1 month ago
«ፍቅር እስከ መቃብር» — የሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ጽሑፍ ውህደት
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታላቅ ሥራ የሆነውን «ፍቅር እስከ መቃብር» በሥዕል የሚያስቃኘው የአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ የሥዕል አውደ-ርዕይ በFendikaHyatt ተከፍቷል።
የአዲስ ዓለማየሁ የሥነ-ጽሑፍ ድንቅ ሥራ በነጋለኝ ሉሌ ሥዕሎች አማካኝነት በአዲስ የጥበብ ትርጓሜ ቀርቧል። የፍቅር፣ የቤተሰብ እና የመንፈሳዊነት ታሪኮችን በምስል የሚያስቃኘው አውደ-ርዕዩ፣ ሥነ-ጽሑፍን ከሥዕል ጥበብ ጋር የሚያገናኝ ልዩ የጥበብ ልምድ ይሰጣል።
የአውደ-ርዕዩ ጋለሪ በማስታወቂያው መሠረት 24/7 ክፍት ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍ ቅርስ በሥዕል መልክ ለመመልከት የሚፈልጉ የጥበብ አፍቃሪዎች እንዲጎበኙት ጥሪ ቀርቧል።
«ፍቅር እስከ መቃብር» — በቃላት የተጻፈው ታሪክ፣ በቀለም እንደገና ሲነገር።
ርዕስ፦ ፍቅር እስከ መቃብር በስዕል
በአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ
ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም - መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም (August 26, 2026 – September 21, 2026)
የአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ ግል ታሪክ (Biography)
በ1958 ዓ.ም በጎጃም በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለዱ። የእድሜያቸው ትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በፍኖተ ሰላም ከተማ፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በደብረ ማርቆስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ። በሥነ ጥበብ ዲዛይን ትምህርት ቤት (Balle Design School) በ1983 ዓ.ም በስዕል ጥናት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
በተለያዩ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች ከ30 ዓመት ያላነሰ በሙያቸው አገልግለዋል። ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የተለያዩ የሥነ ጥበብ ሥራዎችን በመሥራት አሳልፈዋል።
1983 ዓ.ም፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም በጋራ የስዕል ኤግዚቢሽን አሳይተዋል።
1991 እና 1999 ዓ.ም፦ በባህር ዳር ከተማ በቡድን ሥራዎችን አሳይተዋል።
2008 እና 2010 ዓ.ም፦ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ያዘጋጇቸውን የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ የስዕል ሥራዎች አቅርበዋል።
2009 ዓ.ም፦ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በጋራ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በላቀቋቸው የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ገጸ ባሕርያት የስዕል ሥራዎቻቸው የዕድሜ ልክና የምርጥ የሥነ-ጥበብ ተሸላሚ ሆነዋል።
«ፍቅር እስከ መቃብር» — የሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ጽሑፍ ውህደት መነሻ ምክንያት እንደተናገሩት "የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ የገጸ-ባሕርያት ስዕሎችን እንድስል ያነሳሳኝ ምክንያት ዘመን ተሻጋሪ የሆነው የፍቅር እስከ መቃብር ትረካ በወጋየሁ ንጋቱ ድምፅ በሬዲዮ ሲነበብና ሲተረክ መስማቴ፣ እንዲሁም በቤተሰቦቼ ሲነገረኝ በነበረው በነበረው የጎጃም ማኅበረሰብ አኗኗርና ሥርዓት እየተደመምኩ ያደግኩበት ታሪኮች ስዕሎቹን ለመሳል መነሻዎች ናቸው።
የሳልኳቸው የፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ገጸ ባሕርያት ሥራዎች ማኅበራዊ ሕይወትን የተለያዩ ውጣ ውረዶችን የሚጋፈጡ ሰዎችን የሕይወት ጉዞና ፅናት በተምሳሌትነት ይገልጻሉ። ስለዚህም የሥዕሎቹ ዋና ዓላማ ስሜቴንና ፍላጎቴን ከመግለጽ በተጨማሪ በሰው ልጅ መካከል ያለውን የጋራ መግባባትና ስምምነት ማጎልበት ነው።
ነሐሴ 20 ቀን የተከፈተ ሲሆን መስከረም 11 ቀን 2019ዓ.ም የሥነ-ጥበብ እና ሥነ-ጽሑፍ ውህደት የአውደ-ርዕዩ ጋለሪ በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ይጠናቀቃል።
ኢሜይል፦ Fendikagalleryartproposalgmail.com
የአርቲስት ነጋለኝ ሉሌ
+251 91 874 8346
ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል
+251 911 547 577
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ፍቅርእስከመቃብር #ነጋለኝሉሌ #negalegnlulie #fikereskemekaber #ethiopianart #ethiopianliterature #fendika #artexhibition #addisababa

አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የዛጎል ኩባንያ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ
#ethiopia | የኪነ ጥበብ ባለሙያው አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የዛጎል (ZAGOL) የብራንድ አምባሳደር ሆኖ መመረጡን ኩባንያው አስታወቀ።
ዛጎል ሲስተምስ ትሬዲንግ አርቲስቱን የቆየ የስራ ልምዱንና ህዝባዊ ተደማጭነቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቋሙ ውክልና እንዲሰጠው መምረጡን ገልጿል።
በተደረገው ስምምነት መሰረትም አርቲስት አለማየሁ ታደሰ የድርጅቱን የጉዞ እና የትኬት ሽያጭ አገልግሎቶች የማስተዋወቅ ስራ ያከናውናል።
ዛጎል በተለይም የአየር መንገድ በረራ ትኬት መቁረጥን፣ የሆቴል አልጋ ማስያዝንና ሌሎች ተያያዥ የጉዞ አገልግሎቶችን በዘመናዊ የዲጂታል አማራጮች ለማቅረብ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።
በቴአትርና በፊልም ሙያ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያገለገለው አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፣ የመጀመሪያ የሙያ ሽልማቱን ያገኘው በ1988 ዓ.ም እንደነበር አስታውሶ እስከ አሁንም በሙያው ማህበረሰቡን በማገልገል ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
አርቲስቱ ለተሰጠው የብራንድ አምባሳደርነት ማዕረግ ፈጣሪውንና ቤተሰቦቹን አመስግኗል።
ከሙያ ስራው በተጨባጭ ከሚያከናውናቸው ህብረተሰባዊ አገልግሎቶች መካከልም ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች ኢትዮጵያ እና ከብሬክስ ህፃናት መደገፊያ ማህበር ጋር የሚሰራቸው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ይጠቀሳሉ።
አንጋፋው ባለሙያ ባለፉት ረጅም ዓመታት ያካበተውን ልምድና ዝህብራዊ ተቀባይነት በመጠቀም የዛጎልን አገልግሎቶች ለህዝብ ተዳራሽ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።
#alemayehutadesse #zagol #zagolsystems #ethiopianart #travelethiopia #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
"78 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዲጂታል ይደረጋሉ"
- አቶ እንድሪስ አብዱ
#ethiopia | ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የባህል፣ የኪነ-ጥበብ እና የእንቁ እሴቶች ሀብቶች በአግባቡ በማልማት ለሀገር ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትስስር የሚውሉበትን አዲስ የሦስት ዓመት የልማት እና ኢንቨስትመንት አቅጣጫ መዘርጋቱን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስትራቴጂ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንድሪስ አብዱ እንደገለጹት፣ ይፋ የሆነው የሦስት ዓመት የልማት እና ኢንቨስትመንት ዕቅድ የሀገሪቱን ባህልና ኪነ-ጥበብ ወደ ተሻለ ደረጃ ከማሸጋገር ባለፈ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባትና የአሰራር ስርዓቶችን ለማዘመን ያለመ ብለዋል።
በዚሁ መሠረት ሚኒስቴሩ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ሀገራዊ ጥናቶች መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ተሸሽገው የቆዩ የባህል እሴቶችን፣ የባህላዊ እርቅና ሽምግልና ስርዓቶችን እንዲሁም በርካታ የቋንቋ ሀብቶችን ለህዝብ ለህዝብ ትስስርና ለሀገር ገጽታ ግንባታ የማዋል ሰፊ ስራዎች ተቀይሰዋል።
በተለይም ሀገሪቱ በ2030 ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ራዕይ ስኬት ባህልና ቋንቋ ወሳኝ መሆናቸውን በመገንዘብ፣ እስካሁን ዲጂታላይዝ ከተደረጉ 30 የሀገሪቱ ቋንቋዎች በተጨማሪ በቀጣይ የስትራቴጂ ዓመታት ሁሉንም 78 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዲጂታል የማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከዚህ ጎን ለጎን ቤተ-መጻሕፍትንና የጥበብ ክበባትን በማስፋፋት አዲስ የሚያነብ ትውልድ የመፍጠር፣ ሀገር በቀል እውቀቶችንና ባህላዊ ህክምናዎችን ለኢኮኖሚ ጥቅም የማዋል እንዲሁም የኢትዮጵያን ሀብት የኪነ-ጥበብ ባህል በአፍሪካና በአለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ ዲፕሎማሲን የማጠናከር ተግባራት ዋና ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopianculture #ethiopianart #creativeeconomyethiopia #digitalethiopia #digitalethiopia2030 #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
