7 days ago
ባሕር ዳር ❤️
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል።
በህዝብና ደጋፊው ፊት ከዓመታት በኋላ ጨዋታውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድናችን ጥሩ እና አበረታች እንቅስቃሴ ቢያደርም የተገኙ እድሎችን ወደ ውጤት መቀየር ሳይችል ቀርቷል።
የባሕር ዳር ከተማ ህዝብ ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ከጨዋታው መጀመር አንስቶ ያሳየው ድጋፍ የሚደንቅ ነበር።
የባሕር ዳር ስታዲየም ጥራትም በበርካቶች አድናቆት አግኝቷል።
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ባሕርዳር❤️ በባሕር ዳር ያለው አሁናዊ ድባብ ምን ይመስላል ? የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ከቀኑ 10:00 በባህርዳር ስታዲየም ይካሄዳል። በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ የባህር ዳር ስፖርት ወዳድ ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ በስታዲየም አቅራቢያ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ። ደጋፊዎች በተዘጋጁ የትኬት መቁረጫ ቦታዎች ላይ ትኬቶችን ሲገዙ ተመልክተናል። የከተማው ነዋሪዎች በሀገራዊ…

#ባሕርዳር❤️
በባሕር ዳር ያለው አሁናዊ ድባብ ምን ይመስላል ?
የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ከቀኑ 10:00 በባህርዳር ስታዲየም ይካሄዳል።
በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ የባህር ዳር ስፖርት ወዳድ ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ በስታዲየም አቅራቢያ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ።
ደጋፊዎች በተዘጋጁ የትኬት መቁረጫ ቦታዎች ላይ ትኬቶችን ሲገዙ ተመልክተናል።
የከተማው ነዋሪዎች በሀገራዊ ቀለሞች አሸብርቀው ጨዋታው የሚጀምርበትን ሰዓት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ስፖርት
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም
Via @tikvahethsport Video

1 month ago
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ የማኅበረሰባችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መልሰናል - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
************************
የአማራ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ መድረኩን በንግግር ባስጀመሩበት ወቅት፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ያለውን እምቅ አቅም ታሳቢ ያደረገ ዘላቂ የልማት ዕቅድ በማቀድ በተደረገው የተቀናጀ ርብርብ ውጤታማ አፈፃፀም መመዝገቡን ተናግረዋል።
በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፎች በተሠራው ዘርፈ ብዙ ሥራም የማኅበረሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ በክልሉ የህግ የበላይነት ከማረጋገጥ ባሻገር የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለሳቸውንም አመላክተዋል።
በተያዘው 2019 በጀት ዓመትም በክልሉ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት በማፅናት የህግ የበላይነትን የበለጠ በማረጋገጥ እና ከውስጥና ከውጭ የሚታዩ የፅንፈኝነት ዝንባሌዎችንና አዝማሚያዎችን በማክሰም እንደ ሀገር የጋራ ትርክቶችን በመገንባት ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ አረጋ አረጋግጠዋል።
አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ውስጣዊ ድክመቶቻችንን በማረምና ውጫዊ ተግዳሮቶችን በመታገል የማኅበረሰባችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አሁንም መመለስ ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራ አሳስበዋል።
በተስፋሁን ደስታ
#ethiopia #ebc #amahararegion #budgetyearperformance

2 months ago
ባህርዳር ስታዲየም‼️
ባሕርዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የካፍ መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቀደለት።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂድ ተፈቅዶለታል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያደርግ አግዶት ቆይቷል።
በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት እንዲጫወት ተገድዶ ቆይቷል።
ካፍ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሟላት የሚገባውን መስፈርት እንዲያሟላ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።
ባለፉት ዓመታት ስታዲዬሙ የካፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ ግንባታ ሲካሄድለት ቆይቷል። አሁን ላይ መስፈርቶችን በማሟላት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።
Seledadotio

u1273u122au12ad u12a8u1270u1348u1325u122e u12cdu1260u1275 u12ebu12f0u120fu1275 u1263u1215u122du12f3u122d
#bahirdar #pmabiyahmed #amhararegion ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ታሪክ ከተፈጥሮ ውበት ያደሏት ባሕርዳር
#bahirdar #pmabiyahmed #amhararegion
3 months ago
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን የብልጽግና ጉዞ ጀምራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለመላው አፍሪካ ትልቅ ምሳሌ የሚሆን የብልጽግና ጉዞ ጀምራለች አሉ።
በገበታ ለትውልድ መርሐ ግብር የተገነባው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት በዛሬው ዕለት ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሐምሌና በነሐሴ ወራት የሚከሰተውን የክረምት ቁር ለመሸሽ ምቹ የሆነችው አርባምንጭ ጎብኝዎችን በሁለት እጆቿ ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ ሆናለች ብለዋል።
ከተማዋ በሪዞርቶቿና በተፈጥሮ ውበቶቿ ብቻ ሳይሆን በባህላዊ ምግቦቿ እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀቷን ተናግረዋል።
ሰዎች ወደ ከተማዋ የሚመጡት ለመዝናናት ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው ፥ በዚሁ አጋጣሚ እኛ ተጨማሪ የሀብት ልማት እንዲፈጠር ማድረግ ይገባናል ነው ያሉት።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው እያስመዘገበችው ያለውን አህጉራዊ አርአያነት ተመልክተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ለመኖር ማሰብ የሚጀምሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ ታሪካዊ ተግባር እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ፊት እንዳትራመድና ወደ ኋላ እንድትጎተት የሚፈልጉ የውስጥና የውጭ ኃይሎች የሚፈጥሯቸው ፈተናዎችና ችግሮች ቢኖሩም፤ ልማት፣ ሰላምና ብልጽግናን ስለምናስብ እያሸነፍን ጉዟችን እንቀጥላለን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በ10 ነጥብ 2 በመቶ በሆነ ከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ የምትገኝ ብቸኛ ሀገር መሆኗን ገልጸው፥ ይህ ስኬት ለመላው ሕዝብ ኩራት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ኢትዮጵያ ልጆቿን የምትሰበስብ፣ የአንድነትና የሰላም ምሳሌ ሆና እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
ይህ የአህጉሪቱ ምሳሌ የሆነው ዕድገት በተግባር የሚታይባቸውን እንደ አርባምንጭ፣ ጅማ፣ ሶዶ፣ ሀዋሳ፣ ነቀምቴ፣ ባሕርዳር፣ ድሬዳዋና ጅግጅጋ ያሉ በርካታ ከተሞች በምስክርነት ጠቅሰዋል።
በሶስና አለማየሁ

