Logo
Getu Temesgen
🚂 የጉዞ ማስታወሻ
ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል - በባቡር
(ክፍል አንድ)
#ethiopia | ታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም፤ ለቡ የሚገኘው የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ጣቢያ እንደወትሮው ሳይሆን ለየት ባለ ድምቀት አሸብርቋል።

ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የሚጓዙ ምዕመናን የመሳፈሪያ ሰዓት እስኪደርስ ድረስ በታላቁ አዳራሽ ተሰባስበዋል። የአዳራሹ ድባብ በመንፈሳዊ ትምህርት እና ዝማሬ ተሰጥቷል።

ከምሽቱ 12:30 ሲሆን፣ ወደ ድሬዳዋ የሚጓዘው ባቡር መስመር ቁጥር 202 ከቦታው ቆመ። ከ2600 በላይ የሚሆኑ ተሳፋሪዎች በሁለት ረጅም ሰልፎች ተከፍለው፣ የፍተሻ መስመር ካለፉ በኋላ ወደ ባብር ሰረገላዎቹ መግባት ጀመሩ። የባቡሩ ግዙፍነትና ዘመናዊነት ለጉዞው ልዩ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል።

ባቡሩ በዝግታ በተዘጋጀለት የጉዞ መስመር ከምሽቱ 2:40 መንቀሳቀስ ሲጀምር፣ የአዲስ አበባ የምሽት መብራቶች በመስኮት በኩል እየራቁ መሄድ ጀመሩ። ይህ ጉዞ የዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የባቡር ታሪክና የከተሞችን እድገት ወደኋላ የሚያስታውስ ትልቅ ክስተት ነው።

የኢትዮጵያ የባቡር ታሪክ ሲነሳ የአፄ ምኒልክ የፈጠራና የሥልጣኔ ጥማት አብሮ ይነሳል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ኢትዮጵያን ከውጭው ዓለም ጋር ለማገናኘት የታለመው ይህ ፕሮጀክት፣ በ1886 ዓ.ም በአፄ ምኒልክ ፈቃድና በአልፍሬድ ኢልግ አማካኝነት የግንባታው ስምምነት ተፈረመ።

ግንባታው ከጅቡቲ ተነስቶ አዲስ አበባ ለመድረስ ረጅም ዓመታት የፈጀ ሲሆን፣ ከፍተኛ ገንዘብና የሰው ኃይል በወቅቱ የጠየቀ ነበር። ታዲያ ንጉሱ ይህን ኘሮጀክት ሳያጠናቀቅ ህይወታቸው ቢያልፍም በ1910 በልጃቸው ንግሥተ ነገስታት ዘውዲቱ አማካኝነት ተጠናቆ ተመርቋል።

የኢትዮጵያ ምድር ባብር መስመሩ መዘርጋት ለኢትዮጵያ ከተሞች ምስረታና እድገት ከሚጠቀሱ ዋነኛው መንስዔ መካከል አንዱ ነው።

በወቅቱ የባቡሩ ሐዲድ ያረፈባቸው ጣቢያዎች ሁሉ ዛሬ የምናያቸው ታላላቅ ከተሞች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል።

ከነዚህ መካከል አንዷ ድሬዳዋ ነዋ ከተማ ናት ድሬ የባቡር መስመሩ ከአዲስ አበባ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ለረጅም ጊዜ መናኸሪያ ሆና በማገልገሏ፣ ድሬዳዋ በባቡር ምክንያት የተቆረቆረችና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን የበቃች ከተማ ናት።

ሌላኛዋ ከተማ የቀድሞ ናዝሬት የዛሬዋ አዳማ የባቡሩ የንግድ ዕቃዎችን የሚያራግፍበትና የሚጭንበት በመሆኑ፣ አዳማ ከትንሽ መንደርነት ተነስታ የንግድ ማዕከል ከተማ ሆናለች።

ቢሾፍቱ ፣ መተሃራ እና ሞጆ የባቡር ጣቢያዎችን ተከትለው የለሙና የንግድ እንቅስቃሴ የደራባቸው አካባቢዎች ናቸው።

ባቡሩ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ባህልን፣ ቴክኖሎጂንና ዘመናዊነትን ከቦታ ቦታ በማጓጓዝ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ቀይሮታል።

አሁን ባቡር መስመር 202 ጨለማውን እየቀደደ ወደ ምሥራቅ እየገሰገሰ ነው።

ይቀጥላል ....

የጉዞ አጋራችን የኢትዮ - ጁቡቲ ባብር ከልብ እናመሠግናለን 🙏

(ጌትነት ተመስገን )

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.