1 day ago
ዛሬ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተካሔደው መርሐ-ግብር በተጨማሪ፣ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች “ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ አከናውነናል!
የአረንጓዴ ኦፕሬተርነት ጉዟችንን በማጠናከር በዛሬው ዕለት ብቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ 250 ሺህ ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን፣ በዚህም አረንጓዴ አሻራችንን በመላ ሀገሪቱ አሳርፈናል።
በክልሎች የምትገኙ የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ አጋሮቻችን እና የመትከያ ቦታ በማመቻቸት አብራችሁን ለሠራችሁ አካላት በሙሉ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን!
ለበለጠ፡ https://bit.ly/4xhlXxF
#አረንጓዴኢትዮጵያ #greenethiopia
#ethiotelecom #telebirr #zemengebeya #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

የጤናው ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ
📌 ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው እለት ተተክለዋል
#ethiopia | በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች ከኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ከገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በዛሬ እለት በገፈርሳ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ዳርቻ ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው እለት ተተክለዋል።
በሸገር ከተማ በገፈርሳ ጉጄ አካባቢ በተካሄደው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የየደረጃው የአካባቢው አመራሮች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና የማህበረሰብ ክፍሎች ከማለዳው 1 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት ችግኝ ተክለዋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ አረንጓዴ አሻራ እና የጤና ዘርፍ የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ችግኝ ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰብ ጤና፣ ለንጹህ አየር እና ለምግብ ዋስትና ማሻሻያ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በተለይም ለአዲስ አበባ እና ለአካባቢው ህዝብ የንጹህ ውሃ ምንጭ የሆነውን የገፈርሳ አካባቢን መንከባከብ የሁላችንም ህብረ-ብሄራዊ ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በዕለቱ በቦታው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አካባቢዋን ለመጠበቅ የምታደርገው ጥረት በንግግር ሳይሆን በተግባር የሚገለጽ መሆኑን አብራርተዋል።
በዕለቱ ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ከ30 ሺህ በላይ ችግኞችን የተከለ ሲሆን፣ በክረምቱ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 250 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እና ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯ፣ የጤና ባለሙያዎች እና መላው የሀገራችን ህዝብ ቀኑ ሳያልቅ እና ጀምበር ሳትጠልቅ የድርሻቸውን ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ኩነት አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ከችግኝ ተከላው መርሐግብር ባሻገር የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት በሸገር ከተማ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
በጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ministryofhealth #treeplanting
#climateaction #publichealth
#environmentalhealth #gefersa #cleanenvironment #greenethiopia
#communitysupport

2 days ago
"ዛሬ ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው፤ 800 ሚሊዮን ተስፋዎችን አብረን እንትከል"
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #climateaction #greenlegacy #አረንጓዴአሻራ #greenethiopia #ebc

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለነገው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ የተደረገ ቅድመ ዝግጅት (በምሥል)
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #southwestethiopiaregion #greenethiopia #ebc
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #southwestethiopiaregion #greenethiopia #ebc
2 days ago
በነገው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት ለመሳተፍ ተዘጋጅተናል - የኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች
*****************
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል በነገው ዕለት በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን የኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
የዞኑ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በተከሏቸው ችግኞች በየአካባቢያቸው የተራቆቱ ስፍራዎች መልሰው አገግመዋል።
የአካባቢ ጥበቃ ሥራው ሥነ ምሕዳር እንዲያገግም፣ የአፈር ለምነት እንዲሻሻል እንዲሁም ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አስችሏል።
የተከሏቸውን ፍራፍሬ ለምግብነት በማዋል እና ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውንም ነዋሪዎቹ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በዞን ደረጃ የነገውን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ ተገልጿል።
አስቀድሞ በተለዩ 299 የችግኝ ተከላ ሳይቶች የጉድጓድ ቁፋሮ ተከናውኖ የሚተከሉ ችግኞችም ወደየስፍራው ተጓጉዘዋል ነው የተባለው።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #iluabbaborzone #greenethiopia #ebc

በምስራቅ ሸዋ ዞን ለነገው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዝግጅት ተጠናቅቋል
#ethiopia #climateaction #greenlegacy #eastshoazone #greenethiopia #ebc

