16 hours ago
9 days ago
“12ኛ ተጫዋች ለመሆን ተዘጋጅተናል” – የባህር ዳር ነዋሪዎች
#ethiopia | ባህር ዳር ከ5 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨዋታ ታስተናግዳለች።
የጣናዋ ሙሽራ ባህር ዳር የዋልያዎቹ የድል ቦታ በመሆኗ ትታወቃለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በከተማዋ በሚገኝበት ወቅትም ባህር ዳር የፌስቲቫል ዓይነት ድባብ ይኖራታል።
ይህ ስሜትም ከጨዋታው ዋዜማ ጀምሮ በከተማዋ ታይቷል። በኮሪደር ልማቷ የከተማዋን ውበት ካሳደጉት ዘንባባዎች እስከ ጎዳናዎቿ ድረስ የዋልያዎቹ ደጋፊነት የሚያሳይ ድባብ ተፈጥሯል።
በየአቅጣጫው በእግራቸው የሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች የጨዋታውን ድባብ ያደምቃሉ። አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማትን የያዙ ቁሳቁሶችና የብሔራዊ ቡድኑ መለያዎችን የለበሱ ደጋፊዎችም በከተማዋ ተስተውለዋል።
ያነጋገርናቸው የባህር ዳር ነዋሪዎችም በስታዲየም ተገኝተው ዋልያዎቹን ለማበረታታት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
“በስታዲየም ተገኝተን እናበረታታለን፤ እንደ 12ኛ ተጫዋች ለቡድናችን ኃይል ለመሆን ዝግጁ ነን” ሲሉም ተናግረዋል።
ዋልያዎቹን በሜዳ ተገኝተው ማበረታታት የለመዱት ደጋፊዎች፣ ብሔራዊ ቡድኑ ከሴኔጋል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ እስከመጨረሻው ድረስ ድጋፋቸውን እንደማይቆጥቡ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ስታዲየም ካደረጋቸው 8 የነጥብ ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ መሸነፉ የስታዲየሙን ታሪክ የበለጠ ልዩ ያደርገዋል። በተለይም አፍሪካ ላይ ከሚታወቁ ቡድኖች አንዱ የሆነውን አይቮሪኮስትን 2 ለ1 ያሸነፈበት ጨዋታ ከማይዘነጉ የባህር ዳር ስታዲየም ድሎች መካከል ይጠቀሳል።
ዛሬ ደግሞ ዋልያዎቹ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንን ይገጥማሉ። በማለዳውም በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ጨዋታውን ለመታደም በባህር ዳር ስታዲየም መግቢያ በሮች ላይ ተሰልፈዋል።
በሜዳ ላይ የሚደረገው የዋልያዎቹ ፍልሚያ ዋነኛ ቢሆንም፣ የባህር ዳር ደጋፊዎችም በድምፃቸውና በድጋፋቸው ስታዲየሙን ለሴኔጋል ቡድን አስቸጋሪ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሀብታሙ ካሴ
#ethiopia #bahirdar #afcon #senegal #matchday #football #sports #ebc #ethiopia #bahirdar #afcon #senegal #walias #matchday #football #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

18 days ago
ማንቸስተር ዩናይትድና ፉልሃም 1-1 ተለያዩ
#ethiopia | በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1-1 አቻ ተለያይቷል።
በክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ፣ ፉልሃም በ63ኛው ደቂቃ በማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ መረብ ላይ በተቆጠረች ግብ መሪነቱን ወስዷል።
ዩናይትድ ግን ጨዋታው ወደ መገባደጃው ሲደርስ በ89ኛው ደቂቃ ማቲያስ ኩኛ ባስቆጠራት ግብ ውጤቱን አመጣጥኗል።
ይህ ውጤት ማንቸስተር ዩናይትድ በአምስት የሊግ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ሁለተኛው አቻ ውጤት ሲሆን፣ ቡድኑ በ5 ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፉልሃም በበኩሉ በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ አቻ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን፣ በ1 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
#epl #premierleague #manchesterunited #fulham #matchday #football #sports #ebc

23 days ago
በእንግሊዝ ካራባዎ ካፕ አርሰናል እና ሊቨርፑል ወደ 4ኛው ዙር ሲያልፉ፣ ቶተንሃም ከውድድሩ ተሰናበተ
************************
በእንግሊዝ ካራባዎ ካፕ 3ኛ ዙር ወደ ፖርትማን ሮድ አቅንቶ ኢፕስዊች ታውንን የገጠመው አርሰናል 4 ለ 2 አሸንፎ ተከታዩን ዙር ተቀላቅሏል።
የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ማክስ ዶውማን(ሁለት)፣ ኑኖ ማዱዊኬ እና ሚኬል ሜሪኖ አስቆጥረዋል።
ኢስዊች ታውንን ከሽንፈት ያልታደጉትን ግቦች ከመረብ ያሳረፉት ደግሞ አኒስ መህመቲ እና ቹባ አፕኮም ናቸው።
በሌላ የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ በአንፊልድ ቶተንሃምን ያስተናገደው ሊቨርፑል 3 ለ 1 በማሸነፍ ሌላኛው 4ኛውን ዙር የተቀላቀለ ቡድን ሆኗል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሲስ ማካሊስተር፣ ኮዲ ጋክፖ እና ዶሚኒክ ሶቦዝላይ ከመረብ አሳርፈዋል። ለቶተንሃም ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ደግሞ ኮነር ጋላገር ነው።
በሌሎች ጨዋተዎች ፉልሃም ዌስትሃምን 3 ለ 2፣ ፒተርቦሮ በርንስሌይን በመለያ ምት 7 ለ 6 እንዲሁም ብሬንትፎርድ ሬዲንግን 2 ለ 1 በመርታት ወደ 4ኛው ዙር ያለፉ ቡድኖች ሆነዋል።
#eflcup #carabaocup #arsenal #ipswich #liverpool #tottenham #matchday #football #sports #ebc

