6 hours ago
በ2019 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዟል
#ethiopia | በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የ2019 በጀት ዓመት የበጀት መግለጫ ማብራሪያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት በጥቅሉ አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡
ይህ የገቢ ዕቅድ በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት እንዳለው ጠቁመው፤ የ2019 በጀት ዓመት በጀትን 88 ነጥብ 7 በመቶውን ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ መታቀዱንም ጠቁመዋል።
የታክስ ገቢ ዕቅዱን ለማሳካትም በታክስ ፖሊሲና በታክስ አስተዳደር ረገድ የተያዙ ማሻሻያዎችን፣ የታክስ ዲጂታላይዜሽንና የኤክሳይዝ ስታምፕ አሠራርን በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
ለ2019 በጀት ዓመት የተቀመጠው የተጣራ የበጀት ጉድለት መንግሥት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ከተቀመጠው ግብ ጋር የተጣጣመ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡
ከብሔራዊ ባንክ በጀት ጉድለት መሸፈኛ የሚወሰደው ብድር ሙሉ በሙሉ ቆሟል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የዋጋ ንረትን ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ ማገዙን ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ ተግባራዊ በመደረጉ ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲውን የሚያጠናክሩ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ ሲሆን፤ ብሔራዊ ባንክ የዘረጋውን ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ለማስጠበቅ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በምግብ ዘይትና በመሠረታዊ ሸቀጦች እንዲሁም መድኃኒቶችን በተመሳሳይ የድጎማ በጀት በመመደብ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የ10 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ግምት የተቀመጠ ሲሆን፤ በኢኮኖሚ እድገቱ ኢንደስትሪ፤ አገልግሎት ዘርፍና ግብርና ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣፕላስ #በጀት2019 #ታክስ #የልማትእቅድ #አፍሪካ #gazette_plus

5 months ago
ፈረንሳይ ከ15 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የማኅበራዊ ሚዲያ እገዳን አጸደቀች
የፈረንሳይ ብሔራዊ ምክር ቤት ከ15 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን የሚከለክል ረቂቅ ሕግ በድምፅ ብልጫ ማጽደቁን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንደገለጹት፤ ይህ ርምጃ በሳይንሳዊ ጥናትና በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ እንደ ስናፕቻት፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ያሉ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን መጠቀምን ይከለክላል።
ውሳኔው የተላለፈው ማኅበራዊ ሚዲያ በሕፃናት አእምሮ ጤና ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።
ፈረንሳይ ከዚህ ቀደም መሰል የዕድሜ ገደብ ለመጣል ሞክራ በአውሮፓ ሕብረት ደንቦች ምክንያት ሳይሳካላት መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን የጸደቀው ሕግ ከአውስትራሊያ ሕግ ጋር ይመሳሰላል።
ይህ አዲስ ሕግ የሕፃናትን ደኅንነት ለመጠበቅና በማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኝነት የሚመጡ የጤና ችግሮችን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ኢማኑኤል ማክሮን አመልክተዋል።
Gazette Plus

7 months ago
ኢትዮጵያ በሸፍጥ ያጣችውን የባህር በር ለመመለስ እየተሰራ ነው
ኢትዮጵያ በሸፍጥ ያጣችውን የባህር በር ለመመለስ እየተሰራ ነው ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባዔ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱራህማን ገለጹ።
47ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።
የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባዔ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱራህማን እንደገለጹት፤ በፌዴራሊዝም ሥርዓት ጥላ ሥር ለሁሉም የምትሆን እና ሁሉም የሚኖርባት አገር ለመገንባት እየተሰራ ነው።
ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አገር ናትም ነው ያሉት አፈ-ጉባኤዋ።
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በህብረት ለመኖር የተወሰነበት ቀን መሆኑን ተናግረዋል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አሻራ የተሳካ መሆኑን የገለጹት አፈጉባኤዋ፤ መንግሥት ኢትዮጵያ በሸፍጥ ያጣችውን የባህር በር ለመመለስ እየሰራ ነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፤ የውይይት መድረኩ ዓላማ ምሁራን በአገረ መንግሥት ግንባታ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ የሚያስችል ነው።
ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እያሸነፈች መሆኑን ጠቅሰው፤ ያደሩ ፈተናዎችን በምክክር ለመቅረፍም እየሰራች እንደሚገኝ ገልጸዋል።

8 months ago
"የኢትዮጵያ ህዝብ ለአባታችን ላሳየው ገደብ የሌለው ፍቅርና ክብር በቤተሰቦቼ ስም አመሠግናለሁ"
- አህመድ ሐጂ ዑመር (ልጅ)
#ethiopia | የኢትዮጵያ ህዝብ ለአባታችን ላሳየው ገደብ የሌለው ፍቅርና ክብር በቤተሰቦቼ ስም አመሠግናለሁ ሲል የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ልጅ አህመድ ዑመር ገለጸ።
የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ሽኝት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በአዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።
ልጃቸው አህመድ ዑመር በወቅቱ እንደተናገረው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለአባታችን ላሳየው ገደብ የሌለው ፍቅርና ክብር በቤተሰቦቼ ስም አመሠግናለሁ።
አባታችን ሰላምን፣ ፍቅርን እና አንድነትን ሲሰብኩ መኖራቸውን በመግልጽ እኛም የእሳቸውን ፈለግ እንከተል ብሏል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ በ94 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡
በአማን ረሺድ
Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ

ትራምፕ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴን ወቀሱ
ትራምፕ የ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴን ከሰላም ይልቅ ፖለቲካን አስቀድሟል ሲሉ ወቀሱ።
"የሰላም ስምምነቶችን መፍጠር እና ጦርነቶችን ማቆም እንዲሁም ህይወት ማዳን እቀጥላለሁ" በማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ስቲቨን ቼንግ በኤክስ ጋዜጣ ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰላም ስምምነቶችን ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፣ ጦርነቶችን ያስቆማሉ እና ህይወትን ይታደጋሉ ብለዋል።
ለ2025 የኖርዌይ የኖቤል የሰላም ሽልማት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይመረጣሉ ተብሎ ብዙ ግምት ከተሰጣቸው ሰዎች ግንባር ቀደም ነበሩ።
ሆኖም የቬንዙዌላዋ ተቃዋሚ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የ2025 የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሰላምን ለማስፈን ከሚደረገው እውነተኛ ጥረት ይልቅ ለፖለቲካዊ አጀንዳዎች ቅድሚያ ይሰጣል ሲሉ የኖርዌይ የሰላም ኖብል ብራይዝ ኮሚቴን ወቅሰዋል።
ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እና የጦርነት ስምምነቶችን በማስፈን የተጫወቱትን ሚና በመጥቀስ ሽልማቱ እንደሚገባቸው ሲገልፁ መቆየታቸው ይታወቃል።