4 months ago
በባሕር ዳር ለተወዳጁ ሰማኸኝ በለው መንገድ ተሰየመለት!!
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ለጎጃም ግሽ አባይ የኪነት ቡድን አባል ለነበረው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ላተረፈው ለአርቲስት ሰማህኝ በለው መንገድ በስሙ ሰይሟል::
ይህ የታወቀው ዛሬ የባሕር ዳር ህዝብ ለአርቲስቱ መታሰቢያ ባዘጋጀበት ቀን ሲሆን ከባሕር ዳር ልማት ባንክ እሰከ አዲሱ ስቴዲየም ያለው መንገድ "ሰማኸን በለው መንገድ" ተብሎ እዲጠራ መወሰኑን የከተማዋ ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አሳውቀዋል::
አርቲስት ሰማኸኝ በለው በባሕርዳር ተወልዶ ያደገ ሲሆን እጅግ የተዋጣለት የባህል ዘፈችን ማበርክት የቻለና ህይወቱን በሙሉ በሙዚቃ ስራ ላይ ያሳለፈ ተወዳጅ አርቲስት ነበረ::
በባሕር ዳር ለአርቲስቱ መታሰቢያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ውሳኔዎች የሚቀጥሉ መሆናቸውንም መረጃዎች ያሳያሉ::

Sponsored by
Surafel
4 months ago
በባሕር ዳር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
***********************
የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በባሕርዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በመገኘት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት እየገለጹ ይገኛሉ።
በዚህ የሕዝብ ድጋፍና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation

5 months ago
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ምሽት 12 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የኢትዮ ኤሌክትሪክን የማሸነፊያ ግቦች ቤዛ መድህን፣ አሸናፊ ጥሩነህ እና ሙከረም ረሺድ አስቆጥረዋል።
የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ በረከት ግዛው ከመረብ አሳርፏል።
ቀደም ብሎ በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዋች ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 2፣ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ፤ ባሕርዳር ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በጣና ዳርቻ ላይ የሚገነባው የቱሪዝም መዳረሻ
#bahirdar #tourismethiopia #midrocinvestmentgroup #laketana #newproject #ethiopiarising #ባሕርዳር #ኢትዮጵያ
5 months ago
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርትን መርቀዋል ሥራ አስጀመሩ
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሕርዳር እጅግ ብዙ ጸጋ ያላት ከተማ መኾኗን ገልጸዋል።
ከዓመታት በፊት በባሕርዳር የሚንቀሳቀስ ሰው ይሄን የመሰለ የጣና ጸጋ አያይም ነበር፤ አሁን ግን የጣና ጸጋ ተገልጧል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መሥራት አለብን፤ ጭቃ መንካት አለብን፤ ሀገር የሚገነባው በትብብር ነው በማለት እንዲህ አይነት ልማት እንድናይ አድርገውናል፤ እናመሠግናቸዋለን ብለዋል።
የፈለገ ግዮን ሪዞርት መነሻው የጎርጎራ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።
የጎርጎራ እና የፈለገ ግዮን ሪዞርቶች ጎብኝዎች በአማራ ክልል የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ድህነትን እየገፈፈች የልማት ተምሳሌት እየሆነች መምጣቷንም አንስተዋል።
በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች አስገራሚ የልማት ሥራዎች መሠራታቸውን የገለጹት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር የተገነባው ድልድይ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እና የቱሪዝም መዳረሻ መሆኑንም ነው ያነሱት።
የባሕርዳር ስታዲዬምም ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻ የሚሆን፤ ዓለም አቀፍ ክለቦች መጥተው እንዲጫወቱ የሚያደርግ ዘመናዊ ስታዲየም መሆኑን ገልጸዋል።
የልማት ሥራዎች ሲገናኙ ለአካባቢው ታላቅ ጸጋ የሚያጎናጽፉ፤ የድህነትን ታሪክ የሚቀይሩ፤ ኢትዮጵያውያን በላባችን መለወጥ እንደምንችል ማሳያ ናቸው ብለዋል።

6 months ago
ባሕር ዳር ላይ ሰው ገድሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ መቐለ ላይ በትግራይ ክልል ፖሊስ ተያዘ።
በባሕርዳር ከተማ ማህሌት ማሩ የተባለችን እንስት " የአድማ ብተና " አባል በሆነው ተጠርጣሪ ያምራል አለበል አለሙ " ተደፍራ እና ተገድላ ተገኘች " የሚል መረጃ ሲሰራጭ ነበር።
የግድያ ጥቃቱ የደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ ከስፍራው የወጣውና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው አብዛኛው መረጃ፣ ተጠርጣሪው እንስቷ ከምትሰራበት ሆቴል እየተስተናገደ አምሽቶ " አስገድዶ ወደ ሌላ ሆቴል በመውሰድ ከደፈራት በኋላ ገደላት " የሚል ነው።
የወንጀል ድርጊቱ ብዙዎችን ያቆጣ ነው።
የወንጀል ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ ድርጊቱን ፈጽሞ ከአካባቢው ተሰውሮ ነበር።
ምንም እንኳን የአማራ ክልል ፖሊስ ስለ ግድያው ዝርዝር መረጃ ይፋ ባያደርግም ህዝቡ ያለበትን እንዲጦቅም ጥሪ አቅርቦ ፍለጋ ሲያካሂድ ነበር።
ዛሬ የአማራ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ያምራል አለበል አለሙ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስ " ያምራል አለበል አለሙ የተባለው ተጠርጣሪ ግድያ ፈጽሞ ከአካባቢው በመሰወር ለረጅም ጊዜ ሲፈለግ ቆይቷል " ብሏል።
ለመያዝ ክትትል ሲደረግ ቆይቶ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ተሸሽጎ እንደሚገኝ በመረጋገጡ በተደረገ የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ አማራ ፖሊስ ገልጿል።
የአማራ ክልል ፖሊስ፣ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።
በሌላ በኩል ቲክቫህ ኢትዮጵያ እንስቷ በምን ሁኔታ ግድያ እንደተፈጸመባት አንድ የአማራ ክልል ፖሊስ አካልን ጠይቆ " ምርመራ ላይ ስለሆነ የሚገልጹት ምርመራ የሚሰሩት ናቸው " ብለዋል።
እስካሁን ባለው ክትትል ስለእንስቷ አሟሟት የተገኘ መረጃ ካለ በድጋሚ እንዲገልጹ ስንጠይቃቸውም፣ " ገና ምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
@tikvahethiopia

ባሕር ዳር፦ ወጣት ብሩክ የሠራው አዲሱ መኪና
#የጥበበኛ እጆች ባለቤት የሆነውና በባሕር ዳር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ ኤሌክትሪክ ዘርፍ የተመረቀው ወጣት ብሩክ ወንዲፍራው፣ የማይቻል የሚመስለውን በተግባር አሳይቷል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኢንዱስትሪ ማሽኖችን የሠራው ብሩክ፣ አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች የተሠራች ባለ አራት እግር መኪና ይፋ አድርጓል።
የተሽከርካሪዋ ልዩ መገለጫዎች
ሞተር
ባለ 300 ሲሲ (CC) ሞተር የተገጠመላት።
አቅም
በአንድ ጊዜ 4 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላትና ከባጃጅ የተሻለ ፍጥነት የምትጓዝ።
ክብደት
ከ400 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት አላት።
ወጪ
ለመሥራት ከ350 ሺህ ብር በላይ ወጪ ተደርጎባታል።
የብሩክ ትልቅ ራዕይ
የብሩክ ህልም መኪና ሠርቶ ማሳየት ብቻ አይደለም። በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ በጥራት ማምረት እና ለብዙ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ነው። ድጋፍ ካገኘ ደግሞ በቀጣይ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን የማምረት ትልቅ ዕቅድ አለው።
የነገዋ ኢትዮጵያ ከመግዛት ወጥታ ወደ ማምረት የምትገባው በእንዲህ ያሉ ጀግኖች እጅ ነው።
#ቴዎድሮስ ደሴ ( አሚኮ)
#getu #innovationethiopia #bahirdar #techhero #madeinethiopia #engineeringexcellence #youthempowerment #ethiopiadecides #automotiveinnovation #ባሕርዳር #ፈጠራ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
ባሕርዳር ለአንጋፋው የጥበብ ሰው ግዮን ዓለምሰገድ የክብር እውቅና ሰጠች
#ethiopia | በኢትዮጵያ የቲያትርና የፊልም ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፈውና በትውልድ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለው አንጋፋው ተዋናይ ግዮን ዓለምሰገድ በባሕርዳር ከተማ ደማቅ የክብርና የእውቅና ተሰጥቷል።
በውቧ የጣና ዳርቻ ከተማ በተከናወነው በዚህ የክብር መርሀግብር ላይ በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ወዳጅ ቤተሰብ በተገኙበት ለከያኒው የሚገባውን አክብሮት ተሰጥቷል።
አንጋፋው ባለቅኔና ደራሲ ጌትነት እንየው ለግዮን ዓለምሰገድ የክብር ካባ በማልበስ ለጥበብ የከፈለውን የሕይወት ዘመን መስዋዕትነት ዘክሯል።
ግዮን ዓለምሰገድ በመድረክ ላይ ያለውን ገጸ-ባህሪ በሕይወት የመሳል፣ የድምፅ አጠቃቀምና የሰውነት እንቅስቃሴን በተመጣጣኝ ሁኔታ የማዋሃድ ልዩ ክህሎቱ የሚታወቅ ሲሆን ከትወና ባለፈም ለወጣት ባለሙያዎች መንገድ አሳይና አስተማሪ በመሆን የዘርፉን ዕድገት ሲደግፍ የቆየ የጥበብ አውራ ነው።
ይህ በባሕርዳር ከተማ የተዘጋጀው የምስጋና መርሃ-ግብር እንዲሳካ ስንታየሁ ገብሩ፣ አበባው ደረበ ፣ ቻሌ ማረው ፣ ደሳለኝ ድረስ እና ሌሎች የጥበብ ጓደኞቹ ከባሕርዳር ጥበብ አፍቃሪዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ "እንኳን ደስ አለህ" በማለት የማይተካና የማይደፈር የሙያ አበርክቶት እንዳለው ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ አይነቱ በሕይወት እያሉ የመከበር ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#gionalemseged #bahirdar #ethiopiantheatre #artrecognition #getnetenyew #ethiopianart #tana #lifetimeachievement #cinemaethiopia #culturalheritage