Sponsored by
Surafel
25 days ago
199ኛው የማንቹሪያን ደርቢ - ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ማንቸስተር ሲቲ
************************
በእንግሊዝ እግር ኳስ ካሉ የደርቢ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው፣ በቅርብ ዓመታት በማንቸስተር ሲቲ ተደጋጋሚ ውጤታማነት እና በማንቸስተር ዩናይትድ ከሊጉ ኃያልነት ማፈግፈግ የተለየ መልክ እየያዘ የመጣው የከተማ ተቀናቃኞቹ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 12፡30 በኦልድ ትራፎርድ ይደረጋል።
ባለፈው የውድድር ዓመት ጥር ወር ላይ ማንቸስተር ዩናይትድ ያጋጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ተከትሎ የተሰናበቱትን ሩበን አሞሪምን በመተካት ጊዜያዊ አሰልጣኝነቱን የተረከበው ማይክል ካሪክ፣ ቡድኑን ወደ አውሮፓ መድረክ የመለሰውን ውጤታማ መንገድ የጀመረው በዚሁ የደርቢ ጨዋታ በሙሉ የበላይነት 2 ለ 0 በማሸነፍ ነበር። ይኸው ከ33 ወራት በኋላ ወደ አውሮፓ መድረክ የመለሳቸው መንገድ፣ ባሳለፍነው ሐሙስ በአዘርባጃኑ ሳባህ ላይ ባገኙት የ4 ለ 0 ድል ጀምሯል።
የሦስቱ ሳምንታት የፕሪሚየር ሊግ ቆይታው ግን በውጤት ረገድ ወጥነት የጎደለው ነበር። በደረጃ ሰንጠረዡ አራት ነጥብ በመያዝ 11ኛ ላይ ነው የተቀመጠው። ይህ ውጤት ግን የግብ ዕድሎችን በመፍጠር ከሁሉም የሊጉ ክለቦች ልቆ እንዲቀመጥ ያደረገውን ቁጥራዊ መረጃ የሚገልፅ አይደለም። በሦስቱ ሳምንታት ጨዋታዎች 68 የግብ እድሎችን ሲፈጥር፣ ከነዛ ውስጥ 19 የሚሆኑት ዒላማቸውን የጠበቁ ናቸው።
በአዲሱ የውድድር ዓመት ሦስቱንም የመጀመሪያ ጨዋታዎች ያሸነፉት ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል ብቻ ናቸው። ሲቲዎች በመጀመሪያው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታቸውም ወደ ፖርቹጋል ተጉዘው ፖርቶን 2 ለ 0 የረቱበት ሌላኛው ለዚህ ጨዋታ ስንቅ የሚሆናቸው ውጤት ነው።
እያንዳንዳቸው ሦስት ግቦች ያስቆጠሩት ኤርሊንግ ሃላንድ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዚህ ጨዋታም በልዩነት ፈጣሪነት ከሚጠበቁ ተጫዋቾች ቀዳሚዎቹ ናቸው። በተለይ ኤርሊንግ ሃላንድ በ8 ግቦች ከሙሐመድ ሳላህና አለን ሺረር በመቀጠል ዩናይትድ ላይ በርካታ ግብ ያስቆጠረ ሦስተኛው ተጫዋች ነው።
በዩናይትድ የፊት መስመር በተከታታይ ግብ ካስቆጠረው ቤንጃሚን ሼሽኮ በተጨማሪ፣ ብሪያን እምቡሞ እና በዩናይትድም በአስቶንቪላም መለያ ሲቲ ላይ ግብ የማስቆጠር ልምድ ያለው ማርከስ ራሽፎርድ ሌላኛዎቹ የልዩነት ምንጭ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው።
ማንቸስተር ዩናይትድ በቅርቦቹ የማንቹሪያን ደርቢ ጨዋታዎች የበላይነት አለው። ካለፉት አራት ጨዋታዎች በሁለቱ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ ወጥቷል።
አማድ ዲያሎ፣ ካርሎስ ባሌባ እና ማኑኤል ኡጋርቴ ጉዳት ከማንቸስተር ዩናይትድ ስብስብ ውጪ ያደረጋቸው ተጫዋቾች ሲሆኑ፣ የሉክ ሾውም ለጨዋታው ብቁ መሆን ገና አልተረጋገጠም። በሲቲ በኩል ኒኮ ኦራይሊ ለጨዋታው ብቁ እንደሆነ፣ ጄረሚ ዶኩ ግን ተጨማሪ የማገገሚያ ጊዜ እንደሚያስፈልገው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ተናግረዋል።
የኤርሊንግ ሃላንድ እና ፊል ፎደን ሁለት ሃትሪኮች ማንቸስተር ሲቲን 6 ለ 3 አሸናፊ ያደረጉበት፣ የማሪዮ ባሎቴሊ ትዕይንት፣ በ2009 የማይክል ኦውን የሽርፍራፊ ሴኮንዶች ድራማ፣ የዌይን ሩኒ የመቀስ ምት ግብ እና ሌሎችም ብዙ ትዝታዎች ያሉት ማንቹሪያን ደርቢ ዛሬም ሌላ የታሪክ አጋጣሚን ይዞ እንደሚመለስ ይጠበቃል።
ቀን 10፡00 ሰዓት በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ 20ኛ ላይ የሚገኘው አዲስ አዳጊው ኮቨንትሪ ሲቲ ከብራይተን የሚያደርጉትም ከ4ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ማጠቃለያ ጨዋታዎች አንዱ ነው።
#epl #premierleague #manchesterunited #manchestercityfc #matchday #football #sports #ebc