እስራኤልና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሲደረግ የቆየው ድርድር በስምምነት ተጠናቋል።
በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በተካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ሸምጋዮች ሁለቱ ወገኖች በጋዛ ሰርጥ ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሐሙስ ማለዳ ላይ አስታውቀዋል ሲል ሪወተርስ ዘግቧል።
የተኩስ አቁሙ ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን፤ በ72 ሰዓታት ውስጥ የእስረኞች ልውውጥ እንደሚደረግም ታውቋል።
በስምምነቱ የመጀመርያ ምዕራፍ ከሁለቱም ወገን እስረኞች ይለቀቃሉ ሲሉ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ሃማስ በህይወት ያሉ የእስራኤል 20 እስረኞች በአንድ ጊዜ ይፈታሉ፤ በአምስት አቅጣጫ ወደ ጋዛ ሰርጥ ሰብዓዊ እርዳታን የጫኑ መኪኖች መግባት ይጀምራሉ ተብሏል በስምምነቱ ላይ።
ሃማስን ትጥቅ ማስፈታትና የጋዛ ሰርጥን ማን ያስተዳድር የሚለው ጉዳይ ሁለተኛው የድርድር ምዕራፍ ተደርጓል።
ሁለተኛው ምዕራፍ ድርድር ከመጀመርያው አፈፃፀም በኋላ እንደሚቀጥል አል አረቢያ ዘግቧል።
የሐማስ ተጨማሪ የልዑካን ቡድን ማምሻውን በምክትል ዋና ጸሃፊው እየተመራ ግብፅ ገብቷል።
ልዑካኑ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም በሚደረገው ድርድር ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

9 months ago
ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ፖርቹጋልና ብሪታንያ ለፍልስጤም ሀገረ መንግስት እውቅና ሰጡ
ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ፖርቹጋል እና ብሪታንያ ለፍልስጤም ሀገረ መንግስት እውቅና ሰጡ።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሰኞ ከሚካሄደው ስብሰባ ጎን ለጎን በሳውዲ አረቢያ እና በፈረንሳይ መሪነት በርካታ ሀገራት ለፍልስጤም ሀገረ መንግስት እውቅና እንደሰጡ በመሪዎቻቸው በኩል አሳውቀዋል ሲሉ ቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘግበዋል።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ እሁድ እለት በሰጡት መግለጫ “አሁን ካናዳ ለፍልስጤም ሀገረ መንግስት እውቅና ሰጥታለች" ብለዋል።
አውስትራሊያ በበኩሏ ለፍልስጤም ግዛት ዛሬ በይፋ እውቅና ሰጥታለች።
የፖርቹጋሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሀገራቸው ለፍልስጤም ሀገረ መንግስት እውቅና መስጠቷን ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በካቢኔያቸው ስብሰባ ላይ በሰጡት መግለጫ የፍልስጤም መንግስት መመስረት የእስራኤልን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል እና “ለሽብርተኝነት ሽልማት ነው” ብለዋል።
አክለውም "እስራኤል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በሌሎች መድረኮች ሁሉ" በሀገራቸው ላይ የሚነዙትን የውሸት ፕሮፓጋንዳ እና የፍልስጤም መንግስት መመስረትን የሚቃወሙ ናቸው" ሲሉ ገልፀዋል ።

Sponsored by
Surafel
9 months ago
ትራምፕ የሠራተኛ ቪዛ አመልካቾችን የ100 ሺህ ዶላር ክፍያ አጸደቁ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለስራ ወደ አሜሪካ ለሚያቀኑ ቪዛ አመልካቾች ተጨማሪ የ100 ሺህ ዶላር ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያዘውን መመሪያ ፈረሙ፡፡
መመሪያው ፕሮግራሙ ላይ እክል ይፈጥራል የተባለለት ሲሆን፤ ወደ ሀገሪቱ የሚያቀኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች ክፍያውን ካልፈጸሙ ቪዛ ማግኘት እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዝዳን ትራምፕ ጎልድ ካርድ የተባለ ፈጣን ቪዛ የተወሰኑ ስደተኞች በክፍያ እንዲያገኙ መወሰናቸው ተነግሯል፡፡
የቪዛ ፕሮግራሙ ለአሜሪካ ብዙ መቶ ሺህ ዶላሮች የሚያስገኝና ትላልቅ ካምፓኒዎች የተሳተፉበት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ አሜሪካ አሰልጥና ጥቅሟ የሚወሰድበት አሰራር መቆም አለበት ብለዋል፡፡
መመሪያው ከአሜሪካ ውጪ ካምፓኒ ለማቋቋም ላሰቡ ኢንቨስቴሮች ፈታኝ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡
ተቺዎች በH-1B ቪዛ የአሜሪካን የሰው ኃይል ብቃት ይቀንሳል በሚል ሲከራከሩ ቢቆዩም በተቃራኒው ቢሊኒየሩ ኤሎን መስክ ፕሮግራሙ አሜሪካ ከዓለም የተለያዩ ሙያና ባለሙያዎች የሚያስገኝ ነው ይላሉ፡፡
የአሜሪካ የዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት መረጃ እንደሚያሳየው መመሪያው የፕሮግራሙ የቪዛ አመልካቾች ዝቅ እንደሚል ይገመታል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ እስካሁን በፕሮግራሙ በዓመት 85 ሺህ ቪዛ አመልካቾች ወደ አሜሪካ ገብተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በባለፈው በጀት ዓመት አማዞን፣ ታታ ቴክኖሎጂ፣ ማይክሮሶፍት፣ ሜታ ካምፓኒ፣ አፕልና ጎግል ካምፓኒዎች በፕሮግራሙ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን የአሜሪካ መንግስታዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ ቀጣሪዎች የውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ስፖንሰር የሚያደርጉት በሀገሪቱ የሰራተኞችን ቦታ ተክቶ መስራት የሚችል ባለመኖሩ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ክፍያው በቴክኖሎጂውና በኢንደስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪነት እንዲጎለብት ያግዛል፡፡

በኮንጎ 31 ሰዎች በኢቦላ ሞቱ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢቦላ ወረርሽኝ 31 ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደተናገሩት፤ በሀገሪቷ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ 48 ሰዎች በኢቦላ ተይዘዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን በማድረስ፣ ባለሙያዎችን በማሰማራትና የኢቦላ ህክምና ማዕከል በማቋቋም ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ገልጸዋል።
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው በሽታው ቀደም ሲል በሁለት ወረዳዎች ተከስቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ወደ አራት ወረዳዎች ተዛምቷል።
ወረርሽኙ ከሶስት ዓመታት በኋላ የታወጀው ከሁለት ሳምንት በፊት በቡላፔ ከተማ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።
#gazette_plus