⛪ የአዲስ ዘመን ደብረ ደናግል ቅድስት ሐናን አብረን እናልማ!
በዐቢይ ጾም ወቅት የሚደረግ ታላቅ የበረከት ጥሪ!
ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የአዲስ ዘመን ደብረ ደናግል ቅድስት ሐና ካቴድራል በ837 ዓ.ም የተመሠረተችና የታሪክ አሻራ ያረፈባት ቅድስት ስፍራ ናት።
በአሁኑ ወቅት ካቴድራሏን በራስ አገዝ ልማት በማጠናከር፣ ታላቅ የሃይማኖትና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እየተከናወነ ይገኛል።
ይህንን የተጀመረ የተቀደሰ የልማት ሥራ ዳር ለማድረስ፣ በመጪው እሁድ በሚካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያና የወንጌል መርሃ-ግብር ላይ እንድትገኙ ጥሪ ቀርቦላችኋል።
እሁድ፣ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
ከጠዋቱ 7:30 ሰዓት ጀምሮ
*ባሕር ዳር፤ ሰላም አድርጊው ማርያም ቤተክርስቲያን።
የትምህርተ ወንጌል ስርጭት እና የልማት ገቢ ማሰባሰቢያ።
የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን (ድጋፍ ለማድረግ)
በአካል መገኘት ለማትችሉና ከሩቅ ሆናችሁ ለእናታችን ለቅድስት ሐና ቤት አሻራችሁን ማሳረፍ ለምትፈልጉ ሁሉ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የአካውንት ቁጥር፦ 1000709139634
አዘጋጅ፦
የባሕር ዳር አስተባባሪ ኮሚቴ
✨ እኛም ለቤታችን፣ እኛም ለእናታችን!
ይህ ጥንታዊ ቅርስና መንፈሳዊ ማዕከል ተጠግኖና ለምቶ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚደረገው ጥረት የሁላችንንም እገዛ ይሻል።
በጾም ወቅት የሚደረግ ምጽዋትና በጎ ተግባር ደግሞ ድርብ በረከት አለው።
#ቅድስትሐና #አዲስዘመን #ባሕርዳር #ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #የበረከትጥሪ #ethiopia #sainthanna #addiszemen #bahirdar #cbe #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

9 months ago
⚽ ከሀገር ቤት እስከ አውሮፓ ሜዳዎች
#ethiopia | ዛሬ ቅዳሜ የእግር ኳስ አፍቃሪው አይኑን ከስክሪን ላይ የማይነቅልበት ልዩ ዕለት ነው። በሜዳችንም ሆነ በባህር ማዶ የሚደረጉ ጨዋታዎች ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸዋል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የሀገር ውስጥ ሊጉ በደማቅ ፍልሚያዎች ተሞልቷል። በተለይ በ9:00 እና በ10:00 የሚደረጉት ጨዋታዎች የሊጉን መሪነትና ደረጃ ለመቀየር ትልቅ ሚና አላቸው።
* 7:00 | መቻል 🆚 ባሕርዳር ከተማ
* 9:00 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 🆚 ሀድያ ሆሳዕና
* 10:00 | ፋሲል ከነማ 🆚 ኢትዮጵያ ቡና (ተጠባቂ)
* 12:00 | ወላይታ ድቻ 🆚 ኢትዮጵያ መድን
🏴 በእንግሊዝ ሜዳዎች (ኤፍ ኤ ካፕ/ሊግ)
በእንግሊዝ ታላላቆቹ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ፣ ቶተንሀም እና ቼልሲ ወደ ሜዳ የሚገቡበት ምሽት ነው።
* 9:15 | ኤቨርተን 🆚 ሰንደርላንድ
* 12:00 | ማንችስተር ሲቲ 🆚 ኤክስተር
* 12:00 | ኒውካስል 🆚 በርንማውዝ
* 2:45 | ቶተንሀም 🆚 አስቶን ቪላ (የምሽቱ ታላቅ ጨዋታ)
* 5:00 | ቻርልተን 🆚 ቼልሲ
🌍 የአፍሪካ ኃያላን እና ጣሊያን
በአፍሪካ ምድር የሚደረጉት የሀገራት ፍጥጫዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።
* 1:00 | አልጄሪያ 🆚 ናይጄሪያ
* 2:00 | ሮማ 🆚 ሳሱሎ (ሴሪአ)
* 4:00 | ግብፅ 🆚 ኮትዲቯር (የአፍሪካ ደርቢ)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#እግርኳስ #የዛሬጨዋታዎች
#ኢትዮጵያፕሪሚየርሊግ #ማንችስተርሲቲ #ቼልሲ #ቶተንሀም #ኢትዮጵያቡና #ፋሲልከነማ #footballdaily #matchday #ethiopianpremierleague

