እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠት እና የቀይ ባሕር ቀጠና አዲሱ የጂኦፖለቲካዊ ለውጥ
ከመሀመድ ካህላፍ ፅሁፍ የተወሰደ
ሶማሊላንድ ማን ናት?
ሶማሊላንድ በሰሜናዊ ሶማሊያ፣ በኤደን ባህረ ሰላጤ ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ቀጠና ነው። በምስራቅ ከፑንትላንድ፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በምዕራብ ከጂቡቲ ጋር ይካለላል። ቀጠናው እ.ኤ.አ. በ1991 የማዕከላዊ ሶማሊያ መንግስት መፈራረስን ተከትሎ፣ ነጠላ የነጻነት አዋጅ አውጇል። ይህ ውሳኔ የተመሰረተው እስከ 1960 ድረስ የእንግሊዝ ጥበቃ የሚደረግለት ራሱን የቻለ ግዛት እንደነበረና በኋላም ከጣሊያን ሶማሊላንድ ጋር በመቀላቀል የሶማሊያ ሪፐብሊክን መመስረቱን ታሪክ በማጣቀስ ነው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቀጠናው ከቀሪው የሶማሊያ ክፍል ጋር ሲነጻጸር በአንጻራዊ ሁኔታ ውጤታማ የሆኑ የራስ-አስተዳደር ተቋማትን መገንባት ችሏል። እነዚህም የሚመረጥ መንግስት፣ ፓርላማ፣ የጸጥታ አገልግሎት፣ የሀገር ውስጥ ገንዘብ እና የተረጋጋ የአስተዳደር ስርዓትን ያካትታሉ።
ይህም በምዕራባውያን ጽሑፎች ውስጥ ግጭት በበዛበት አካባቢ እንደ "የመረጋጋት ደሴት" ተደርጎ እንዲገለጽ አድርጎታል። ሆኖም ግን፣ እስካሁን ድረስ ይፋዊ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላገኘ ሲሆን፣ በህግ ደረጃም የሶማሊያ ሪፐብሊክ አካል ሆኖ ይቆጠራል።
የእስራኤል እውቅና መስጠት
ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን የዲፕሎማሲ ግንብ የሰበረ ታሪካዊ እርምጃ በመውሰድ፣ እስራኤል ሶማሊላንድን ዋና ከተማዋ ሃርጌሳ የሆነ ሉዓላዊ እና ገለልተኛ ሀገር አድርጋ በይፋ ማወቋን አስታውቃለች።
እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ያሳለፈች የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገር ሆናለች።
ይህ ለውጥ ሊመጣ የቻለው በኅዳር 2024 በሶማሊላንድ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ የሥልጣን መዋቅሩ በመቀየሩና እስካሁን ከነበረው የተለየ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን መንገድ በመከፈቱ ነው። በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው የዋታኒ ፓርቲ መሪ የሆኑትና በሶማሊያ የዲፕሎማሲ መስክ ልምድ ያላቸው የተቃዋሚው ዕጩ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (በቅጽል ስማቸው "አይሮ") ማሸነፋቸው ለዚህ ምክንያት ሆኗል።
እንደ እስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ መስኮች ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት በፍጥነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
ከዚህም በተጨማሪ በኤደን ባህረ ሰላጤ እና በባብ አል-መንደብ ሰርጥ አቅራቢያ ካለው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ጋር የተያያዙ ያልተገለጹ የደኅንነት ትብብሮችንም ታደርጋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለዚህ "የዲፕሎማሲ ስኬት" አስተዋጽኦ ላደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩና ለሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ ምስጋና አቅርበዋል።
የዓረብ እና የቱርክ ቁጣ - የግዳጅ ጥምረት
ለዚህ ውሳኔ ከቀጠናው የተሰጠው ምላሽ ፈጣንና ጠንካራ ነበር። ግብፅ፣ ሶማሊያ፣ ቱርክ እና ጅቡቲ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ የእስራኤልን ውሳኔ አውግዘዋል። የሶማሊያን አንድነትና ሉዓላዊነት የሚጥስ ማንኛውንም እርምጃ እንደሚቃወሙና ለሶማሊያ ሕጋዊ ተቋማት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ ይህ የእስራኤል እውቅና ግብፅና ቱርክን "የግዳጅ ጥምረት" ውስጥ በመክተት በሞቃዲሾ የሚገኘውን የፌዴራል መንግሥት በወታደራዊ ኃይል እንዲደግፉ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህ ደግሞ በተለይ በሶማሊላንድና በፑንትላንድ መካከል በሚገኘው "ሱል" ግዛት ላይ ቀጠናዊ ኃይሎችን ወደ ውክልና ጦርነት ሊያስገባ ይችላል ተብሎ ይፈራል።
