ባሕርዳር : በዘይት ምርት ላይ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎች ታሰሩ
#ethiopia | በባሕርዳር ከተማ አሳማኝ ምክንያት በሌለበት ተመሳጥረው በዘይት ምርት ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 27 ነጋዴዎች መታሰራቸውን የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ 221 ድርጅቶች እና 8 ስቶሮችን በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱም ተገልጿል።
በከተማው ዘይትን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ እና ምርት ስወራ አስተመልክቶ የባሕርዳር ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አደራ ጋሼ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ለመንግስት ሠራተኞች የተደረገውን የደሞዝ ማሻሻያ ተከትሎ በግብይት ላይ እየተፈጠረ ያለውን ጭማሪ ለመግታት እየተሰራ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።
ጭማሪው በኢንደስትሪ ምርቶች ላይ በተለይም ስኳርና ዘይት ላይ መታየቱን ገልጸው፤ በተለይ የዘይት ምርት ላይ የታየው ጭማሪ ቀድሞ በገበያው ከነበረበት ከ80 እስከ 100 ብር የሚደርስ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተጠቀሰው።
በዘይት ምርቶች ላይ የሀገርውስጥ የዘይት ምርት አከፋፋዮች ጭማሪ አድርገው መልሰው ወደ ነበረበት ማውረዳቸውን አስተውለናል ያሉት ኃላፊው፤ ከጭማሪ ባለፈ ምርት የመደበቅ እንቅስቃሴ ታይቷል ብለዋል፡፡
በአንፃሩ የግብርና ምርቶች የተረጋጋ ዋጋ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።
በገበያ በምርቶች ላይ ከታየው ጭማሪ ባለፈ፣ በቤት ኪራይ ላይ ተስተውሏል የተባለውን የዋጋ ጭማሪ በመመርመር ላይ መሆናቸውን ኃላፊው አንስተዋል።
ለዚህም ከደሞዝ ማሻሻያው በፊት ከነበረው ዋጋ የተለየ ጭማሪ የተደረገባቸው ግለሰቦች በክፍለ ከተሞች መበቅረብ ጥቆማ መስጠት እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል፡፡
ገበያው ላይ የታየው ንረት ህዝብን በማማረር ከመንግስት ሀሳብ የመነጠል ፍላጎት ነውያሉት ኃላፊው፤ ለሕግ ተገዥና ምስጉን ነጋዴዎች፣ የመንግስት ሠራተኛው መላ ማህበረሰቡ እና የፀጥታ አካላት ለሕግ ማስከበር ተግባሩ ስኬታማነት በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

11 months ago