Logo
SeledaPost
ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሀይል ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ‼️

ባለፉት አራት ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሀይል ከ46 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ተቋሙ በሀገር ውስጥ ላሉ ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች፣ ለኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር እና በማይኒንግ ዘርፍ ተሰማርተው ክፍያን በዶላር ለሚፈፅሙ አካላት እያቀረበ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ለውጭ ኤሌክትሪክ ሃይል ፈላጊ ሀገራት የሚያቀርብ ሲሆን በዋነኝነት ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ታንዛንያ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ በ2018 በጀት አመት ባለፉት አራት ወራት ለኬንያ፣ ጁቡቲ እና ታንዛንያ በሽያጭ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 46 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.