Logo
Getu Temesgen
ምድቡን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ከ ኬንያ ይጫወታሉ
#ethiopia | በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ውድድር የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ደርሷል፡፡ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ እየተደረገ በሚገኘው መድረክ ዛሬ የሁለቱም ምድብ የመጨረሻ ጨዋታች ይደረጋሉ፡፡

ምድብ አንድ ላይ የሚገኝው የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን አሸንፎ በአንዱ ደግሞ ነጥብ ተጋርቶ ከምድቡ ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በዚሁ ምድብ የምትገኝው ኬንያም በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡

ሁለቱ ቡድኖች አንድ ጨዋታ እየቀራቸው ማለፋቸውን ቢያረጋግጡም ምድቡን በበላይነት ለማጠናቀቅ 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡

ሁለቱ ወጣት ቡድኖች እኩል ነጥብ መያዛቸው ጨዋታውን እንዲጠበቅ የሚደርገው ሲሆን አሸናፊው በቀጥታ ምድቡን በአንድኝነት ያጠናቅቃል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ዛሬ ጨዋታውን ከማድረጉ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ትላንት በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም አከናውኗል፡፡በዚሁ ምድብ 7 ሰዓት ለይ ከምድባቸው የተሰናበቱት ደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

ምድብ ሁለት ላይ የሚገኙት ሀገራት በዴሬዳዋ ስታዲየም የሚጫወቱ ሲሆን በ6 ነጥብ 2ኛ ላይ ያላችው ዩጋንዳ ከጂቡቲ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ትጫወታለች፡፡ 10 ሰዓት ላይ ደግሞ ሱዳን ከ ቡሩንዲ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.