Logo
YenetaTube
ትራምፕ የሠራተኛ ቪዛ አመልካቾችን የ100 ሺህ ዶላር ክፍያ አጸደቁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለስራ ወደ አሜሪካ ለሚያቀኑ ቪዛ አመልካቾች ተጨማሪ የ100 ሺህ ዶላር ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያዘውን መመሪያ ፈረሙ፡፡

መመሪያው ፕሮግራሙ ላይ እክል ይፈጥራል የተባለለት ሲሆን፤ ወደ ሀገሪቱ የሚያቀኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች ክፍያውን ካልፈጸሙ ቪዛ ማግኘት እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዝዳን ትራምፕ ጎልድ ካርድ የተባለ ፈጣን ቪዛ የተወሰኑ ስደተኞች በክፍያ እንዲያገኙ መወሰናቸው ተነግሯል፡፡

የቪዛ ፕሮግራሙ ለአሜሪካ ብዙ መቶ ሺህ ዶላሮች የሚያስገኝና ትላልቅ ካምፓኒዎች የተሳተፉበት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ አሜሪካ አሰልጥና ጥቅሟ የሚወሰድበት አሰራር መቆም አለበት ብለዋል፡፡

መመሪያው ከአሜሪካ ውጪ ካምፓኒ ለማቋቋም ላሰቡ ኢንቨስቴሮች ፈታኝ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ተቺዎች በH-1B ቪዛ የአሜሪካን የሰው ኃይል ብቃት ይቀንሳል በሚል ሲከራከሩ ቢቆዩም በተቃራኒው ቢሊኒየሩ ኤሎን መስክ ፕሮግራሙ አሜሪካ ከዓለም የተለያዩ ሙያና ባለሙያዎች የሚያስገኝ ነው ይላሉ፡፡

የአሜሪካ የዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት መረጃ እንደሚያሳየው መመሪያው የፕሮግራሙ የቪዛ አመልካቾች ዝቅ እንደሚል ይገመታል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ እስካሁን በፕሮግራሙ በዓመት 85 ሺህ ቪዛ አመልካቾች ወደ አሜሪካ ገብተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በባለፈው በጀት ዓመት አማዞን፣ ታታ ቴክኖሎጂ፣ ማይክሮሶፍት፣ ሜታ ካምፓኒ፣ አፕልና ጎግል ካምፓኒዎች በፕሮግራሙ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን የአሜሪካ መንግስታዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ፤ ቀጣሪዎች የውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ስፖንሰር የሚያደርጉት በሀገሪቱ የሰራተኞችን ቦታ ተክቶ መስራት የሚችል ባለመኖሩ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ክፍያው በቴክኖሎጂውና በኢንደስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪነት እንዲጎለብት ያግዛል፡፡

Gazette Plus

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.