26 days ago
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል አራተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
*********************
በአራተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ስታዲየም ኦፍ ላይት አቅንቶ ሰንደርላንድን የገጠመው አርሰናል 2 ለ 0 በማሸነፍ አራተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
የአርሰናልን ግቦች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከኒውካስል ቡድኑን የተቀላቀለው ብሩኖ ጊማሬሽ 58ኛው ደቂቃ እንዲሁም ቡካዮ ሳካ 90+7 ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎም 12 ነጥብ የሰበሰበው አርሰናል ነገ ጨዋታውን የሚያደርገውን ማንቸስተር ሲቲን በመብለጥ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀምሯል።
#epl #premierleague #arsenal #sunderland #matchday #football #sports #ebc

28 days ago
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ ሳባህን 4 ለ 0 አሸነፈ
*********************
በ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ሦስተኛ ቀን በኦልድ ትራፎርድ የአዘርባጃኑን ሳባህ ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ከ2023 የውድድር ዓመት ወዲህ፣ ከ33 ወራት ቆይታ በኋላ የመጀመሪያ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን ላደረገው ማንቸስተር ዩናይትድ የማሸነፊያዎቹን ግቦች ማቲያስ ኩኛ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ቤንጃሚን ሼሽኮ በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥሩ፤ በሁለተኛው አጋማሽ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
ባየር ሙኒክ የኖርዌዩን ቦዶ ግሊምት አስተናግዶ በጀማል ሙሲያላ፣ ሃሪ ኬን፣ አልፎንሶ ዴቪስ እና ማይክል ኦሊሴ(2) ግቦች 5 ለ 0 አሸንፏል።
የመጀመሪያ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኘው፣ በሴስክ ፋብሪጋስ የሚመራው የጣሊያኑ ኮሞ የጀርመኑን አርቢ ሌይፕዢግን 4 ለ 1 ረቷል።
የስሎቫኪያው ክለብ ስላቪያ ፕራግ በፈረንሳዩ ሌንስ 3 ለ 2 የተረታበት ሌላኛው ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀ መርሐ-ግብር ነው።
ቀደም ብለው ፌነርባቼ ከ ሮማ እንዲሁም ሻካታር ዶኔስክ ከ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ያደረጓቸው ጨዋታዎች በተመሳሳይ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል።
#uefa #uefachampionsleague #manchesterunited #bayernmunich #sabahfk #asroma #como1907 #matchday #football #sports #ebc

30 days ago
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሪያል ማድሪድ ኢንተር ሚላንን 2 ለ 1 አሸነፈ
********************
በ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ቀን ሪያል ማድሪድን ከኢንተር ሚላን ያገናኘው ተጠባቂው የሳንቲያጎ በርናባዎ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለሪያል ማድሪድ ግቦቹን በመጀመሪው አጋማሽ 14ኛው ደቂቃ ላይ ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም 23ኛው ደቂቃ ላይ ፌደሪኮ ቬልቫርዴ አስቆጥረዋል።
ለኢንተር ሚላን ብቸኛዋን ግብ በሁለተኛው አጋማሽ 77ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ካርሎስ አውጉስቶ ነው።
ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ በቀደመው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 15 ግቦች በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው ኪሊያን ምባፔ የወርቅ ጫማ ሽልማቱን ከቀድሞ ፖርቹጋላዊ ኮከብ ሉዊስ ፊጎ እጅ ተቀብሏል።
በሌላ ጨዋታ ማንቸሰተር ሲቲ ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ በኤርሊንግ ሀላንድ ግቦች ፖርቶን 2 ለ 0 አሸንፏል። ግቦቹ ለሃላንድ በ59 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ያስቆጠራቸው 58ኛ እና 59ኛ ሆነው ተመዝግበዋል።
ሪያል ቤቲስ ሊልን 3 ለ 2 ያሸነፈበት እንዲሁም ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ቪያሪያልን 3 ለ 1 የረታበት ሌሎች የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ቀን መርሐ ግብሮች ናቸው።
#ucl #uefachampionsleague #uefa #realmadrid #intermilanfc #manchestercityfc #porto #matchday #football #sports #ebc

