3 days ago
የአውሮፓ ሱፐር ካፕ የዋንጫ ፍልሚያ
#ethiopia | የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የዩሮፓ ሊግ አሸናፊዎችን እርስ በርስ የሚያገናኘው ታላቁ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ጨዋታ በፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና በአስቶንቪላ መካከል ሊደረግ መርሀ ግብር ተይዞለታል።
የፈረንሳዩ ፒኤስጂ የለንደኑን አርሰናል በመለያ ምት በመርታት ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ክብርን መቀናጀቱ ይታወሳል።
በሌላ በኩል የእንግሊዙ አስቶንቪላ የጀርመኑን ፍራንክፈርት በመርታት የዘንድሮውን የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ማሳካቱ አይዘነጋም።
ይህ የሁለቱ አሸናፊዎች ፍልሚያ በሁለቱ ስፔናውያን ታክቲሺያኖች ሉዊስ ኤንሪኬ እና ኡናይ ኤምሬ መካከል የሚደረግ በመሆኑ ከፍተኛ ግምት አግኝቷል።
የአውሮፓን ቁንጮዎች የሚያገናኘው ይህ ታላቅ ጨዋታ በኦስትሪያዋ ሳልዝበርግ ከተማ በሚገኘው ሬድ ቡል ስታዲየም ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
#europesupercup #psg #astonvilla #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 days ago
ፒኤስጂ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በፓሪስ ሁከት ተቀሰቀሰ
#ethiopia | የፓሪሰን ዠርሜን (PSG) የሻምፒዮናነት ድልን ተከትሎ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ እና በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ስርዓት አልበኝነት እስካሁን 416 ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከታሰሩት ደጋፊዎች መካከል 283ቱ በፓሪስ ከተማ ውስጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ድርጊቱን ለማስቆም በነበረው ግጭት ሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።
የክለቡ ደጋፊዎች በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው አራት ዋና ዋና የቀለበት መንገዶችን ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፥ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ የነበረው የእልልታና የደስታ አገላለጽ እስከ ንጋት ድረስ ቀጥሎ አድሯል።
በሌላ በኩል ፒኤስጂ ይፋዊ የዋንጫ ድሉን በፓሪስ በሚገኘው "Champ-de-Mars" ክፍት የሕዝብ መናፈሻ በጎዳና ላይ እንደሚያከብር ታውቋል።
በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ የድል ክብረ በዓል ላይ እስከ 90,000 የሚደርሱ የክለቡ አድናቂዎችና ነዋሪዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#psg #paris #ligue1 #footballnews #france #breakingnews

የአርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ህልም በፍጹም ቅጣት ምት መክሸፍ እና አጨቃጫቂው የምሽቱ ጨዋታ
#ethiopia | በለንደን የሚገኙት አለባቸው ደሳለኝ አበሻ እንደዘገቡት የፒኤስጂ እና የአርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ፍልሚያ በዳኝነት ውሳኔዎች ታጅቦ እጅግ አነጋጋሪ በሆነ መልኩ ተጠናቋል።
በውድድር ዘመኑ በሻምፒዮንስ ሊጉ ምንም ሳይሸነፍ ለፍጻሜ የደረሰው አርሰናል መደበኛውና ተጨማሪው ሰዓት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት 4 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል። ይህ ምሽት ለአርሰናል ደጋፊዎች እጅግ ልብ ሰባሪ ነበር።
