6 days ago
ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ስምንት አገራትን ያካተተ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ አዲስ የደህንነት ጥምረት ተቀላቀሉ፡፡
ሳዑዲ አረቢያ ስምንት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚገኙ ሀገራትን በማስተባበር አዲስ ተጨማሪ የባህር ላይ የደህንነት ጥምረት አዋቅራለች።
ከእነዚህ ስምንት ሀገራት መካከል አምስቱ ሀገራት ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ናቸው።
የታቀደው ህብረት ሳዑዲ አረቢያን፣ ዮርዳኖስን፣ የመንን እና አምስቱን የአፍሪካ ሀገራት ያካተተ ነው።
የሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ጥምረቱ ዓላማው በቀይ ባህር ላይ በሚያዋስኑ ሀገራት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር እና ዓለም አቀፍ የባህር ላይ መስመሮችን፣ የንግድና የኃይል ማጓጓዣ መንገዶችን እንዲሁም የጋራ የባህር ላይ ጥቅሞችን መጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።
ጥምረቱ የተመሰረተው በቀጠናው ውጥረቶች እና በንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሱ መስተጓጎሎች እየጨመሩ የመጡበት ወቅት ላይ ነው።
Seledadotio

7 days ago
የአረንጓዴ ዐሻራ የሰባት ዓመታት ሰባት አንኳር ስኬቶች
*************
አረንጓዴ ዐሻራ በኢትዮጵያ ምድር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ ሀገራችንን ከአፈር መሸርሸር እና ከበረሃማነት የመታደግ ሀገራዊ ራዕይ ብቻ ሳይሆን፤ የምድርን ሕይወት የሚያድስ፣ የዜጎችን ሥነ-ልቦናዊ አስተሳሰብ የሚቀርጽ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም የሚገነባ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሆኖ ዘልቋል።
ይህ ሀገራዊ የሕልውና ጥረት ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስትራቴጂዎች ጋር ተናብቦ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያስመዘገባቸው ሰባት ዋና ዋና ተጨባጭ ስኬቶች እንደሚከተለው ተተንትነዋል።
1. የችግኝ ብዛትን ከጽድቀት ምጣኔ ጋር ያጣመረ አዲስ ታሪካዊ ሽግግር
ባለፉት ሰባት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የተከላው ዋና ትኩረት ወደ ጥራት እና ድኅረ-ተከላ እንክብካቤ በማደጉ የችግኞች ጽድቀት ምጣኔ ከ80 በመቶ በላይ ማደግ ችሏል።
ይህም ቀደም ሲል የነበረውን "መተከል እንጂ አለመጽደቅ" የሚል የብክነት ታሪክን በመቀየር በቆላ እና በደጋ አካባቢዎች የተጎዱ መሬቶች በፍጥነት አረንጓዴ እንዲለብሱ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ሚዛን እንዲጠበቅ አድርጓል።
2. ከአካባቢ ጥበቃ ወደ የምግብ ዋስትና የተደረገ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር
አረንጓዴ ዐሻራ ከተፈጥሮ የደን ዛፎች ባሻገር እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አፕል እና ቡና ያሉ ፍሬያማ ተክሎችን በስፋት አካትቷል።
ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ ፕሮጀክቱን ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ እና አባወራዎችን የገበያ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ብሎም የሀገራችን የግብርና ምርት የወጪ ንግድ የሚያሳድግ የኢኮኖሚ ሞተር አድርጎታል።
ይህም የአካባቢ ጥበቃን ከዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ማሻሻል ግብ ጋር በማስተሳሰር ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የልማት ምሰሶ እንዲሆን አስችሎታል።
3. የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ
በመላ ሀገራችን የተቋቋሙት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ለብዙ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች እና ለሴቶች አዲስ እና ዘላቂ የገቢ ምንጭ ሆነዋል።
ችግኝ ማፍላት፣ መንከባከብ እና ለገበያ ማቅረብ በራሱ አዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የሀገራችንን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጅማሮ በጠንካራ መሠረት ላይ አኑሮታል።
ችግኞች ከተተከሉ በኋላ የሚደረገው ጥበቃ እና ክብካቤም በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ቋሚ የሥራ ዘርፍ መሆን ችሏል።
4. የውኃ ሀብት እና የታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ዋስትና
በስፋት የተከናወነው የደን ልማት እና የአፈር ጥበቃ ሥራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች በደለል እንዳይሞሉ የመከላከል ታሪካዊ ሚና ተጫውቷል።
በተጨማሪም የከርሰ ምድር ውኃ መጠን እንዲያገግም እና የደረቁ የምንጭ ውኃዎች መልሰው እንዲፈልቁ በማድረግ አስተማማኝ የውኃ ዋስትናን እያረጋገጠ ይገኛል።
ይህ ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የመጠበቅ አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን የውኃ ምንጭ ለሆነችላቸው የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ትልቅ ትሩፋት ነው።
5. አረንጓዴ ዲፕሎማሲ እና የቀጣናዊ ትሥሥር ማጠናከሪያ
ኢትዮጵያ ያዘጋጀቻቸውን ችግኞች እንደ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ላሉት ጎረቤት ሀገራት በማጋራት፣ የምሥራቅ አፍሪካን እና የአፍሪካ ቀንድን የቀጣና አየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት በጋራ የመከላከል መሪነት ሚናዋን በተግባር አሳይታለች።
ይህም አረንጓዴ ዐሻራን የድንበር ተሻጋሪ ዲፕሎማሲ፣ የቀጠናው ሰላም እና የጋራ ልማት መሣሪያ አድርጎታል።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል የአረንጓዴ ልማትን በሀገሮቻቸው እያስፋፉ ይገኛሉ።
ከዚህ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ባመጣቻቸው ተጨባጭ ስኬቶች “ዘላቂ የደን ልማት አያያዝ እና አጠቃቀም” በሚል ዘርፍ ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) ከፍተኛ እውቅናን አግኝታለች።
6. የከተሞች ሥነ-ምኅዳር መታደስ እና የኮሪደር ልማት ውበት
አረንጓዴ ዐሻራ በገጠር ተራራዎች ብቻ ተወስኖ ሳይቀር ወደ ከተሞች በመግባት የዘመናዊ ፓርኮች ግንባታ፣ የከተማ አረንጓዴ ልማት እና አሁን ላይ በስፋት እየተተገበረ ላለው የኮሪደር ልማት ዋነኛ አካል ሆኗል።
ይህም የከተሞችን የአየር ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩም በላይ፣ የሥነ-ሕይወት ስብጥርን ወደ ነበረበት በመመለስ እና ለዜጎች ምቹ የመዝናኛ እና የኑሮ አካባቢን በመፍጠር የከተሞቻችንን ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመለወጥ ላይ ይገኛል።
7. ሕዝባዊ ንቅናቄ እና የዜግነት አገልግሎት ባህል ግንባታ
በአንድ ጀምበር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ችግኝ የመተከል ልምዳቸው፣ የአካባቢ ጥበቃን ከዘመቻነት አውጥቶ የባህል እና የዜግነት ግዴታ አካል አድርጎታል።
ይህም የሕዝባዊ ወንድማማችነትን ያጠናከረ እና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤን በማሳደግ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር እጅግ ግዙፍ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ስኬት ነው።
በአጠቃላይ አረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተፈጥሮ ሀብታችንን ከመመለስ አልፎ ሀገራዊ አንድነትን ያጠናከረ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ አቅማችንን የገነባ እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አቅራቢ ሀገር ያደረገ አንጸባራቂ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #climateaction #greendiplomacy #greeneconomy

13 days ago
"የዜሮ እዳ ባለቤቶች"
#ethiopia | በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) በኩል የሚሰጡ የብድር አቅርቦት እና የፋይናንስ ድጋፍ ለብዙ አፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው።
2026 ከተቋሙ አነስተኛ የብድር እዳ ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ወቅታዊ መረጃ አነስተኛ የብድር እዳ ካለባቸው ሀገራት መካከል በመጀመሪያው ተሰልፈው የሚገኙት በድርጅቱ አሰራርና አጠራር መሠረት የዜሮ እዳ ባለቤት የሆኑት ሀገራት ናቸው።
በዚህም ቦትስዋና፣ ሊቢያ፣ ኤርትራ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ እና ሞሪሸስ ከIMF ጋር አሁናዊ የብድር እዳ የሌለባቸው ሀገራት በመሆን የዝርዝሩን አናት ይዘዋል።
በሌላ በኩል ከተቋሙ ጋር ንቁ የብድር ፕሮግራም እያካሄዱ ነገር ግን በዝቅተኛ የብድር መጠን ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት 10 የአፍሪካ ሀገራትም አሉ።
ሌሶቶ፣ ኤስዋቲኒ፣ ጂቡቲ፣ ኮምሮስ፣
ሳኦ ቶሜ ፕሬንስፔ፣ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ጊኒ ቢሳዎ፣ኬፕ ቨርዴ፣ ሲሸልስ እና ቡሩንዲ ከድርጅቱ አነስተኛ የብድር መጠን ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ናቸው ተብሏል።
አነስተኛ የብድር እዳ ካለባቸው ሀገራት መሀከል አብዛኞቹ ደሴትና አነስተኛ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ናቸው።
የIMF እዳ አነስተኛ መሆኑ ሀገራቱ የራሳቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በነጻነት ለመቅረጽና ከውጭ ጫና ለመጠበቅ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላቸው ነው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚናገሩት።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #imf #debt #economi

