርንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር ጠንካራ ድልድይ ሆኗል።
በቢሊዮን ቶን የሚቆጠር የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን የሚምጡት ደኖቻችን፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ ትልቁ የካርቦን ማከማቻ ባለቤት በማድረግ በዓለም አቀፍ ድርድር ላይ የቢሊዮን ዶላር አረንጓዴ የፋይናንስ ፈንድ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችል የካርቦን ገበያ ዕድል እየፈጠሩላት ነው።
በአጠቃላይ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ ዘላቂ ብልጽግናን የምታረጋግጥበት፣ በዓለም መድረክም ክብሯንና ብሔራዊ ጥቅሟን በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ የምታስከብርበት የትውልድ አሻራ ነው፤ ይህንኑ አኩሪ ውጤት ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ደግሞ የሁላችንም ታሪካዊ ኃላፊነት ነው!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #greenliving #አረንጓዴአሻራ

የተስፋው ትውልድ አሻራ፡ ከሀገራዊ ራዕይ እስከ ዓለም አቀፍ ልዕልና
**************
ሀገር ማለት የትናንት ታሪክ፣ የዛሬ ጥረት እና የነገ ተስፋ ድምር ውጤት ናት። ዛሬ የምናሳርፈው እያንዳንዱ አሻራ ለነገው ትውልድ የምናወርሰው የእድገት እና የሰላም ተሥፋ ነው።
በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ይፋ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ ሀገራዊ እይታ መፍጠር ችሏል። የኢትዮጵያ መንግስት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ የወሰደው ቁርጠኝነት የሚመነጨው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የ"መደመር" ዕሳቤ ነው።
ይህ ዕሳቤ በአረንጓዴ አሻራ በተግባር ሲተረጎም አካባቢን፣ ኢኮኖሚን እና ብሔራዊ ማንነትን በማዋሃድ አዲስ ዓይነት ስነ-ምህዳራዊ የመንግስት አስተዳደር እንዲፈጠር አድርጓል።
ታሪክ ሰሪው የመደመር ትውልድ ደግሞ ይህንን የሀገር ውስጥ ራዕይ ይዞ በመነሳት፣ ታላላቅ ሀገራዊና አህጉራዊ ብሎም ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን በብቃት እየከወነ ይገኛል።
የአረንጓዴ አሻራ ጉዳይ አንድምታው ከችግኝ ተከላ የዘለለ መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ያለው ይህ ትውልድ፣ የራሱን አቅምና ሁለንተናዊ ብቃት በዓለም አደባባይ እያስመሰከረ ነው።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የትናንት የነጻነት አርበኝነታችንን በተፈጥሮ ጥበቃ የምንደግምበት የዘመናችን ድንቅ «ዓድዋ» ነው። ይህ የዘመናችን አድዋ ደግሞ የዛሬውን «የመደመር ትውልድ» የታሪክ አሻራ እና ሁለንተናዊ አቅም የሚፈትን ታላቅ አገራዊ ጥሪ ነው።
የዛሬው የመደመር ትውልድ እውቀቱን፣ ጉልበቱንና ፍቅሩን አስተባብሮ በተከታታይ ዓመታት አገሩ አረንጓዴ እያለበሳት ይገኛል። ዛሬ በእኛ (በመደመር) ትውልድ ጥረት እየተሰራ ያለ ስራ አገራችን የምግብ ዋስትናዋ በዘላቂነት የተረጋገጠና የአየር ንብረት መዛባት የማይበግራት ጽኑ እንድትሆን ያደርጋታል።
"የችግኝ ተከላ ተግባራችን ስለ ዛፎች ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ለትውልድ ጥላ እና ተስፋን ስለመፍጠር ነው።" የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርህ በመከተል እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያሉ የዘመናችንን ሜጋ ፕሮጀክቶች ከደለል የሚታደግ፣ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ፣ በኢንዱስትሪው ለሚፈጠሩ የግብርና ማቀነባበሪያዎች ጥሬ ዕቃ የሚያቀርብ እና በአጠቃላይ በኢኮኖሚ, በልማት እና በማህበራዊ ስነ-ልቦና ላይ ጠንካራ መሠረት የሚጥል ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ነው።
ይህም የመደመር ትውልድ የተፈጥሮ ሚዛንን ከመጠበቅ ባሻገር ሀገራዊ የልማት ምሰሶዎችን እንዴት ማፅናት እንደሚቻል ያሳየበት ህያው ማረጋገጫ ነው።
"ተስፋን እንትከል" ሲባል መሬት ላይ ችግኝ ማፅደቃችን ብቻ ሳይሆን፣ በልጆቻችን እና በቀጣዩ ትውልድ አዕምሮ ውስጥ የሀገር ፍቅርን፣ አብሮነትን እና የማይበገር ጥንካሬን መዝራታችን ነው።
የትናንት ታሪካችን የቱንም ያህል በፈተናዎች የተሞላ ቢሆንም ዛሬ የመደመር ትውልድ በእጆቹ የሚተክለው ተስፋ፣ ለነገው ትውልድ የማያልፍ ጥላ፣ የማይነጥፍ የኢኮኖሚ በረከት እና ቀና ብሎ የሚኮራባት ቅርስ ሆኖ ይፀድቃል። ስለዚህ ተስፋችንን እንትከል፤ የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ ዛሬ በጋራ እንገንባ!
በበረከት ሽመልስ
Ethiopian Broadcasting Corporation #የመደመርትውልድ #ethiopia #greenliving #አረንጓዴአሻራ #ተፈጥሮ #ኢትዮጵያ

Comments