ረዳት ፕሮፌሰር እና ሠዓሊ ልዑል ሣኅለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውስጥ ለረጅም ዘመናት በሥነጥበብ መምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ታዋቂው ሰዓሊና ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም በሀገራችን ዘመናዊ የሥነጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ ታዋቂ ሰዓልያን መካከል አንዱ ሲሆኑ የፖይንት ግሩፕ የሥነጥበብ ስብስብ መሥራችና አባልም ነበሩ።
ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በትምህርት ቤቱ ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነትና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት በመሥራት በርካታ ተተኪ የጥበብ ባለሙያዎችን ያፈሩ ተወዳጅ መምህር ነበሩ።
በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ጠንካራ ሙያተኛ እንደነበሩ ይነገራል።
ታዋቂው የጥበብ ሰው ልዑል ሣኅለማርያም በሙያዊ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ሕይወት ተሳትፏቸው፣ በደግነታቸውና በሰው ወዳድነታቸው በብዙዎች ዘንድ የተመሰገኑ ነበሩ።
የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውንም በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በግልና በቡድን ለዕይታ በማቅረብ ትልቅ ስም ያተረፉ ባለሙያ ናቸው።
የደራሽ የጥበብ ሰው የቀብር ሥነሥርዓት ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈጸም ታውቋል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የጥበብ ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍስ ይማር።
#aleschooloffineartsanddesign #addisababauniversity #ethiopianart #leulsahlemaryam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
የሦስት አስርተ ዓመታት የፍቅር እና የጽናት ጉዞ የአንጋፋዎቹ ተወዛዋዦች ዳምጠው ወርቁ እና ጌጤ በሰይፉ አስደናቂ የትዳር ምስጢር
#ethiopia | በትዳር መፍረስ ዜናዎች በበዙበት በዚህ ዘመን ለሰላሳ ዓመታት በፍቅር እና በአንድነት የዘለቁት አንጋፋዎቹ የሀገር ፍቅር ቴአትር ተወዛዋዦች ዳምጠው ወርቁ እና ጌጤ በሰይፉ ሾው ላይ ቀርበው ያካፈሉት ተሞክሮ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ነው። ይህ ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የትዳር ሕይወታቸው ስኬት ቁልፉ መቻቻል እና ትዕግስት መሆኑን ጥንዶቹ ገልጸዋል።
ትዳር እንደ አንድ ትልቅ ተቋም በሂደት የሚገነባ መሆኑን የገለጹት እነዚህ ጥንዶች ከባልና ሚስትነት ባለፈ ወደ ጥልቅ ጓደኝነት እና እንደ እህትና ወንድም ወደ መተሳሰብ ደረጃ መሸጋገር መቻሉ ለፍቅራቸው መጽናት ትልቁ ምስጢር እንደሆነ አስረድተዋል።
ለአስራ ስምንት ዓመታት በአሜሪካ ቢኖሩም ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን እና ባህላቸውን ጠብቀው የቆዩት ጥንዶቹ ዛሬም ድረስ በማንኛውም የደስታ ስፍራ አብረው በመጨፈር ይታወቃሉ።
ዳምጠው ወርቁ እንደገለጸው እንደ ጉራጊኛ፣ ወላይትኛ እና ትግርኛ ያሉ የሀገራችን ባህላዊ ውዝዋዜዎች ከየትኛውም የሰውነት ማጎልመሻ ስፖርት በላይ ለጤና ተመራጭ እና ለረጅም ዕድሜ ጠቃሚ ናቸው።
ባለቤቱ ጌጤ በበኩሏ ስጋን ከመመገብ በመቆጠብ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በመከተል ውበቷን እና ወጣትነቷን መጠበቅ እንደቻለች ተናግራለች።
በስደት ዓለም የሚገጥሙትን የሥራ ጫናዎች በጽናት በማለፍ እና ልጃቸውን በመልካም ስነምግባር በማሳደግ ውጤታማ መሆን የቻሉት ጥንዶቹ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለወገናቸው ያላቸውን ፍቅር በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
በተለይም ባለቤታቸው ለሥራ ጉዳይ ለስምንት ወራት በራቁበት ወቅት ጌጤ በብቸኝነት ያሳለፈችው የእርግዝና ጊዜ ለትዳራቸው ጥንካሬ ትልቅ ትምህርት እንደሆነ አስታውሰዋል።
በመጨረሻም ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት ያላቸውን መልካም ምኞት በመግለጽ ለፍቅር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ መክረዋል።
#ethiopianart #marriageadvice #loveandresilience #ethiopianculture #relationshipgoals #inspiration #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel

የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ መታሰቢያ ሐውልት በክብር ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ዘርፍ በተለይም በትወና እና በኮሜዲ ሥራዎቹ በብዙሃኑ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎ የነበረው የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ መታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
አርቲስቱ በሕይወት ዘመኑ በበርካታ ፊልሞች፣ በመድረክ ተውኔቶች እና በሬዲዮ ድራማዎች ላይ በነበረው የላቀ ተሳትፎ እንዲሁም በማስታወቂያ ሥራዎቹ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ለሀገሪቱ የኪነ ጥበብ እድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት የቆመ ነው።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የቤተሰቦቹ አባላት፣ የጥበብ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል።
አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ሥራዎቹ ግን ዛሬም ድረስ በትውልዱ ዘንድ በደመቀ ሁኔታ ሲታወሱ ይኖራሉ።
#art #artist #memorial #culture #ethiopianart #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
የጥበብ ዓምዱ አታኽልቲ ነጋ በአዲስ ስራ ተመለሰ
* "ውሽጥን ደገን" ሊመረቅ ነው
#ethiopia | ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ በትግራይ የፊልምና ድራማ ዘርፍ ላይ የማይደበዝዝ አሻራ ያሳረፈው፣ መምህር፣ ደራሲና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ ዳግም ወደ ስክሪን ተመልሷል።
በ"ማሾ" እና "ምትሓታዊ ዓለባ" (ብርሆን ገይፀን) የብዙዎችን ልብ የገዛው ይህ የጥበብ ሰው፣ አሁን ደግሞ "ውሽጥን ደገን" (Inside/Outside) በተሰኘ አዲስ የሲትኮም ድራማ ብቅ ብሏል።
ቀን፦
እሁድ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት።
ቦታ፦
በመቀለ ሰማዕታት ሐውልት በሚገኘው ሲኒማ አዳራሽ።
በሸባ ኢንተርተይመንት አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ በቅርቡ በትግራይ ቴሌቪዥን በሳምንት ሦስት ጊዜ ለተመልካች ይደርሳል።
አታኽልቲ ነጋ "ያለ ግንድ ቅርንጫፍ የለም" የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየ፣ ለብዙ ወጣት ባለሙያዎች ፈር ቀዳጅ የሆነ የጥበብ መምህር ነው። ይህ አዲስ ስራው የቀድሞውን ጣፋጭ የትግርኛ ድራማ ለዛ ይዞ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም። ሁላችሁም እሁድ በመቐለ በመገኘት ይህንን የጥበብ ጀግና እንድታበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
(Trailer) ለማየት፦ እዚህ ይጫኑ
ጥበብን በባለቤቱ፣ ታሪክን በፈጣሪው!
ብቸኛ አዘጋጅ
( Exclusive producer ) ሸባ ኢንተርተይመንት
በክብሮም ገ/መስቀል
የዚህን ተከታታይ ድራማ ማስተዋወቂያ (Trailer) ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://youtu.be/T6zFaqse6...
#getu #atakltinega #tigrayfilm #wishtindegen #shebaentertainment #tigrinyadrama #ethiopianart #mekelle #insideoutside #አታኽልቲነጋ #መቀሌ #ጥበብ #ትግርኛፊልም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ታላቁ የሥነ ጥበብ ሰው ረዳት ፕሮፌሰር በኃይሉ በዛብህ አረፉ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ ቤተሰብ ሌላኛውን ታላቅ ምሰሶውን አጥቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት መምህርና አንጋፋው የሥነ ጥበብ ሰው ረዳት ፕሮፌሰር በኃይሉ በዛብህ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ስለ ረዳት ፕሮፌሰር በኃይሉ በዛብህ
ተምሳሌታዊ መምህር፦
በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው፣ ጥንቅቅ ያሉ ባለሙያና ለብዙዎች አርአያ የሆኑ መምህር ነበሩ።
የአመራር ሚና፦
በቀድሞው የሥነ ጥበባት ኮሌጅ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተባባሪ ዲን በመሆን በቁርጠኝነት አገልግለዋል።
ተወዳጅነት፦
በትህትናቸውና ለጥበብ ባላቸው ፍቅር በተማሪዎቻቸው፣ በሥራ ባልደረቦቻቸውና በመላው የሥነ ጥበብ ማኅበረሰብ ዘንድ እጅግ የሚከበሩና የሚወደዱ ሰው ነበሩ።
የቀብር ሥነ-ሥርዓት፦
የአቶ በኃይሉ በዛብህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ አርብ ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. በኮተቤ ሐና ወእያቄም ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና በአጠቃላይ ለሥነ ጥበብ ማኅበረሰቡ መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍስ ይማር!🙏🎨
#getu #behailubezabih #ethiopianart #alleschooloffinearts #arthistory #ethiopia #addisababauniversity #inmemoriam #በኃይሉበዛብህ #ሥነጥበብ #ዜናእረፍት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

"ብልፅግናን የምደግፈው ኢትዮጵያን ስለምወድ ነው!"