1 month ago
ከምድር ጥበቃ ወደ ማዕድ በረከት፤ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ያሳደገው የአረንጓዴ ዐሻራ ታሪካዊ ስኬት
************
ዛሬ ዓለማችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የመጣውን የሙቀት መጨመር፣ የሰደድ እሳት፣ የጎርፍ እንዲሁም የድርቅ አደጋዎችን ለመቋቋም በብርቱ ትግል ውስጥ ትገኛለች።
አፍሪካ ለዓለም የሙቀት መጨመር ያበረከተችው አስተዋጽኦ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ የችግሩ ቀዳሚ ተጠቂ መሆኗ አልቀረም።
ኢትዮጵያ ይህንን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቀነስ ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተስፋን ማለምና ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በተግባር እያሳየች ትገኛለች።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው "የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር" በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ ስኬት ብቻ መሆኑ አብቅቶ፣ ለመላው የአፍሪካ አህጉር ብሩህ የተስፋ ስንቅና ታላቅ የተሞክሮ ምንጭ ለመሆን በቅቷል።
መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በመላው ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፤ ይህም የሀገራችንን የደን ሽፋን በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 17.2 በመቶ በአሁኑ ወቅት ወደ 23.6 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል።
በዘንድሮው የችግኝ ተከላ ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያ ያስቀመጠችውን የ65 ቢሊዮን ታሪካዊ ግብ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ዝግጁ ተደርገዋል።
ይህ ዓይነቱ መጠነ-ሰፊ ንቅናቄ የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ፣ የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
መርሐ ግብሩ የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙ ከማድረጉ ባሻገር፣ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና አፕል ያሉ ለምግብነትና ለገበያ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት አካትቷል።
ይህም የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ “ከምድር ጥበቃ ወደ ማዕድ በረከት” የተሻገረ ስትራቴጂ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ሲያስጀምሩ የነበራቸው ራዕይ በሀገር ውስጥ ብቻ የተገደበ አልነበረም።
የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር የለሽ በመሆኑ፣ መከላከል የሚቻለውም በጋራና በትብብር ሲሰራ ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ የቀጣናውን በረሃማነት በጋራ ለመግታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ለጎረቤት ሀገራት ማለትም ለጂቡቲ፣ ለደቡብ ሱዳንና ለኬንያ አበርክታለች።
ይህ ተግባር የፓን-አፍሪካኒዝም እሴትን በተግባር ያሳየ፣ ለመላው አፍሪካውያን አንድነትና አብሮነት አዲስ ትርጉም የሰጠ አርዓያነት ያለው ስኬት ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅም፣ በጋራና በትብብር መፍታት እንደሚችሉ ያሳዩበት ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ኢትዮጵያ ያበሰረችው የአረንጓዴ ተስፋ ብርሃን አህጉሪቱን ከተጋረጠባት የበረሃማነትና የአየር ንብረት መዛባት አደጋ ታድጎ፣ የነገዋን አፍሪካ ውብና ለምለም ለማድረግ የበኩሉን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ
#greenlegacy #climateaction #greenethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation

2 months ago
ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ ሀገራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ እና ብልጽግናን ከማምጣት የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ሕልም ጋር በቀጥታ የተቆራኘ አንኳር ጉዳይ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ አርዓያ ያደረገ እና የምትታወቅበት መገለጫ ሆኗል፡፡
መርሐ ግብሩ የተመጣጠነ ዝናብ እንዲኖር፣ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ለመኖር እና በምግብ ራስን ለመቻል ትልቅ እገዛ እያደረገም ይገኛል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ተግባራት እንደ ሀገር በተጨባጭ የደን መመናመንን በማስቀረት ሽፋኑን ማሳደግ ተችሏል፡፡
ለካርበን ሽያጭና ዛፍ መትከል ስለሚያስገኘው የቢሊየን ዶላሮች የኢኮኖሚ ምንጭ ማወቅ የአሁኑ ዘመን የሕልውና እና የብልጽግና መሠረትን ለመረዳት ወሳኝ መነሻ ነው።
አረንጓዴ ዐሻራ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ከመቋቋም ባለፈ ታላቅ ሀገራዊና አሕጉራዊ ፋይዳ ያለው ሲሆን÷ ይህ ታሪካዊ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ አዲስ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ጊዜያዊ ዘመቻ ሳይሆን የሀገርን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወስን ሆኖ ቀጥሏል።
በዚህም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውና የምግብ ዋስትናን በተግባር የሚያረጋግጡ የፍራፍሬ ዝርያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ችግኞች በመተከላቸው የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየሩ ይገኛሉ።
ከተከላው ጎን ለጎን ችግኞችን በማፍላትና በመንከባከብ ሂደት ውስጥ ለሚሊየኖች ሰፊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
በአረንጓዴ ዐሻራ የሚተከሉ ችግኞች ከከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው በካይ ጋዝ የመምጠጥ እና የማከማቸት አቅም ስላላቸው ለኢትዮጵያ አዲስ እና ዘላቂ የዶላር መገኛ መስመር እየከፈቱም ይገኛሉ።
መርሐ ግብሩ ከሀገራዊ ፋይዳው ባሻገር የኢትዮጵያን ስልታዊ የውጭ ፖሊሲ እና ቀጣናዊ ትስስር የሚያጠናክር የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ መሳሪያ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ለጂቡቲ፣ ለኬንያ፣ ለሶማሊያ እና ለደቡብ ሱዳን በሚሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን በነጻ በማካፈል በጋራ የመልማትና ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ሀብትን በጋራ የመጠበቅ ራዕይን በተግባር አሳይታለች።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛፍ ከመትከል በእጅጉ የላቀ፣ ሀገራዊ ብልጽግናን ከዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጋር ያስተሳሰረ ታላቅ ስትራቴጂካዊ ርምጃ ነው። ይህ ንቅናቄ ለተተኪው ትውልድ የሚለምልም እና የሚጠቅም ሕያው ቅርስ እና የማያረጅ ውርስ ጥሎ የሚያልፍ የአዲሱ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ማሳያ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄው ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት እያደረገም ይገኛል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ

Sponsored by
Surafel
4 months ago
በነዳጅ ዋጋ መጨመር እና እጥረት ምክንያት የወጭና የገቢ ሸቀጦች በባቡር ሊጓጓዝ ነው
በአሁነ ወቅት በነዳጅ ዋጋ መጨመር እና አልፎ አልፎ በሚከሰተው እጥረት ምክንያት፣ የወጭና የገቢ ሸቀጦች በባቡር መጓጓዝን አጠናክሮ ለመቀጠል ተጨማሪ የባቡር ፉርጎዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ማዘጋጀቱን ነው የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ያስታወቀው።
በኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለየጉምሩክ ኮሚሽን በጻፉት ደብዳቤ አሁን ላይ ባለው የነዳጅ እጥረትና ዋጋ መጨመር ምክንያት ተጨማሪ የጭነት ባቡር ወደ ሥራ ማስገባት አስፈላጊ ሆኗል።
እነዚህ ጎንዶላ ዋጎኖች (CW3 እና CW4) ከላይ ክፍት (Open Top) የሆነና በጭነቱ አይነትና ባህሪ መሠረት በቀላሉ ማኅተም ለመደረግ የማይመቹ ስለሆነ፣ አረንጓዴ ማኅተም (Green Seal) ተደርጎ የሚታወቁ እና በተለየ ሁኔታ የሚታዘዙ የመንግስት ሸቀጦች በእነዚህ ዋጎኖች እንዲጓጓዙ ፈቃድ እንዲሰጥ ኮሚሽኑን ጠይቀዋል።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በባቡር መስመር ላይ የኮንቴነር ጭነቶች (የመንግስትና የግል) ፍላጎት ከፍ ብሎ በመገኘቱ፣ አርባ ፊት ኮንቴነሮችን በጎንዶላ ዋጎኖች (CW3 እና CW4) ላይ መጫን ተጨማሪ መፍትሄ ሆኖ እንደተገኘ አስታውቀዋል።
የዚህ አይነቱ ጭነት በዳዋንሌ ጣቢያ ላይ በቀጥታ ለጉምሩክ ምርመራ የማይታይ ስለሆነ፣ በተለይም ለመንግስት ጭነቶች፣ ከዳዋንሌ ጣቢያ በፊት የቅድሚያ ፍቃድ እንዲሰጥ እና ምርመራው በመዳረሻ ጣቢያ እንዲከናወን ነው የተጠየቀው።
seledadotio