የዓባይ ግድብ የምርቃት መርሀግብር ከቆይታ በኋላ ይጀምራል
ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 የዓባይ ግድብ ምረቃ ስነ ስርዓት መርሃ ግብር ከቆይታ በኋላ ይጀምራል።
የግድቡ የምርቃት ዋዜማ በትናንትናው ዕለት የድሮን ትርዒቶችን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በአሁኑ ሰዓት ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የዓባይ ግድብ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ 233 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደገ ሲሆን፤ ቦንድ በመግዛት፤ ስጦታ በመስጠት እና በሌሎች መንገዶች ህዝብ ትልቅ ተሳትፎ እንዳደረገ በስፋት ተግልጿል፡፡
የግድቡ መጠናቀቅም የኢትዮጵያን አቅም በሁሉም ዘርፍ የሚያሳግ እንደሆነም የተለያዩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ዓባይ ግድብ የሚገኘው በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ሲሆን ግድቡ ግንባታ የተጀመረው መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነው፡፡
ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው የግድቡ የውሃ የመያዝ አቅም 74 ትሪሊዮን ሊትር ውሃ ነው።
የግድቡ ከፍታ ርዝመት 145 ሜትር ሲሆን የግድቡ የጎን ርዝመት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር መሆኑን ታውቋል።ትናንት ዋዜማው በሰማይ ላይ ድሮኖች ትይንት የደመቀው ዓባይ ዛሬ የሲሳይ ብስራት ይበሰርበታል።
በዓባይ ግድብ ንጋት ሀይቅም ከ80 በላይ ደሴቶች መፈጠራቸው ታውቋል።

የሺኖዬ እና ጎቤ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው
በኦሮሞ ወጣቶች ዘንድ የሚከበረው የሺኖዬ እና ጎቤ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በዓሉ የሚከበረው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶች በሚያደርጉት ጨዋታ ነው።
ጎቤ ወጣት ወንዶች የሚጫወቱት ጭፈራ መጠሪያ ሲሆን፤ ሺኖዬ ደግሞ የሴቶች ጭፈራ ነው።
የጎቤ እና የሺኖዬ ባህላዊ ጨዋታ ከጳጉሜን እስከ መስቀል ድረስ የሚከበር ሲሆን፤ ከጭጋጋማዉ የክረምት ወራት ወደ ፀደይ ብርሐን የመሸጋገሪያ ብስራት የሚገለጽበት ነው።
የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል ዕድሜያቸው ከአስራዎቹ መጀመሪያ እስከ ሃያዎቹ አጋማሽ ድረስ ያሉ ልጃገረዶች እና ወጣት ወንዶች ተሰባስበው የሚያከብሩት ባህላዊ ጨዋታ ነው።

እሁድ ጷጉሜ 2 2017 ዓ.ም ቀይ የጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል
የጨረቃ ግርዶሹ በመላው ኢትዮጵያ እንደሚታይ ይጠበቃል፡፡ ጨረቃ ቀይ ሆና እንደምትታይም ይጠበቃል።
ክስተቱን ለመመልከት ምንም መመልከቻ መሳሪያ ሳያስፈልግ በዐይን መመልከት የሚቻል ሲሆን፤ በዐይን ላይ ምንም ጉዳት እንደማያስከትል ተገልጿል።
Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
የጨረቃ ግርዶሹ በመላው ኢትዮጵያ እንደሚታይ ይጠበቃል፡፡ ጨረቃ ቀይ ሆና እንደምትታይም ይጠበቃል።
ክስተቱን ለመመልከት ምንም መመልከቻ መሳሪያ ሳያስፈልግ በዐይን መመልከት የሚቻል ሲሆን፤ በዐይን ላይ ምንም ጉዳት እንደማያስከትል ተገልጿል።
Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ
9 months ago
አራት ሺህ ለሚልቁ ወጣቶች እንጀራ ማግኘት ሰበብ የሆነችው እንስት
#ethiopia | ሜላት ንጉሴ ትባላለች። ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ናት። ትውልዷ ከመዲናዋ አዲስ አበባ ነው።
ዕድገቷ ደግሞ ቦረና እና አዲስ አበባ። ቦረና ከሴት አያቷ ዘንድ አድጋለች። ከአያቷ ማደጓና ከእርሳቸው የወረሰቻቸው በጎ ባህሪያት ከመልካም ስራዎች ጋር እንዳቆራኛት ትናገራለች።
ሜላት ማህበራዊ ሚዲያን በወጉ የምትጠቀም እንስት ናት። በፌስቡክ ላይ 185 ሺህ ተከታዮች አሏት። ያላትን ተሰሚነት በመጠቀም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ትከውናለች።
ክረምትና በጋ ሳትል ለመልካም ነገር ሳትቦዝን ትለፋለች። የተለያዩ ተፈጥሯዊና ሠው ሠራሽ ችግሮች ሲደርሱ አለሁ ባይ ናት።
በተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ማዕከል ውስጥ በርካታ መልካም ተግባራትን ከውናለች። ለአካል ጉዳተኞች ዊልቼር አሰብስባ ሰጥታለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በሌላ በጎ ምግባር ተከስታለች።
ይህም የማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም ስራ ፈላጊና አሰሪን የማገናኘት ተግባር ነው። ለዚህ ስራ ምንም አይነት ክፍያ አትጠይቅም። ይህን ለማድረጓም መነሻ ምክንያት ነበራት።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስራ በማጣት ራሱን ያጠፋ ልጅ ነበር መነሳሳት የሠጣት። በአንድ ሰው ምክንያት የተጀመረው የሜላት በጎ ስራ ከአራት ሺህ ለሚልቁ ጉሮሮዎች እንጀራ ማቀበል ችሏል። በእሷ ምክንያት ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች ስራ ማግኘት ችለዋል።
ለዚህና ሌሎችም መልካም ተግባሮቿ በርካታ እውቅናና ሽልማቶች ተሠጥተዋታል። ሰሞኑንም ትልልቅ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች እና ባለስልጣናት እጩ በተደረጉበት የስታር ዋይድ አዋርድ (star wide award) ላይ አሸንፋ ተሸልማለች።
"ለሶሻል ሚድያ ጊዜ መስጠታችን ካልቀረ ለበጎ እናውለው ብንል ይኸው እውቅና እያሰጠን ይገኛል።" ስትልም ስሜቷን ገልፃለች።
በመልዕክቷም "ይሄ ሽልማት የኔ ብቻ አይደለም፤ የምታበረታቱኝ ወዳጅ ቤተሰቦቼ ውጤት ነው። ልትኮሩ ይገባል" ብላለች።
በዳግማዊት ግርማ