ስለ ጨዋታው የስፖርት ተንታኞችና ጋዜጠኞች የሰጧቸውን ዋና ዋና አስተያየቶች ከመመልከታችን በፊት የጨዋታውን አጠቃላይ ገጽታ በወፍ በረር እንቃኝ።
የአርሰናል የመከላከል ጥበብ እና የኮከቦች መዛል
ጨዋታው ከተጀመረበት ደቂቃ አንስቶ እስከ ፍጹም ቅጣት ምት ድረስ የአርሰናል የመከላከል ብቃት ፍጹም ሊደነቅ የሚገባው ነበር። ፒኤስጂ በዚህ የውድድር ዘመን እንደፈለገ ጎል እያዘነበ የመጣ ፈጣንና ጠንካራ የፊት መስመር ጥቃት ያለው ክለብ መሆኑ ይታወቃል።
አርሰናል ግን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ በከፍተኛ ዲሲፕሊን ተቆልፎ የፒኤስጂን አስፈሪ የማጥቃት ኃይል አምክኖ የዋለበት መንገድ ቡድኑ ምን ያህል ጠንካራ መዋቅር እንዳለው ያሳየበት ምሽት ነበር። ነገር ግን የኳስ ጨካኝነት እዚህ ላይ ነው 120 ደቂቃ ሙሉ በጥንካሬ ተከላክለህ በመጨረሻው የዕድል ፈተና በፍጹም ቅጣት ምት ዋንጫውን ማጣት በእውነትም ያማል።
በርካታ ተንታኞች በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የአሰላለፍ ውሳኔ ላይ ትኩረት አድርገዋል። በተለይም ቶማስ ፓርቴይን ወይም የተለመዱ ተከላካዮችን ከመጠቀም ይልቅ ክሪስቲያን ሞስኬራን በቀኝ ተከላካይነት መሰለፉ ስህተት እንደነበር አንስተው ተችተዋል። ፒኤስጂ በሁለተኛው አጋማሽ በክቪቻ ኳራፅኬሊያ በኩል ጫና ሲፈጥር ሞስኬራ ፍጹም ቅጣት ምት የተሰጠበትን ጥፋት በመስራቱ የጨዋታውን አቅጣጫ ቀይሮታል ብለዋል።
አርሰናል ጨዋታውን በካይ ሀቨርትዝ ቀደመ ግብ ድንቅ አጀማመር ቢያደርግም በሁለተኛው አጋማሽ እና በትርፍ ሰዓት ላይ ቡድኑ በከፍተኛ ሁኔታ መዛሉ ታይቷል። ፒኤስጂ 72 በመቶ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት የነበረው ሲሆን አርሰናል ሙሉ ጨዋታውን በመከላከል ማሳለፉ ለፍጹም ቅጣት ምት ሲደርሱ ተጫዋቾቹ ላይ የትኩረት ማጣት እንዲከሰትና የአርሰናል አስደናቂ ጥንካሬ እንዲዝል አድርጎታል።
የዳኝነት ውሳኔዎች እና የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውዝግብ
የዳኝነት ውሳኔው በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በኤክስ እና በፌስቡክ ላይ በደጋፊዎችና በስፖርት ተንታኞች መካከል እጅግ ሞቅ ያለና የአርሰናልን ደጋፊዎች ያስቆጣ አጀንዳ ሆኗል። ዳኛው አድላዊ ነበሩ በሚል ማህበራዊ ሚዲያውን እያነጋገሩ ያሉት 3 ዋና ዋና አጨቃጫቂ ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው።
በኖኒ ማዱዌኬ ላይ የተፈጸመው ጥፋት እና የቪዲዮ ረዳት ዳኛ ዝምታ ጉዳይ በትክክል ፍጹም ቅጣት ምት መሆን ነበረበት ተብሏል። የፒኤስጂው ተከላካይ ኑኖ ሜንዴስ በሳጥን ውስጥ ማዱዌኬን በግልጽ ሲገፋውና ሲያንገላታው ቢታይም የቪዲዮ ረዳት ዳኛው ዋናውን ዳኛ ሄዶ በስክሪን እንኳ እንዲያይ አለመጋበዙ ግልጽ አድሎ ነው በሚል የአርሰናል ደጋፊዎች ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። ገለልተኛ ተንታኞችም የግፊው ኃይል ለፍጹም ቅጣት ምት በቂ ባይሆን እንኳ ጉዳዩ ቢያንስ በቪዲዮ ረዳት ዳኛ መታየት እንደነበረበት ይስማማሉ።
የእርምጃዎች ድርብ መስፈርት በሁለተኛው አጋማሽ ክሪስቲያን ሞስኬራ በክቪቻ ኳራፅኬሊያ ላይ በሰራው ጥፋት ፒኤስጂ በቀላሉ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቷል። ብዙዎች ኳራፅኬሊያ በቀላሉ ነው የወደቀው ዳኛው ግን ለፒኤስጂ የነበራቸው አዝማሚያ ለስላሳ ስለነበር ወዲያውኑ ፍጹም ቅጣት ምት ሰጡ በማለት ይተቻሉ። በተመሳሳይ ጥፋት በአርሰናል በኩል የቀረቡት ጥያቄዎች ውድቅ መደረጋቸው የዳኛውን ሚዛናዊነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