2 months ago
ማንቸስተር ሲቲ ከ ቦርንመዝ እና ኒውካስል ከ ሊቨርፑል - የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች
**********************
ቀን 10:00 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ቦርንመዝን የሚገጥም ሲሆን፣ ምሽት 12:30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ በሴንት ጄምስ ፓርክ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል።
ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ከቦርንመዝ ጋር ባደረጋቸው ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሁሉንም በማሸነፍ እና 34 ግቦችን በማስቆጠር ፍጹም የበላይነት አለው።
አዲሱ የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፣ ቡድኑ ባለፉት 15 የውድድር ዓመታት ውስጥ በ14ቱ የመክፈቻ ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።
ሮድሪን ለባርሴሎና አሳልፎ የሰጠው ማንቸስተር ሲቲ ፣ በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የጄረሚ ዶኩን ግልጋሎት እንደማያገኙ ታውቋል።
በነሐሴ ወር ባደረጋቸው 14 ጨዋታዎች 22 ግቦችን ያስቆጠረው የሊጉ ኪከብ ግብ አስቆጣሪ ኤርሊንግ ሃላንድ በዛሬው ጨዋታ ላይም ልዩነት ፈጣሪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በአዲሱ አሰልጣኝ ማርኮ ሮዝ የሚመራው ቦርንመዝ፣ ካለፈው የውድድር ዓመት መጨረሻ ጀምሮ የያዘውን የ18 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ለማስቀጠል ወደ ኢትሃድ ያመራል። በተመሳሳይ ሰዓት ብራይተን በአሜክስ ስታዲየም ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታል፡፡
በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ካለፉት 19 የሊግ ግንኙነቶቹ አንድም ጊዜ ያላሸነፈውን ሊቨርፑልን ይገጥማል።
ሁለቱም ክለቦች በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ውጤታማ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሊቨርፑል ባለፉት 13 ዓመታት፣ ኒውካስል ደግሞ ባለፉት አራት ዓመታት በመክፈቻ ጨዋታ ተሸንፈው አያውቁም።
ይህ ጨዋታ በሁለቱም ክለብ በአዳዲስ አሰልጣኞችና የቡድን ስብስብ የሚደረግ በመሆኑ ልዩ ትኩረትን ስቧል። ኒውካስል ዩናይትድ በዚህ ክረምት እንደ አንቶኒ ጎርደን፣ ሳንድሮ ቶናሊ እና ብሩኖ ጊማሬሽ ያሉ ኮከቦቹን ከ200 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በሆነ ዋጋ የሸጠ ሲሆን፣ አዲሱ አሰልጣኝ ማትያስ ያይስለ ቡድኑን መልሶ የመገንባት ከባድ ኃላፊነት ወድቆባቸዋል።
እስካሁን በሁለቱ ቡድኖች ግንኙነት 198 ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን፣ ዛሬ በጨዋታው ሁለት ግቦች ከተቆጠሩ በሊጉ ታሪክ 200 ግቦች የተመዘገቡበት ሦስተኛው መርሐ-ግብር ይሆናል።
በዘረንቶስ ሰለሞን
#premierleague #epl #manchestercityfc #liverpool #newcastle #bournemouth #matchday #football #ebcdotstream

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሀል ሲቲ - የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ቀን ተጠባቂ ጨዋታ
***********************
ማንቸስተር ዩናይትድ 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ካስገኙለት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስንብት በኋላ፤ ከዋንጫው የራቀባቸውን 13 ዓመታት ማብቂያ እንዲሆን የሚያደርገውን ሌላ ሙከራ ዛሬ 8:30 ላይ ሀል ሲቲን በመግጠም የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።
አማካይ ክፍሉን በማጠናከሩ ሂደት ላይ አተኩሮ በዝውውር መስኮቱ የተሳተፈው ዩናይትድ፣ ከቀደመው የውድድር ዓመት አጋማሽ በኋላ በማይክል ካሪክ ስር ያሳለፈውን ውጤታማ ጊዜ የማስቀጠል ውጥን ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል።
ካሪክ ዩናይትድን በመራባቸው 17 ጨዋታዎች በ12ቱ በማሸነፍ ፣ ከሁሉም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በላቀ ሁኔታ 39 ነጥብ ነው የሰበሰበው። ለዚህም ነው ሀሪ ማጓየር “በዚህ የውድድር ዓመት 21ኛ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫችንን ለማንሳት አቅደናል” የሚል ሀሳብ የሰነዘረው።
ማንቸስተር ዩናይትድ ከሀል ሲቲ ጋር በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጋቸው አስር ጨዋታዎች በስምንቱ አሸንፎ፣ በሁለት ጨዋታዎች አቻ በመውጣት ሙሉ የበላይነት አለው።
በዛሬው የኤም ኬ ኤም ስታዲየም ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ አዲስ ፈራሚዎቹን ዩሪ ቴሌማንስና አንድሬ ሳንቶስን እንደሚጠቀም ይጠበቃል።
ማቲያስ ዴሊክት በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፍ፣ ቤንጃሚን ሼሽኮ ወደ ልምምድ እንደተመለሰ እንዲሁም ሜሰን ማውንት በስብስቡ ውስጥ ሊካተት እንደሚችል አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ተናግሯል። ማርከስ ራሽፎርድም ከ18 ወራት በኋላ በሊጉ ለዩናይትድ ሊጫወት እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።
በቀደመው የውድድር ዓመት በጥቂት ርቀት ከመውረድ የተረፈውና ሳንድሮ ቶናሊን እንዲሁም ማቲየስ ፈርናንዴዝን በመሰሉ ውድ ዝውውሮች ቡድኑን ያጠናከረው ቶተንሃም ሆትስፐር ብሬንትፎርድን ምሽት 1:30 ሲል የሚገጥምበት ሌላኛው የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ-ግብር ነው።
ኤቨርተን ከ ክሪስታል ፓላስ፣ ኢፕስዊች ታውን ከ ሰንደርላንድ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ሊድስ ዩናይትድ ሌሎቹ የዛሬ የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ናቸው።
ትላንት በአርሰናል የ 3 ለ 0 ድል በተጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፤ ዛሬስ ማንቸስተር ዩናይትድና ሌሎቹ ክለቦች ምን ሊገጥማቸው ይችላል? ግምታችሁን አጋሩን።
በእድሪስ አህመድ
#premierleague #epl #manchesterunited #hullcity #sports #football #matchday #ebcdotstream

አርሰናል ከ ኮቨንትሪ ሲቲ - የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ጨዋታ
***********************
በመጀመሪያው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ሻምፒዮኑ አርሰናል አዲስ አዳጊውን ኮቨንትሪ ሲቲን በኢሚሬትስ ያስተናግዳል።
በፕሪሚየር ሊጉ ከ22 ዓመታት በኋላ ሻምፒዮን የሆነው አርሰናል ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ሁሉንም የመክፈቻ ጨዋታዎቹን በድል ጀምሯል። በተለይም መድፈኞቹ ወደ ሊጉ አዲስ ከሚመጡ ቡድኖች ጋር በሜዳቸው ባደረጓቸው ያለፉት 45 ጨዋታዎች ሽንፈት አለማስተናገዳቸው ለዛሬው ጨዋታ ትልቅ የሞራል የበላይነት ይሰጣቸዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ ምሽት በጨዋታው ቡድናቸውን ለድል ካበቁ ከፔፕ ጋርዲዮላ፣ ከጆዜ ሞሪንሆ፣ከየርገን ክሎፕ እና ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በመቀጠል በታሪክ በ249 ጨዋታዎች 150 የፕሪሚየር ሊግ ድሎችን ያስመዘገቡ አምስተኛው አሰልጣኝ በመሆን ስማቸውን በታሪክ መዝገብ ላይ ያሰፍራሉ።
በተቃራኒው እንግዶቹ ኮቨንትሪ ሲቲዎች ከ25 ዓመታት ረጅም የሊጉ ቆይታ በኋላ ወደ ታላቁ መድረክ ተመልሰዋል። ይህ ረጅም ቆይታ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ በአንድ ቡድን የተመዘገበ ከፍተኛው ጊዜ ነው።
በቀድሞ የቼልሲ ኮከብ ፍራንክ ላምፓርድ የሚመሩት ኮቨንትሪዎች፣ ምንም እንኳን በ1993 የውድድር ዘመን መክፈቻ አርሰናልን በሜዳው 3 ለ 0 ያሸነፉበት ትዝታ ቢኖራቸውም፣ ከዚያ በኋላ ባደረጓቸው 14 የሊግ ግንኙነቶች ግን ማሸነፍ የቻሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
አርሰናል ወሳኞቹን ተከላካዮች ዊሊያም ሳሊባን እና ዩሪየን ቲምበርን በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የማያገኝ ሲሆን፣ በኮቬንትሪ በኩል ደግሞ ሀጂ ራይት በተመሳሳይ ምክንያት እንደማይሰለፍ ታውቋል።
ዛሬ በሚደረገው በዚህ የመክፈቻ ጨዋታ፣ አርሰናል አሸንፎ ይወጣ ይሆን? ወይስ ኮቨንትሪ? ግምታችሁን አጋሩን።
በዘረንቶስ ሰለሞን
#arsenal #coventrycity #premierleague #epl #arteta #lampard #football #matchday #ebcdotstream

