Logo
FBC
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ምሽት 12 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የኢትዮ ኤሌክትሪክን የማሸነፊያ ግቦች ቤዛ መድህን፣ አሸናፊ ጥሩነህ እና ሙከረም ረሺድ አስቆጥረዋል።

የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ በረከት ግዛው ከመረብ አሳርፏል።

ቀደም ብሎ በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዋች ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 2፣ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ፤ ባሕርዳር ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.