2 hours ago
ታዋቂዋ የአትሌቶች መፍለቂያ ቦቆጂ ከተማ የልወቅሽ የኢትዮጵያ ክላሲክ 2018 የሩጫ ውድድርን በደመቀ ሁኔታ ማስተናገድ ጀመረች
#ethiopia | የበርካታ የዓለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኖችን በማፍራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀሰው የቦቆጂ ከተማ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመሆን ያዘጋጀውን ልወቅሽ የኢትዮጵያ ክላሲክ ታላቅ የሩጫ ውድድር በዛሬው ዕለት ማስተናገድ ጀምራለች።
ውድድሩ መነሻና መድረሻውን ታሪካዊው የቦቆጂ ስታዲየም ላይ ያደረገ ሲሆን፣ ከ100 በላይ አንጋፋና ፕሮፌሽናል አትሌቶች፣ ከ2 ሺህ 500 በላይ የቦቆጂ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ የተጓዙ ከ70 በላይ የስፖርቱ አፍቃሪያን ተሳታፊ ሆነዋል።
ይህ ትልቅ ስፖርታዊ መርሃ ግብር የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማሳደግ ከሚኖረው ሚና ባሻገር፣ የቦቆጂን ከተማ የቱሪዝም መስህቦችና አቅሞች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኝዎች በሰፊው ለማስተዋወቅ ታላቅ ዕድል የፈጠረ ነው።
የመጀመሪያው ምዕራፉ በደብረ ብርሃን ከተማ ተጀምሮ አሁን በቦቆጂ ይፋዊ ጉዞውን የቀጠለው ይህ መርሃ ግብር፣ በኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም ልማት ላይ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ክስተት ሆኗል።
በዚህ ደማቅ የማስጀመሪያ ዝግጅት ላይ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ፣ የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሒም ከድር እና የቦቆጂ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ብርሃኔ ነገሰ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የቱሪዝም ዘርፍ ተወካዮች፣ ታዋቂ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የብዙኃን መገናኛ ባለሙያዎች በከተማዋ በመገኘት መርሃ ግብሩን ታድመዋል።
#bekoji #ethiopianclassic #greatethiopianrun #sportstourism #tourismethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments