Logo
FastMereja
‎ለባህርዳር ከተማ ሌላ ውበት ይሰጣታል የተባለለት አስፓልት በመጠናቀቅ ላይ ነው
‎
‎በሬማ ጀኔራል ቢዝነስና ኮንስትራክሽን አማካኝነት ከአልማ ዋተርፍሮንት ሆቴል እየተነባ የሚገኘው በጣም ዘመናዊና ልዩ መንገድ በቅድመ ክፍያ ብቻ አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማናጀር አቤኔዘር ማስረሻ ተናገሩ።
‎
‎ይህ መንገድ በመሠራቱ የአካባቢው ነዋሪ እጅግ ደስተኛ በመሆኑ የባህርዳር ከተማ አመራሮችንና ሬማ ኮንስትራክሽንን እያመሠገነ እንደሚገኝ አቶ አቤኔዘር ገልጸዋል።
‎
‎የአስፓልት ስራው የ3 ወር እቅድ ቢሆንም በመሀል የነበረው የክረምት ሁኔታ ቲኒሽ ቀናቶችን ቢገፋውም በአድቫንስ ብቻ በአጭር ጊዜ መንገዱን ሰርቶ ማጠናቀቅ ተችሏል።
‎
‎በትላንትናው ዕለትም አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ፣ አቶ ሞላ ሁሴን የባሕርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ አቶ አስሜ ብርሌ የባሕርዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል።
‎
‎የኮንክሪት አስፓልት መንገዱ 8 መቶ ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይህ አስፓልት በፍጥነትና በቅድመ ክፍያ ብቻ እየተሰራ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤትና መሥራች አቶ ፍቅሬ አስፋው ተናግረዋል።
‎
‎መንገዱ ለነዋሪዎች ዘመናዊ እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር የሚያስተሳስር መሆኑ ተገልጧል።
‎
‎የመንገዱ ግንባታ የመኪና፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የግሪነሪ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን የመብራት፣ የቴሌ፣ የውሀ መስመሮች በዘላቂነት በመሰረተ ልማት ስራው ተቀናጅተው የተሰሩ መሆኑ የተናገሩት የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳላማው ጎሹ ናቸው።

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.