5 months ago
ባሕርዳር ለአንጋፋው የጥበብ ሰው ግዮን ዓለምሰገድ የክብር እውቅና ሰጠች
#ethiopia | በኢትዮጵያ የቲያትርና የፊልም ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፈውና በትውልድ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለው አንጋፋው ተዋናይ ግዮን ዓለምሰገድ በባሕርዳር ከተማ ደማቅ የክብርና የእውቅና ተሰጥቷል።
በውቧ የጣና ዳርቻ ከተማ በተከናወነው በዚህ የክብር መርሀግብር ላይ በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ወዳጅ ቤተሰብ በተገኙበት ለከያኒው የሚገባውን አክብሮት ተሰጥቷል።
አንጋፋው ባለቅኔና ደራሲ ጌትነት እንየው ለግዮን ዓለምሰገድ የክብር ካባ በማልበስ ለጥበብ የከፈለውን የሕይወት ዘመን መስዋዕትነት ዘክሯል።
ግዮን ዓለምሰገድ በመድረክ ላይ ያለውን ገጸ-ባህሪ በሕይወት የመሳል፣ የድምፅ አጠቃቀምና የሰውነት እንቅስቃሴን በተመጣጣኝ ሁኔታ የማዋሃድ ልዩ ክህሎቱ የሚታወቅ ሲሆን ከትወና ባለፈም ለወጣት ባለሙያዎች መንገድ አሳይና አስተማሪ በመሆን የዘርፉን ዕድገት ሲደግፍ የቆየ የጥበብ አውራ ነው።
ይህ በባሕርዳር ከተማ የተዘጋጀው የምስጋና መርሃ-ግብር እንዲሳካ ስንታየሁ ገብሩ፣ አበባው ደረበ ፣ ቻሌ ማረው ፣ ደሳለኝ ድረስ እና ሌሎች የጥበብ ጓደኞቹ ከባሕርዳር ጥበብ አፍቃሪዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ "እንኳን ደስ አለህ" በማለት የማይተካና የማይደፈር የሙያ አበርክቶት እንዳለው ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ አይነቱ በሕይወት እያሉ የመከበር ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#gionalemseged #bahirdar #ethiopiantheatre #artrecognition #getnetenyew #ethiopianart #tana #lifetimeachievement #cinemaethiopia #culturalheritage

Comments