4 months ago
የኔዘርላንድ እና የጃፓን ብሄራዊ ቡድኖች በአቻ ውጤት ተለያዩ
#ethiopia | በአለም ዋንጫ የምድብ ስድስት መክፈቻ ጨዋታ የኔዘርላንድ እና የጃፓን ብሄራዊ ቡድኖች ተገናኝተው የሁለት ለሁለት አቻ ውጤት አስመዝግበዋል።
በዳላስ በተካሄደው ጨዋታ ቨርጂል ቫን ዳይክ እና ክሪሰንሲዮ ሱመርቪል የኔዘርላንድን የግብ መረቦች ማናጋት የቻሉ ሲሆን የጃፓንን የአቻነት ግቦች ደግሞ ናካሙራ እና ዲያቺ ካማዳ በጨዋታው ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ አስቆጥረዋል።
#worldcup #football #netherlands #japan #matchday #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
የሸገር ንግሥና ለቡናማዎቹ
#ethiopia | ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ረታ
መላው የአዲስ አበባ ስፖርት ቤተሰብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የሸገር ደርቢ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል።
ቡናማዎቹ በወጣት ተጫዋቾቻቸው ፈጣን እንቅስቃሴና በታክቲክ ብልጫ ፈረሰኞቹን በማስገረም የ3 ነጥብና የክብር ባለቤት ሆነዋል።
ለኢትዮጵያ ቡና ግቦቹን ያስቆጠሩ፦
ኦካይ ጁል (በእረፍት ሰዓት ቡድኑን ወደ ጨዋታው የመለሰች ወሳኝ ግብ)
ቢኒያም ጌታቸው
ዘላለም አባተ
ለቅዱስ ጊዮርጊስ፦ ፍፁም ጥላሁን ቀዳሚዋን ግብ ቢያስቆጥርም፣ የፈረሰኞቹን መሪነት ማስጠበቅ አልተቻለም።
የአዲስ አበባ ስታዲየም በቡናማና በአረንጓዴ/ቢጫ ቀለማት ደምቆ የዋለ ሲሆን፣ በተለይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በታላቅ የደስታ ስሜት ሸገርን አውርተዋታል።
ይህ ድል ለቡናማዎቹ ከ3 ነጥብ በላይ የክብርና የኩራት ምንጭ ሆኖላቸዋል።
ዛሬ ለኢትዮጵያ ስፖርት ልዩ ቀን ነው። ለንደን ላይ ዮሚፍና ትዕግስት አሰፋ ታሪክ ሲሰሩ፣ አዲስ አበባ ደግሞ በሸገር ደርቢ ሙቀት ስትቃጠል ውላለች። ኢትዮጵያ ቡና ያሳየው ቁርጠኝነትና የወጣቶቹ ብቃት የሚደንቅ ነው። ፈረሰኞቹ መሪነታቸውን ማስጠበቅ አለመቻላቸው ለደጋፊዎቻቸው ባይዋጥም፣ ለኳስ አፍቃሪው ግን ጨዋታው እጅግ አስደሳች ነበር።
ሸገር ዛሬ ቡናማ ሆና አድራለች። እንኳን ደስ አላችሁ ቡናማዎቹ!
#getu #shegerderby #ethiopiabunna #stgeorge #ethiopianpremierleague #footballethiopia #addisababa #derbyday #matchday #ኢትዮጵያቡና #ቅዱስጊዮርጊስ #የሸገርደርቢ #ድል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago
"ማንችስተር ሲቲን የማንረታበት ምክንያት የለም" ሊያም ሮሴንየር
#ethiopia | የቼልሲው አሰልጣኝ ሊያም ሮሴንየር ቡድናቸው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው ወሳኝ የሊግ ፍልሚያ በፊት ለተጋጣሚያቸው ያላቸውን አክብሮት ቢገልጹም፣ በድል ላይ ያላቸው እምነት ግን ፍጹም አልተናወጠም።
ሮሴንየር በሰጡት መግለጫ ላይ ያተኮሩባቸው ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፦
"ለፔፕ ትልቅ ክብር አለኝ፤ እሱ የማይታመንና ለሁላችንም መነሳሳት የሆነ አሰልጣኝ ነው" በማለት ለተቃራኒው ጎራ አድናቆታቸውን ችረዋል።
ምንም እንኳን ጨዋታው ከባድ ፈተና እንደሚሆን ቢገነዘቡም፣ ቡድናቸው እሁድ ዕለት በሜዳ ላይ ምን መስራት እንደሚችል ለማሳየት በጉጉት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።
አሰልጣኙ በልበ ሙሉነት "ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ እንችላለን" በማለት ለተጫዋቾቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው የድል መልእክት አስተላልፈዋል።
ከዚህ ቀደም ከሲቲ ጋር የነበራቸው ሪከርድ ለአሁኑ ጨዋታ ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ትኩረታቸው በአሁኑ 90 ደቂቃ ላይ ብቻ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ሮሴንየር እና ልጆቻቸው የፔፕን ስብስብ በመግጠም ጥንካሬያቸውን ለማሳየት ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። እሁድ የሚደረገው ጨዋታ የሮሴንየር ታክቲክ በሲቲ ላይ ይሰራ እንደሆነ የሚታይበት ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#tikvahsport #getutemesgen #getu #chelseafc #mancity #liamrosenior #premierleague #footballnews #matchday #ethiopia

7 months ago
የዛሬው የደመቀ የእግር ኳስ ምሽት! ⚽️
#ethiopia | በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረክ ተጠባቂ የሆኑ ታላላቅ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፍልሚያዎች ከሰዓት በጉጉት ሲጠበቁ፣ ምሽቱን ደግሞ የአውሮፓ ሀያላን ክለቦች እርስ በእርስ የሚፋለሙበት ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ዝርዝር፦
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
* 10:00 | አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
* 10:00 | ሀዋሳ ከተማ ከ መቐለ 70 እንደርታ
በዓለም አቀፍ መድረክ
* 2:45 | ጋላታሳራይ ከ ሊቨርፑል
* 5:00 | አታላንታ ከ ባየር ሙኒክ
* 5:00 | አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ቶተንሀም
* 5:00 | ኒውካስል ዩናይትድ ከ ባርሴሎና
ለኳስ አፍቃሪያን ድንቅ ምሽት ይሁንላችሁ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianpremierleague #football #matchday #liverpool #barcelona #bayernmunich #sportsnews #አዳማ #ሀዋሳ #የዛሬጨዋታዎች

