Logo
SeledaPost
የአየር ሀይል ጥንካሬ‼️
በ2026 ግሎባል ፋየር ፓወር የአገራት የአየር ሀይል አቅምን ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ 104 ጠቅላላ የአየር ሀይል ብዛት በመያዝ ከአለም ሀገራት 70ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከአፍሪካ ሀገራት ደግሞ በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ግብፅ(1088)፣አልጀሪያ (620)፣አንጎላ(278)፣ሞሮኮ(271) እና ሱዳን (183) አየር ሀይል በመያዝ ከአንድ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ወታደራዊ አቅም ደረጃ ዝርዝር ውስጥ ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት 38ቱ ብቻ የተካተቱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችው ጂቡቲ ካልተካተቱት ውስጥ ናት።
በአጠቃላይ ወታደራዊ አቅም ሲታይ ከአፍሪካ ከአንድ እስከ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ግብፅ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ናቸው።
የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤርትራ በ 20 ወታደራዊ አየር ሃይል ከአለም 118ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

seledadotio
seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.