ዝግባ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለገና በአል ድጋፍ አደረገ!
#fastmereja : ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ወላጆቻቸዉን በሞት ላጡና ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ፣ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸዉ አረጋዉያን፣ ለችግረኛ ሴቶች የመዓድ ማጋራት፣ የአልባሳት እና ቁሳቁስ ስጦታ በዛሬዉ እለት አካሂዷል።
በዛሬዉ እለት ከህፃናትና አረጋውያን እንዲሁም ከችግረኛ ሴቶች መካከል በአዲስ አበባ ድጋፍ የሚደረግላቸውን ከ2ዐዐ በላይ ሰዎች ነዉ በአልን ምክንያት በማድረግ ድጋፉ የተደረገዉ።
ይህ የድጋፍ እንክብካቤ እና የበጎነት ተግባርም የ2018ዓ.ም የገና በአልን ምክንያት በማድረግ የተካሄደ ነዉ።
በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ድጋፍ ላይ ድጋፍ ላደረጉ እና አብረዋቸዉ እየሰሩ ለሚገኙ ድርጅቶች ምስጋና በማቅረብ ለአባይ ባንክ እና ፀደይ ባንክ የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።
እንዲሁም ዝግባ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኮሜዲያን ምትኩ ፈንቴ እና ኮሜዲያን አዝመራዉን በጎ ፈቃድ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጁ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው እንደገለፁት ሁሉም ግለሰብ እና ድርጅት ይህን ዘላቂ ድጋፍ ለሚሰጠዉ ድርጅት ድጋፋቸዉን እንዲሰጡ በመግለፅ እስካሁን አብረዋቸዉ ሲሰሩ ለቆዩት እየሰሩም ላሉት ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
በምሳ ፕሮግራሙ የተገኙት አረጋውያኖች ድጋፉን ላበረከተላቸው ድርጅት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ዝግባ የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሀያ ሶስት ህፃናት እና ሀያ ሁለት አረጋውያንን በማቀፍ የተጀመረው ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ለችግር የተጋለጡ ህጻናት ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው አረጋውያን፣ ለችግረኛ ሴቶችና ለማህበረሰብ ክፍሎች የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እየሰጠ ያለ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን አገልግሎቱን በባሕርዳር እንጅባራ እና በአዲስ አበባ እየሰጠ ይገኛል።

10 months ago
ባሕርዳር : ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር የሚያስተሳስር የመንገድ ግንባታ አየተገነባ ነው
#ethiopia | የባሕርዳር ከተማ አስተዳድር የኮሪደርና የጣናዳር ልማት አካል የሆነው ከአማራ ልማት ማህበር እስከ ዋተርፍሮንት ሆቴል አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ።
የመንገድ ግንባታ ሂደቱ የከተማው የመንግስት አመራሮች በተጎበኘበት ወቅት እንደተገለጸው መንገዱ ለነዋሪዎች ዘመናዊ እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር በማስተሳሰር ተጨማሪ ውበት እንደሚፈጥር ተገልጿል።
የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳላማው ጎሹ በጉብኝት መርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት "የመንገዱ ግንባታው የመኪና፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የግሪነሪ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን የመብራት፣ የቴሌ፣ የውሀ መስመሮች በዘላቂነት በመሰረተ ልማት ስራው ተቀናጅተው መሠራቱን ገልጸዋል።
በሬማ ጀኔራል ቢዝነስና ኮንስትራክሽን አማካኝነት ከአልማ ዋተርፍሮንት ሆቴል እየተነባ የሚገኘው ዘመናዊ መንገድ በቅድመ ክፍያ ብቻ አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አቤኔዘር ማስረሻ ገልጸዋል።
ይህ መንገድ በመሠራቱ የአካባቢው ነዋሪ እጅግ ደስተኛ በመሆኑ የባህርዳር ከተማ አመራሮችንና ሬማ ኮንስትራክሽንን እያመሠገነ እንደሚገኝ አቶ አቤኔዘር ገልጸዋል።
የአስፓልት ስራው የ3 ወር እቅድ ቢሆንም በመሀል የነበረው የክረምት ሁኔታ ተጨማሪ ቀናቶችን ቢወስድም በአድቫንስ ብቻ በአጭር ጊዜ መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቅቅ በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮንክሪት አስፓልት መንገዱ 8 መቶ ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይህ አስፓልት በፍጥነትና በቅድመ ክፍያ ብቻ እየተሰራ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤትና መሥራች አቶ ፍቅሬ አስፋው ተናግረዋል።
በጉብኝቱ መርሐግብር ላይ አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ፣ አቶ ሞላ ሁሴን የባሕርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ አቶ አስሜ ብርሌ የባሕርዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ በቦታው ተገኝተዋል።