አርቲስት ካሙዙ ካሳ
#ethiopia | ታዋቂው የዜማና የቅንብር ባለሙያ ካሙዙ ካሣ በ "Art + plus" ፕሮግራም ላይ ተገኝቶ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በፖለቲካ አቋሙና በኪነ-ጥበብ ዙሪያ የማያሻማ አንኳር ነጥቦችን አንስቷል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
"ልማትንና እድገትን መደገፍ ትልቅ ሀገር ወዳድነት ነው። ብዙ ጊዜ መቃወም ብቻ ሀገር ወዳድነት ተደርጎ መታሰቡ ስህተት ነው።"
"ክቡር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን የምደግፈው ሀገሬን እያሳደጉ ስለሆነ ነው። እኔ ስለደገፍኩ የሚደረግልኝ ነገር የለም፤ ብሔራዊ ግዴታዬ ነው።"
"ዜና እና ዜማ መለየት አለበት። ለትችት ብቻ ግጥምና ዜማ ሰርቶ ስቱዲዮ መግባት ዜና እንጂ ጥበብ አይደለም፤ ጥበብ መፍትሄን መጠቆም አለበት።"
"አርቲስቱ መብቴ አልተከበረም ብሎ ከመጮህ ይልቅ ወደ መንግስት ጠጋ ብሎ መብቱን መጠየቅና ምን ላግዝ ብሎ መጠየቅ አለበት።"
"ተቺዎች ቢተቹኝም ግድ አይሰጠኝም፤ ለሙዚቃና ለአርት እድገት መስራቴን እቀጥላለሁ።"
ኢትዮጵያን በኪን (በጥበብ) በዓለም ህዝብ ዘንድ ታላቅ መሆኗን አስመስክረናል!
https://youtu.be/hTo3GqMrA...
#getu #kamuzukassa #ethiopianart #artplus #prosperityparty #ethiopianmusic #patriotism #abiyahmed #musicindustry #ethiopia #ካሙዙካሳ #ብልፅግና #ኢትዮጵያ #ጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

“ፍሬው” የተሰኘ አዲስ ቲያትር ለእይታ ሊቀርብ ነው
#ethiopia | በተሻለ ወርቁ ተደርሶና ተዘጋጅቶ የቀረበው አዲሱ “ፍሬው” የተሰኘ ቲያትር የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ፍላሚንጎ በሚገኘው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት በድምቀት ይመረቃል።
በናታይ ጌታቸው እና በሞሪያድ ኢቨንት ፕሮዲውሰርነት የቀረበው ይህ ተውኔት አንጋፋዎቹን ተሻለ ወርቁንና ካሳሁን ፍስሃን (ማንዴላ) ጨምሮ ሰለሞን ሙሄ፣ ናታይ ጌታቸው፣ የምስራች ግርማ እና ህሊና ደረጄን የመሰሉ ተወዳጅ ተዋናዮችን በአንድ መድረክ ያሳያል።
ቲያትሩ ከመዝናኛነት ባለፈ የላቀ የጥበብ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑን የገለጹት አዘጋጆቹ ታዳሚዎች ትኬቶችን በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች፣ በግራንድ ኩዳ፣ በባኮስ ላውንጅ፣ በባልደራስ ስፖርት ባር ወይም በዕለቱ በበሩ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ferew #newplay #addisababatheater #ethiopianart #comedyshow #weekendvibes

7 months ago
ባሕርዳር ለአንጋፋው የጥበብ ሰው ግዮን ዓለምሰገድ የክብር እውቅና ሰጠች
#ethiopia | በኢትዮጵያ የቲያትርና የፊልም ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፈውና በትውልድ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለው አንጋፋው ተዋናይ ግዮን ዓለምሰገድ በባሕርዳር ከተማ ደማቅ የክብርና የእውቅና ተሰጥቷል።
በውቧ የጣና ዳርቻ ከተማ በተከናወነው በዚህ የክብር መርሀግብር ላይ በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ወዳጅ ቤተሰብ በተገኙበት ለከያኒው የሚገባውን አክብሮት ተሰጥቷል።
አንጋፋው ባለቅኔና ደራሲ ጌትነት እንየው ለግዮን ዓለምሰገድ የክብር ካባ በማልበስ ለጥበብ የከፈለውን የሕይወት ዘመን መስዋዕትነት ዘክሯል።
ግዮን ዓለምሰገድ በመድረክ ላይ ያለውን ገጸ-ባህሪ በሕይወት የመሳል፣ የድምፅ አጠቃቀምና የሰውነት እንቅስቃሴን በተመጣጣኝ ሁኔታ የማዋሃድ ልዩ ክህሎቱ የሚታወቅ ሲሆን ከትወና ባለፈም ለወጣት ባለሙያዎች መንገድ አሳይና አስተማሪ በመሆን የዘርፉን ዕድገት ሲደግፍ የቆየ የጥበብ አውራ ነው።