የምስጢራዊ ጉብኝት ውጤት
በዚህ ወር የተሰጠው እውቅና በድንገት የመጣ ሳይሆን፣ በከፍተኛ የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ሥራዎች የታጀበ ነበር። ፕሬዝዳንት አይሮ ጥቅምት ላይ ወደ እስራኤል ምስጢራዊ ጉብኝት በማድረግ ከሞሳድና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። ይህ ጉብኝት "እውቅና በስትራቴጂካዊ ቦታ" በሚል ቀመር የደኅንነትና የፖሊሲ መሠረቶችን ጥሏል።
ለኔታንያሁ ይህ ስምምነት ዲፕሎማሲያዊ ድል ሲሆን፣ ይህም በዋሽንግተን ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት ስብሰባ እንደ ትልቅ ስኬት ይዘውት ያቀረቡት ጉዳይ ነው።
ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማዛወር ዕቅድ
የእስራኤል ውሳኔ ከወራት በፊት እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ወደ የአፍሪካ ቀንድ (ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድን ጨምሮ) ለማዛወርና ለማስፈር እያሰበች ነው ከሚለው ዘገባ ጋር ተያይዟል። እስራኤል ለሶማሊላንድ ለሰጠችው እውቅና እና የገንዘብ ድጋፍ በምትኩ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ፍልስጤማውያን ሶማሊላንድእንድትቀበል ለማድረግ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አባስም ይህንን የእውቅና እርምጃ ፍልስጤማውያንን ለማፈናቀል የሚደረግ የቴል አቪቭ ተስፋ የቆረጠ ሙከራ አካል ነው በማለት ተቃውመዋል።
የሦስቱ ዋና ዋና ተግባራት መድረክ
ከሁሉም በላይ ሶማሊላንድ ለእስራኤል በርካታ መልክዓ ምድራዊ ጥቅሞችን ትሰጣለች። የ850 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ ያላት ሶማሊላንድ፣ የባብ አል-መንደብ መግቢያን ለመቆጣጠር ትረዳለች። የእስራኤል ብሔራዊ የደኅንነት ጥናት ተቋም (INSS) እንደሚለው፣ ይህ አካባቢ ለእስራኤል ሦስት ዋና ዋና ጥቅሞችን ይሰጣል፦
ከየመን የሚተኮሱ ሚሳይሎችንና ድሮኖችን ለመከታተልና የራዳር መሣሪያዎችን መትከል።
በጠላት ዒላማዎች (በተለይም በሁቲዎች) ላይ ለሚደረጉ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች እንደ መነሻ መጠቀም።
ቀይ ባሕር "የኢራን ሐይቅ" እንዳይሆንና ለሁቲዎች የሚደርሰውን የባሕር ላይ የአቅርቦት መስመር መቁረጥ።
ወታደራዊ ካምፕ... በርበራ ወይስ ዘይላ?
አንዳንድ ዲፕሊማቶች እንደሚሉት ይህ እውቅና ከእስራኤል ውጭ ትልቁን ወታደራዊ ካምፕ ለመመሥረት የሚደረግ የፖለቲካ ዝግጅት ነው። ምርጫው በሁለት ቦታዎች መካከል ነው፦
የበርበራ ወደብ፦ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የፈሰሰበት፣ ዘመናዊ መሠረተ ልማትና ወታደራዊ አየር ማረፊያ ያለው፣ እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው አውራ ጎዳና መነሻ በመሆኑ የተመረጠ ነው።
የዘይላ ከተማ፦ ከጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝና ለባብ አል-መንደብ በጣም ቅርብ የሆነች ታሪካዊ ቦታ ናት። ይህም ለየመንና ለኤርትራ ቅርብ በመሆኑ ለኤሌክትሮኒክስ የስለላ ሥራዎች ተመራጭ ያደርጋታል።
የኢኮኖሚ ማበረታቻዎች እና የኢትዮጵያ ሚና
እስራኤል በ "በርበራ ኮሪደር" አማካኝነት ኢኮኖሚዋን ከአፍሪካ ገበያ ጋር ለማገናኘት ትፈልጋለች። ይህ ኮሪደር ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ ሲሆን፣ እስራኤል በጅቡቲ ላይ ብቻ ከመደገፍ እንድትወጣና የቴክኖሎጂ ምርቶቿን ወደ ሰፊው የኢትዮጵያ ገበያ እንዲሁም ወደ ኬንያና ኡጋንዳ እንድታደርስ ይረዳታል።
የቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምላሾች
ሶማሊያ፦ እርምጃውን "የሉዓላዊነት ጥሰት" በማለት አውግዛለች። ከግብፅ ጋር የፈረመችውን የጋራ መከላከያ ስምምነት ወደ መተግበር ተሸጋግራለች።
ግብፅ፦ በእስራኤልና በኢትዮጵያ መካከል የሚፈጠር ጥምረት ከደቡብ በኩል ይከበኛል የሚል ስጋት አላት። ይህም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ የኢትዮጵያን አቋም ሊያጠናክር ይችላል ብላ ታምናለች።
የአፍሪካ ሕብረት፦ የቅኝ ግዛት ድንበሮች መከበር አለባቸው የሚለውን መርህ በመጥቀስ እውቅናውን ውድቅ አድርጓል። ይህም በሌሎች ሀገራት (እንደ ናይጄሪያና ካሜሩን) የመገንጠል እንቅስቃሴን ሊያነሳሳ ይችላል የሚል ስጋት አለው።

7 months ago