4 hours ago
የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መቋቋም ስጋት የሕክምናው ዘርፍ ፈተና
#ethiopia | በተለያዩ የመድኃኒት መሸጫ ፋርማሲዎች፣ በሙያ ማህበራት፣ በጤና ተቋማትና በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሰሞኑን ስለ ፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መቋቋም ወይም Antimicrobial Resistance (AMR) ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች ሲስተላለፉ ቆይተዋል።
ይህ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ትኩረት ሊሰጠው የቻለው በየዓመቱ የሚታሰበውን ዓለም አቀፍ የባለሙያዎችና የህዝብ ንቅናቄ መድረክን ተከትሎ ነው።
የመድኃኒት መቋቋም የሚባለው ክስተት ባክቴሪያዎች፣ ፈንገሶች፣ ቫይረሶችና መሰል ጥቃቅን ተህዋሲያን እነሱን ለማጥፋት የሚታዘዙ መድኃኒቶችን የመላመድና የመቋቋም አቅም ሲያዳብሩ የሚፈጠር የጤና እክል ነው።
ይህ ሁኔታ ቀደም ሲል በቀላሉ መፈወስ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ውስብስብ ከማድረጉም በላይ ለተጨማሪ የሕክምና ወጪና ለከፋ የህይወት መጥፋት አደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ይነገራል።
ችግሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ቢገኝም አሁንም ድረስ ከብዙሃኑ ህብረተሰብ ተገቢውን ትኩረት አላገኘም።
በተለይም አንቲባዮቲክስ ወይም የፀረ-ባክቴሪያ መድኃኒቶችን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ በራስ ፍቃድ መውሰድ፣ የተጀመረን የሕክምና ጊዜ አጠናቆ አለመጨረስና መድኃኒቶችን ያለአግባብ መጠቀም ለችግሩ መባባስ ዋነኛ መንስኤዎች ሆነዋል።
የዘርፉ ባለሙያዎች ይህንን የጤና ስጋት ዝምተኛው ወይም ቀዝቃዛው ሱናሚ ሲሉ ይጠሩታል።
እንደ ድንገተኛ ወረርሽኝ በአንድ ጊዜ ህዝብን ባያጠቃም በሂደት ግን በዝግታ እየተስፋፋ የዘመናዊ ሕክምና ስኬቶችንና መሠረቶችን ትልቅ አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል።
ስለሆነም መድኃኒቶችን በከፍተኛ ኃላፊነት መጠቀም፣ የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር በአግባቡ መተግበርና ህብረተሰቡን ማስተማር የሁሉንም አካላት ርብርብ ይጠይቃል።
ዛሬ የምናሳየው ጥንቃቄና የምንወስደው እርምጃ ወደፊት ውጤታማና ፈዋሽ መድኃኒቶች እንዲኖሩን ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ሃና ልካስ
#amr #antimicrobialresistance #healthnews #publichealth #medicine #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments