Logo
Getu Temesgen
⛪ የአዲስ ዘመን ደብረ ደናግል ቅድስት ሐናን አብረን እናልማ!

በዐቢይ ጾም ወቅት የሚደረግ ታላቅ የበረከት ጥሪ!

ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የአዲስ ዘመን ደብረ ደናግል ቅድስት ሐና ካቴድራል በ837 ዓ.ም የተመሠረተችና የታሪክ አሻራ ያረፈባት ቅድስት ስፍራ ናት።

በአሁኑ ወቅት ካቴድራሏን በራስ አገዝ ልማት በማጠናከር፣ ታላቅ የሃይማኖትና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እየተከናወነ ይገኛል።

ይህንን የተጀመረ የተቀደሰ የልማት ሥራ ዳር ለማድረስ፣ በመጪው እሁድ በሚካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያና የወንጌል መርሃ-ግብር ላይ እንድትገኙ ጥሪ ቀርቦላችኋል።

እሁድ፣ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
ከጠዋቱ 7:30 ሰዓት ጀምሮ
*ባሕር ዳር፤ ሰላም አድርጊው ማርያም ቤተክርስቲያን።

የትምህርተ ወንጌል ስርጭት እና የልማት ገቢ ማሰባሰቢያ።

የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን (ድጋፍ ለማድረግ)
በአካል መገኘት ለማትችሉና ከሩቅ ሆናችሁ ለእናታችን ለቅድስት ሐና ቤት አሻራችሁን ማሳረፍ ለምትፈልጉ ሁሉ፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የአካውንት ቁጥር፦ 1000709139634

አዘጋጅ፦
የባሕር ዳር አስተባባሪ ኮሚቴ

✨ እኛም ለቤታችን፣ እኛም ለእናታችን!

ይህ ጥንታዊ ቅርስና መንፈሳዊ ማዕከል ተጠግኖና ለምቶ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚደረገው ጥረት የሁላችንንም እገዛ ይሻል።

በጾም ወቅት የሚደረግ ምጽዋትና በጎ ተግባር ደግሞ ድርብ በረከት አለው።
#ቅድስትሐና #አዲስዘመን #ባሕርዳር #ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #የበረከትጥሪ #ethiopia #sainthanna #addiszemen #bahirdar #cbe #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.