ይህ በባሕርዳር ከተማ የተዘጋጀው የምስጋና መርሃ-ግብር እንዲሳካ ስንታየሁ ገብሩ፣ አበባው ደረበ ፣ ቻሌ ማረው ፣ ደሳለኝ ድረስ እና ሌሎች የጥበብ ጓደኞቹ ከባሕርዳር ጥበብ አፍቃሪዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ "እንኳን ደስ አለህ" በማለት የማይተካና የማይደፈር የሙያ አበርክቶት እንዳለው ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ አይነቱ በሕይወት እያሉ የመከበር ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#gionalemseged #bahirdar #ethiopiantheatre #artrecognition #getnetenyew #ethiopianart #tana #lifetimeachievement #cinemaethiopia #culturalheritage

የጨዋታው ጌታ፣ የጥበብ ሰው ተመስጌን ባዲሶ አረፈ 🕯️
#ethiopia | የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ አድማስ በልዩ ጨዋታ አዋቂነቱ ሲያስውብ፣ በደግነቱና በክህሎቱ የብዙዎችን ልብ ሲያሸንፍ የቆየው ታዋቂው አርቲስት ተመስጌን ባዲሶ፣ ከቆየበት ሕመም በኋላ ዛሬ ሌሊት በአውቶብስ ተራ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የታሪክ ንጉሥ፦
ድርጊቶችንና ትዝታዎችን በንግግር የመሳል (Storytelling) ልዩ ተሰጥኦ የነበረው፣ ተመልካችንና አድማጭን የመቆጣጠር ታላቅ ኃይል ያለው ባለሙያ ነበር።
ጽናትና ጥንካሬ፦
በሕመሙ ወቅት እንኳ ሳይበገር፣ ለጥበብ ባለው ፍቅርና በጠንካራ መንፈስ ለብዙዎች አርአያ ሆኖ ቆይቷል።
ተወዳጅነት፦
ከሙያ አጋሮቹ አልፎ ከሰፊው ሕዝብ ጋር በቀላል ተግባቦትና በደግነት የተቆራኘ የሕዝብ ሰው ነበር።
🕊️ "የጥበብ ሰው አይሞትም!"
ተመስጌን ባዲሶ ቢለየንም፣ ያሳረፋቸው የኪነ-ጥበብ አሻራዎችና በሰዎች ልብ ውስጥ የዘራቸው ጣፋጭ ትዝታዎች ሁሌም ሲዘክሩት ይኖራሉ። ጥበብ የሞትን ድልድይ የምትሻገር ሕያው ሀብት ናትና ተመስጌን በስራዎቹ ህያው ነው።
ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ አጋሮቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጣሪ መጽናናትን ይስጥልን።
ነፍስ ይማር! 😭
#ተመስጌንባዲሶ #ጥበብ #ኢትዮጵያ #ለቅሶ #አርቲስት #temesgenbadisso #ethiopianart #storytelling #rip #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago
🎭 የአንጋፋው አርቲስት ግዮን ዓለምሰገድ የክብር ምሽት! 🌟
#ethiopia | ከ"ፍቅር መጨረሻ" እስከ "ገዳይ"፤ ከመድረክ ቴአትር እስከ ቴሌቪዥን መስኮት... በገጸ-ባህሪያት ውስጥ ሕይወት እየዘራ ጥበብን ያከበረው ጉምቱው ባለሙያ አርቲስት ግዮን ዓለምሰገድ ሊመሰገን ነው!
ብዙዎች "የሞተ ገጸ-ባህሪ ቢሰጡትም ከሞት ቀስቅሶ አላዘር ያደርገዋል" የሚሉለት ይህ ድንቅ ተዋናይ፣ ለሀገራችን ጥበብ ላበረከተው ድንቅ አስተዋጽኦ የሚገባውን ክብርና ምስጋና ይቸረው ዘንድ የጥበብ ወዳጆቹና ጓዶቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በዕለቱ ምን ይጠበቃል?
🎬 ዘጋቢ ፊልም፦
ከታላቁ ጌትነት እንየው እስከ ሱራፌል ተካ ምስክርነት የተሰጠበትና የአርቲስቱን የሕይወትና የጥበብ ጉዞ የሚዘክር ድንቅ ፊልም ይቀርባል።
🏆 የክብር ሽልማት፦
ለአርቲስቱ የሥራ አሻራ እውቅና የሚሰጥ የክብር ሽልማት ይበረከታል።
🎁 የስጦታ መርሐ-ግብር፦
ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ያላችሁ ወዳጆቹ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ስጦታችሁን በማበርከት ምስጋናችሁን መግለጽ ትችላላችሁ።
የዝግጅቱ ዝርዝር፦
📅 እሁድ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 ዩኒሰን ሆቴል (Unison Hotel)
🕒 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ
ለበለጠ መረጃና ስጦታ ለማበርከት የኮሚቴ አባላትን ያነጋግሩ፦
📞 ስንታየሁ ገብሩ፡ 0910206765
📞 አበባው ደረበ (ኒቆ)፡ 0913504087
📞 ደሳለኝ ድረስ (መረዋ)፡ 0912491788
📞 ቻሌ ማረው (ቻቻ)፡ 0918766188
ኑ!