10 months ago
ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከክልል ኤርፖርቶች ማስተናገድ ሊጀመር ነው
ዓለም አቀፍ በረራዎች ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ከክልል ኤርፖርቶች ማስተናገድ ሊጀመር መሆኑን የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ከግል የበረራ ድርጅቶች ጋር በበረራ አገለልግሎት ዙሪያ እየተወያየ ነው።
በባለስልጣኑ የአየር ትራንስፖርትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አማካሪ አቶ እንደሻው ይገዙ ባቀረቡት ሪፖርት በ2018 ዓ.ም ዓለም አቀፍ በረራዎችን ከአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በተጨማሪ በሌሎች የሃገሪቱ ክልል ኤርፖርቶች ማስስተናገድ እንደሚጀመር ተናግረዋል።
የክልል ኤርፖርቶችን ማስተሳሰ የቱሪዝም ፍሰቱ እንዲጨምር እንዲሁም የደበኛውን እንግልት መቀነስ የሚያስችል ነው ያሉት አቶ እንደሻው፤ ለአብነትም ከሚዛን ቴፒ - ጅማ - ጋምቤላ - አሶሳ እንዲሁም ከድሬደዋ - ሃረር - ባሌሮቤ የተሳሰረ በረራ እንዲኖር ለማድረግ በታሰቡን ገልፀዋል።
ይህም አንድ ሰው በሀገር ውስጥ በረራ ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ለመሄድ የግድ አዲስ አበባ መምጣት እንዳይኖርበት እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የዓለም አቀፍ በረራዎች ከአዲስ አበባ ኤርፖት በተጨማሪ በክልል አየር ማረፊያዎች ለማስተናገድ መታቀዱንም ተቁመዋል።
ለአብነት ዓለም አቀፍ በረራዎቹን ከባህር ዳር፣ መቀሌ እና ድሬደዋ ቢደረጉ የሃገሪቱን የወጪ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ልማቱን የሚደግፍ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም መንፈሳዊ ጉዞዎችን ከክልል ኤርፖርቶች ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸው የሃጂ ኡምራ ጉዞ፣ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ገናን በላሊበላ እና ጥምቀትን በጎንደር ጉዞዎችን ለማስተናገድ ታቅዷል ነው ያሉት።

ቴሌቪዥን ግብር ቅሬታ አስነሳ
ነዋሪዎች ከመብራት ክፍያ ጋር እየከፈሉለት ለሚገኘው የቴሌቪዥን አገልግሎት ድጋሚ ክፍያ እየተጠየቅን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ "ቤት ለቤት እየዞሩ ክፍያ አስገድደውናል" እና "ያለፉት ዓመታት ያልተከፈለ ውዝፍ ክፍያ እንድትከፍሉ ተብለን ደብዳቤ እየተሰጠን ነው" ሲሉ ለGazette Plus ገልጸዋል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪ አቶ አስማማው በሪሁ፣ በየወሩ እየከፈሉበት ላለው አንድ ቴሌቪዥን ተጨማሪ ክፍያ እየተጠየቁ መሆኑን ገልጸው፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የተዘበራረቀ አሰራር እንዳለው ይጠቁማሉ።
በተቃራኒው፣ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞላልኝ መለሰ በሰጡት ምላሽ፣ ቤት ለቤት የሚሰበሰበው ክፍያ በአንድ ቤት ውስጥ ለተጨማሪ ቴሌቪዥን ወይም ለንግድ ተቋማት ብቻ መሆኑን ገልጸው፣ በአዋጅ ቁጥር 1278/2015 መሰረት ለእያንዳንዱ መኖሪያ ቤት ለሚገኝ አንድ ቴሌቪዥን ክፍያ ከመብራት ጋር እንደሚከፈል ተናግረዋል።
ሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ተቋማትም ከአንድ በላይ ቴሌቪዥን ካላቸው፣ በቀጣይ ከንግድ ፈቃድ እድሳት ጋር ተያይዞ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይደረጋል ብለዋል።
Seledadotio

ታዋቂው የፍርድ ቤት ዳኛ ፍራንክ ካፕሪዮ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ዳኛ ካፕሪዮ በእጃቸው የፍርድ መዶሻ፣ በደረታቸው የሩህሩህ ልብ ባለቤት መሆናቸው ይነገርላቸዋል።
ዳኛው በጥልቅ ርህራሄያቸው፣ በትህትናቸውና በሰዎች መልካምነት ላይ ባላቸው ጽኑ እምነት በዓለም ዙሪያ ተወዳጅ ነበሩ።
በፍርድ ቤት ስራቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ የነኩ ሲሆን፣ በሰብዓዊነት ምሳሌነታቸው ደግሞ ብዙ ሰዎች ያውቋቸዋል።
እሳቸውን ለማወቅ ወይም ቃላቸውን ለመስማት ዕድሉን ያገኙ ሁሉ፣ ስለቀልዳቸውና ደግነታቸውን ይመሰክራሉ።
እሳቸው የተከበሩ ዳኛ ብቻ ሳይሆኑ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት እና ወዳጅ እንደነበሩም ይገለጻል።
ዳኛው በርህራሄ፣ በመግባባትና በልባዊ ፍቅራቸው ይታወሳሉ። በህልፈታቸውም የዓለም መገናኛ ብዙሃን በአንድ ቃል የሀዘን ዜና ይዘው ወጥተዋል።
ይህ ዜና የዓለም ሩህሩሁ ዳኛ ፍራንክ ካርፒዮ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋውን የሚያትት ነው። ዜናው የዓለም ልበቅኑ ዳኛ በ88 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ያትታል።
የፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ መዘጋጃ ቤት ዳኛ የነበሩት ፍራንክ ካፕሪዮ መዶሻቸው የህግ አንቀፆችን ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነትን ለማወጅ የሚታዘዝ ነበር። ይህም በመላው ዓለም ብዙ ወዳጅና አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓቸዋል።
በራሳቸው የቴሌቪዥን ዝግጅትም በዓለማቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፉት ዳኛው፣ በፍርድ ወንበር ላይ ለተቀመጡ ሁሉ በሚያሳዩት ርህራሄ እውቅ ናቸው።
በዳኝነት ሚዛን ህጉ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነትም እንደሚፈርድ ያስመሰከሩት ዳኛው፤ ተከሳሾችን የሚያናግሩበት የትህትናና የመረዳት እንዲሁም የወዳጅ ያህል ቀለል ማለት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የዓለም አገራት በርካታ አድናቂዎችን አስገኝቶላቸዋል።
ይሄ ርህራሄ በቀላሉ የመጣ ሳይሆን በመኖር ያገኙት መሆኑ ይገለጻል።
አነስተኛ የገቢ ምንጭ ካላቸው ቤተሰቦቻቸው የተገኙት ዳኛው ህይወትን ለማሸነፍ በብዙ መውጣት መውረድ ውስጥ አልፈዋል።
በታዳጊነት ዘመናቸው ህይወትን ለማሸነፍ ጫማ በማፅዳት፣ ጋዜጣ በማከፋፈልና ወተት የጫነ መኪና ላይ ሰርተዋል።
በልጅነት ዘመናቸው ታግለው ያሸነፏት ዓለም በማምሻ ዘመናቸውም ከጣፊያ ካንሰር ጋር አታግላቸዋለች።
ዳኛው ከጣፊያ ካንሰር ጋር መታገላቸውን ይፋ ካደረጉበት 2023 ጀምሮ ህይወታቸው ሊያልፍ የሰዓታት ዕድሜ እስከቀረበት ድረስ አድናቂዎቻቸውን በፀሎት እንዲያስቧቸው ተማፅነው ነበር።
ሞታቸውን ይፋ ያደረጉ ቤተሰቦቻቸውም እርሳቸው የተከበሩ ዳኛ ብቻ ሳይሆኑ ተወዳጅ ባል፣ አባት አያትና ቅድመ አያት እንደነበሩ መስክረዋል።
በፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር በ1985 የተጀመረው የዳኝነት ጉዟቸው በጡረታ እስከተሰናቱበት 2023 ድረስ የዘለቀ ነበር ሲል ኒውዮርክ ፖስት ዘግቧል።
ዳኛው ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት የሰባት የልጅ ልጆች አያትና የሁለት የልጅ ልጅ ልጆች ቅድመአያት ነበሩ።

ሩሲያና ህንድ ስልታዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተወያዩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህንድ በሚገቡ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ከጣሉ ከአንድ ቀን በኋላ ሩሲያ እና ህንድ በሁለትዮሽና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ስልታዊ አጋርነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል የህንድ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አጂት ዶቫልን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በዓመቱ መጨረሻ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኒው ዴሊን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዶቫል ከሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌይ ሾይጉ ጋር ባደረጉት ውይይት ሁለቱም ወገኖች የሀገራቱ ግንኙነት አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት ሰጥተው ተወያይተዋል።
ትራምፕ ከህንድ በሚመጡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ የ25 በመቶ ታሪፍ ከጣሉ ወዲህ የዩናይትድ ስቴትስ እና ህንድ ግንኙነት መሻከር አሳይቷል የተባለ ሲሆን፤ ይህም የህንድን ትልቅ የኤክስፖርት ገበያ እንዳያስተጓጉል ተፈርቷል።
የህንድ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አጂት ዶቫልን ፍትሃዊ እና ቀጣይነት ያለው የዓለም ስርአት ለመመስረት፣ የዓለም አቀፍ ህግን የበላይነት ለማረጋገጥ፣ ፈተናዎችን እና ስጋቶችን በጋራ ለመዋጋት የበለጠ ትብብር ለማድረግ ቆርጠናል ሲሉ ተናግረዋል።

ከትራምፕ ጋር በገቡት ዕልህ ሕንዳዊያን የሀገራቸውን ምርት ብቻ እንዲገዙ ትዕዛዝ ተሰጣቸው
አሜሪካ በሕንድ ላይ የጣለችውን ታሪፍ ተከትሎ ዕልህ የተጋቡት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ናሬንድራ ሞዲ ሕንዳዊያን የሀገራቸውን ምርት ብቻ እንዲገዙ ትዕዛዝ አዘል መልዕክት አስተላለፉ።
የትራምፕ አስተዳደር ህንድ ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ከጣለ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን በመረዳት የሕንድ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት የገለጹት።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ዛቻን በመቃወም ህዝቡ የሀገር ውስጥ እቃዎችን እንዲገዛ ያሳሰቡ ሲሆን፤ አስተዳደሩ የሩሲያ ዘይት መግዛቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሜናዊ ኡታር ፕራዴሽ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የዓለም ኢኮኖሚ በአስፈሪ ሂደቶች ውስጥ እያለፈ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ህንድ የሩስያ ዘይት ግዢን ከቀጠለች ዋይት ሀውስ ተጨማሪ እርምጃ እንደሚወስድ እያስፈራራ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አሁን የምንገዛው ማንኛውም ምርት በህንድ ላብ የተሰሩትን ብቻ መሆን አለበት” ብለዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት ህንድን የብሪክስ ቡድን አባል መሆኗን እና ከሩሲያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት በመተቸት “የሞተ ኢኮኖሚያቸውን በአንድ ላይ ሊያወርዱ ይችላሉ” ሲሉ ተችተዋል።

በሰው መነገድ ወንጀል ላይ የተሳተፉ 5 ሰዎች ሞት ተፈረደባቸው
በሰው መነገድ ወንጀል ላይ በተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወሰን መደረጉን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የብዙ የሰዎች ህይወት እየቀጠፈ ያለ ወንጀል ነው፡፡
በወንጀሉ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወንጀለኞች በአዋጅ ቁጥር አንድ ሺህ 178 መሰረት የሞት ቅጣት፣ የዕድሜ ልክ እስራትና እስከ 25 ዓመት እስራት ያስቀጣል ብለዋል፡፡በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሂደቱ የተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወስን መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በሰው የመነገድ ወንጀል ለመከከላከልና ለመቆጣጠርም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና በክልሎች መካከል ቅንጅትና ትብብር የሚፈጥሩ ስራዎችና መመሪያ የማጽደቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡በተጨማሪም በህገወጥ ድርጊቱ በስፋት ተጠቂ ለሆኑት ወጣቶች በሀገር ወስጥ የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልም ድንበር ተሻጋሪ የተደራጀ ወንጀል መሆኑን አንስተው፤ ይህንንም ለመቆጣጠር ከጅቡቲ፣ ኬንያና ማላዊ ጋር ዓለም አቀፍ ትብበር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በመሆኑም ባለፈው በጀት ዓመት የተወሰደው የህግ እርምጃ እንደሀገር የተሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው፡፡በቀጣይም የተሻለ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Via Gazette Plus

11 months ago
"በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ አላበቃም" -የእስራኤል ጦር አዛዥ
#ethiopia | ከኢራን ጋር የሚደረገው ጦርነት ገና አላበቃም ሲሉ የእስራኤል ጦር ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር ተናገሩ።
ኢራንና አጋሮቿ በእኛ እይታ ውስጥ ናቸው ሲሉ በወታደራዊ ግምገማ ስብሰባ ወቅት ተናግሯል። በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻም አላበቃምም ብለዋል።
በጋዛ የሚካሄደው ጦርነት የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ያደረገው እጅግ ውስብስብ ጦርነት መሆኑን ጠቅሰው በጦርነት ብዙ ዋጋ እየከፈልን ነው፤ ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
ከጥቂት ወራት በፊት እስራኤል በኢራን የኒኩሊየር ተቋማት ላይ በፈፀመችው ድንገተኛ የአየር ጥቃት ሁለቱ ሀገራት ወደ ሙሉ ጦርነት መግባታቸው ይታወቃል። በጦርነቱ አሜሪካ ከእስራኤል ጎን በመሰለፍ ኢራን ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ፈፅመለች።
የሁለቱ ሀገራት ጦርነት ከ12 ቀናት በኃላ በተኩስ አቁም ስምምነት የተቋጨ ቢሆንም ዳግም ሊቀሰቀስ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ይነገራል። #gazette_plus

የዩክሬን ፓርላማ ዩሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾመ
#ethiopia | የዩክሬን ፓርላማ የዩሊያ ስቪሪደንኮ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ በ262 ድምጽ አጽድቋል።
ስቪሪደንኮ ከህዳር 2021 ጀምሮ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
የዩክሬንን ኢኮኖሚና ማህበራዊ አቅም ማጠናከር፤ የዩክሬናውያንን የድጋፍ ፕሮግራሞችን ማስፋፋትና የሀገር ውስጥ የጦር መሳሪያ ምርትን ማስፋፋት የመንግስታቸው ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የተረከበች ሁለተኛዋ ሴት መሆኗን አናዶሉ ዘግቧል፡፡ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ስቪሪደንኮን በእጩነት ማቅረባቸውን ይታወሳል። #gazette_plus

ከቤት ሰራተኝነት እስከ ባንክ ባለሙያነት
#ethiopia | ገነት ጌታቸው ትባላለች፡፡ ከምድር የነበራት ትውውቅ የጀመረው በውቦቹ መፍለቂያ ወሎ በኩል ነበር፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ልዩ ስሙ መቅደላ ወይም ይሎል ተብሎ በሚጠራ ገጠራማ ቦታ ተወለደች፡፡
አስተዳደጓ ከገጠራማ እኩዮቿ ጋር አቻ ነው፡፡ ከብት ስትጠብቅ፣ ውሃ ከምንጭ ስትቀዳና እንጨት ስትለቅም አድጋለች፡፡
በሚገባ መመገብ ከመቻሏ በፊት ምግቧን እያበሰለች ነው ያደገችው፡፡
ለቤተሰቧ ቶና ናት - ፈጣንና ደፋሪቷ ገነት ጌታቸው፡፡ እናቷ በ1983 ከ7ኛ ክፍል ትምህርት አቋርጣ በትዳር ታሰረች፡፡
አባቷ አርሶ አደፋርሶ የሚያበላ ገበሬ ነው፡፡ እናቷ ለትምህርት ልዩ ፍቅር ነበራት፡፡
ትንሿ ገነት የእናቷን የመማር ቁጭት አዝላ አስኳላ ዘለቀች፡፡ ከአንድ እስከ አራት እዛው በቅርቧ ያለ ትምህርት ቤት ተማረች፡፡
ከዚያም በኋላ አምስተኛ ክፍል ለመማር ከምትኖርበት ስምንት ኪሎ ሜትር በየቀኑ እየተመላለሰች ተማረች፡፡
ይህ ስፍራ ተራራማ ቦታ ስለነበር መንገዱ ለትንሿ ገነት ፍጹም አመቺ አልነበረም፡፡ የተሻለ ትምህርት ፍለጋ ዘመድ ጋር መጣች።
የዘመድ ቤት ሌላ ፈተና ሌላ መንገድ ታቅፎ ተቀበላት፡፡ ረሀብ፣ መገረፍ የስነልቦና ጉዳት እና ፍቅር ማጣት እንደ ልጅ አለመታየት የሠርክ ቀለቦቿ ሆኑ።
ብዙ የልጅነት አእምሮዋ መቋቋም የማይችላቸውን አጥንት ድረስ የሚሰረስሩ ንግግሮች ታደምጥ ነበር።
ለትንሽ ልቧ የሚከብደውን ፈተና በምን እንደቻለችው እሷም አታውቅም፡፡ “ምን እንዳስቻለኝ ባላውቅም ሁሉንም እናቴ ለተነጠቀችው ትምህርት ስል ዋጥ አድርጌ አልፈው ነበር” ትላለች።
የቅርብ ዘመዷ (የአጎቷ ልጅ) እሷ እህቴ የምትላት በአንፃራዊነት ጥሩ ነበረች። ብዙ ጫና ታሳድርባት የነበረው የምታኖራት ሴት ነበረች።
ትንሽ ልቧ ብዙ ጊዜ ከቤት ለመጥፋት ከጅሎ ያውቃል። የሶኬት ግርፋት ሰልችቷት ነበር ከቤት ለመውጣት ያሰበችው፡፡
ጠግባ ስለማትበላ ጎረቤት ስትላክ እንጀራ ስጡኝ ማለት ከጅላም ታውቃለች፡፡ ከዓመታት ቆይታ በኋላ ስምንተኛ ክፍልን ተፈትና ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ተመለሰች፡፡
በዚሁ ቦታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከመኖሪያዋ 17 ኪሎ ሜትር በየቀኑ መመላለስ ስለከበዳት እዛው ተከራይታ መማር ጀመረች። የ11 እና 12ኛ ክፍል ትምህርቷንም ተጨማሪ 7 ኪሎ ሜትር ተጉዛ ተማረች፡፡
ያኔ ራሷን በገንዘብ መደገፍ ነበረባት፡፡ ለዚያም የተንታ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ውስጥ በተወዛዋዥነት ተቀጥራለች፡፡
የዩኒቨርሲቲ ውጤት እስኪመጣ ድረስ ክረምቱን ከዓመታት በፊት ወደኖረችባት አዲስ አበባ መጣች፡፡ በዚህ ጊዜ የዘመድ ቤት አይታሰብም፡፡
ያንን በመተው በሰው ቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ መስራት ያዘች፡፡ጊዜውን ጠብቆ የዩኒቨርሲቲ ውጤት መጣላት።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ዘርፍ ትምህርቷን አጠናች። በዩኒቨርሲቲውም ብዙ ነገሮች አስቻጋሪ ነበሩ፡፡
ክረምት ክረምት አሁንም ያገኘችውን ከመስራት አታርፍም፡፡ በዚህም ጊዜ ሆቴሎች ላይ መስተንግዶ ትሰራ ነበር።
ከሶስት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ በኋላ ህይወት ሀዋሳ ወሰደቻት። በሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ከአንድ ዓመት በላይ በረዳት የሰው ኃይል አስተዳደር የስራ መደብ ሰራች፡፡
ቀጥላም ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገባች፡፡ በዚህ ጊዜ ደስታዋ ወደር አልነበረውም፡፡
ቀጥላም ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ገባች። ቡና ባንክም የተገልጋይ መስኮት የስራ መደብ ከአንድ ዓመት በላይ ሰርታለች፡፡
አሁን ደግሞ በአማራ ባንክ በቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ኦፕሬሽን የስራ መደብ ስር እየሰራች ትገኛለች፡፡
በፕሮጀክት ማኔጅመንት የጀመረችውን የማስተርስ ትምህርት ትምህርትም አጠናቃለች፡፡
አዲስ አበባ የከፈለችው ዋጋ ልጅነቴን ሰርቶታል ትላለች። ጥንካሬዋ የተሰራው እዛ ነው።
ያበረታት የእናቷ ትምህርት አቋርጦ ማግባት ሁልጊዜም ስትቆጭ ስለምታያት በእሷ እንድትካስ ትፈልግ ነበር።
እሱን ለማድረግ መጠንከር የማይሞከረውን መሞከር ነበረባትና በርትታ አሳይታለች።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ከ34 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ
#ethiopia | አገልግሎት ከክልል መዝጋቢ እና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ የሴክተር ጉባኤ እያካሄደ ነው።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተው ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በወቅቱ እንደገለፁት፤ አገለግሎቱ የጉዞ ሰነዶችን በማዘጋጀት ከ100 ዓመት በላይ ቢያልፈውም ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ሰፊ ክፍተቶች ነበሩበት።
የአገልግሎቱ አሰራር የማህበረሰቡን ፍላጎት ያላሟላና ተገልጋዮችን ለእንግልትና ላልተፈለገ ወጪ ሲዳርግ የቆየ ነበር ብለዋል።
በጠጨማሪም በአገልግሎቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች እርካታ ያልበረባቸው ነበሩ ያሉት ዳይሬክተሯ በዚህም በ2016 ዓም 11 የሪፎርም አጀምዳዎች ተቀርጸው ወደ ስራ ገብተዋል ነው ያሉት።
ሪፎርሙ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም የኤክትሮኒክስ ፓስፖርት ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አብራርተዋል።
ሪፎርሙ በዘርፉ የሚታዩ የአገልግሎት ክፍተቶችን ከመቅረፍ ባሻገር አገልግሎት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዲያገኝ አድርጓል ብለው በዚህም በ2017 ዓ.ም ከዘርፉ ከ34 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የነበረውን የሰው ሃይል እጥረት እንዲሁም የደንበኞችን እርካታ በሚታይ ሁኔታ መቀየር ተችሏል ብለዋል።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አርበኛ በ110 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | የብሪታንያ አንጋፋው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አርበኛ ዶናልድ ሮዝ በ110 ዓመታቸው አረፉ።
ሮዝ 1944 በኖርማንዲ የባህር ዳርቻ ላይ በተደረገው የዲ-ዴይ ማረፊያ ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ በሰሜን ጀርመን የሚገኘውን የበርገን-ቤልሰን ማጎሪያ ካምፕን ነጻ ባደረገው ክፍል ውስጥ ነበሩ።
በሰሜን እንግሊዝ የኤረዋሽ ቦሮው ካውንስል መሪ የሆኑት ጄምስ ዳውሰን የሮዝን ሞት ሲያስታውቁ “የጦርነት ጀግና” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
“ኤረዋሽ እንደዚህ አይነት ነዋሪ በማግኘቷ ትልቅ ክብር ይሰማታል” ሲሉም አክለዋል።
ሮዝ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በ1914 የተወለዱት ነው የተወለዱት።
ከለንደን በስተደቡብ ምዕራብ ከምትገኘው የዌስትኮት መንደር የመጡት ሮዝ፣ በ23 ዓመታቸው ጦር ሠራዊቱን ተቀላቅለው በሰሜን አፍሪካ፣ ጣሊያንና ፈረንሳይ አገልግለዋል።
በርካታ ሜዳሊያዎችን የተቀበሉ ሲሆን የፈረንሳይ ከፍተኛ ሽልማት የሆነው ሌጌዎን ዲ’ኦኑር (Legion d’Honneur) ተሸልመዋል። #gazette_plus

