ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ የተባለውን ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ለመቀጠል ካይሮ ገቡ
የኔታ ሚዲያ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ወደ ግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አቅንተዋል።
ይህ ጉዞ ግብፅ እና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በኢትዮጵያ ላይ የጀመሩትን የዲፕሎማሲ እና የደህንነት ከበባ ይበልጥ ለማጥበቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹት ይገኛሉ።
የኤርትራ ማዕከላዊ መረጃ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ በካይሮ ቆይታቸው ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ ጋር የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ትብብር በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ።
ይሁን እንጂ የሁለቱ መሪዎች የውይይት ማዕከል የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ የሱዳን ቀውስ እና የቀይ ባህር ደህንነት መሆናቸው ተገልጿል።
ይህም ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና ለማገዝ እና ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችውን የባህር በር የማግኘት ህጋዊ ጥረት በጋራ ለመቃወም የተወጠነ ስልታዊ ሴራ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው።
ካይሮ እና አስመራ ከዚህ ቀደም ከሞቃዲሾ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ የሶስትዮሽ ጥምረት መፍጠራቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ስብሰባም ይሄንኑ የኃይል አሰላለፍ ለማጠናከር ያለመ ነው።
በተለይም "የቀይ ባህር ደህንነት ጥበቃ የባህር ዳርቻው ባለቤት ለሆኑ ሀገራት ብቻ የተተወ መሆን አለበት" በሚል የሚያነሱት አቋም የኢትዮጵያን ስልታዊ ጥቅም እና የቀጣናውን የጋራ ተጠቃሚነት ያላገናዘበ ይልቁንም ለአካባቢው አለመረጋጋት በር የሚከፍት አካሄድ መሆኑን ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ።

6 days ago