ለባህርዳር ከተማ ሌላ ውበት ይሰጣታል የተባለለት አስፓልት በመጠናቀቅ ላይ ነው
በሬማ ጀኔራል ቢዝነስና ኮንስትራክሽን አማካኝነት ከአልማ ዋተርፍሮንት ሆቴል እየተነባ የሚገኘው በጣም ዘመናዊና ልዩ መንገድ በቅድመ ክፍያ ብቻ አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማናጀር አቤኔዘር ማስረሻ ተናገሩ።
ይህ መንገድ በመሠራቱ የአካባቢው ነዋሪ እጅግ ደስተኛ በመሆኑ የባህርዳር ከተማ አመራሮችንና ሬማ ኮንስትራክሽንን እያመሠገነ እንደሚገኝ አቶ አቤኔዘር ገልጸዋል።
የአስፓልት ስራው የ3 ወር እቅድ ቢሆንም በመሀል የነበረው የክረምት ሁኔታ ቲኒሽ ቀናቶችን ቢገፋውም በአድቫንስ ብቻ በአጭር ጊዜ መንገዱን ሰርቶ ማጠናቀቅ ተችሏል።
በትላንትናው ዕለትም አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ፣ አቶ ሞላ ሁሴን የባሕርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ አቶ አስሜ ብርሌ የባሕርዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል።
የኮንክሪት አስፓልት መንገዱ 8 መቶ ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይህ አስፓልት በፍጥነትና በቅድመ ክፍያ ብቻ እየተሰራ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤትና መሥራች አቶ ፍቅሬ አስፋው ተናግረዋል።
መንገዱ ለነዋሪዎች ዘመናዊ እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር የሚያስተሳስር መሆኑ ተገልጧል።
የመንገዱ ግንባታ የመኪና፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የግሪነሪ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን የመብራት፣ የቴሌ፣ የውሀ መስመሮች በዘላቂነት በመሰረተ ልማት ስራው ተቀናጅተው የተሰሩ መሆኑ የተናገሩት የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳላማው ጎሹ ናቸው።

መድረክ ላይ ወደቁ!!
አርቲስት ሰሎሞን ተካ ባሕርዳር ለደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በአገልግሎት ላይ እያሉ የምሥራች ዜና ሰምተዋል። በዚኽም በዝማሬ መሐል ደስታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ታይተዋል። ከመድረክም ወድቀዋል። አጠገባቸው የነበሩ ልጆችም ከመሬት አንስተው እንደገና እሰይ ነጋ እያሉ እንዲዘምሩ አድርገዋቸዋል።
ከሥፍራው የዘገበው ሎዛ ሚዲያ

11 months ago
ዶክተር አንዷለም ዳኜ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
#ethiopia | ተከሳሽ እሱባለው (ሳሙኤል) ነበረ የተባለው ግለሰብ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡00 – 2፡00 በሆነ ሰዓት ባሕርዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ የጦር መሳሪያ ይዞ ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በሰዓቱ ከባሕርዳር ከተማ ወደ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሄድ የነበረውን ዶክተር አንዷለም ዳኜን የያዘውን ንብረት ለመውሰድ እንዲመቻቸው በማሰብ ያሽከረክር የነበረውን መኪና እንዲያቆም ሲጠይቁት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሁለት ጥይት በመተኮስ ዶ/ር አንዷለም ዳኜን ደረቱን እና ክንዱን በመምታት ገድለውታል።
ስለሆነም ተከሳሹ እሱባለው (ሳሙኤል) ነበረ በፈጸመው የከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ ወይም በአማራጭ የመግደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል የመጀመሪያ ክስ ተከሷል።
በተመሳሳይ ጊዜ እና ቦታ ላይ ወደ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሄድ የነበረው ዶ/ር በረከት አማረ ላይ ሁለት ጥይት በመተኮስ የመኪናውን ቦዲ በመምታት ተበዳዩን የሳተው በመሆኑ በፈጸመው ከባድ የሆነ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል የሚል ሁለተኛ ክስ ተከሷል።
እንዲሁም በሶስተኛ ክስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23(3) ላይ የተመለከተውን ተላልፎ ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያ ሰነዶችን መገልገል ወንጀል ፈጽሟል በሚል በሰሜን ጎጃም ዞን ፍትሕ መምሪያ ክሶች ቀርበውበታል፡፡
ተከሳሹም የቀረቡበትን ክሶች ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የባሕርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን ማስረጃዎች በመስማት ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ የመከላከያ ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የቀረቡበትን ክሶች መካለከል አልቻለም።
በመሆኑም በ1ኛው ክስ ስር በወ/ህግ አንቀጽ 671(2) ስ፣ በ2ኛው ክስ በወ/ህግ አንቀጽ 27(1) እና 671(1)(ሐ) ስር፣ እንዲሁም በሦስተኛው ክስ በወ/ህጉ አንቀጽ 378 ስር ድንጋጌዎችን በመቀየር የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ፣ የቅጣት አስተያየቶችን በመመርመር ተከሳሹ በአጠቃላይ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ መስጠቱን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።
ከአማራ ክልል ፖሊስ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ።