የሰዓት ማጥፋት እርምጃዎች መዘግየትን በተመለከተ የፒኤስጂ ተጫዋቾች ሆን ብለው ሰዓት ሲያጠፉ እና ጨዋታውን ሲያደናቅፉ ዳኛው ጥብቅ እርምጃ አለመውሰዳቸው ሌላው ቅሬታ ነው። በተቃራኒው በአርሰናል ተጫዋቾች ላይ የተሰጡት የቅጣት ውሳኔዎች ፍጹም ጥብቅ እና ቡድኑን የተጫኑ ነበሩ ተብሏል።
የአርሰናል የቀድሞ ኮከብ አለን ስሚዝ ጨምሮ በርካታ ተንታኞች እንደሚስማሙት ዳኛው በጨዋታው ላይ የተጠቀሙት ድርብ መስፈርት አርሰናል ዋንጫውን እንዲያጣ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሯል።
የስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት የፍጹም ቅጣት ምት ሁሌም የዕድል ጉዳይ ነው።
በጨዋታው ላይ ኤበሬቺ ኤዜ ሳይጠቀምበት የቀረውን ኳስ ዴቪድ ራያ የኑኖ ሜንዴስን መቅጫ ምት በማዳን ተስፋ ቢመልስም በመጨረሻው ወሳኝ ምት ተከላካዩ ጋብሬል ማጋልሃሽ ኳሱን ወደ ላይ መስቀሉ ጨካኝ የሆነ የውጤት መደምደሚያ ነበር። ሆኖም ጋብሬል በጨዋታው ላይ የነበረው ድንቅ የመከላከል ብቃት ሳይዘነጋ ይህ ስህተት እሱን ብቻ ተጠያቂ ሊያደርገው እንደማይገባ ተንታኞች ይሟገታሉ።
የሳካ እና ኦዴጋርድ መቀየር ስህተት ነበር?
ሚኬል አርቴታ ቡካዮ ሳካንና ማርቲን ኦዴጋርድን በማስወጣቱ ለሽንፈቱ ምክንያት ሆኗል ለሚለው ጥያቄ ተንታኞች ሁለት ዋና ዋና እይታዎችን እያነሱ ነው።
በአንድ በኩል ሳካ እና ኦዴጋርድ የቡድኑ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በፍጹም ቅጣት ምት ወቅት እጅግ አስተማማኝ የተረጋጉና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ናቸው። እነሱ በሌሉበት ሜዳ ላይ የቀሩት ወጣት ወይም የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች እንደ ጋብሬል ማጋልሃሽ የፍጹም ቅጣት ምት የመምታት ከባድ ጫና እንዲወድቅባቸው አድርጓል። በተጨማሪም ሁለቱ ኮከቦች ሲወጡ አርሰናል ኳስን መስርቶ ማጥቃትና ፒኤስጂን ወደ ኋላ ማስጨነቅ ሙሉ በሙሉ አቆመ።
ይህም ፒኤስጂዎች ያለ ምንም ስጋት ሙሉ ኃይላቸውን ወደ አርሰናል ሳጥን እንዲልኩና በአርሰናል ተከላካዮች ላይ ከፍተኛ የአእምሮና የሰውነት ድካም እንዲፈጠር አድርጓል ይላሉ።
በሌላ በኩል ጨዋታው ወደ ትርፍ ሰዓት ሲያመራ ሳካ እና ኦዴጋርድ በፒኤስጂ ተጫዋቾች ከፍተኛ ክትትልና ጫና ስለነበረባቸው በከፍተኛ ሁኔታ ዝለው ነበር።
አርቴታ እነሱን የቀየረው የጡንቻ ጉዳት እንዳይገጥማቸውና ትኩስ ጉልበት ያላቸውን ተጫዋቾች ለምሳሌ ማዱዌኬን በማስገባት የፒኤስጂን መስመር ለመስበር በማሰብ ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ።
ሆኖም አርቴታ ጨዋታውን በ120 ደቂቃ ውስጥ ለመጨረስ ወይም በመከላከል ለመጨረስ አስቦ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ጨዋታው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ማምራቱ የማይቀር መሆኑን እያወቀ ሁለቱን ምርጥ የቅጣት ምት መቺዎቹን እና የቡድኑን የልብ ትርታዎች ቀይሮ ማስወጣቱ በታክቲክ ደረጃ ትልቅ ስህተት እንደነበር ይነገራል።
ይህ የሻምፒዮንስ ሊግ ሽንፈት ለአርሰናል እና ለደጋፊዎቹ እጅግ መራራ ምሽት ቢሆንም ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በማንሳቱ ትልቅ ስኬት ማስመዝገቡ አይዘነጋም።
ቡድኑ ካሳየው አስደናቂ ጥንካሬ እና መዋቅር አንፃር በቀጣይ ዓመታት ይበልጥ ጠንክሮ እና ተምሮበት እንደሚመለስ የስፖርት ተንታኞች ትልቅ ተስፋ ጥለውበታል።
አለባቸው ደሳለኝ ለንደን 🇬🇧
#arsenal #psg #championsleague #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

