(ዘ-ሐበሻ ዜና) በምርምር እና በስትራቴጂያዊ ትንተና የተደገፈ “የተከዜ ፖለቲካ፤ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ።
የመጽሐፉ ደራሲ ዶክተር ቹቹ አለባቸው ሲሆኑ፣ ደራሲው በአማራና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ትንታኔዎችን በማቅረብ የሚታወቁ ነባር ፖለቲከኛ ናቸው፡፡
ዶክተር ቹቹ በአዲሱ ሥራቸው በተከዜ ተፋሰስ እና በወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምት ቀጠና ዙሪያ የሚታዩ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ፣ ማኅበራዊ እና የደኅንነት ጉዳዮችን በምሁራዊ መንገድ የሚተነትን መሆኑ ተጠቁሟል።
ደራሲው እንደሚገልጹት፣ የተከዜ ተፋሰስ የውኃ ምንጭ ወይም የተፈጥሮ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ከቀጠናዊ የኃይል ሚዛን፣ ከሕዝቦች ማንነት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ስትራቴጂያዊ ቀጠና ነው። መጽሐፉም ይህንን አቀራረብ በመነሻ በማድረግ የአካባቢውን ፖለቲካዊ እውነታ በጂኦ-ፖለቲካ፣ በኃይል፣ በማንነት እና በብሔራዊ ደኅንነት ማዕቀፎች አንጻር ይመረምራል።
መጽሐፉ በተለይ በ2013 ዓ.ም. በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት እንደ መነሻ በመውሰድ፣ የተከዜ ተፋሰስ በሀገሪቱ የደኅንነት አወቃቀር ውስጥ ያለውን ስልታዊ ሚና በዝርዝር ያስረዳል። ደራሲው እንደሚገልጹት፣ የተፋሰሱን ይዞታ መቆጣጠር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት፣ በውኃ ሀብት አስተዳደር እና በቀጠናዊ ግንኙነቶች ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ ያሳድራል።
በአጠቃላይ 20 ምዕራፎችን ያካተተው መጽሐፉ በአራት ዋና ክፍሎች ተዋቅሯል።
የመጀመሪያው ክፍል በጂኦ-ፖለቲካ ላይ ያተኩራል፤ የተከዜ ተፋሰስ ከኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ከዓባይ ተፋሰስ ፖለቲካ እና ከቀጠናዊ የኃይል አሰላለፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ይተነትናል።
ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ኃይልን እንደ ፖለቲካዊ መሣሪያ በመመልከት፣ አካባቢውን መቆጣጠር ለባለቤቱ የሚሰጠውን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ተምሳሌታዊ ጥቅሞች ያብራራል። እንደ መጽሐፉ ገለጻ፣ ተከዜ ተራ የመሬት ክፍል ሳይሆን የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የሚገናኙበት የኃይል መድረክ ነው።
ሦስተኛው ክፍል በማንነት ፖለቲካ ላይ ያተኩራል። በዚህ ክፍል የብሔር ፌዴራሊዝም፣ የሥነ-ሕዝብ ለውጦች፣ የነባር እና የመጤ ትርክቶች እንዲሁም የማንነት ጥያቄዎች በታሪካዊ እና በንድፈ-ሐሳባዊ መሠረቶች ይመረመራሉ።
ደራሲው በወልቃይት፣ በጠገዴ እና በጠለምት አካባቢዎች የተፈጠሩ የማንነት ግጭቶችን እና የሕዝብ አወቃቀር ለውጦችን በሕጋዊ እና በታሪካዊ ማስረጃዎች ተደግፈው መቅረባቸውን ያስረዳሉ።
አራተኛው እና የመጨረሻው ክፍል የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮችን ያዳስሳል። ይህ ክፍል የውኃ ደኅንነት፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት፣ የውጭ ስጋቶች፣ የፌዴራላዊ አንድነት ተግዳሮቶች እና የሰላም ግንባታ አማራጮችን በስፋት ይተነትናል።
በመጨረሻም ለፖሊሲ አውጪዎች እና ለውሳኔ ሰጪዎች የሚጠቅሙ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን ያቀርባል።ከይዘቱ ባሻገር መጽሐፉ የተለያዩ የአገር ውስጥ፣ የቀጠና እና የዓለም አቀፍ ተዋናዮችን ሚና በጥልቀት የሚያብራራ መሆኑ ተገልጿል። የፌዴራል መንግሥት፣ የክልል ፖለቲካ ኃይሎች፣ ጎረቤት አገራት እና በቀጠናው ፍላጎት ያላቸው ዓለም አቀፍ ኃይሎች በተከዜ ፖለቲካ ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ በተለየ ትኩረት ቀርቧል።
ደራሲው መጽሐፉ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለታሪክ ተመራማሪዎች፣ ለደኅንነት ባለሙያዎች፣ ለዲፕሎማቶች እና ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጠቃሚ የማጣቀሻ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል።
የመጽሐፉ ዋና ዓላማም በተከዜ ተፋሰስ ዙሪያ ያሉ ውስብስብ ጉዳዮችን በምሁራዊ እይታ በማቅረብ፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ለአገራዊ አንድነት እና ለጋራ ልማት የሚረዱ የፖሊሲ አማራጮችን ማበርከት መሆኑ ተጠቅሷል።
መጽሐፉ በከፍተኛ የቋንቋ ደረጃ እና በምሁራዊ ጥልቀት የተጻፈ ነው የተባለለት ሲሆን፤ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትንተናዎች ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር ይበልጥ የተሰናሰሉ፣ መሆኑ ሥራው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ዶክተር ቹቹ አለባቸው እንዳረጋገጡት፣ “የተከዜ ፖለቲካ፤ ኃይል፣ ማንነትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት” የተሰኘው መጽሐፋቸው የፊታችን ዕረቡ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በገበያ ላይ ይውላል፡፡

2 days ago