ከሀገር ውስጥ ደርቢ እስከ አውሮፓ ክላሲኮዎች ድረስ ሜዳው ላይ እሳት የሚነድድበት ቅዳሜ ነው!
#ethiopia | ⚽️ የቤት ውስጥ ትንቅንቅ፡ የደቡብ ደርቢ
ቀኑን በሀገር ውስጥ ትልቅ ጨዋታ
እንጀምራለን። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደቡብ ድምቀት የሆኑት ሁለቱ ክለቦች ይፋለማሉ።
* 10:00 | ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ###
🏴 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፡ የነጥብ አደን
ሊቨርፑልና ማንችስተር ሲቲ የሻምፒዮንነት ግስጋሴያቸውን ለማሳመር፣ ኒውካስል ደግሞ የአውሮፓ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ ይጫወታሉ።
* 12:00 | ሊቨርፑል ከ ዌስትሀም
* 12:00 | ኒውካስል ዩናይትድ ከ ኤቨርተን
* 2:30 | ሊድስ ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ
የጀርመን 'ደር ክላሲከር' (Der Klassiker)
የዛሬው የቅዳሜ ምሽት ትልቁ ማጣፈጫ! በሲግናል ኢዱና ፓርክ ዶርትመንድና ባየር ሙኒክ የሚገናኙበት ጨዋታ የአውሮፓን ትኩረት ስቧል።
* 2:30 | ዶርትመንድ ከ ባየር ሙኒክ
ላሊጋ፣
ሴሪ አ እና
ሊግ 1
ባርሳ ወደ ድል ጎዳና ለመመለስ፣ ናፖሊና ኢንተር ደግሞ በጣሊያን የበላይነታቸውን ለማሳየት ይወጣሉ።
* 12:15 | ባርሴሎና ከ ቪያሪያል
* 2:00 | ሄላስ ቬሮና ከ ናፖሊ
* 4:45 | ኢንተር ሚላን ከ ጂኖኣ
* 5:05 | ሌ ሀቭሬ ከ ፒኤስጂ
የእርስዎ ግምትስ? በተለይ በሀገር ውስጥ ደርቢ እና የዶርትመንድ-ባየር ሙኒክ ጨዋታ በስንት በስንት ያልቃል ብለው ያስባሉ? ኮሜንት ላይ ያጋሩን!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የዛሬጨዋታ #ኳስናእኛ #ethiopianfootball #premierleague #derklassiker #laliga #seriea #matchday

8 months ago
የዛሬ ጨዋታዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የጥሎ ማለፍ ፍልሚያዎች
የአገር ውስጥ እግር ኳስ ዛሬ በታላላቅ ክለቦች ግጥሚያ ይሞቃል። በተለይ በ "አፄዎቹ" እና በ "ፈረሰኞቹ" መካከል የሚደረገው ጨዋታ የሁሉንም ትኩረት ስቧል።
* 07:00 | ወልዋሎ አዲግራት ዩ. ከ አርባምንጭ ከተማ
* 09:00 | መቐለ 70 እንደርታ ከ ኢትዮጵያ ቡና
* 10:00 | ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ተጠባቂው የሳምንቱ ጨዋታ)
* 12:00 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ነጌሌ አርሲ
🏴 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
በእንግሊዝ ሊግ ዛሬ የምሽቱ ማሳረጊያ የሚሆነው በቶተንሀም እና በማንችስተር ሲቲ መካከል የሚደረገው ፍልሚያ ነው። ፔፕ ጋርዲዮላ ወደ ሰሜን ለንደን የሚያቀኑት ወሳኝ ነጥብ ፍለጋ ነው።
* 11:00 | አስቶን ቪላ ከ ብሬንትፎርድ
* 11:00 | ማንችስተር ዪናይትድ ከ ፉልሀም
* 01:30 | ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ
ላ ሊጋ እና
ሴሪ አ
በስፔን ሪያል ማድሪድ የደረጃ ሰንጠረዡን ለመምራት ራዮን ያስተናግዳል፤ በጣሊያን ደግሞ ጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን የድል ጉዟቸውን ለመቀጠል ወደ ሜዳ ይገባሉ።
* 10:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ራዮ ቫይካኖ
* 11:00 | ኮሞ ከ አታላንታ
* 02:00 | ክሪሞኔንሴ ከ ኢንተር ሚላን
* 04:45 | ፓርማ ከ ጁቬንቱስ
መልካም የኳስ ምሽት ይሁንላችሁ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianpremierleague #premierleague #laliga #seriea #matchday #footballethiopia #realmadrid #mancity #saintgeorgesa

9 months ago
🔴 ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታውን ገለበጠው! 🔥
"ከመመራት ወደ መሪነት! በኤምሬትስ ድራማ እየተፈጠረ ነው!"
በኤምሬትስ ስታዲየም እየተደረገ በሚገኘው ተጠባቂ ጨዋታ፤ ማንችስተር ዩናይትድ በ1 ጎል ሲመራ ቆይቶ፤ አሁን በድንቅ ብቃት ጨዋታውን በማዞር 2-1 እየመራ ይገኛል።
⚽️ የለውጡ ተዋንያን:
ብሪያን ምቤሞ እና ፓትሪክ ዶርጉ የዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
ጨዋታው ቀጥሏል... አርሰናል ወደ ጨዋታው ይመለስ ይሆን ወይስ ዩናይትድ 3 ነጥብ ይዞ ይወጣል?
ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ! 👇
#arsenal #manutd #premierleague #comeback #mbeumo #dorgu #matchday #liveupdate