14 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የአርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ቡድናቸው የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታውን ካደረገ ማግስት በለንደን ጎዳናዎች ስለተዘጋጀው የዋንጫ የአደባባይ ዙረት (Parade) ተጠይቀው አጭር እና ቁርጠኝነት የተሞላበት ምላሽ ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ በመጪው ሜይ 30 ከፓሪስ ሴንት ዠርመን (PSG) ጋር የሚያደርጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በድል በማጠናቀቅ፣ አስቀድመው ካረጋገጡት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ጋር አጣምረው ደስታቸውን ከደጋፊዎቻቸው ጋር ለማክበር ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት ገልጸዋል። በመግለጫቸው ማጠቃለያ ላይም "የዋንጫ ዙረታችንን በሁለቱም ዋንጫዎች ታጅበን ማክበር እንፈልጋለን" በማለት ቡድናቸው አውሮፓን ለማንገስ እና ለታሪካዊው ድል ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጠዋል::

24 days ago
የአርሰናል እና የፒኤስጂ ጨዋታን የሚዳኙት ዳኛ ታወቁ
#ethiopia | በጉጉት ለሚጠበቀው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ፍልሚያ፣ በአርሰናል እና በፒኤስጂ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ መታወቃቸው ተረጋግጧል።
ጀርመናዊው የ42 ዓመቱ ዳኛ ዳንኤል ሴበርት ይህንን ታላቅ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ በኃላፊነት ተሰይመዋል።
ከ20 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ ወደ ፍጻሜው የተመለሱት መድፈኞቹ፣ በግማሽ ፍጻሜው አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት በመርታት ነው ለዚህ ደረጃ የበቁት።
ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ለንደን ለመውሰድ ቆርጦ ተነስቷል።
የአምናው ውድድር አሸናፊው የፈረንሳዩ ክለብ፣ በግማሽ ፍጻሜው ባየርን ሙኒክን በማሸነፍ ለፍጻሜው ደርሷል።
ፒኤስጂ ክብሩን አስጠብቆ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማል።
ይህ ተጠባቂ የፍጻሜ ጨዋታ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚገኘው ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#championsleague #arsenal #psg #uclfinal #danielsiebert #footballnews #ethiopia

28 days ago
ለሻምፒዮንስ ሊግ፤ ለታላቁ ክብር ይፋለማሉ
#ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ ከባየር ሙኒክ ጋር አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በአሊያንዝ አሬና በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ኡስማን ዴምቤሌ ለፒኤስጂ ቀዳሚዋን ግብ ሲያስቆጥር የባየር ሙኒኩ ሃሪ ኬን በጭማሪ ሰዓት የቡድኑን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል።
ሆኖም ፓሪስ ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 5 ለ 4 አሸንፎ የነበረው ፒኤስጂ በድምር ውጤት 6 ለ 5 በመርታት ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
የአምናው የሻምፒዮንስ ሊግ ባለክብር ፒኤስጂ በሉዊስ ኤንሪኬ መሪነት በቡዳፔስት በሚደረገው የፍጻሜ ፍልሚያ ከአርሰናል ጋር ለዋንጫ የሚፋለም ይሆናል።
