Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#ባሕርዳር❤️

በባሕር ዳር ያለው አሁናዊ ድባብ ምን ይመስላል ?

የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ከቀኑ 10:00 በባህርዳር ስታዲየም ይካሄዳል።

በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ የባህር ዳር ስፖርት ወዳድ ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ በስታዲየም አቅራቢያ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ።

ደጋፊዎች በተዘጋጁ የትኬት መቁረጫ ቦታዎች ላይ ትኬቶችን ሲገዙ ተመልክተናል።

የከተማው ነዋሪዎች በሀገራዊ ቀለሞች አሸብርቀው ጨዋታው የሚጀምርበትን ሰዓት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ስፖርት
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም

Via @tikvahethsport Video
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.