⚽ ከሀገር ቤት እስከ አውሮፓ ሜዳዎች
#ethiopia | ዛሬ ቅዳሜ የእግር ኳስ አፍቃሪው አይኑን ከስክሪን ላይ የማይነቅልበት ልዩ ዕለት ነው። በሜዳችንም ሆነ በባህር ማዶ የሚደረጉ ጨዋታዎች ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸዋል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የሀገር ውስጥ ሊጉ በደማቅ ፍልሚያዎች ተሞልቷል። በተለይ በ9:00 እና በ10:00 የሚደረጉት ጨዋታዎች የሊጉን መሪነትና ደረጃ ለመቀየር ትልቅ ሚና አላቸው።
* 7:00 | መቻል 🆚 ባሕርዳር ከተማ
* 9:00 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 🆚 ሀድያ ሆሳዕና
* 10:00 | ፋሲል ከነማ 🆚 ኢትዮጵያ ቡና (ተጠባቂ)
* 12:00 | ወላይታ ድቻ 🆚 ኢትዮጵያ መድን
🏴 በእንግሊዝ ሜዳዎች (ኤፍ ኤ ካፕ/ሊግ)
በእንግሊዝ ታላላቆቹ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ፣ ቶተንሀም እና ቼልሲ ወደ ሜዳ የሚገቡበት ምሽት ነው።
* 9:15 | ኤቨርተን 🆚 ሰንደርላንድ
* 12:00 | ማንችስተር ሲቲ 🆚 ኤክስተር
* 12:00 | ኒውካስል 🆚 በርንማውዝ
* 2:45 | ቶተንሀም 🆚 አስቶን ቪላ (የምሽቱ ታላቅ ጨዋታ)
* 5:00 | ቻርልተን 🆚 ቼልሲ
🌍 የአፍሪካ ኃያላን እና ጣሊያን
በአፍሪካ ምድር የሚደረጉት የሀገራት ፍጥጫዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።
* 1:00 | አልጄሪያ 🆚 ናይጄሪያ
* 2:00 | ሮማ 🆚 ሳሱሎ (ሴሪአ)
* 4:00 | ግብፅ 🆚 ኮትዲቯር (የአፍሪካ ደርቢ)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#እግርኳስ #የዛሬጨዋታዎች
#ኢትዮጵያፕሪሚየርሊግ #ማንችስተርሲቲ #ቼልሲ #ቶተንሀም #ኢትዮጵያቡና #ፋሲልከነማ #footballdaily #matchday #ethiopianpremierleague

⚽️ ታላቁ የኤምሬትስ ፍልሚያ! | አርሰናል ከ ሊቨርፑል
#ethiopia | የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቅን ለመስበር እየገሰገሰ የሚገኘው አርሰናል፤ ዛሬ ምሽት 5:00 ላይ ከሊቨርፑል ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ያደርጋል።
የጨዋታው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
ወርቃማ እድል፡ ማንችስተር ሲቲ እና አስቶን ቪላ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ፤ አርሰናል ካሸነፈ ከሲቲ ያለውን ልዩነት ወደ 8 ነጥብ፤ ከሊቨርፑል ያለውን ደግሞ ወደ 17 ነጥብ ያሰፋል።
የአርቴታ ቃል፡ “ከፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ጋር የምናደርገው ጨዋታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለን ማረጋገጫ የምንሰጥበት ነው” - ሚካኤል አርቴታ።
የቡድን ዜና፡ ካይ ሀቨርዝ ለጨዋታው ዝግጁ ሲሆን፤ ሪካርዶ ካላፊዮሪ እና ክርስቲያን ሞስኬራ በጉዳት አይሰለፉም።
የሊቨርፑል ፈተና፡ በአሰልጣኝ አርን ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል በተከላካይ መስመሩ ላይ ክፍተቶች ያሉበት ሲሆን (በ20 ጨዋታ 28 ግብ አስተናግዶ)፤ በአርሰናል የአጥቂ መስመር እንደሚፈተን ይጠበቃል።
ይህ ጨዋታ ለአርሰናል የ3 ነጥብ ብቻ ሳይሆን፤ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን የሚያጸናበት እና የአንፊልዱን ሽንፈት የሚበቀልበት ነው።
ግምቶን ያጋሩን! 👇
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#arsenalvsliverpool #premierleague #mikelarteta #matchday #ethiopia

🔥 "የግብፅ ተጨዋቾች በጣም ተናደዋል!" - የሳላህ ወኪል
#ethiopia | የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ከቤኒን ጋር የሚያደርገው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሊጀመር ደቂቃዎች ሲቀሩት፤ አንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ምስል የፈርኦኖቹን ቁጣ ቀስቅሷል።
ጉዳዩ ምንድን ነው?
ከጨዋታው አስቀድሞ የቤኒን ብሔራዊ ቡድን መረጃዎችን የሚያሰራጭ አንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ፤ የግብፁን ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ መሬት ላይ ወድቆ በቤኒን ተጫዋች ሲገረፍ የሚያሳይ አወዛጋቢ ምስል አጋርቷል።
የሳላህ ወኪል ምላሽ
ይህ ምስል መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ የሞሀመድ ሳላህ ወኪል ሁኔታውን አረጋግጠዋል፡-
"ምስሉ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጋር ደርሷል፤ በዚህም የተነሳ ተጫዋቾቹ በጣም ተናደዋል!"
ይህ የቤኒን ደጋፊዎች ድርጊት በሜዳ ላይ በግብፃውያን ዘንድ ምን አይነት ተነሳሽነት ይፈጥር ይሆን? ጨዋታው ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል!
𝐌𝐎 𝐒𝐀𝐋𝐀𝐇 𝐇𝐄𝐋𝐏𝐒 𝐄𝐆𝐘𝐏𝐓
𝐓𝐎 𝐓𝐇𝐄 𝐐𝐔𝐀𝐑𝐓𝐄𝐑-𝐅𝐈𝐍𝐀𝐋𝐒 𝐎𝐅 𝐓𝐇𝐄 𝐀𝐅𝐂𝐎𝐍 💪
They will face Ivory Coast
or Burkina Faso
on Saturday for a place in the semi-finals 🌍
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#egyptvsbenin #mohamedsalah #afcon #matchday #footballnews

Comments