በጨዋታው ላይ የፒኤስጂው ኡስማን ዴምቤሌ ገና በ3ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ለፓሪዚያኑ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረች ሲሆን የባየር ሙኒኩ ተከላካይ ኡፓሜካኖ በፈጣን የፒኤስጂ አጥቂዎች ሲፈተን አምሽቷል።
ባየር ሙኒክ ጨዋታውን ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የፒኤስጂው ግብ ጠባቂ ድንቅ ብቃት እና የተደራጀው የተከላካይ መስመር የባቫሪያኑን ጉዞ ሊያግዱ ችለዋል።
ግንቦት 22 በሃንጋሪ ፑሽካሽ አሬና በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ዋንጫውን ለማስጠበቅ ሲጫወት አርሰናል ደግሞ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ወክሎ ለበቀልና ለታላቁ ክብር ይፋለማል።
#psg #bayernmunich #championsleague #football #ucl #arsenal #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን በጎል ናዳ አሸነፈ
#ethiopia | በፓሪስ ፓርክ ዴ ፕሪንስ ስታዲየም የተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ እጅግ አስደናቂ እና በጎሎች የታጀበ ምሽት ነበር።
ዘጠኝ ጎሎች የተቆጠሩበት ይህ ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ቀልብ የገዛ ሲሆን ፒኤስጂ ባየርን ሙኒክን 5 ለ 4 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ መጠነኛ ብልጫ መያዝ ችሏል።
ጨዋታው እንደተጀመረ ሃሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት ባየርን ሙኒክን ቀዳሚ ቢያደርግም ፓሪሶች በክቫራትስኬሊያ እና በጆአኦ ኔቬስ አማካኝነት ተከታታይ ጎሎችን በማስቆጠር መሪነቱን ተረክበዋል።
ባየርኖች በሚካኤል ኦሊሴ ጎል አቻ መሆን ቢችሉም በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ኡስማን ዴምቤሌ በቪዲዮ ረዳት ዳኛ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ፒኤስጂን 3 ለ 2 መሪ አድርጎ ወደ እረፍት አምርተዋል።
ከእረፍት መልስ ፒኤስጂዎች ብልጫቸውን በማስፋት በክቫራትስኬሊያ እና በዴምቤሌ አማካኝነት ተጨማሪ ጎሎችን አስቆጥረው ልዩነቱን ወደ ሶስት አሳድገው ነበር።
ሆኖም የጀርመኑ ሀያል ክለብ ባየርን ሙኒክ ተስፋ ሳይቆርጥ በመታገል በኡፓሜካኖ እና በሉዊስ ዲያዝ አማካኝነት ሁለት ጎሎችን በማከታተል የጎል ልዩነቱን ወደ አንድ ማጥበብ ችሏል።
ፒኤስጂ በዚህ ጨዋታ ያስመዘገበው ውጤት በታሪኩ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን በተለይም ክቫራትስኬሊያ ክለቡን ከተቀላቀለ በኋላ እያሳየ ያለው ድንቅ ብቃት ለቡድኑ ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
ባየርን ሙኒክ ምንም እንኳን በሜዳው ቢሸነፍም ያስቆጠራቸው አራት ጎሎች ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ ትልቅ ተስፋ የሚሰጡት ናቸው።
የሁለቱ ቡድኖች ወሳኝ የሁለተኛ ዙር ፍልሚያ ረቡዕ ግንቦት 6 ቀን በሙኒክ አሊያንዝ አሬና የሚካሄድ ይሆናል።
#ucl #psg #bayernmunich #championsleague #football #sports #goal #paris #munich #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
2 months ago
አትሌቲኮና ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ተቃረቡ! 🇫🇷🇪🇸
#ethiopia | የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስተናግደዋል። የ
ሊቨርፑልና የባርሴሎና ደጋፊዎች ምሽቱን በሀዘን ሲያሳልፉ፣ አትሌቲኮና ፒኤስጂ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለመጓዝ ትልቅ በር ከፍተዋል።
