Logo
Getu Temesgen
ባሕርዳር : ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር የሚያስተሳስር የመንገድ ግንባታ አየተገነባ ነው
#ethiopia | የባሕርዳር ከተማ አስተዳድር የኮሪደርና የጣናዳር ልማት አካል የሆነው ከአማራ ልማት ማህበር እስከ ዋተርፍሮንት ሆቴል አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የመንገድ ግንባታ ሂደቱ የከተማው የመንግስት አመራሮች በተጎበኘበት ወቅት እንደተገለጸው መንገዱ ለነዋሪዎች ዘመናዊ እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር በማስተሳሰር ተጨማሪ ውበት እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳላማው ጎሹ በጉብኝት መርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት "የመንገዱ ግንባታው የመኪና፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የግሪነሪ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን የመብራት፣ የቴሌ፣ የውሀ መስመሮች በዘላቂነት በመሰረተ ልማት ስራው ተቀናጅተው መሠራቱን ገልጸዋል።

በሬማ ጀኔራል ቢዝነስና ኮንስትራክሽን አማካኝነት ከአልማ ዋተርፍሮንት ሆቴል እየተነባ የሚገኘው ዘመናዊ መንገድ በቅድመ ክፍያ ብቻ አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አቤኔዘር ማስረሻ ገልጸዋል።

‎ይህ መንገድ በመሠራቱ የአካባቢው ነዋሪ እጅግ ደስተኛ በመሆኑ የባህርዳር ከተማ አመራሮችንና ሬማ ኮንስትራክሽንን እያመሠገነ እንደሚገኝ አቶ አቤኔዘር ገልጸዋል።

‎የአስፓልት ስራው የ3 ወር እቅድ ቢሆንም በመሀል የነበረው የክረምት ሁኔታ ተጨማሪ ቀናቶችን ቢወስድም በአድቫንስ ብቻ በአጭር ጊዜ መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቅቅ በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮንክሪት አስፓልት መንገዱ 8 መቶ ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይህ አስፓልት በፍጥነትና በቅድመ ክፍያ ብቻ እየተሰራ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤትና መሥራች አቶ ፍቅሬ አስፋው ተናግረዋል።

በጉብኝቱ መርሐግብር ላይ አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ፣ አቶ ሞላ ሁሴን የባሕርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ አቶ አስሜ ብርሌ የባሕርዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ በቦታው ተገኝተዋል።



6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.