ጅቡቲ ውስጥ ህጻናት በፍንዳታ ተገደሉ
ደቡባዊ ጂቡቲ ውስጥ አራት ህጻናት በፍንዳታ ተገድለዋል ሲሉ ባለሥልጣናት አስታወቁ። አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ግን ህጻናቱ የተገደሉት በድሮን ጥቃት ነው ማለቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የጅቡቲ አቃቤ ሕግ ሀሰን መሐመድ ሀሰን ትናንት ማምሻውን ባወጡት መግለጫ ህጻናቱ አፋር ድሂኪል በተባለው ክልል ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ መገደላቸውን አስታውቀዋል።
የጅቡቲ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ የተባለው ድርጅት በምህጻሩ LDDH ደግሞ አንዲት የስድስት ዓመት እና አንድ የሰባት ዓመት ህጻናት ወዲያውኑ ሲሞቱ በአደጋው የቆሰሉ ሌሎች ሁለት ህጻናት ደግሞ የሕክምና እርዳታ ባለማግኘታቸው ማክሰኞ መሞታቸውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሌሎች 6 ህጻናትም መቁሰላቸውንና ከመካከላቸው አንዱ ከባድ ጉዳት እንደረሰበትም ገልጿል። ድርጅቱ እንዳለው ህጻናቱ የተገደሉት ከብቶች በመጠበቅ ላይ ሳሉ ነበር።
ህጻናቱ በድሮን ጥቃት ነው የተገደሉት የሚለው ድርጅቱ የአሁኑ ጥቃትም በአካባቢው ለስድስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው ብሏል። አቃቤ ሕግ ሀሰን የፍንዳታውን መንስኤ የሚያጣራ አንድ ቡድን በስፍራው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
DW Amharic

3 months ago