🇫🇷 ፒኤስጂ 2-0 ሊቨርፑል
ዲዘር ዱዌ እና ኪቪቻ ካቫርስኬሊያ ባስቆጠሯቸው ግቦች ፒኤስጂ ድል ቀንቶታል።
መርሲሳይዶቹ በጨዋታው አንድም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ (0 shots on target) ሳያደርጉ ወጥተዋል።
ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ በአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ሲሸነፍ ከ14 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።
🇪🇸 ባርሴሎና 0-2 አትሌቲኮ ማድሪድ 🇪🇸
የሲሚዮኒ ታሪክ፦ አሰልጣኝ ዲየጎ ሲሚዮኒ ባርሴሎናን በሜዳው (ካምፕ ኑ) ለመጀመሪያ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
ባርሴሎና በሜዳው በአትሌቲኮ ማድሪድ የተሸነፈው ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ፓዎ ኩባርሲ በቀይ ካርድ መውጣቱ ለባርሳ ሽንፈት ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደርግ፣ ሁሊያን አልቫሬዝ እና አሌክሳንደር ሶርሎዝ ድሉን አረጋግጠዋል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #championsleague #ucl #psg #liverpool #barcelona #atleticomadrid #simeone #footballnews #ethiopia #የአውሮፓሻምፒዮንስሊግ #ስፖርት #ባርሴሎና #ሊቨርፑል

የሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት
የፓሪስ ፈተና ለሊቨርፑልና የስፔኖቹ ፍጥጫ በካታላን
#ethiopia | ትላንት አርሰናል ድል ቀንቶት ምሽቱን በደስታ ብናሳልፍም፣ ዛሬ ደግሞ ሌሎች ታላላቅ ክለቦች ለግማሽ ፍጻሜ አልጋ ለመለየት ይፋለማሉ።
. 🇫🇷 ፒኤስጂ ከ ሊቨርፑል 🏴 (ምሽት 4፡00)
በኤፍ ኤ ዋንጫ በማንችስተር ሲቲ የ 4 ለ 0 መራር ሽንፈት የደረሰባቸው አርን ስሎት፣ ዛሬ በፓሪስ ራሳቸውን ማዳን ይኖርባቸዋል።
ለሦስት ወራት በጉዳት ተለይቶ የነበረው ስዊዲናዊው አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳቅ ወደ ስብስብ መመለሱ ለመርሲሳይዱ ክለብ ትልቅ የምስራች ነው።
ፒኤስጂ በቅርብ ጊዜያት ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች ሽንፈት አላስተናገደም። ብራድሊ ባርኮላና ፋቢያን ሩይዝ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም።
🇪🇸 ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ 🇪🇸 (ምሽት 4፡00)
ባርሴሎና በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት 25 ጨዋታዎች በአትሌቲኮ ተሸንፎ አያውቅም። ከሦስት ቀን በፊትም በላሊጋው 2 ለ 1 ማሸነፉ ለዛሬው ጨዋታ የሥነ-ልቦና የበላይነት ይሰጠዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ የስፔን ክለቦችን ከሜዳው ውጪ አሸንፎ የማያውቅበትን ታሪክ ለመቀየር ይፋለማል።
ባርሴሎና ራፊንሀና ዲዮንግን ቢያጣም ሮናልድ አራውሆ ለጨዋታው ደርሶለታል። በአንጻሩ ያን ኦብላክ ለአትሌቲኮ ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።
#getu #championsleague #psg #liverpool #barcelona #atleticomadrid #arneslot #alexanderisak #footballnews #uclquarterfinals #ጌጡተመስገን #getutemesgen #ስፖርት #ሻምፒዮንስሊግ

3 months ago
ቼልሲ በአስከፊ ውጤት ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሰናበተ!