የአስከበሩንን እናክብር፤ የሰሩልንን እናመስግን።
#gyionalemseged #ethiopianart #theatre #cinema #recognition #ethiopia #artisthonor #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
🏅 የ43 ዓመታት የጥበብ እና የሚዲያ ባለውለታ ተፈሪ ዓለሙ ተከበረ! 👏
* "ብሬማን ፕሮዳክሽን ለጋዜጠኛ እና አርቲስት ተፈሪ ዓለሙ ካባ ደረበለት"
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ እና የሚዲያ መድረክ ላለፉት 43 ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ያገለገለው ተፈሪ ዓለሙ፤ በብሬማን ፕሮዳክሽን ልዩ የክብር እውቅና እና ካባ ተበርክቶለታል።
ተፈሪ ዓለሙ ማነው?
📻 ሚዲያ: የሸገር 102.1 ሬዲዮን የዛሬ 18 ዓመት ከመሠረቱት አውራዎች አንዱ።
🎭 ኪነ-ጥበብ: በሀገር ፍቅር ቴአትር በስራ አስኪያጅነት የመራ፣ በርካታ ቴአትሮችን የፃፈ እና የተወነ የጥበብ ሰው።
🤝 አርአያነት: ወጣቶችን በማበረታታት እና በጎነትን በማስተማር ለብዙዎች መምህር የሆነ ባለሙያ።
ልዩ ዝግጅት በፋና ፕላስ:
ይህንን ታላቅ ሰው የሚዘክረው፣ ምስክርነቶች እና ሙዚቃዊ ዝግጅቶች የተካተቱበት ልዩ ፕሮግራም፤ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በፋና ፕላስ (Fana Plus) ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ይተላለፋል።
ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ታላቅነት ነው!
እንኳን ደስ አለህ!
ለተጨማሪ መረጃ፡ https://tewedajewikipedia....
#teferialemu #legend #ethiopianart #shegerfm #bremanproduction #recognition #fanaplus

🎨 "ትስስር" - ከቨርጂኒያ ወደ አዲስ አበባ
የ3 ትውልድ ቀለማት በ"አዲስ የሲኒማ ማዕከል"
#ethiopia | በአንጋፋው ሰዓሊ ልዑል ሰገድ ረታ አስተባባሪነት፤ ባለፈው ነሐሴ ወር በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ቀርቦ አድናቆትን ያገኘው "ትስስር" (Connection) የተሰኘው የሥነ-ጥበብ ኤግዚቢሽን አሁን በቤታችን አዲስ አበባ ለእይታ በቅቷል!
የሦስት ትውልድ ውህደት!
ይህ አውደ ራዕይ የተለያዩ የአሳሳል ጥበቦችን እና የዘመናት ተሞክሮዎችን ያቀናጁ 6 ምርጥ ኢትዮጵያውያን ሰዓሊያንን ስራዎች በአንድነት ይዞ ቀርቧል፦
አንጋፋው ሰዓሊ ልዑል ሰገድ ረታ
ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ
ሰዓሊ ስዩም አያሌው
ሰዓሊ ዑስማን ሀሰን
ሰዓሊ ታምራት ስልጣን
ሰዓሊ ያሬድ ኦሌቪሊ
📍 ቦታ: ሰንጋተራ በሚገኘው አዲሱ የሲኒማ ማዕከል ጋለሪ
📅 ቀን: ከጥር 7 እስከ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ለአንድ ወር)
የቀለማትን ውህደት እና የጥበብን ጥልቀት ለማድነቅ እርሶም ተጋብዘዋል! በስራ ሰዓት ጎራ ይበሉ።
#tisisir #artexhibition #ethiopianart #addiscinemacenter #lulsegedretta #fineart #addisababa

🎨 የኪነ-ጥበብ መንደር በታሪካዊቷ ጎንደር! 🏰
#ethiopia | "ጎንደርን የኪነ-ጥበብ መናገሻ የሚያደርግ የጥናት ስራ ተጀምሯል።"
የ«ኪን-ኢትዮጵያ» የጥበብ እና የባህል መድረክ የመጀመሪያ ሀገር አቀፍ ጉዞውን በጎንደር ከተማ ባደረገበት ወቅት አንድ ትልቅ ብስራት ተሰምቷል።
ምን ተባለ?
