የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር የመጓዝ ፍጥነትን በሰዓት ወደ 120 ኪሎ ሜትር ለማሳደግ እየተሠራ ነው
#ethiopia | የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር ፍጥነት እንዲጓዝ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርዖ ሐሰን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ መስመሩ በመጀመሪያ ሲገነባ 120 ኪሎ ሜትር በሰዓት ፍጥነት እንዲኖረው ታስቦ የተሠራ ነበር።
ሆኖም ቀደም ሲል በአካባቢው በነበሩ የጸጥታ ችግሮችና የስርቆት ድርጊቶች ምክንያት የመጓዝ ፍጥነቱ ወደ 40 ኪሎ ሜትር በሰዓት ዝቅ ብሎ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተከናወኑ የተቀናጁ የጥበቃና የክትትል ሥራዎች አሁን ላይ ፍጥነቱን ወደ 60 ኪሎ ሜትር በሰዓት ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በቀጣይም የባቡሩን የመጓዝ ፍጥነት ወደ ታለመለት 120 ኪሎ ሜትር በሰዓት ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።
የባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ሥራውን ከተረከቡ በኋላ የጥገና ወርክሾፖችን በማጠናከርና የቴክኒክ አቅማቸውን በማሳደግ፣ የሚገጥሙ ችግሮችን በፍጥነት የመፍታት አቅም መፈጠሩም ለፍጥነቱ መጨመርና ለሥራው ቅልጥፍና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተገልጿል ሲል ጋዜጣ ፕላስ ዘግቧል።

7 months ago