5 months ago
ማኅበረሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን "በከፍተኛ ቁጠባ" እንዲጠቀሙ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሳሰቡ
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት እና በዚሁ ምክንያት የተፈጠረው የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ስለማይታወቅ ሕብረተሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን "በከፍተኛ ቁጠባ" እንዲጠቀሙ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ አሳሰቡ።
በጦርነቱ ምክንያት የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ "አስፈሪ" ሲሉ የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት "በቅርቡ ተጨማሪ የነዳጅ ቁጠባ እርምጃዎችን" ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ይህንን ማሳሰቢ የሰጡት ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 2/2018 ዓ.ም. የኢራን ጦርነት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የፈጠረውን ቀውስ እና በአገር ውስጥ ያለውን የነዳጅ ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ሚኒስትሩ ይህንን መግለጫ የሰጡት መንግሥት በነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ እስከ 17 ብር የሚደርስ ጭማሪ ባደረገ ማግሥት ነው። ማክሰኞ ይፋ በተደረገው የዋጋ ጭማሪ መሠረት 129 ብር ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን 132 ብር ከ18 ሳንቲም ገብቷል።
ተመሳሳይ ዋጋ የነበረው ነጭ ናፍጣ ደግሞ የ10 ብር ጭማሪ ተደርጎበት ዋጋው ወደ 139 ብር ከ84 ሳንቲም ከፍ ብሏል። ከፍተኛ የሆነው የ17 ብር ጭማሪ ያስተናገደው ኬሮሲን ደግሞ 146 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ ከታየው ከፍተኛ ጭማሪ አንጻር መንግሥት ያደረገው ማሻሻያ "በጣም ዝቅተኛ ተደርጎ የሚታይ" እንደሆነ ገልጸዋል።
አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የከፈቱባት ኢራን በአጸፋው ከዓለም ነዳጅ አንድ አምስተኛው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥ ዘግታለች። በተጨማሪም በጦርነቱ የኢራን እና የሌሎች የመካለኛው ምሥራቅ አገራት የነዳጅ መሠረተ ልማቶች ጥቃት ተፈጽሙባቸዋል።
በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ከአውሮፓውያኑ 2022 ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 120 ዶላር ገብቶ ነበር። ኋላ ላይ ግን ቅናሽ ያሳየ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በበርሜል 89 ዶላር እየተሸጠ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ "የዓለም ዋጋ በትንናትነው ዕለት ደረሰበት፣ ጂቡቲ ላይ የምንረከብበት ዋጋ በምናይበት ጊዜ ቤንዚን 205 ብር ከ74 ሳንቲም መሆን ነበረበት። […] አሁንም መንግሥት ቤንዚንን በሊትር 73 ብር ከ56 ሳንቲም እየደጎመ የሚገኝ መሆኑን ያሳያል" ብለዋል።
ነጭ ናፍጣም በዓለም ዋጋ በሊትር 238 ብር ከ13 ሳንቲም እንደደረሰ በመጥቀስም፤ በሊትር 98 ብር ከ29 ሳንቲም በመንግሥት እየደጎመ መሆኑን አስረድተዋል።
"የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ፣ አስፈሪ በሆነ መልኩ እየጨመረ ባለበት ጊዜም ቢሆን በከፍተኛ ድጎማ አሁንም እየቀረበ [ነው]" ያሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ ነዳጅ "በተቀመጠለት የግብይት ሰንሰለት" እና "መንግሥት ባስቀመጠው ዋጋ ብቻ" መሸጥ እንዳለበት አሳስበዋል።
መንግሥት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት እና ዋጋ ቀውስ ሊያስከትል ሚችለውን "ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን አማራጭ" እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል። ከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከል ከዲፖ ማቅረብ እና አጣዳፊ ግዢ መፈጸም የሚሉትን ጠቅሰዋል።
በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት ሊያጋጥም የሚችለውን መስተጓጎል "ለመቋቋም እንዲቻል በሌሎች አማራጮች በአፋጣኝ የነዳጅ ግዢ" ለመፈጸም ጥረት እየተደረገ መሆኑም ገልጸዋል።
አህመድ አክለውም የመካከለኛው ምሥራቅ ፈጠረው ይህ ቀውስ ምን ያህል ሊቆይ እንደሚችል እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል አንስተዋል።
"በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ጦርነት መቼ እንደሚያቆም እና የተፈጠረው የነዳጅ ምርት ላይ ደረሰው ውድመት እንዲሁም የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠረው ችግር እስከ መቼ እንደሚዘልቅ መገመት [እንደማይቻል]" ተናግረዋል።
በመንግሥት ጉዳዩን እየተከታተለ በአገር ውስጥ የነዳጅ "በአስተማማኝ መልኩ እንዲቀርብ" እንደሚደርግ ያነሱት አህመድ፤ "ከዚህ ጎን ለጎን ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ ቁጠባ ሥራ ውስጥ መግባት ይኖርብናል" ብለዋል።
"ሁሉም ነዳጅ ተጠቃሚ አካላት፣ እና መላው ማኅበረሰቡ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ መንግሥዊ ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ሁሉም ነዳጅ ተጠቃሚ አካላት በሙሉ ነዳጅን በከፍተኛ ቁጠባ መጠቀም እንዳለባችሁ ማሳሰብ እንፈልጋለን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከዚህም ባሻገር "በቅርቡ በተጠና ሁኔታ ተጨማሪ [የነዳጅ] የቁጠባ እርምጃዎች ለሕብረሰቡ የሚገለጹ ይሆናል" ሲሉ በመንግሥት ይፋ የሚደረጉ አሠራሮች እንደሚኖሩ አስታውቀዋል።
በአገር ውስጥ የሚታየውን ትክከለኛውን የግብይት ሰንሰለት አለመጠቀም እና መንግሥት ባስቀመጠው ዋጋ ያለመሸጥ ሁኔታ ለማስተካከል የሚወሰደው እርምጃ እንደሚጠናከርም የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ገልጸዋል።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው።

በደወሌ ጉምሩክ ጣቢያ በጥቅም በመመሳጠር በመንግሥት ላይ ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ የኢኮኖሚ ጉዳት አድርሰዋል የተሻሉ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሠረተ
የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው የጉምሩክ ሠራተኞቹ አማኖ መገርሳ እና አብነት ደምስ እንዲሁም ግለሰብ ነጋዴው አዲሱ ግርማ ላይ ነው።
ተከሳሾቹ ታኅሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጂቡቲ ወደ ሀገር የገቡ 2 ሺህ 229 ቴሌቪዥኖችን፣ በሐሰተኛ ሰነድ "የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች" በሚል ስያሜ ያለ ፍተሻ እንዲያልፉ አድርገዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
የጉምሩክ ባለሙያዎቹ ዕቃዎቹን በአካል ሳይፈትሹ "ተፈትሸዋል" የሚል የሐሰት ማረጋገጫ ማኅተም በመምታት ወንጀሉን ማመቻቸታቸው በክሱ ተመላክቷል።
ይህም በመንግሥት ላይ ሊከፈል የሚገባውን 125 ሚሊዮን 900 ሺህ ብር የታክስ እና ቀረጥ ገቢ አሳጥቷል።
ጉዳዩን የሚመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት፣ ተከሳሾች በክሱ ላይ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via ታሪክ አዱኛ

ጅቡቲ ውስጥ ህጻናት በፍንዳታ ተገደሉ
ደቡባዊ ጂቡቲ ውስጥ አራት ህጻናት በፍንዳታ ተገድለዋል ሲሉ ባለሥልጣናት አስታወቁ። አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ግን ህጻናቱ የተገደሉት በድሮን ጥቃት ነው ማለቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የጅቡቲ አቃቤ ሕግ ሀሰን መሐመድ ሀሰን ትናንት ማምሻውን ባወጡት መግለጫ ህጻናቱ አፋር ድሂኪል በተባለው ክልል ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ መገደላቸውን አስታውቀዋል።
የጅቡቲ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ የተባለው ድርጅት በምህጻሩ LDDH ደግሞ አንዲት የስድስት ዓመት እና አንድ የሰባት ዓመት ህጻናት ወዲያውኑ ሲሞቱ በአደጋው የቆሰሉ ሌሎች ሁለት ህጻናት ደግሞ የሕክምና እርዳታ ባለማግኘታቸው ማክሰኞ መሞታቸውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሌሎች 6 ህጻናትም መቁሰላቸውንና ከመካከላቸው አንዱ ከባድ ጉዳት እንደረሰበትም ገልጿል። ድርጅቱ እንዳለው ህጻናቱ የተገደሉት ከብቶች በመጠበቅ ላይ ሳሉ ነበር።
ህጻናቱ በድሮን ጥቃት ነው የተገደሉት የሚለው ድርጅቱ የአሁኑ ጥቃትም በአካባቢው ለስድስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው ብሏል። አቃቤ ሕግ ሀሰን የፍንዳታውን መንስኤ የሚያጣራ አንድ ቡድን በስፍራው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
DW Amharic

