Logo
Getu Temesgen
⛪️የጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የልማት ሥራዎች በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተመረቁ! ✨
#ethiopia | ​"ይህ ሥራ የምዕመናን አንድነትና ለቤተክርስቲያን ያላቸው ፍቅር ውጤት ነው" - ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

​በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ሲከናወኑ የቆዩ የልማት ሥራዎች ተጠናቀው ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል።

​በምረቃው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ፣ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፤ የተሰራው የልማት ስራ ለአገልግሎት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ ለሌሎች አድባራትም ትልቅ ምሳሌ መሆኑን መስክረዋል።

​የስኬቱ ሚስጥር:
እነዚህ የልማት ሥራዎች ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ድረስ በምዕመናን ከፍተኛ ርብርብ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና የሞራል ተነሳሽነት የተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል።

​በእለቱም ለልማቱ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።

​ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች እና ለደብሩ ምዕመናን እንኳን ደስ አላችሁ!

​#eotc #straphael #gulele #churchdevelopment #abunehiryakos #addisababa #ethiopianorthodox #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.