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለጹት፤ ከተማዋ ያላትን የኪነ-ጥበብ አቅም ለመጠቀም እና ለባለሙያዎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር "ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ መንደር" ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተላለፉ ቁልፍ መልዕክቶች፡-
✅ ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ: "ኪነ-ጥበብ የአንድነታችን ማገር ነው" ሲሉ የጎንደር ህዝብ ላደረገው ኢትዮጵያዊ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።
✅ አቶ መልካሙ ጸጋዬ: በክልሉ ነጠላ ትርክቶችን በማክሰም አሰባሳቢ ትርክትን ለመፍጠር ኪነ-ጥበብ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የኪነ-ጥበብ መንደር እውን ሲሆን ለሀገራችን ጥበብ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።
ጌትነት ተመስገን
#gonder #artvillage #ethiopianart #culture #unity #addisababa #kinethiopia #gonder #ethiopianarts

የያየህይራድ አላምረው "የንባብ ክፍል" በወመዘክር ተመረቀ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር)፣ ለሀገራችን የጥበብ ባለውለታ ያየህይራድ አላምረው መታሰቢያ የሚሆንና የእርሱን ስም የያዘ ልዩ የንባብ ክፍል በይፋ ከፍቷል። ይህ ክፍል ያየህይራድ ለዓመታት በጥንቃቄ ያሰባሰባቸውን የጥበብ ማዕድናት ለትውልድ ማስተላለፊያ ይሆናል።
🔍 ስለ ንባብ ክፍሉ ቁልፍ መረጃዎች፦
የስብስቡ ብዛት፦ ከ5,000 በላይ መጻሕፍት፣ ጋዜጦች፣ የጽሑፍ እና የሙዚቃ ኅትመት ውጤቶችን ይዟል።
ልዩነቱ፦ እነዚህ ስብስቦች ያየህይራድ በሕይወት ዘመኑ በከፍተኛ ፍቅር ያሰባሰባቸው እና እስከ ሕልፈቱ (ታኅሣሥ 24/2017) ድረስ የጥበብ ስራዎቹን ሲያበለጽግባቸው የነበሩ ብርቅዬ ሀብቶች ናቸው።
ታሪካዊ ስጦታ፦ ወመዘክር በ1936 ዓ.ም ሲመሰረት የነበረው የመተዳደሪያ ደንብ በያየህይራድ እጅ ተጠብቆ ቆይቶ፣ በእህቱ አማካኝነት ለተቋሙ በስጦታ ተመልሷል።
🎙 የታዋቂ ሰዎች ምስክርነት
አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት (ዋና ዳይሬክተር)፦ "ያየህይራድ የሙዚቃ ፕሮጀክቶች ነዳፊ ብቻ ሳይሆን፣ መጻሕፍትን ለማስቀመጥ ቦታ እስኪጠበው ድረስ የሚሰበስብ አስደናቂ መጽሐፍ ሰብሳቢ ነበር።"
ክቡር ጌታቸው ረዳ፦ ያየህይራድ ንባብን በቁም ነገር የሚያነብና የኢትዮጵያ የጥበብ ፈርጥ እንደነበር መስክረዋል።
ረ/ፕ ነብዩ ባዬ፦ የያየህይራድ ስራዎች ውበትና ጥልቀት ያላቸው በእውቀትና በአንባቢነቱ የታጀቡ በመሆናቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
💡 የዚህ ጅማሮ ፋይዳ ምንድነው?
ለጥናትና ምርምር፦ የሙዚቃ እና የስነ-ጽሑፍ ተመራማሪዎች ያየህይራድ ለፈጠራ ስራዎቹ የተጠቀመባቸውን ጥሬ ግብዓቶች በቀላሉ እንዲያገኙ ይረዳል።
ለታሪክ ማስታወሻ፦ የጥበብ ሰዎችን አሻራ በሕይወት ዘመናቸው ከሰበሰቧቸው መጻሕፍት ጋር በማስተሳሰር ለትውልድ ማስተላለፍ ያስችላል።
አርአያነት፦ አንድ ስኬታማ የጥበብ ሰው ከስራው ጀርባ ያለውን የንባብ ልምድ ለወጣቱ ትውልድ ትምህርት ይሰጣል።
ውድ የጥበብ ቤተሰቦች፦ የወመዘክር ይህ እርምጃ ሌሎች የጥበብ ሰዎችም ስብስቦቻቸውን ለሕዝብ ተደራሽ እንዲያደርጉ በር ይከፍት ይሆን? የያየህይራድን ስራዎች ይበልጥ ለማወቅ የእርሱን የንባብ ክፍል መጎብኘት አይዘንጉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #yayehiradalamrew #wemezekir #readingculture #ethiopianart #musichistory #libraryethiopia #literature #nationalarchive

Comments