Logo
EBC
በባሕር ዳር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
***********************

የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በባሕርዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በመገኘት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት እየገለጹ ይገኛሉ።

በዚህ የሕዝብ ድጋፍና የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation

10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.