6 months ago
ከወረቀት ወደ ተግባር፦ በድሬዳዋ የሚከፈተው የነዳጅ ላብራቶሪ ተስፋና ስጋት
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከጠቅላላ የውጭ ንግድ ገቢዋ ውስጥ ከ 60% እስከ 80% የሚሆነውን ለነዳጅ ግዥ እንደምታውል መረጃዎች ያሳያሉ። ሆኖም ይህን ግዙፍ ሀብት ጥራትና ይዘት የሚቆጣጠር ብሔራዊ ተቋም አለመኖሩ ሀገሪቱን ለዘመናት "ለኬሚካላዊ ወረራ" አጋልጧት ቆይቷል። በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ ስራ ይጀምራል የተባለው የመጀመሪያው የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ፣ ይህንን ክፍተት ለመድፈን የተቃጣ ትልቅ "ተስፋ" ቢሆንም፣ አተገባበሩ ግን በርካታ "ስጋቶች" ተደቅነውበታል።
1. የድሬዳዋው ተስፋ፦ የኢኮኖሚ ደህንነት ጥበቃ
ላብራቶሪው በድሬዳዋ መከፈቱ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አለው። አብዛኛው ነዳጅ የሚገባው በጂቡቲ በኩል እንደመሆኑ፣ ነዳጁ ወደ መሀል ሀገር ተሰራጭቶ ጉዳት ሳያደርስ በድንበር አካባቢ መቆጣጠር ያስችላል።
ተስፋ አንድ፦ የውጭ ምንዛሬ ቁጠባ ከዚህ ቀደም ነዳጅን ወደ ውጭ ሀገር ልኮ ለማስፈተሽ የሚወጣው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በሀገር ውስጥ ይቃለላል። ይህም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በትንሹም ቢሆን ለማቃለል ይረዳል።
ተስፋ ሁለት፦ የመሠረተ ልማት ዕድሜ መጨመር በኢትዮጵያ የሚገኙ ተሽከርካሪዎችና የኢንዱስትሪ ማሽኖች ጥራት በሌለው ነዳጅ ምክንያት አላስፈላጊ ለሆነ ብልሽት ይዳረጋሉ። ላብራቶሪው ይህንን በማስቀረት የሀገር ሀብትን ይከላከላል።
2. ዓለም አቀፍ ተሞክሮ፦ ከኬንያ እስከ ህንድ
ኢትዮጵያ የምታስጀምረው ይህ ስራ በሌሎች ሀገራት እንዴት ይተገበራል?
የኬንያ ስኬት (Kenya Bureau of Standards): ኬንያ በነዳጅ ጥራት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ታደርጋለች። በተለይም በነዳጅ ላይ የማይታይ የኬሚካል ምልክት (Fuel Marking) በማድረግ፣ ነዳጁ ከወደብ እስከ ማደያ ድረስ መበረዝ አለመበረዙን በየቦታው ትፈትሻለች። ይህም በመንግስት ላይ ይደርስ የነበረውን የታክስ ስወራ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
የህንድ ተሞክሮ፦ ህንድ ውስጥ የነዳጅ ላብራቶሪዎች በዲጂታል ትስስር የተሳሰሩ ናቸው። ፍተሻው እንደተጠናቀቀ ውጤቱ በቀጥታ ለዋናው መቆጣጠሪያ ማዕከል ይላካል። ይህም የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነትንና ሙስናን ይቀንሳል።
3. ጥልቁ ስጋት፦ የ"ወረቀት ላይ" ትርፍ ወይስ እውነተኛ ቁጥጥር?
ላብራቶሪው ቢገነባም በሚከተሉት ነጥቦች ዙሪያ ትልቅ ስጋት አለ፦
ሀ. የሙስና እና የታማኝነት ፈተና
ነዳጅ ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ ነው። በናይጄሪያ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የነዳጅ ላብራቶሪዎች ቢኖሩም፣ ባለሙያዎች ከአስመጪዎች በሚቀርብላቸው ጉቦ ምክንያት ጥራት የሌለውን ነዳጅ "አልፏል" ብለው የምስክር ወረቀት የሚሰጡበት አጋጣሚ አለ። በድሬዳዋ የሚሰማሩ ባለሙያዎች ከዚህ ፈተና ምን ያህል ነጻ ይሆናሉ? የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነው።
ለ. "ነዳጅ ማቀላቀል" (Fuel Adulteration)
በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ችግር ርካሹን ኬሮሲን ከቤንዚን ወይም ከናፍጣ ጋር ማቀላቀል ነው። ይህን ወንጀል ለመለየት ላብራቶሪው እጅግ ዘመናዊ የሆኑ እንደ Gas Chromatography (GC) ያሉ መሣሪያዎች ሊኖሩት ይገባል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ዋና ዳይሬክተር መዓዛ አበራ "ዘመናዊ መሣሪያዎች ተዘጋጅተዋል" ቢሉም፣ እነዚህ መሣሪያዎች በየጊዜው ካልታደሱና ኬሚካላዊ ለውጦችን መለየት ካልቻሉ ተቋሙ ስም ብቻ ሆኖ ይቀራል።
4. የጥናት ዳታ፦ የጥራት መጓደል ጉዳት
በአፍሪካ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፦
ጥራት የሌለው ነዳጅ አጠቃቀም የተሽከርካሪዎችን የሞተር ዕድሜ በአማካይ በ 30% ያሳጥራል።
በአየር ላይ የሚለቀቀውን የካርቦንና የሰልፈር መጠን በ 20% በመጨመር ለዜጎች የመተንፈሻ አካላት በሽታ ምክንያት ይሆናል።
ኢትዮጵያ በዚህ ቁጥጥር አለመኖር ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ለማሽነሪዎች ጥገናና ለጤና ወጪ እንደምታባክን ይገመታል።
5. ማጠቃለያ
የድሬዳዋው የነዳጅ ላብራቶሪ መከፈት ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ነጻነት ትልቅ እርምጃ ነው። ሆኖም ግን ላብራቶሪው ውጤታማ የሚሆነው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር ተያይዞ ሲሰራ ብቻ ነው፦
ገለልተኝነት፦ ተቋሙ ከፖለቲካዊና ከንግድ ተፅዕኖ ነጻ ሆኖ ሳይንሳዊ ውጤቱን ብቻ መሰረት አድርጎ መስራት አለበት።
ተከታታይ ቁጥጥር፦ ፍተሻው በድሬዳዋ ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም። ነዳጁ ማደያ ላይ እስኪፈስ ድረስ በየቦታው ድንገተኛ ፍተሻ የሚያደርግ ቡድን ሊኖር ይገባል።
ዓለም አቀፍ እውቅና (Accreditation): ላብራቶሪው የ ISO/IEC 17025 እውቅና ካላገኘ፣ ዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅራቢዎች የፍተሻ ውጤቱን ባለመቀበል በሕግ ሊሞግቱ ይችላሉ።
ባጠቃላይ፣ የድሬዳዋው ላብራቶሪ የተቃጣው ተስፋ ወደ ተግባር ተተርጉሞ ሀገሪቱን ከነዳጅ ማፊያዎችና ከብክነት ይታደጋል ወይስ በቢሮክራሲ ተተብትቦ ሌላው "የወረቀት ላይ" ስኬት ሆኖ ይቀራል? የሚለው ለጊዜ የሚተው ቢሆንም፣ ጅማሮው ግን አበረታች ነው።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ምስል

🚂 የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ለዓመታት ቆመው በነበሩ ዋጎኖች ነዳጅ ማጓጓዝ ጀመረ ⛽️🇪🇹🇩🇯
#ethiopia | 120,000 ሊትር ናፍጣ በሙከራ ሂደት በስኬት ተጓጉዟል
የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ለዓመታት አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ 110 የነዳጅ ማጓጓዣ ዋጎኖችን ወደ ሥራ በማስገባት፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅን በባቡር የማጓጓዝ የሙከራ ሂደት በስኬት ማጠናቀቁን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።
የስኬቱ ድምቀቶች:
✅ አስቸኳይ መፍትሄ:
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጂቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል ባደረጉት ጉብኝት የሰጡትን አቅጣጫ ተከትሎ፤ ለዓመታት አገልግሎት አልባ የነበሩ ዋጎኖች ወደ ስራ ገብተዋል።
✅ የሙከራው ውጤት:
ከናሽናል የነዳጅ ኩባንያ (ኖክ) ጋር በመተባበር 120,000 ሊትር ናፍጣ ከአዲስ አበባ ደቡባዊ ዳርቻ ወደሚገኘው ኢንዶዴ የባቡር ዴፖ በስኬት ተጓጉዟል።
✅ መሰረተ ልማት:
በሆራይዘን የነዳጅ ጄቲ እና በባቡር ጣቢያው መካከል የ1.5 ኪ.ሜ የባቡር መስመር ትስስር ለመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው።
ፋይዳው ምንድን ነው?
እንደ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ያሉ ስልታዊ ምርቶችን በባቡር ማጓጓዝ መጀመሩ፤ የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ እና አቅርቦትን እንደሚያቀላጥፍ ይታመናል።
ወደ ሙሉ የንግድ እንቅስቃሴ ለመግባት የደህንነት መስፈርቶች እየተፈተሹ ነው።
ለኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ ትልቅ እመርታ!
#ethiodjiboutirailway #fueltransport #logistics #ethiopia #djibouti #development #takeleuma #pmabiy #noc #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የአየር ሀይል ጥንካሬ‼️
በ2026 ግሎባል ፋየር ፓወር የአገራት የአየር ሀይል አቅምን ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ 104 ጠቅላላ የአየር ሀይል ብዛት በመያዝ ከአለም ሀገራት 70ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከአፍሪካ ሀገራት ደግሞ በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ግብፅ(1088)፣አልጀሪያ (620)፣አንጎላ(278)፣ሞሮኮ(271) እና ሱዳን (183) አየር ሀይል በመያዝ ከአንድ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ወታደራዊ አቅም ደረጃ ዝርዝር ውስጥ ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት 38ቱ ብቻ የተካተቱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችው ጂቡቲ ካልተካተቱት ውስጥ ናት።
በአጠቃላይ ወታደራዊ አቅም ሲታይ ከአፍሪካ ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ናቸው።
የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤርትራ በ 20 ወታደራዊ አየር ሃይል ከአለም 118ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

7 months ago
🇪🇹🇩🇯 ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ቀጠናዊ ንግድን ልታሳድግ መሆኑን የጅቡቲው ባለሥልጣን ገለፁ
💱 ይህ እንቅስቃሴ ሀገሪቱ የውጭ ምርቶችን ከማስገባት ይልቅ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ወደተመሰረተ የምጣኔ ሀብት ሞዴል ለማሸጋገር ያላትን ስትራቴጂያዊ እቅድ የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉ የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለሥልጣን ኃላፊ አብዲቃድር ኡመር ሀዲ ለጂቡቲ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አሳውቀዋል፡፡
"ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን በመቀነስ የምትልከውን ለመጨመር ትሻለች፡፡ አንድ ሀገር ከፍጆታዋ በላይ ስታመርት ኢኮኖሚዋ እየጠነከረ ይሄዳል" በማለት ጅቡቲ ለውጡን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አብዲቃድር ተናግረዋል።
🚢 ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 1.8 ሚሊየን ቶን የግብርና ማዳበሪያ ታስገባለች ያሉት ባለሥልጣኑ፣ አሁን ግን የነዳጅ ምርቶችን እና የግብርና ግብዓቶችን ወደ ውጭ ለመላክ አቅዳለች፤ ጅቡቲም ቀዳሚ የሎጂስቲክስ መተላለፊያ ሆና ታገለግላታለች ብለዋል።
ከሰሞኑ ወደ ጅቡቲ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶራሌህ ሁለገብ ወደብ እና የሆራይዘን ነዳጅ ተርሚናልን ጎብኝተዋል፡፡
Sputnik