6 days ago
አረንጓዴ ዐሻራ፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ አዲስ የኅብረት እና የጋራ ዓላማ ባህልን የፈጠረ መርሐ-ግብር
**********************************
ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የጀመረችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዛሬ ላይ የኢትዮጵያን ገጽታ ከመስዋብ አልፎ የምግብ ዋስትና እና የዲፕሎማሲ አቅም የለወጠ ታላቅ ሀገራዊ እና አህጉራዊ ንቅናቄ ሆኖ ታይቷል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ላይ ያሳየችውን ተግባራዊ ምላሽ እና ያስመዘገበችውን ዘላቂ ፍሬ በጥልቀት የሚያስረዱ ናቸው።
ከሥነ ምህዳር እና ተፈጥሮ ጥበቃ አንጻር ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ከ48 ቢሊዮኖች በላይ ችግኞችን በመትከል ምድርን ለማከም ተችሏል። ይህም የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በማስወጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ የደን ሽፋኗ እንዲያገግም አስችላል።
በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ዘመቻ የአፈር መሸርሸርን ከመቀነስ፣ የከርሰ ምድር ውኃን ከማጎልበት እና የተጎዱ የሥነ ምህዳር ክፍሎችን መልሶ ከመገንባት አንጻር እጅግ የጎላ ሚና ተጫውቷል።
ቀደም ሲል በድርቅ እና በአፈር መሸርሸር የተጠቁ አካባቢዎች ዛሬ ላይ አረንጓዴ ለብሰው በማገገም ይገኛሉ።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከተራ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለፈ ወደ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ምንጭነት ተሸጋግሯል። በተለይም ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጣቸው የተቀናጁ የፍራፍሬ (አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን) እና የቡና ችግኞች ተከላ ዐበይት ውጤቶችን እያስገኙ ይገኛሉ።
ይህም ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ አባወራዎች አዲስ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም በላይ በሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለውጭ ገበያ የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማጠናከር ትልቅ መሠረት ጥሏል።
መርሐ-ግብሩ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አዲስ የኅብረት እና የጋራ ዓላማ ባህልን ፈጥሯል።
እድሜ፣ ጾታ፣ የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት ሳይበግረው በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሚሊዮኖች ዜጎች በአንድ ጀምበር ወጥተው ችግኝ የመትከል ልምድን ማዳበራቸው ሀገራዊ አንድነትን እና የመረዳዳት መንፈስን አጠናክሮታል።
ይህም ኢትዮጵያውያን በትብብር ከተነሱ የማይሻገሩት ፈተና እንደሌለ በተግባር ያሳዩበት ታላቅ ማኅበራዊ ሀብት ሆኗል።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ የሀገር ወሰንን ተሻግሮ ለአጎራባች ሀገራት ችግኞችን በማካፈል የቀጣናዊ ትስስር እና የ አረንጓዴ ዲፕሎማሲ ማሳያ መሆን ችሏል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመመከት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የፖለቲካ መሪዎች በሚታገሉበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ይህ ንቅናቄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሙገሳ እና ዕውቅና እንድታገኝ አድርጓታል።
ባለፉት 7 ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በምግብ እራስን መቻል፣ በሕዝባዊ አንድነት እና በዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ያስመዘገበችው ድል ነው።
ኢትዮጵያውያን ይህን የተተከለውን ተስፋ ጠብቀው በማሳደግ እና ወደ ተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ፣ የተረጋጋች እና የበለፀገች ሀገርን ለማስረከብ ተሰናድተዋል።
በሃና ምንዳሁን
#ebc #ethiopia #ebcdotstream #greenlegacy #greenethiopia #climateaction #ethiopiarising

1 month ago
ከምድር ጥበቃ ወደ ማዕድ በረከት፤ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ያሳደገው የአረንጓዴ ዐሻራ ታሪካዊ ስኬት
************
ዛሬ ዓለማችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የመጣውን የሙቀት መጨመር፣ የሰደድ እሳት፣ የጎርፍ እንዲሁም የድርቅ አደጋዎችን ለመቋቋም በብርቱ ትግል ውስጥ ትገኛለች።
አፍሪካ ለዓለም የሙቀት መጨመር ያበረከተችው አስተዋጽኦ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ የችግሩ ቀዳሚ ተጠቂ መሆኗ አልቀረም።
ኢትዮጵያ ይህንን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቀነስ ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተስፋን ማለምና ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በተግባር እያሳየች ትገኛለች።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው "የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር" በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ ስኬት ብቻ መሆኑ አብቅቶ፣ ለመላው የአፍሪካ አህጉር ብሩህ የተስፋ ስንቅና ታላቅ የተሞክሮ ምንጭ ለመሆን በቅቷል።
መርሐ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በመላው ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፤ ይህም የሀገራችንን የደን ሽፋን በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 17.2 በመቶ በአሁኑ ወቅት ወደ 23.6 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል።
በዘንድሮው የችግኝ ተከላ ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያ ያስቀመጠችውን የ65 ቢሊዮን ታሪካዊ ግብ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ዝግጁ ተደርገዋል።
ይህ ዓይነቱ መጠነ-ሰፊ ንቅናቄ የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ፣ የሕዝቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
መርሐ ግብሩ የተራቆቱ መሬቶች እንዲያገግሙ ከማድረጉ ባሻገር፣ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና አፕል ያሉ ለምግብነትና ለገበያ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት አካትቷል።
ይህም የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ “ከምድር ጥበቃ ወደ ማዕድ በረከት” የተሻገረ ስትራቴጂ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ሲያስጀምሩ የነበራቸው ራዕይ በሀገር ውስጥ ብቻ የተገደበ አልነበረም።
የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር የለሽ በመሆኑ፣ መከላከል የሚቻለውም በጋራና በትብብር ሲሰራ ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ የቀጣናውን በረሃማነት በጋራ ለመግታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ለጎረቤት ሀገራት ማለትም ለጂቡቲ፣ ለደቡብ ሱዳንና ለኬንያ አበርክታለች።
ይህ ተግባር የፓን-አፍሪካኒዝም እሴትን በተግባር ያሳየ፣ ለመላው አፍሪካውያን አንድነትና አብሮነት አዲስ ትርጉም የሰጠ አርዓያነት ያለው ስኬት ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅም፣ በጋራና በትብብር መፍታት እንደሚችሉ ያሳዩበት ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ኢትዮጵያ ያበሰረችው የአረንጓዴ ተስፋ ብርሃን አህጉሪቱን ከተጋረጠባት የበረሃማነትና የአየር ንብረት መዛባት አደጋ ታድጎ፣ የነገዋን አፍሪካ ውብና ለምለም ለማድረግ የበኩሉን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ
#greenlegacy #climateaction #greenethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation

Sponsored by
Surafel
Comments