Logo
YenetaTube
የዓባይ ግድብ የምርቃት መርሀግብር ከቆይታ በኋላ ይጀምራል

ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 የዓባይ ግድብ ምረቃ ስነ ስርዓት መርሃ ግብር ከቆይታ በኋላ ይጀምራል።

የግድቡ የምርቃት ዋዜማ በትናንትናው ዕለት የድሮን ትርዒቶችን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በአሁኑ ሰዓት ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የዓባይ ግድብ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ 233 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደገ ሲሆን፤ ቦንድ በመግዛት፤ ስጦታ በመስጠት እና በሌሎች መንገዶች ህዝብ ትልቅ ተሳትፎ እንዳደረገ በስፋት ተግልጿል፡፡

የግድቡ መጠናቀቅም የኢትዮጵያን አቅም በሁሉም ዘርፍ የሚያሳግ እንደሆነም የተለያዩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ዓባይ ግድብ የሚገኘው በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ሲሆን ግድቡ ግንባታ የተጀመረው መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነው፡፡

ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው የግድቡ የውሃ የመያዝ አቅም 74 ትሪሊዮን ሊትር ውሃ ነው።

የግድቡ ከፍታ ርዝመት 145 ሜትር ሲሆን የግድቡ የጎን ርዝመት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር መሆኑን ታውቋል።ትናንት ዋዜማው በሰማይ ላይ ድሮኖች ትይንት የደመቀው ዓባይ ዛሬ የሲሳይ ብስራት ይበሰርበታል።

በዓባይ ግድብ ንጋት ሀይቅም ከ80 በላይ ደሴቶች መፈጠራቸው ታውቋል።

Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.