ሁቲዎች ሁለተኛዋን የጭነት መርከብ በቀይ ባህር አሰመጡ
#ethiopia | የየመን ሁቲዎች በጭነት መርከብ ላይ ባደረሱት ጥቃት በቀይ ባህር አሰመጡ።
በጥቃቱም በትንሹ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን የአውሮፓ የባህር ኃይል ተልዕኮ አስታውቋል።
25 ሠራተኞችን የጫነው ኢተርኒቲ ሲ ከትናንሽ ጀልባዎች በተተኮሱ ሮኬቶች እና በእጅ ቦምቦችን በመመታቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ሲል የእንግሊዝ የባህር ንግድ ኦፕሬሽን ኤጀንሲ ገልጿል።
በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት ሁቲዎች ኢተርኒቲ ሲን ያጠቁት ወደ እስራኤል በማምራት ላይ እያለ ሲሆን፤ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሠራተኞችን ወደ "ድብቅ ቦታ" መውሰዳቸውም ተመላክቷል።
በየመን የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሁቲዎች ብዙ በህይወት የተረፉ ሠራተኞችን ማገታቸውን ገልጾ፤ የታገቱት ሠራተኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል።
ከህዳር 2023 ጀምሮ ሁቲዎች በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ በሚሳኤል፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በትንንሽ ጀልባዎች ጥቃት ወደ 70 የሚጠጉ የንግድ መርከቦችን ኢላማ ማድረጋቸው ተገልጿል። #gazette_plus

አንድ የደጋ አጋዘን በ15 ሺህ ዶላር እየታደነ ነው
አንድ የደጋ አጋዘን በ15 ሺህ ዶላር እየታደነ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦና ያዴሳ እንደገለጹት፤ በክልሉ ደንን ማዕከል ያደረገ የአካባቢ ጥበቃ ስራ በስፋት ይሰራል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የነበረው አሰራር ደኖችን ለመጠበቅ ህዝብን ያሳተፈ አልነበረም ያሉት አቶ ቦና፤ ይህን አሰራር በመቀየር ህብረተሰቡ እንዲደራጅ በማድረግ ደኖችን እንዲከልልና በውስጡ ያሉ ሃብቶች እንዲጠብቅ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኘውን የደጋ አጋዘን ለውጪ ሀገር ዜጎች ለሕጋዊ አደን በማቅረብ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የደጋ አጋዘን በአርሲ እና ባሌ ተራራማ ስፍራዎች እንዲሁም በምዕራብ ሀረርጌ በስፋት የሚገኝ ነው ብለው፤ የውጪ ሀገር ዜጎችም ለስፖርታዊ አደን የሚመርጡት ብርቅዬ እንስሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በአዳባ እና ዶዶላ አካባቢዎች ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ለውጪ ዜጎች የደጋ አጋዘንን ለአደንነት እንዲያቀርቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አደኑን የሚያደርጉት የውጪ ዜጎች ፈቃድ የሚሰጣቸው ሲሆን፤ በአካባቢው ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመሆን ያረጀ ወንድ የደጋ አጋዘን ተመርጦ እንዲያድኑ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
ማንኛውንም የደጋ አጋዘን ማደን ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንም አክለዋል፡፡
አንድ የውጪ ዜጎች ለአንድ አጋዘን ለማደን 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፍላል ያሉት አቶ ቦና፤ አዳኙ ያደነውን የደጋ አጋዘን ከአንገት በላይ ያለው አካል ይዞ መሄድ ይችላል ብለዋል፡፡
ከአደኑ የሚገኘው ገቢ 70 በመቶ የሚሆነው ለኢንተርፕራዞች የሚገባ መሆኑና 30 በመቶውን መንግስት እንደሚወሰድም ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን መውጣት “በሀገሪቱ ታሪክ አሳፋሪ ነው” አሉ
#ethiopia | የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን መውጣቷን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳፋሪ ሲሉ ጠቅሰውታል።
ለዚህም የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን አስተዳደርን ክፉኛ ተወቃሽ ማድረጋቸውን አል ጀዚራ ዘግቧል።
ትራምፕ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ በወቅቱ በስልጣን እኔ ብኖር ኖሮ "የመውጣት ስራው በጉልበት እና በክብር ይፈጸም ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።
የድሮው ቤታችን ሲሉ የጠቀሱት በባግራም የሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካ ጦር ሰፈር አሁን በቻይና ቁጥጥር ስር መሆኑን በቁጭት አንስተዋል።
አሜሪካ በጊዜው የወሰደችው ርምጃ “ትልቅ ስትራቴጂካዊ ስህተት” መሆኑንም ጠቁመዋል።

