የጉዞ ማስታወሻ
ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል
(ክፍል ሁለት - የድሬዳዋ አቀባበል)
#ethiopia | የሌሊቱን ጉዞ በግርማ ሞገስ ሲያደርግ ያደረው የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር ቁጥር 202፣ የምሥራቋን ፈርጥ ድሬዳዋን ከተማ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 ሲሆን ደረሰ።
ድሬዳዋን "የበረሃዋ ንግሥት" ይሏታል። ዛሬ ግን ከንግሥትነቷ በላይ "የፍቅር ከተማ" መሆኗን በተግባር አሳይታናለች። ባቡሩ ቆሞ እግራችንን መሬት ሲረግጥ የጠበቀን አቀባበል ከመንፈሳዊ ጉዞ በላይ የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ማሳያ ነበር።
ከባቡር ጣቢያው ጀምሮ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተዘጋጁት በርካታ መርሃ-ግብሮች እጅግ ደማቅ ነበሩ።
የከተማዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ስፍራዎች ተገኝተው፣ እንግዶችን ያለ እረፍት ሲያስተናግዱና ሲቀበሉ መዋላቸው የድሬዳዋን እንግዳ ተቀባይነት ሌላ ከፍታ ላይ ሰቅሎታል። ይህ ተግባር የሃይማኖት ልዩነት ሳይገታን፣ በፍቅርና በሰላም አብሮ የመኖር ትልቅ ተምሳሌት ነው።
ከሰዓት በኋላ ጉዟችን የድሬዳዋን ሙቀት ትቶ ወደ ቀዝቃዛማውና ተራራማው የሐረርጌ ምድር አቀና።
አረንጓዴ የለበሱት የሐረርጌ ተራሮችና በየመንገዱ ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የሚጓዙ በእግሩ የሚጓዘው ወጣት፣ አዛውንትና ህጻናት ማየት ጉልበት ይሆነናል። አሁን አቅጣጫችን በመንፈሳዊ ዝማሬ ታጅበን ወደ ደብረ ኃይል ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሆነ።
ይቀጥላል...
(ጌትነት ተመስገን)
የጉዞ አጋራችን
🙏 የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር
🙏 የዮዳሄ ሀገር አቀፍ መንፈሳዊ የጉዞ ማህበርን ከልብ እናመሠግናለን።

6 months ago