የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ጪሮ በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ እስራኤል መግባታቸውን አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ በእስራኤሉ አቻቸው አይዛክ ኸርዞግ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸውም ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ጪሮ ባወጡት ይፋዊ መግለጫ የሶማሊላንድ ህዝብ ላለፉት 35 ዓመታት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ጠንካራ ሀገር መገንባቱን አስታውሰዋል። "ዓለምን 'ታዩናላችሁ ወይ?' ብለን ጠየቅን፤ ለእዚህ ጥያቄያችን የመጀመሪያዋ መላሽ እስራኤል ነች" በማለት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችበትን ታሪካዊ ክስተት አድንቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህ ጉብኝት በሶማሊላንድ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን አብራርተዋል።
ለመላው የሶማሊላንድ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት የህዝባቸውን ተስፋ እና ምኞት ሰንቀው እንደተጓዙ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ በርካታ ትውልዶች ሀገሪቱን ወደዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ለማድረስ ከፍተኛ ትግል እና መስዋዕትነት መክፈላቸውን አውስተዋል። አክለውም፣ "ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በልበ ሙሉነት፣ በጥበብ እና በቁርጠኝነት እንጠቀምበታለን፤ ሁሌም ቢሆን መመሪያችን የህዝባችን እና የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ነው" ብለዋል።
ሶማሊላንድ ከእስራኤል ጋር በጓደኝነት፣ በትብብር እና በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ የጋራ የወደፊት ተስፋን ለመገንባት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል። "ዛሬ አዲስ ታሪክ እየተጻፈ ነው" ሲሉም መልዕክታቸውን አጠቃልለዋል።
ይህ የፕሬዝዳንት አብዲራህማን ጪሮ የእስራኤል ጉብኝት፣ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ይበልጥ ሊለውጠው እና ሊያጦፈው የሚችል ከባድ ክስተት ነው። እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷ እና የሀገሪቱን መሪ በይፋዊ የስራ ጉብኝት ደረጃ መቀበሏ፣ ሱማሊላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ለማግኘት ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ነው።
በአንጻሩ የሶማሊያ መንግስት ሶማሊላንድን እንደራሱ አካል አድርጎ ስለሚቆጥር እና እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና "በታሪካችን ከታዩት የጨለማ ቀናት አንዱ ነው" በማለት አጥብቆ በማውገዝ ላይ በመሆኑ፣ ይህ ጉብኝት የሞቃዲሾን ቁጣ በእጅጉ የሚቀሰቅስ እና የቀጣናውን የፖለቲካ አሰላለፍ በአዲስ መልክ የሚቀርጽ ታሪካዊ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።

3 hours ago