44 የአፍሪካ ሀገራት
የጉዞ እገዳ (Travel Ban) ተጥሎባቸዋል
#ethiopia | እስካሁን 44 የአፍሪካ ሀገራት በጉዞ እገዳ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 10 ሀገራት ብቻ ከእገዳው ነጻ መሆናቸውን ጠበቃ ሙላለም ጌታቸው ከአሜሪካ አስታውቀዋል።
✅ የጉዞ እገዳ የሌለባቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት፡-
🇧🇼 ቦትስዋና
🇰🇲 ኮሞሮስ
🇩🇯 ጂቡቲ
🇸🇿 ኢስዋቲኒ (ስዋዚላንድ)
🇰🇪 ኬንያ
🇲🇬 ማዳጋስካር
🇲🇺 ሞሪሸስ
🇳🇦 ናሚቢያ
🇸🇨 ሲሸልስ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
ሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት በእገዳ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል።
ጠበቃ ሙላለም ጌታቸው
#travelban #africa #news

🇪🇹🇩🇯 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከልዑክ ቡድናቸው ጋር ጁቡቲ ገቡ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ጂቡቲ በማምራት ከፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
🤝 አቀባበልና የውይይቱ ጭብጦች
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ ሲደርሱ በፕሬዚዳንት ጉሌህ ደመቅ ያለ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ መሪዎቹ በዝግ ባደረጉት ቆይታ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተው መክረዋል፦
* ጂኦፖለቲካ እና ደህንነት፦ በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በጋራ ለመጋፈጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።
* የኢኮኖሚ ትስስር፦ የሁለቱን ሀገራት የንግድ፣ የሎጂስቲክስ እና የልማት ስራዎች ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
* የጋራ ራዕይ፦ ይህ ውይይት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትስስርና ለጋራ ብልጽግና ያለውን ጽኑ አቋም የሚያሳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
💡 "የወል ጽኑ አቋም"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሁለቱ ሀገራት ትብብር ከንግድ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መረጋገጥ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ጂቡቲ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የገቢና ወጪ ንግድ በር መሆኗን ተከትሎ፣ መሰል ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ውይይቶች ለሎጂስቲክስ ዘርፉ ቅልጥፍና ወሳኝ ናቸው ተብሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢትዮጵያ #ጂቡቲ #ዐቢይአሕመድ #ኢስማኤልኦማርጉሌህ #ዲፕሎማሲ #ቀጣናዊሰላም #ንግድናሎጂስቲክስ #ምሥራቅአፍሪካ #ethiopia #djibouti #regionalintegration

እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠት እና የቀይ ባሕር ቀጠና አዲሱ የጂኦፖለቲካዊ ለውጥ
ከመሀመድ ካህላፍ ፅሁፍ የተወሰደ
ሶማሊላንድ ማን ናት?
ሶማሊላንድ በሰሜናዊ ሶማሊያ፣ በኤደን ባህረ ሰላጤ ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ቀጠና ነው። በምስራቅ ከፑንትላንድ፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በምዕራብ ከጂቡቲ ጋር ይካለላል። ቀጠናው እ.ኤ.አ. በ1991 የማዕከላዊ ሶማሊያ መንግስት መፈራረስን ተከትሎ፣ ነጠላ የነጻነት አዋጅ አውጇል። ይህ ውሳኔ የተመሰረተው እስከ 1960 ድረስ የእንግሊዝ ጥበቃ የሚደረግለት ራሱን የቻለ ግዛት እንደነበረና በኋላም ከጣሊያን ሶማሊላንድ ጋር በመቀላቀል የሶማሊያ ሪፐብሊክን መመስረቱን ታሪክ በማጣቀስ ነው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቀጠናው ከቀሪው የሶማሊያ ክፍል ጋር ሲነጻጸር በአንጻራዊ ሁኔታ ውጤታማ የሆኑ የራስ-አስተዳደር ተቋማትን መገንባት ችሏል። እነዚህም የሚመረጥ መንግስት፣ ፓርላማ፣ የጸጥታ አገልግሎት፣ የሀገር ውስጥ ገንዘብ እና የተረጋጋ የአስተዳደር ስርዓትን ያካትታሉ።
ይህም በምዕራባውያን ጽሑፎች ውስጥ ግጭት በበዛበት አካባቢ እንደ "የመረጋጋት ደሴት" ተደርጎ እንዲገለጽ አድርጎታል። ሆኖም ግን፣ እስካሁን ድረስ ይፋዊ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላገኘ ሲሆን፣ በህግ ደረጃም የሶማሊያ ሪፐብሊክ አካል ሆኖ ይቆጠራል።
የእስራኤል እውቅና መስጠት
ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን የዲፕሎማሲ ግንብ የሰበረ ታሪካዊ እርምጃ በመውሰድ፣ እስራኤል ሶማሊላንድን ዋና ከተማዋ ሃርጌሳ የሆነ ሉዓላዊ እና ገለልተኛ ሀገር አድርጋ በይፋ ማወቋን አስታውቃለች።
እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ያሳለፈች የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገር ሆናለች።
ይህ ለውጥ ሊመጣ የቻለው በኅዳር 2024 በሶማሊላንድ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ የሥልጣን መዋቅሩ በመቀየሩና እስካሁን ከነበረው የተለየ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን መንገድ በመከፈቱ ነው። በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው የዋታኒ ፓርቲ መሪ የሆኑትና በሶማሊያ የዲፕሎማሲ መስክ ልምድ ያላቸው የተቃዋሚው ዕጩ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (በቅጽል ስማቸው "አይሮ") ማሸነፋቸው ለዚህ ምክንያት ሆኗል።
እንደ እስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ መስኮች ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት በፍጥነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
ከዚህም በተጨማሪ በኤደን ባህረ ሰላጤ እና በባብ አል-መንደብ ሰርጥ አቅራቢያ ካለው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ጋር የተያያዙ ያልተገለጹ የደኅንነት ትብብሮችንም ታደርጋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለዚህ "የዲፕሎማሲ ስኬት" አስተዋጽኦ ላደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩና ለሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ ምስጋና አቅርበዋል።
የዓረብ እና የቱርክ ቁጣ - የግዳጅ ጥምረት
ለዚህ ውሳኔ ከቀጠናው የተሰጠው ምላሽ ፈጣንና ጠንካራ ነበር። ግብፅ፣ ሶማሊያ፣ ቱርክ እና ጅቡቲ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ የእስራኤልን ውሳኔ አውግዘዋል። የሶማሊያን አንድነትና ሉዓላዊነት የሚጥስ ማንኛውንም እርምጃ እንደሚቃወሙና ለሶማሊያ ሕጋዊ ተቋማት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ ይህ የእስራኤል እውቅና ግብፅና ቱርክን "የግዳጅ ጥምረት" ውስጥ በመክተት በሞቃዲሾ የሚገኘውን የፌዴራል መንግሥት በወታደራዊ ኃይል እንዲደግፉ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህ ደግሞ በተለይ በሶማሊላንድና በፑንትላንድ መካከል በሚገኘው "ሱል" ግዛት ላይ ቀጠናዊ ኃይሎችን ወደ ውክልና ጦርነት ሊያስገባ ይችላል ተብሎ ይፈራል።
የምስጢራዊ ጉብኝት ውጤት
በዚህ ወር የተሰጠው እውቅና በድንገት የመጣ ሳይሆን፣ በከፍተኛ የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ሥራዎች የታጀበ ነበር። ፕሬዝዳንት አይሮ ጥቅምት ላይ ወደ እስራኤል ምስጢራዊ ጉብኝት በማድረግ ከሞሳድና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። ይህ ጉብኝት "እውቅና በስትራቴጂካዊ ቦታ" በሚል ቀመር የደኅንነትና የፖሊሲ መሠረቶችን ጥሏል።
ለኔታንያሁ ይህ ስምምነት ዲፕሎማሲያዊ ድል ሲሆን፣ ይህም በዋሽንግተን ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት ስብሰባ እንደ ትልቅ ስኬት ይዘውት ያቀረቡት ጉዳይ ነው።
ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማዛወር ዕቅድ
የእስራኤል ውሳኔ ከወራት በፊት እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ወደ የአፍሪካ ቀንድ (ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድን ጨምሮ) ለማዛወርና ለማስፈር እያሰበች ነው ከሚለው ዘገባ ጋር ተያይዟል። እስራኤል ለሶማሊላንድ ለሰጠችው እውቅና እና የገንዘብ ድጋፍ በምትኩ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ፍልስጤማውያን ሶማሊላንድእንድትቀበል ለማድረግ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አባስም ይህንን የእውቅና እርምጃ ፍልስጤማውያንን ለማፈናቀል የሚደረግ የቴል አቪቭ ተስፋ የቆረጠ ሙከራ አካል ነው በማለት ተቃውመዋል።
የሦስቱ ዋና ዋና ተግባራት መድረክ
ከሁሉም በላይ ሶማሊላንድ ለእስራኤል በርካታ መልክዓ ምድራዊ ጥቅሞችን ትሰጣለች። የ850 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ ያላት ሶማሊላንድ፣ የባብ አል-መንደብ መግቢያን ለመቆጣጠር ትረዳለች። የእስራኤል ብሔራዊ የደኅንነት ጥናት ተቋም (INSS) እንደሚለው፣ ይህ አካባቢ ለእስራኤል ሦስት ዋና ዋና ጥቅሞችን ይሰጣል፦
ከየመን የሚተኮሱ ሚሳይሎችንና ድሮኖችን ለመከታተልና የራዳር መሣሪያዎችን መትከል።
በጠላት ዒላማዎች (በተለይም በሁቲዎች) ላይ ለሚደረጉ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች እንደ መነሻ መጠቀም።
ቀይ ባሕር "የኢራን ሐይቅ" እንዳይሆንና ለሁቲዎች የሚደርሰውን የባሕር ላይ የአቅርቦት መስመር መቁረጥ።
ወታደራዊ ካምፕ... በርበራ ወይስ ዘይላ?
አንዳንድ ዲፕሊማቶች እንደሚሉት ይህ እውቅና ከእስራኤል ውጭ ትልቁን ወታደራዊ ካምፕ ለመመሥረት የሚደረግ የፖለቲካ ዝግጅት ነው። ምርጫው በሁለት ቦታዎች መካከል ነው፦
የበርበራ ወደብ፦ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የፈሰሰበት፣ ዘመናዊ መሠረተ ልማትና ወታደራዊ አየር ማረፊያ ያለው፣ እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው አውራ ጎዳና መነሻ በመሆኑ የተመረጠ ነው።
የዘይላ ከተማ፦ ከጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝና ለባብ አል-መንደብ በጣም ቅርብ የሆነች ታሪካዊ ቦታ ናት። ይህም ለየመንና ለኤርትራ ቅርብ በመሆኑ ለኤሌክትሮኒክስ የስለላ ሥራዎች ተመራጭ ያደርጋታል።
የኢኮኖሚ ማበረታቻዎች እና የኢትዮጵያ ሚና
እስራኤል በ "በርበራ ኮሪደር" አማካኝነት ኢኮኖሚዋን ከአፍሪካ ገበያ ጋር ለማገናኘት ትፈልጋለች። ይህ ኮሪደር ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ ሲሆን፣ እስራኤል በጅቡቲ ላይ ብቻ ከመደገፍ እንድትወጣና የቴክኖሎጂ ምርቶቿን ወደ ሰፊው የኢትዮጵያ ገበያ እንዲሁም ወደ ኬንያና ኡጋንዳ እንድታደርስ ይረዳታል።
የቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምላሾች
ሶማሊያ፦ እርምጃውን "የሉዓላዊነት ጥሰት" በማለት አውግዛለች። ከግብፅ ጋር የፈረመችውን የጋራ መከላከያ ስምምነት ወደ መተግበር ተሸጋግራለች።
ግብፅ፦ በእስራኤልና በኢትዮጵያ መካከል የሚፈጠር ጥምረት ከደቡብ በኩል ይከበኛል የሚል ስጋት አላት። ይህም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ የኢትዮጵያን አቋም ሊያጠናክር ይችላል ብላ ታምናለች።
የአፍሪካ ሕብረት፦ የቅኝ ግዛት ድንበሮች መከበር አለባቸው የሚለውን መርህ በመጥቀስ እውቅናውን ውድቅ አድርጓል። ይህም በሌሎች ሀገራት (እንደ ናይጄሪያና ካሜሩን) የመገንጠል እንቅስቃሴን ሊያነሳሳ ይችላል የሚል ስጋት አለው።

የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር የመጓዝ ፍጥነትን በሰዓት ወደ 120 ኪሎ ሜትር ለማሳደግ እየተሠራ ነው
#ethiopia | የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር ፍጥነት እንዲጓዝ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርዖ ሐሰን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ መስመሩ በመጀመሪያ ሲገነባ 120 ኪሎ ሜትር በሰዓት ፍጥነት እንዲኖረው ታስቦ የተሠራ ነበር።
ሆኖም ቀደም ሲል በአካባቢው በነበሩ የጸጥታ ችግሮችና የስርቆት ድርጊቶች ምክንያት የመጓዝ ፍጥነቱ ወደ 40 ኪሎ ሜትር በሰዓት ዝቅ ብሎ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተከናወኑ የተቀናጁ የጥበቃና የክትትል ሥራዎች አሁን ላይ ፍጥነቱን ወደ 60 ኪሎ ሜትር በሰዓት ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በቀጣይም የባቡሩን የመጓዝ ፍጥነት ወደ ታለመለት 120 ኪሎ ሜትር በሰዓት ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።
የባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ሥራውን ከተረከቡ በኋላ የጥገና ወርክሾፖችን በማጠናከርና የቴክኒክ አቅማቸውን በማሳደግ፣ የሚገጥሙ ችግሮችን በፍጥነት የመፍታት አቅም መፈጠሩም ለፍጥነቱ መጨመርና ለሥራው ቅልጥፍና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገልጿል ሲል ጋዜጣ ፕላስ ዘግቧል።

የጉዞ ማስታወሻ
ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል
(ክፍል ሁለት - የድሬዳዋ አቀባበል)
#ethiopia | የሌሊቱን ጉዞ በግርማ ሞገስ ሲያደርግ ያደረው የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር ቁጥር 202፣ የምሥራቋን ፈርጥ ድሬዳዋን ከተማ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ሲሆን ደረሰ።
ድሬዳዋን "የበረሃዋ ንግሥት" ይሏታል። ዛሬ ግን ከንግሥትነቷ በላይ "የፍቅር ከተማ" መሆኗን በተግባር አሳይታናለች። ባቡሩ ቆሞ እግራችንን መሬት ሲረግጥ የጠበቀን አቀባበል ከመንፈሳዊ ጉዞ በላይ የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ማሳያ ነበር።
ከባቡር ጣቢያው ጀምሮ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተዘጋጁት በርካታ መርሃ-ግብሮች እጅግ ደማቅ ነበሩ።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ስፍራዎች ተገኝተው፣ እንግዶችን ያለ እረፍት ሲያስተናግዱና ሲቀበሉ መዋላቸው የድሬዳዋን እንግዳ ተቀባይነት ሌላ ከፍታ ላይ ሰቅሎታል። ይህ ተግባር የሃይማኖት ልዩነት ሳይገታን፣ በፍቅርና በሰላም አብሮ የመኖር ትልቅ ተምሳሌት ነው።
ከሰዓት በኋላ ጉዟችን የድሬዳዋን ሙቀት ትቶ ወደ ቀዝቃዛማውና ተራራማው የሐረርጌ ምድር አቀና።
አረንጓዴ የለበሱት የሐረርጌ ተራሮችና በየመንገዱ ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የሚጓዙ በእግሩ የሚጓዘው ወጣት፣ አዛውንትና ህጻናት ማየት ጉልበት ይሆነናል። አሁን አቅጣጫችን በመንፈሳዊ ዝማሬ ታጅበን ወደ ደብረ ኃይል ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሆነ።
ይቀጥላል...
(ጌትነት ተመስገን)
የጉዞ አጋራችን
🙏 የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር
🙏 የዮዳሄ ሀገር አቀፍ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበርን ከልብ እናመሠግናለን።

8 months ago
ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን ይፋ አደረገች
በርበራን፣ ሞምባሳን፣ ጂቡቲና ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ሁሉንም ወደቦች በባቡር መስመር ለማገናኘት ያቀደውን ፕሮጀከት ጥናት በኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች መሠራቱን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርዖ ሐሰን፣ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ እንደገለፁት፣ ወደቦችን ለማገናኘት የተጠኑ አዳዲስ የባቡር መስመሮችም ወደ ተግባር እንዲገቡ አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የባቡር መሠረተ ልማት ዝርጋታ የሀገሪቱን የሎጅስቲክስ ቅልጥፍና በእጅጉ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።

