(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የካርሎ አንቸሎቲ የጋዜጣዊ መግለጫ ሊጠናቀቅ ሲል.. ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ሁሌም በሚታወቁበት የሰከነ እና ጥልቅ በሆነ መንገድ ማንም ሊያነሳው ያልደፈረውን ጉዳይ አንስተው መናገር ጀመሩ። በግንቦት ወር መገባደጃ ላይ ብራዚል ከፓናማ ጋር ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አስቀድሞ፣ አዲሱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አንቸሎቲ እንዲህ አሉ፡...
"ሰዎች አሁን ላይ ብራዚል ኮከብ ተጫዋች የላትም ሲሉ እሰማለሁ። ምናልባት እውነት ሊሆን ይችላል። እንደ ፔሌ፣ ሮማሪዮ ወይም ሮናልዶ አይነት ተጫዋች ላይኖረን ይችላል፤ ነገር ግን የጋራ ኃላፊነት ስሜት ሊኖረን ይችላል፣ ያ ደግሞ እጅግ ኃይለኛ መሳሪያ ነው።"
ይህ የአንቸሎቲ ንግግር የብዙዎችን ቀልብ የሳበው፣ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ቪኒሽየስ ጁኒየር እስካሁን ድረስ የብሔራዊ ቡድኑ የማይነካ መሪ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ... በተግባር ግን ያ ባለመሆኑ ነው። በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በክሮኤሺያ በመለያ ምት ተሸንፈው ከወጡ ከአራት ዓመታት በኋላም.... በ25 ዓመቱ አጥቂ ላይ አሁንም በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ።
ይህ ጥርጣሬ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ለማሳየት... በመጋቢት ወር ብራዚል በፈረንሳይ 2ለ1 መሸነፏን ተከትሎ፣ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ "ቪኒሽየስ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ መካተት ይገባዋል ወይ?" የሚል የከረረ ክርክር እስከመክፈት ደርሷል። በክለብ ደረጃ ለቪኒሽየስ እጅግ ስኬታማ ጊዜያትን ያመጣው እና ትልቅ ተጽዕኖ የፈጠረው አንቸሎቲ ብሔራዊ ቡድኑን ቢረከብም፣ "ቪኒሽየስ በሪያል ማድሪድ የሚያሳየውን ድንቅ አቋም ለምን በብሔራዊ ቡድን መድገም አቃተው?" የሚለው ጥያቄ አሁንም እንደ ጥላ እየተከተለው ነው።
በእርግጥም ቪኒሽየስ በዚህ የዓለም ዋንጫ ዑደት ውስጥ በብሔራዊ ቡድኑ ብዙ የግብ ተሳትፎ ያደረገ ተጫዋች ነው፤ ሆኖም በ28 ጨዋታዎች 7 ግቦችን እና 6 አሲስቶችን ብቻ ማስመዝገቡ ለሱ ደረጃ አነስተኛ ነው። በ2018 እና 2022 የዓለም ዋንጫዎች የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ክሌበር ዣቪየር ይህንን ሲያብራራ "በክለብ ደረጃ የምታሳየውን አቋም በብሔራዊ ቡድን መድገም እጅግ ከባድ ነው። ክለብ ውስጥ የተለየ ልምምድ፣ የተለየ የጨዋታ መንገድ እና የዕለት ተዕለት ቆይታ አለ። ግልጹ ምሳሌ የሜሲ እና የአርጀንቲና ጉዳይ ነው። ሜሲ ሁሌም ይተች ነበር፣ ሊሳካለት የቻለው በ2022 ነው። ምክንያቱም አርጀንቲና ቡድን መገንባት ስለቻለች ነው። ለተጫዋች ተገቢውን መዋቅር መፍጠር ወሳኝ ነው" ይላል።
ቪኒሽየስም ይህንን እውነታ አይክድም። በቅርቡ ለካዜ ቲቪ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ፣ "በክለብ ውስጥ በየሶስት ቀኑ አዲስ ዕድል አለ። ከ10 ጨዋታዎች ሁለቱን መጥፎ ብጫወት ማንም ብዙ አያወራም። በብሔራዊ ቡድን ግን በአንድ ጨዋታ እና በሌላኛው መካከል ያለው ጊዜ ረጅም ነው፤ ጫናውም ሁልጊዜ ከፍተኛ ነው። ሰዎች ሁሌም በምርጥ አቋሜ ላይ እንድገኝ ይጠብቃሉ። ነገር ግን ወደ ዓለም ዋንጫ ሄጄ አራት ወይም አምስት ግቦችን አግብቼ ሻምፒዮን ብንሆን፣ ታሪኩ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። ያኔ መጥፎ በተጫወትኩባቸው ጨዋታዎች ላይ እንኳን ለዓለም ዋንጫ እየተዘጋጀሁ እንደነበር አድርገው ያወራሉ" ብሏል።
ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን መጫወት ለቪኒሽየስ ቀላል ሆኖ አያውቅም። አንድ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንዳሉት፣ የ2024 የባሎን ዶር ሁለተኛ ደረጃን የያዘው ቪኒሽየስ፣ "ሁሌም ዋናው ተዋናይ የመሆን ከፍተኛ ጉጉት" ያጠቃዋል። ቪኒሽየስ በሙያ ዘመኑ ሁሉ የለመደውም ይሄንኑ የዋና ተዋናይነት ቦታ ነው።
ወደ ሁለተኛው የዓለም ዋንጫው ሲያቀና... ቪኒሽየስ 14 የንግድ ስምምነቶች ያሉት ሲሆን፣ ይህ ከማንኛውም ብራዚላዊ ተጫዋች የላቀ ነው። ከሜዳ ውጪ ይህ ሁሉ ስኬት ቢኖረውም፣ አሁንም ድረስ ኔማር ከብራዚል እግር ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ጋር ያለውን አይነት ጥልቅ ስሜታዊ ቁርኝት እና ፍቅር ማግኘት አልቻለም። ይህ ሁኔታ እጅግ አስገራሚ ነው፤ አንደኛው (ኔማር) ኮከብነቱ እያለፈ ቢሆንም አሁንም በህዝቡ ልብ ውስጥ አለ፤ ሌላኛው (ቪኒሽየስ) ደግሞ በብቃቱ ጣሪያ ላይ ቢሆንም ያንን የህዝብ ፍቅር አላገኘም።
የግብይት ባለሙያ እና የቀድሞው የኔማር አማካሪ ኤድዋርዶ ሙሳ ይህንን ሲያብራራ፣ "ቪኒሽየስ በብራዚል ደጋፊዎች ይወደዳል፤ ነገር ግን እንደ ኔማር አይደለም። ኔማር አስቀድሞ በብሔራዊ ቡድኑ ግልጽ የሆነ ታሪክ (Legacy) ሰርቷል፤ የዘመናት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ቪኒሽየስ ግን በሪያል ማድሪድ ያሳየውን ብቃት በብሔራዊ ቡድን ገና አላሳየም። ሌላው ነጥብ፣ ኔማር በሳንቶስ ቆይታው ብራዚላውያን በየሳምንቱ አስደናቂ ብቃቱን ይመለከቱ ነበር። ቪኒሽየስ ግን በፍላሜንጎ ቋሚ ተሰላፊ እንኳ ሳይሆን ነው በልጅነቱ ሀገር ለቆ የወጣው" ይላል።
ዳታፎልሃ የተሰኘው የብራዚል የምርምር ተቋም ባወጣው መረጃ፣ አሁንም 53 በመቶ የሚሆኑ ደጋፊዎች አንጋፋው ኔማር በዓለም ዋንጫው ስኳድ ውስጥ መካተቱን ይደግፋሉ።
"አሁን ሁሉም የሚያወራው ስለእኔ ነው"
የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቪኒሽየስን የብሔራዊ ቡድኑ ማዕከል ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርጓል። ባለፈው መጋቢት ወር ሮድሪጎ በጉዳት ከዓለም ዋንጫው ውጪ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ ዝነኛዋን ቁጥር 10 ማልያ ለቪኒሽየስ ሰጥተውት ነበር። ዓላማው ግልጽ ነበር... ቪኒሽየስ የብራዚል ፊት እንዲሆን ማድረግ። ነገር ግን ኔማር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ሲመለስ፣ የ34 ዓመቱ የሳንቶስ አጥቂ ዳግም የቁጥር 10 ማልያውን ተረክቧል።
ምንም እንኳን ኔማር ማልያውን ቢወስድም፣...በቅርብ ጊዜያት እያስተናገደው ያለው ተደጋጋሚ የአካል ብቃት ችግር ቀድሞ ይጣልበት የነበረውን ተስፋ አደብዝዞታል። አሁን የብዙዎች አይን ያረፈው ቪኒሽየስ ላይ ነው። ብራዚል 6ኛዋን የዓለም ዋንጫ ለማንሳት በምታደርገው ጉዞ ላይ ቪኒሽየስ የጥርጣሬ ደመናን ገፎ ደምቆ መውጣት ይኖርበታል።
ቪኒሽየስም ለዚህ የትኩረት ማዕከልነት ዝግጁ መሆኑን ይናገራል። "አሁን ሁሉም የሚያወራው ስለእኔ ነው፤ ምክንያቱም በሪያል ማድሪድ አምስት ወይም ስድስት ምርጥ የውድድር ዘመናትን አሳልፌያለሁ፣ ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች ተርታም ተሰልፌያለሁ። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ተጨማሪ ኃላፊነት ያመጣል። እኔም የምፈልገው ይሄንኑ ኃላፊነት ነው። አቅሜ የት ድረስ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ምክንያቱም የኔ ጣሪያ ሁሌም በጣም ከፍተኛ ነው" በማለት ቆራጥነቱን አሳይቷል። ይህ የዓለም ዋንጫ ቪኒሽየስ የብራዚል ደጋፊዎችን ልብ ሙሉ በሙሉ የሚያሸንፍበት ይሆን? ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል።

22 hours ago