ዶክተር አንዷለም ዳኜ ላይ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ተገለጸ
በባህር ዳር ከተማ የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪም በነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል በፈፀመው ተከሳሽ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት መወሰኑን የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት አስታውቋል።
ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሽ እሱባለው (ሳሙኤል) ነበረ የተባለው ግለሰብ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡00 እስከ 2፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስ ባሕርዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ የጦር መሳሪያ ይዞ ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ወንጀሉን መፈጸሙ ተነግሯል።
ወንጀል ፈጻሚዎቹ በሰዓቱም ከባሕርዳር ከተማ ወደ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሄድ የነበረውን ዶክተር አንዷለም ዳኜን የያዘውን ንብረት ለመውሰድ እንዲመቻቸው በማሰብ፤ ያሽከረክር የነበረውን መኪና እንዲያቆም ሲጠይቁት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሁለት ጥይት በመተኮስ ዶ/ር አንዷለምን ደረቱን እና ክንዱን በመምታት ግድያውን መፈጸማቸው በችሎቱ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት ተከሳሹ እሱባለው (ሳሙኤል) ነበረ በፈጸመው የከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ ወይም በአማራጭ የመግደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል የመጀመሪያ ክስ ተከሷል።
በተመሳሳይ ጊዜ እና ቦታ ላይ ወደ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሄድ የነበረው ዶ/ር በረከት አማረ ላይ ሁለት ጥይት በመተኮስ የመኪናውን ቦዲ በመምታት ተበዳዩን የሳተው በመሆኑ፤ በፈጸመው ከባድ የሆነ ሰው መግደል ሙከራ ወንጀል የሚል ሁለተኛ ክስ ተከሷል።
እንዲሁም በሦስተኛ ክስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23(3) ላይ የተመለከተውን ተላልፎ "ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያ ሰነዶችን መገልገል ወንጀል ፈጽሟል" በሚል በሰሜን ጎጃም ዞን ፍትሕ መምሪያ ክሶች እንደቀረቡበት ተመላክቷል፡፡
ተከሳሹም የቀረቡበትን ክሶች ክዶ የተከራከረ ቢሆንም፤ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የባሕርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዐቃቤ ሕግን ማስረጃዎች በመስማት ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ የመከላከያ ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ ተከሳሹ የቀረቡበትን ክሶች መካለከል ሳይችል መቅረቱ ተገልጿል።
በመሆኑም በሦስቱም ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ፣ የቅጣት አስተያየቶችን በመመርመር ተከሳሹ በአጠቃላይ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ መስጠቱን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።
#አሐዱ

የዶክተሩ ገዳይ 25 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት።
በባህር ዳር ዩንቨርስቲ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር በሚገኘው የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ መግደሉን አረጋግጫለሁ ባለው ግለሰብ ላይ በ25 አመት ፅኑ እስራት መቅጣቱን የባሕርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት እሱባለው ነበረ የተባለው ግለሰብ ጥር 24/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 ገደማ በከተማው ሰባታሚት "ቆሸ" ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ዶክተሩ እያሽከረከረ በነበረበት መኪና ላይ ሁለት ግዜ በመተኮስ መግደሉን የወንጀሉን ፈፃሚ ለማግኘት በተቋቋመው ግብረሀይል በኩል በተገኘው መረጃና ማስረጃ መሰረት ውሳኔውን ማስተላለፉን ገልጿል።
በዕለቱ ዶ/ር አንዱአለም ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለታካሚዎቻቸው የቀዶ ህክምና አገልግሎት ሲሰጡ አምሽተው ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል ወደ ሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እየሄዱ በነበሩበት ወቅት በሚያሽከረክሩት መኪና ላይ በቀኝ በኩል በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን በወቅቱ ፖሊስ መረጃውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ፓሊስ በዚህ የምርመራ ሒደት ከክልሉ ፖሊስ ዋና መምሪያ እና ከከተማ አስተዳደሩ የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ መረጃና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የወንጀሉን አፈፃፀምና ፈጻሚውን ማወቅ እንደተቻለ ይፋም አድርጎ ነበር።
ፍርድ ቤቱም የቀረቡለትን የምርመራ ውጤቶች መሰረት በማድረግ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ወንጀሉን በፈጸመው ግለሰብ እሱባለው ነበረ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኖበታል።
ዶክተሩ በተገደለበት ምሽትም በተመሳሳይ በሌላ የሕክምና ዶክተር ላይ ጥይት በመተኮስ የመኪናውን አካል በመምታት የግድያ ወንጀል ሙከራ ስለመደረጉም ፍርድ ቤቱ አመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#tikvahethiopiafamilybahirdar

ፈረሰኞቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !
#ethiopia | በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባሕርዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 አሸንፈዋል።
የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው 2x እና አዲሱ አቱላ ሲያስቆጥሩ በረከት ጥጋቡ ለጣና ሞገዶቹ ከመረብ አሳርፏል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመጀመሪያ አራት የሊግ መርሐግብሮች ሶስቱን በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።
ባሕርዳር ከተማ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም በሶስቱ አቻ ሲለያይ በአንዱ ተሸንፏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
6️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 9 ነጥብ
8️⃣ ባሕርዳር ከተማ :- 6 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀድያ ሆሳዕና
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ባሕርዳር ከተማ #ts #sport #gtmc