🚂 የጉዞ ማስታወሻ
ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል - በባቡር
(ክፍል አንድ)
#ethiopia | ታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ለቡ የሚገኘው የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ጣቢያ እንደወትሮው ሳይሆን ለየት ባለ ድምቀት አሸብርቋል።
ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የሚጓዙ ምዕመናን የመሳፈሪያ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ በታላቁ አዳራሽ ተሰባስበዋል። የአዳራሹ ድባብ በመንፈሳዊ ትምህርት እና ዝማሬ ተሰጥቷል።
ከምሽቱ 12:30 ሲሆን፣ ወደ ድሬዳዋ የሚጓዘው ባቡር መስመር ቁጥር 202 ከቦታው ቆመ። ከ2600 በላይ የሚሆኑ ተሳፋሪዎች በሁለት ረጅም ሰልፎች ተከፍለው፣ የፍተሻ መስመር ካለፉ በኋላ ወደ ባብር ሰረገላዎቹ መግባት ጀመሩ። የባቡሩ ግዙፍነትና ዘመናዊነት ለጉዞው ልዩ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል።
ባቡሩ በዝግታ በተዘጋጀለት የጉዞ መስመር ከምሽቱ 2:40 መንቀሳቀስ ሲጀምር፣ የአዲስ አበባ የምሽት መብራቶች በመስኮት በኩል እየራቁ መሄድ ጀመሩ። ይህ ጉዞ የዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የባቡር ታሪክና የከተሞችን እድገት ወደኋላ የሚያስታውስ ትልቅ ክስተት ነው።
የኢትዮጵያ የባቡር ታሪክ ሲነሳ የአፄ ምኒልክ የፈጠራና የሥልጣኔ ጥማት አብሮ ይነሳል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ኢትዮጵያን ከውጭው ዓለም ጋር ለማገናኘት የታለመው ይህ ፕሮጀክት፣ በ1886 ዓ.ም በአፄ ምኒልክ ፈቃድና በአልፍሬድ ኢልግ አማካኝነት የግንባታው ስምምነት ተፈረመ።
ግንባታው ከጅቡቲ ተነስቶ አዲስ አበባ ለመድረስ ረጅም ዓመታት የፈጀ ሲሆን፣ ከፍተኛ ገንዘብና የሰው ኃይል በወቅቱ የጠየቀ ነበር። ታዲያ ንጉሱ ይህን ኘሮጀክት ሳያጠናቀቅ ህይወታቸው ቢያልፍም በ1910 በልጃቸው ንግሥተ ነገስታት ዘውዲቱ አማካኝነት ተጠናቆ ተመርቋል።
የኢትዮጵያ ምድር ባብር መስመሩ መዘርጋት ለኢትዮጵያ ከተሞች ምስረታና እድገት ከሚጠቀሱ ዋነኛው መንስዔ መካከል አንዱ ነው።
በወቅቱ የባቡሩ ሐዲድ ያረፈባቸው ጣቢያዎች ሁሉ ዛሬ የምናያቸው ታላላቅ ከተሞች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል።
ከነዚህ መካከል አንዷ ድሬዳዋ ነዋ ከተማ ናት ድሬ የባቡር መስመሩ ከአዲስ አበባ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ለረጅም ጊዜ መናኸሪያ ሆና በማገልገሏ፣ ድሬዳዋ በባቡር ምክንያት የተቆረቆረችና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን የበቃች ከተማ ናት።
ሌላኛዋ ከተማ የቀድሞ ናዝሬት የዛሬዋ አዳማ የባቡሩ የንግድ ዕቃዎችን የሚያራግፍበትና የሚጭንበት በመሆኑ፣ አዳማ ከትንሽ መንደርነት ተነስታ የንግድ ማዕከል ከተማ ሆናለች።
ቢሾፍቱ ፣ መተሃራ እና ሞጆ የባቡር ጣቢያዎችን ተከትለው የለሙና የንግድ እንቅስቃሴ የደራባቸው አካባቢዎች ናቸው።
ባቡሩ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ባህልን፣ ቴክኖሎጂንና ዘመናዊነትን ከቦታ ቦታ በማጓጓዝ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ቀይሮታል።
አሁን ባቡር መስመር 202 ጨለማውን እየቀደደ ወደ ምሥራቅ እየገሰገሰ ነው።
ይቀጥላል ....
የጉዞ አጋራችን የኢትዮ - ጁቡቲ ባብር ከልብ እናመሠግናለን 🙏
(ጌትነት ተመስገን )

"የትራፊክ ቅጣቱ አንሷል" ሚንስትሩ
"በትራፊክ ቅጣቱ ተማረናል" አሽከርካሪዎች
በኢትዮጵያ ከሚፈፀመው የትራፊክ ደንብ ጥፋት ብዛት ጋር ሲተያይ የሚቀጣው አሽከርካሪ አነስተኛ ነው ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከአባላቱ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።
የምክር ቤት አባሉ አቶ ዳዉድ መሃመድ አሽከርካሪዎች የመንግስት ገቢ እቅድን ለማሳደግ በሚል በትራፊክ እንደሚቀጡ መናገራቸውን አስረድተዋል።
አቶ ዳውድ አሽከርካሪዎች በተለይም በአዲስ አበባ የመንግስት ገቢ ለማሳደግ በሚል እቅድ አሽከርካሪዎች እንቀጣለን የሚል ቅሬታ እንደሚቀርቡ ጠቁመዋል።
ከፍተኛ ገቢ ለማግኝት እንደሚታቀድ፤ እቅዱን ለማሳካት ደግሞ በወሩ አልያም በዓመቱ መጨረሻ ላይ ብዙ አሽከርካሪዎች እንደሚቀጡ ይናገራሉ እውነቱ ይህ የደንብ ማስከበር ሂደት የትራፊክ ስርዓቱን ለማስከበር ነው ወይስ ገቢ እንዲጨምር ነው? ግባቹ የቱ ነው ሲሉ ጠይቀዋል።
ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ "በእኛ አገር፣ በእኛ እምነት ቅጣት ነው የሌለው" ሲሉ መልሰዋል።
"ስላልተቀጣ ነው ሰው የሚያጠፋው" ያሉት ሚኒስትሩ ‘’የምናሽከረክር ሰዎች ብንታዘብ ሰው መብራት አያከብርም የሚቆጣጠር ትራፊክ ከሌለ ቀይ መብራትም ይጥሳል" ሲሉ ተናግረዋል።
ቅጣት የሚጣለው ጥፉት ሲፈፀም እንደሆነ ያስረዱት ሚኒስትር አለሙ "ሳያጠፋ ሰው አይቀጣም፤ በዝቷል፣ አንሷል ከማለታችን በፊት አሽከርካሪው ቅጣትን መፍራት አለበት" ብለዋል።
ሰው ካሜራ ተገጥሞ እንኳን አይፈራም ህግንም አያከብርም የተለመደውን ዩኒፎርም የለበሰ ፖሊስ ካላየ በቀር ሲሉ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ አሽከርካሪ ህግን እንዲያከብር ነው መረባረብ ያለብን እንጂ ቅጣት በዛ የሚሊው ከሌሎች ጎረቤት ሀገሮች አንጻር ገና የእኛ አገር ቅጣት በጣም ትንሽ ነው ሲሉ ከምክር ቤት አባል ለተነሳላቸው ጥያቄ መልሰዋል።
‘’ያለአግባብ የሚቀጡ ካለ እነሱን ማረም ይገባል ነገር ግን በእኛ ድምዳሜ ግን ቅጣት ያንሳል" ብለዋል።
ይህ ደግሞ ከጂቡቲ ጋር እንኳን ምን እንደሚመስል ማየት ይቻላል ሲሊ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ዘገባው የሸገር ሬዲዬ ነው

ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሀይል ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ‼️
ባለፉት አራት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሀይል ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ተቋሙ በሀገር ውስጥ ላሉ ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች፣ ለኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር እና በማይኒንግ ዘርፍ ተሰማርተው ክፍያን በዶላር ለሚፈፅሙ አካላት እያቀረበ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ለውጭ ኤሌክትሪክ ሃይል ፈላጊ ሀገራት የሚያቀርብ ሲሆን በዋነኝነት ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ታንዛንያ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በ2018 በጀት አመት ባለፉት አራት ወራት ለኬንያ፣ ጁቡቲ እና ታንዛንያ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 46 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ሁለተኛው ምዕራፍ የደቡብ ሱዳን -ኢትዮጵያ- ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሁለተኛው ምዕራፍ የደቡብ ሱዳን -ኢትዮጵያ- ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር ግንባታ ማስጀመሪያ የ214 ነጥብ 47 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ አፀደቀ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ 181 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በኢትዮጵያ በኩል ለሚካሄደው የፕሮጀክቱ አካል ድጋፍ ይውላል ብሏል።
ገንዘቡ ለ67 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ እና የ50 ኪሎ ሜትር መጋቢ መንገዶች ማሻሻያ ይውላል።
የመንገድ ግንባታው የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ብሎም ቀጠናዊ የንግድ ትስስር እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ባንኩ አስታውቋል።

9 months ago
ምድቡን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ከ ኬንያ ይጫወታሉ
#ethiopia | በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ውድድር የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ደርሷል፡፡ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ እየተደረገ በሚገኘው መድረክ ዛሬ የሁለቱም ምድብ የመጨረሻ ጨዋታች ይደረጋሉ፡፡
ምድብ አንድ ላይ የሚገኝው የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን አሸንፎ በአንዱ ደግሞ ነጥብ ተጋርቶ ከምድቡ ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በዚሁ ምድብ የምትገኝው ኬንያም በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
ሁለቱ ቡድኖች አንድ ጨዋታ እየቀራቸው ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም ምድቡን በበላይነት ለማጠናቀቅ 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡
ሁለቱ ወጣት ቡድኖች እኩል ነጥብ መያዛቸው ጨዋታውን እንዲጠበቅ የሚደርገው ሲሆን አሸናፊው በቀጥታ ምድቡን በአንድኝነት ያጠናቅቃል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ዛሬ ጨዋታውን ከማድረጉ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ትላንት በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አከናውኗል፡፡በዚሁ ምድብ 7 ሰዓት ለይ ከምድባቸው የተሰናበቱት ደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
ምድብ ሁለት ላይ የሚገኙት ሀገራት በዴሬዳዋ ስታዲየም የሚጫወቱ ሲሆን በ6 ነጥብ 2ኛ ላይ ያላችው ዩጋንዳ ከጂቡቲ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ትጫወታለች፡፡ 10 ሰዓት ላይ ደግሞ ሱዳን ከ ቡሩንዲ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ

በሀበሻ ባህር ዓለምአቀፋዊ ውድድር !
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | በዛሬው ነገረ-ሀሳቤ በታሪክ ውስጥ የሀበሻ ባህር ተብሎ ስለሚጠራው እና ቀይ ባህር ላይ ያተኩራል ።በትውልድ ውስጥ ዘላለማዊ አሻራ ማሳረፍ ( Permanent Interest ) ዘላቂ እና ታሪክ የማይረሳው ተግባር ነው፤ ይህ ለእኛ ለእኔ ዘመን ትውልድ ትልቅ እድል ነው።
ቀይ ባህር በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁልፍ ከሆኑ የንግድ እና የስትራቴጂክ የውሃ መስመሮች መካከል አንዱ ሲሆን (ለምሳሌ፡ በስዊዝ ካናል እና በባብ ኤል-ማንደብ በኩል) በመሆኑም የዓለምና የቃጣናው ኃያላን ሀገራት ትኩረት የሚስብ የጂኦፖለቲካል ውድድር ማዕከል ሆኗል።
ይህ ውድድር የንግድ ፍሰትን ከመቆጣጠር እስከ ወታደራዊ መንደሮች ማስፋፋት ድረስ የተዘረጋ ሲሆን፣ እንደ ጂቡቲ ባሉ አካባቢዎች የቻይና፣ የአሜሪካ፣ የፈረንሳይ፣ የጃፓን እና የዐረብ ሀገራት ወታደራዊ መንደሮች መገንባታቸው የውድድሩን መጠን ያሳያል። (ምንጭ፡ The International Politics of the Red Sea እና ሌሎች ጽሑፎች) በዚህ ውስብስብ ዓለምአቀፋዊ ውድድር ውስጥ፣ "ኢትዮጵያ" ቁልፍ ሚና ያላት ሀገር ናት ።
🔴የኢትዮጵያ ሚና፦
ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላት ሚና በበርካታ ምሁራዊ ስራዎች ተንጸባርቋል፤ በተለይም በ"Ethiopia and the Red Sea: The Rise and Decline of the Solomonic Dynasty" በሞርደካይ አቢር (Mordechai Abir) እና በቅርብ ጊዜ በተሰሩ ጥናቶች ላይ። እነዚህ ማጣቀሻዎች የኢትዮጵያን ሚና በሦስት ዋና ዋና ገጽታዎች ይመረምራሉ፦
🔴 ታሪካዊ እና የህልውና ጥያቄ፦
እንደ አቢር እና ሌሎች የታሪክ ተመራማሪዎች ገለጻ፣የኢትዮጵያ ስልጣኔ (ለምሳሌ አክሱም) እና ኢኮኖሚ ከጥንት ጀምሮ ከቀይ ባህር ጋር የተቆራኘ ነው። ኢትዮጵያ እስከ 1993 እ.ኤ.አ. (ኤርትራ ነፃ እስከወጣችበት ጊዜ) ድረስ የባህር በር ነበራት፤ ቀይ ባህርም ቀደም ባሉት ዘመናት "የሀበሻ ባህር" ተብሎ ይጠራ እንደነበር ይታወቃል።(ምንጭ፡ ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል እና ሌሎች)
አሁን ያላት የየብስ የተከበበች ሀገር (Landlocked country) አቋም ከፍተኛ የሆነ የንግድና የሎጂስቲክስ ጥገኝነት (በተለይ በጅቡቲ ወደቦች ላይ) እንዲፈጠር አድርጓል።
መንግስት የቀይ ባህርን መዳረሻ እንደ "የህልውና ጉዳይ" መመልከቱ፣ ይህም ታሪካዊ መብቶችን እና የኢኮኖሚ ደህንነትን ለማረጋገጥ መሆኑን ያመለክታል። (ምንጭ፡-ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የተናገሩት ንግግሮች፣ "Ethiopia's Red Sea Politics" - Biruk Terrefe) መጽሐፍ መመልከት ይቻላል ።
🔴የሎጂስቲክስ እና ኢኮኖሚያዊ ስትራቴጂ:-
የኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደሮች ለሀገር ውስጥ የሚገቡና የሚወጡ ሸቀጦች መተላለፊያ ብቻ ሳይሆኑ፣ የቃጣናው፣የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተዋናዮች የሉዓላዊነት እና የደህንነት ራዕያቸውን የሚደራደሩበት ወሳኝ መድረኮች ናቸው። (ምንጭ፡ "Ethiopia's Red Sea Politics: Corridors, Ports and Security in the Horn of Africa")የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ ወጪ ለመቀነስ እና የንግድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በርካታ አማራጭ የወደብ መዳረሻዎችን መፈለጓ የአገሪቱን ሰፋ ያለ የዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ ያላትን ተዕጽኖ ፈጣሪነትናራዕይ አካል እንደሆነ አሳይታለች ።
🔴የቃጣናዊ ደህንነት፦
ኢትዮጵያ ጥንካሬ እና ድክመት በቀይ ባህር ጂኦፖለቲካ ላይ ታሪካዊ ተጽዕኖ አለው።በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የህዝብ ብዛት እና ኢኮኖሚ ያለን ሀገር እንደመሆናችን፣የውስጥ መረጋጋቷ የቀይ ባህርን ጨምሮ ለቀጣናው ደህንነት ወሳኝ ነው።
ከ"ቀይ ባህር ፎረም"(The Red Sea Forum) መገለል ኢትዮጵያ በቀይ ባህር አዋሳኝ ሀገራት ከተመሰረተው ውጭ መደረጓ ተገቢ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ አስታውቃለች። ይህ ደግሞ በባህር ደህንነት እና ትብብር ዙሪያ በቃጣናዊ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ያላትን ሙሉ ሚና ለመጫወት ያላትን ፍላጎት ያሳያል።የቀይ ባህር መድረክ አባለ ሀገራት ለግንዛቤ (ግብፅ፣ሳውዲ አረቢያ ፣ጆርዳን፣የመን፣ሱዳን ፣ኤርትራ ፣ጅቡቲ እና ሱማሊያ ናቸው)
🖊እንደ መውጫ ⁉️
በቀይ ባህር ዙሪያ ያለው ዓለም አቀፋዊ ውድድር በኃያላን ሀገራት የወታደራዊ መንደር ማስፋፋት እና በቃጣናዊ ሀገራት መካከል ባለው የሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ጥቅም ጥበቃ የተሞላ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የኢትዮጵያ ሚና ከታሪካዊ መብቷ በመነሳት፣ የባህር በር መዳረሻ የማግኘት የህልውና ጥያቄዋን ከማረጋገጥ እንዲሁም ለቃጣናዊ ደህንነትና ልማት አስተዋጽኦ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-https://x.com/HDebasu?t=eR...
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

በግብፅ የተመራው የባህር ሀይል በቀይ ባህር ላይ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርግ ጂቡቲ፣ ሱዳን ጆርዳን እና የመን ተሳትፈዋል።
አላማው በቀይ ባህር ላይ አደጋ የሚያመጣ አካል ከመጣ በጋራ ለመመከት ነው ሲል የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
seledadotio
seledadotio
አላማው በቀይ ባህር ላይ አደጋ የሚያመጣ አካል ከመጣ በጋራ ለመመከት ነው ሲል የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
seledadotio
seledadotio
9 months ago
በቀን 4 ሺሕ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ለአንድ ወር ወረፋ እንደሚጠብቁ ገለጸ
ይህን የሚያስቀር አዲስ የገበያ ድርሻ አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል
ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርት ለማስገባት በቀን ከ4 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ለአንድ ወር ወረፋ እንደሚጠብቁ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኮነን (ዶ/ር) ይህን ችግር የሚያስቀር አሰራር እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በነዳጅ ኩባንያዎች አቅርቦትና ሥርጭት ዙሪያ በተደረገ ጥናት ላይ 'የተመሰረተ የገበያ ድርሻ ቀመርና የአሰራር ሥርዓት' ተግባራዊ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የገበያ ድርሻ አሰራር ሥርዓት መሠረት ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ለየትኛው ማደያ እንደሚጪኑ ፕሮግራም እንደሚወጣና፤ የኩባንያዎችን ፕሮግራም መሠረት በማድረግ 'የነዳጅ አቅራቢያ ድርጅት የጭነት ፕሮግራም' እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡
ወደ ጂቡቲ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች በሚወጣላቸው ፕሮግራም መሠረት እንዲሄዱ መደረጉ፤ አሽከርካሪዎች የሚያወጡትን ወጭ እና እንግልት እንዲሁም ኩባንያዎች የሚያወጡትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር እንደሚሆንም አመላክተዋል።
በተጨማሪም የሚገመት የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር፣ በሁሉም አካባቢዎች እኩል ተደራሽ እንዲሆንና በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን የጤና ችግር የሚቀንስ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት ከጂቡቲ ጀምሮ የነዳጅ ሥርጭቱን ለመከታተል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
ይህም አሰራር የነዳጅ አቅርቦት እንዲሻሻል፣ ለሕብረተሰቡ የሚቀርበው የነዳጅ መጠን ፍትሃዊ እንዲሆን እንዲሁም፤ ለኮንትሮባንድ ተጋላጭ የሆኑ ድንበር አካባቢ የሚገኙ አካባቢዎች ላይ ኮታን መሰረት ያደረገ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።
አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉንም ኩባንያዎች ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አሰራሩ በዚህ ሳምንት ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

አሐዱ

10 months ago
አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ቃለ መኃላ ፈጸሙ
#ethiopia | በጂቡቲ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል ቃለ መኃላ ፈጽመዋል።
አምባሳደሩ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፊት ቀርበው ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።
ፕሬዚዳንት ታየ ለተሿሚ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና የጂቡቲን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችል የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ታድመዋል። #fmc

Comments