የከንቲባ ቀውስ ያጋጠማት አፍሪካዊት ከተማ
#ethiopia | እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምሮ በአፍሪካ በኢኮኖሚዋ ትልቅ ቦታ የምትይዘው ከተማዋ ዘጠኝ ከንቲባዎች ተፈራርቀውባታል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የከተማዋ የፖለቲካ አመራር ችግር ሀገራዊና አህጉራዊ አንድምታ እናዳለውም እየተነገረ ይገኛል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማዕከል የሆነችው የጆሃንስበርግ ከተማ ከ2016 ጀምሮ ባሉት ዓመታት ውስጥ ዘጠኝ ከንቲባዎች እንዳሻት ቀያይራለች፡፡
ይህ ቀውስም ነዋሪዎች እንደኃይል፣ ውሃና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን በአግባቡ እንዳያገኙ በማድረግ ችግር ውስጥ እየከተታቸው ይገኛል ተብሏል፡፡
በከፋ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የፍጆታ ዋጋ መጨመር እና በፖለቲካዊ ሽኩቻ ጆሃንስበርግ በየወቅቱ የከንቲባ ቀውስ እንዲያጋጥሟት ሆኗል።
በሶዌቶ ዱቤ ከተማ ውስጥ የብላክ ኮንሸስ ንቅናቄ አቀንቃኝ እና ለረጅም ጊዜ ነዋሪ የሆኑት ምፖትሰንግ ጃይረስ እንደሚሉት፤ ከሆነ የከተማው ምክር ቤት አባላት አለመታወቃቸውና ከዜጎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማቋረጣቸው የአገልግሎት አሰጣጥ መዳከም ለከንቲባዎቹ መቀያየር ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ይገልጻሉ።
በሶዌቶ የሀገሬው ተወላጅና በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት ማሴቻባ ኖናያና በበኩላቸው፤ በአመራሩ መካከል ያለው ይህ ልዩነት በከተማዋ ውስጥ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር እየፈጠረ ስለመሆኑ ይናገራሉ፡፡
አክለውም በተደጋጋሚ እየተከሰተ ስላለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እና የታሪፍ ጭማሪ እንደ ሻማ፣ የፀሐይ ኃይልና ጋዝ ያሉ አማራጮችን እየተጠቀሙ ስለመሆኑ ገልጸው፤ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ዜጎች እነዚህ አማራጮች እንደሌላቸው አውስተዋል።
እ.ኤ.አ ነሀሴ 16 ቀን 2024 በይፋ ቃለ መሃላ የፈጸሙት የወቅቱ ከንቲባ ዳዳ ሞሬሮ የካቤሎ ጉማንዳ ስልጣን መልቀቅ ተከትሎ በምትካቸው ጆሃንስበርግን ለማረጋጋት እና መሰረታዊ ተግባራትን ወደነበረበት ለመመለስ የታለሙ ስራዎችን ተግባራዊ አድርገዋል።
በኤሌክትሪክ በ12 ነጥብ 7 በመቶ፣ በውሃ እና በንፅህና አጠባበቅ በ13 ነጥብ 9 በመቶ እንዲሁም በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ ለማህበረሰቡ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ሊያባብሰው እንደሚችል ተነግሯል፡፡
በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ተንታኝ ፕሮፌሰር ፓትሪክ ቦንድ በአካዳሚክ መጽሔት ጽሁፋቸው ላይ ይህንን ቀውስ በሰፊው አቅርበዋል።
"የከተማዋ ውድቀት ስር የሰደደ እና ኢ-ፍትሀዊነት የተንሰራፋበት ነው። አመራሩ ከተምሳሌታዊ ሪፎርም ወደ መዋቅራዊ ለውጥ እስኪሸጋገር ድረስ ድሃው ህዝብ ከፍተኛውን ዋጋ እየከፈለ ይቀጥላል" ብለዋል።
ጆሃንስበርግ ወደ 2026 የማዘጋጃ ቤታዊ ምርጫ እያመራች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ጥያቄው ቀጣዩ ከንቲባ ማን ይሆናል የሚለው ብቻ አይደለምም ይላሉ።
የቀድሞ ዘጠኝ ከንቲባዎችን ውድቀት ያስከተሉት መዋቅራዊ ችግር ይሆን ወይስ የግል ብቃታቸው የሚለውም ነው።
አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ከመንግስታቸው አስተማማኝ የኤሌክትሪክ፣ የንፁህ ውሃ እና የመሠረታዊ አገልግሎቶችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ #gazette_plus

"የኢኮኖሚና የቢዝነስ ዘገባ አዘጋጆች ግልጽና ቀላል ቋንቋን መጠቀም ይጠበቅባቸዋል"
- ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር)
#ethiopia | የኢኮኖሚና የቢዝነስ ዘገባ አዘጋጆች ግልጽና ቀላል ቋንቋን መጠቀም ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር)፤ የዘመን ኢኮኖሚ መጽሄት የይዘትና የቅርጽ ሙያዊ ቅኝት አቅርበዋል።
ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ የኢኮኖሚ እና የቢዝነስ ዘገባዎች ቁጥር፣ ሙያዊና ከባድ ቃላት የሚበዛባቸው ናቸው።
የኢኮኖሚ እና የቢዝነስ ሪፖርተሮች ቀላል እና ግልጽ ቋንቋ መጠቀም እና ቁጥርን ወደቃላት ቀይረው ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ዘመን ኢኮኖሚን መጽሄት በሚመለከት የሚቀርቡት ጹሁፎች ወቅታዊ መሆን፣ መረጃዎች ተተንትነው መቅረባቸው፣ የምንጭ አጠቃቀም፣ የማህበረሰቡን ጉዳይ ሽፋን መሰጠት፣ የፎቶ ግራፍና የዲዛይን አጠቃቀም፣ የአምድ ስብጥር ጠንካራ ጎኖች መሆናቸውን ተናግረዋል።

Comments