የአለም ክለቦች ሻምፒዮን የነበረው ቼልሲ፣ በፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ (PSG) ያልተጠበቀና እጅግ አስደንጋጭ ሽንፈት አስተናግዷል። በሁለቱ ክለቦች መካከል በተደረገው ወሳኝ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ፣ ፒኤስጂ ቼልሲን በደርሶ መልስ አጠቃላይ ውጤት 8 ለ 2 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት በመርታት ከውድድሩ ውጭ አድርጎታል።
ይህን ተከትሎ በመላው አለም የሚገኙ የቼልሲ ደጋፊዎች በውጤቱ ክፉኛ ማዘናቸውንና በቡድናቸው አቋም መከፋታቸውን እየገለጹ ይገኛል። በሌላ በኩል፣ ፒኤስጂ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ተከትሎ ደጋፊዎቹ በታላቅ ደስታ ላይ ናቸው።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፦
ሪያል ማድሪድ ሲቲን፣ ፒኤስጂ ቼልሲን አሸነፉ
#ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች አስገራሚ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በሳንቲያጎ ቤርናባው የተደረገው ታላቅ ፍልሚያ በሪያል ማድሪድ የበላይነት ተጠናቋል።
ሪያል ማድሪድ 3 - 0 ማንችስተር ሲቲ
የጨዋታው ኮከብ፦
ኡራጓያዊው አማካይ ፌደሪኮ ቫልቨርዴ በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ውስጥ ብቻ ሀትሪክ በመስራት ማድሪድን ለድል አብቅቷል።
ያመለከተ ዕድል፦
ቪኒሺየስ ጁኒየር ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት የቀረ ቢሆንም፣ ማድሪድ ለሩብ ፍጻሜው ያለውን ዕድል በሰፊው አስፍቷል።
የመልስ ጨዋታ፦
ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ ሳምንት በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ማድሪድን በድምር ውጤት ለማሸነፍ ቢያንስ 4 ግቦችን አስቆጥሮ ማሸነፍ ይኖርበታል።
ፒኤስጂ 5 - 2 ቼልሲ
የፒኤስጂ ግቦች፦ ኪቪቻ ካቫርስኬሊያ (2 ግቦች)፣ ኡስማን ደምቤሌ፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ቪቲንሃ አስቆጥረዋል።
የቼልሲ ግቦች፦ ማሎ ጉስቶ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለለንደኑ ክለብ መጽናኛ ግቦችን አስገኝተዋል።
ፒኤስጂ በፓርክ ዴስ ፕሪንስ ያሳየው የማጥቃት ብቃት ለቼልሲ የመልስ ጨዋታ ከባድ የቤት ስራ ጥሎባቸዋል።
የዓመቱ ክስተት፦ ቦዶ ግሊምት
ኖርዌያዊው ክለብ ቦዶ ግሊምት ስፖርቲንግ ሊዝበንን 3 ለ 0 በማሸነፍ በውድድሩ እያስመዘገበ ያለውን አስገራሚ ጉዞ ቀጥሏል።
ጎል አግቢዎች፦
ሶንደር ፊት፣ ኦሌ ብሉምበርግ እና ካስፐር ሆጅ።
የዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ባልተጠበቁ ውጤቶችና በግል ብቃቶች የታጀበ ሆኗል። በተለይ የቫልቨርዴ ሀትሪክ እና የቦዶ ግሊምት ጥንካሬ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
#ucl #realmadrid #mancity #psg #chelsea #bodoglimt #championsleague #football #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን