Logo
Getu Temesgen
ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ወሰን አቅራቢያ የሚገኘውን የግብፅ የጦር ሰፈር እንዲዘጋ አደረገች
#ethiopia | ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር በሚገናኘው የበላይኛው ናይል ክፍለ ሀገር ፓጋክ በተባለ ስፍራ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የግብፅ ወታደራዊ ማዕከል እንዲዘጋ ወስነች።

ይህ የጦር ሰፈር ግብፅ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያላትን ጥቅምና ፍላጎት ለመጠበቅ ስትጠቀምበት የነበረ ስትራቴጂያዊ የክትትል ቦታ እንደነበር ተመልክቷል።

ይህ የጁባ ውሳኔ በቀጠናው የፖለቲካና የኃይል ሚዛን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የገለጹት የፖለቲካ ምሁራን፣ ደቡብ ሱዳን በሱዳን ጦርነት ምክንያት የተስተጓጎለባትን የነዳጅ ንግድ ለመተካት ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችውን የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ የያዘችውን አቋም የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በፓጋክ ይንቀሳቀስ በነበረው በዚህ የግብፅ ወታደራዊ ጣቢያ ውስጥ የቴክኒክና የሎጂስቲክስ ባለሙያዎችን ጨምሮ ወደ 260 የሚጠጉ የግብፅ ዜጎች ይገኙበት እንደነበር ተገልጿል።

ባለፉት ሳምንታት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር አሳይቶ የነበረ ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳን የአሁኑ እርምጃ በምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ አሰላለፍ ላይ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
#southsudan #egypt #gerd #grandethiopianrenaissancedam #pagak #eastafrica #politics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.