ባሕርዳር : በዘይት ምርት ላይ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎች ታሰሩ
#ethiopia | በባሕርዳር ከተማ አሳማኝ ምክንያት በሌለበት ተመሳጥረው በዘይት ምርት ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 27 ነጋዴዎች መታሰራቸውን የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ 221 ድርጅቶች እና 8 ስቶሮችን በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱም ተገልጿል።
በከተማው ዘይትን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ እና ምርት ስወራ አስተመልክቶ የባሕርዳር ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አደራ ጋሼ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ለመንግስት ሠራተኞች የተደረገውን የደሞዝ ማሻሻያ ተከትሎ በግብይት ላይ እየተፈጠረ ያለውን ጭማሪ ለመግታት እየተሰራ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።
ጭማሪው በኢንደስትሪ ምርቶች ላይ በተለይም ስኳርና ዘይት ላይ መታየቱን ገልጸው፤ በተለይ የዘይት ምርት ላይ የታየው ጭማሪ ቀድሞ በገበያው ከነበረበት ከ80 እስከ 100 ብር የሚደርስ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተጠቀሰው።
በዘይት ምርቶች ላይ የሀገርውስጥ የዘይት ምርት አከፋፋዮች ጭማሪ አድርገው መልሰው ወደ ነበረበት ማውረዳቸውን አስተውለናል ያሉት ኃላፊው፤ ከጭማሪ ባለፈ ምርት የመደበቅ እንቅስቃሴ ታይቷል ብለዋል፡፡
በአንፃሩ የግብርና ምርቶች የተረጋጋ ዋጋ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።
በገበያ በምርቶች ላይ ከታየው ጭማሪ ባለፈ፣ በቤት ኪራይ ላይ ተስተውሏል የተባለውን የዋጋ ጭማሪ በመመርመር ላይ መሆናቸውን ኃላፊው አንስተዋል።
ለዚህም ከደሞዝ ማሻሻያው በፊት ከነበረው ዋጋ የተለየ ጭማሪ የተደረገባቸው ግለሰቦች በክፍለ ከተሞች መበቅረብ ጥቆማ መስጠት እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል፡፡
ገበያው ላይ የታየው ንረት ህዝብን በማማረር ከመንግስት ሀሳብ የመነጠል ፍላጎት ነውያሉት ኃላፊው፤ ለሕግ ተገዥና ምስጉን ነጋዴዎች፣ የመንግስት ሠራተኛው መላ ማህበረሰቡ እና የፀጥታ አካላት ለሕግ ማስከበር ተግባሩ ስኬታማነት በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

12 months ago
#ethiopia | “የጥጥ ምርትን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የማምረት አቅም አለ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የአየር ፀባይ ለጥጥ ምርታማነት ጥሩ ነው፡፡ ወጣት አምራች ሀይልም እንዲሁ በከፍተኛ ቁጥር ማግኘት ይቻላል፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ ለምሳሌ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጨርቃ ጨርቅ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ በአንድ ላይ የራሱ አበርክቶ ይኖረዋል” ሲሉ የግብርና ዘርፍ ባለሙያው በጋሻው መብራቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ጥጥን እሴት በመጨመር ማምረትና በራስ አቅም ለገበያ ማቅረብ አዳዲስ የሥራ እድል እንዲፈጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማደረግ ኢኮኖሚውን እንደሚያግዝ ባለሙያው ገልፀዋል፡፡
ወደ ጨርቃጨርቅ ምርት በመቀየር የሀገር ውስጥ ገበያን ብሎም የወጪ ንግዱን በእኩል ተደራሽ ማድረግ የሚቻልበት አዋጭ ስርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ሲል ስፑትኒክ ነው።
1 year ago
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ "ሠላም አካዳሚ" የማህበረሰብ ትምህርት ቤት በይፋ አስጀመረ
#ethiopia | የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አካል የሆነው "ሠላም አካዳሚ" የተሰኘው የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቀብሎ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። አካዳሚው የዩኒቨርሲቲውን ሠራተኞች ለመደገፍና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
ከዚህ ቀደም በ2017 ዓ.ም. የቅድመ መደበኛ (KG 1 እስከ KG 3) ትምህርትን ሲሰጥ የቆየው ሠላም አካዳሚ፣ በዚህ ዓመት ደግሞ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በመቀበል ሙሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መስጠት ጀምሯል።
ይህ መስፋፋት የዩኒቨርሲቲው ለሠራተኞቹ ከሚሰጣቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን፣ በተለይም የሠራተኞችን ከኑሮ ውድነት አንጻር ያለውን ጫና በማቅለል ረገድ ትልቅ ድጋፍ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ለትምህርት ቤቱ መቋቋም የቅርብ ክትትል በማድረግ በሰው ሃይልና በግብዓት ተሟልቶ በሙሉ አቅም ስራ እንዲጀምር አድርገዋል።
ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX- BDU) ሰራተኞች አካዳሚው እንዲቋቋም ከፍተኛ ድርሻ ተወጥተዋል።
ትምህርት ቤቱን ስራ ለማስጀመር ከሠራተኞችና ከተማሪ ወላጆች ጋር የውይይት መድረክ የተደረገ ሲሆን፣ የትምህርት ጥራት መላሸቅና የግል ትምህርት ቤቶች የዋጋ መናር ባለበት ወቅት ትምህርት ቤቱ መከፈቱ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው ወላጆች ገልጸዋል።
በውይይቱ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ከ60ዓመታት በላይ ያለምንም ሞዴልና ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የቆየ በመሆኑ አሁን በቁጭት መስራት እንደሚያስፈልግና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም ጥሪ ቀርቧል።
የሠላም አካዳሚ መማር ማስተማር ሂደት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ሁሉም አስፈላጊ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ተሟልተውለት እንደተጀመረ ተገልጿል።
አካዳሚው በቀጣይ ብቁ የሀገር ተተኪዎችን በመቅረጽ የጎላ ሚና እንዲጫወት ታስቦ ትኩረት ተሰጥቶት ለወደፊቱ ሞዴል ትምህርት ቤት ለመሆን ያለመ ነው።
ትምህርት ቤቱ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባለቤትነት በመስራት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል፤ በአሁኑ ጊዜም በዩኒቨርሲቲው ዋና የትኩረት መስክ ሆኖ እየተሰራ ይገኛል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም የስቲም (STEM) ማዕከል በማቋቋም በቴክኖሎጂ ትምህርት ዙሪያ ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሠላም አካዳሚ መጀመርም ጥራት ያለው ትምህርትን ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ በማስተማር ልዩ ትምህርት ቤት ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

Comments