የንግሥተ አድባራት ደብረ ብርሃን ሥላሴ ዓመታዊ በዓል ተከበረ
📌 ቤተክርስቲያኑ ሁለገብ እድሳት እንዲደረግለት ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የሚገኘውና በኪነ-ህንፃ ጥበቡ የሚታወቀው የንግሥተ አድባራት ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል ዛሬ ጥር 7 ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አብነ ዮሐንስ፣ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በታላቁ ንጉሥ ዐፄ ኢያሱ (አድያም ሰገድ) የንግሥና ዘመን (1674-1698 ዓ.ም) የተገነባ መሆኑ ይታወቃል።
የኪነ-ህንፃ ባለሙያው፦ ቤተክርስቲያኑ በታዋቂው ባለሙያ ገብረ ሥላሴ አማካኝነት በኖኅ መርከብ ቅርፅ የተገነባ ነው።
በንጹህ ኖራና በተጠረቡ ድንጋዮች የተገነባ ሲሆን፣ የህንፃው ቅርፅ ምዕመናንን ከኃጢአት ማዕበል ጠብቃ ለሰማያዊ ክብር የምታበቃ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ተደርጎ ይወሰዳል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁትንና የቤተክርስቲያኑን ጣሪያና ግድግዳ ያጌጡትን ድንቅ ሥዕላት የሳሉት ባህታዊ አባ ኃይለ መስቀል ወልዱ እንደሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።
ቤተክርስቲያኑ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረና የኢትዮጵያ የጥበብና የሃይማኖት መታወቂያ ቢሆንም፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ምንም ዓይነት እድሳት ሳይደረግለት መቆየቱ ተገልጿል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት ብጹዕ አብነ ዮሐንስ እንደገለጹት፤ ይህንን ታሪካዊ ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና ከጉዳት ለመታደግ ሁለገብ እድሳት ማድረግ አሁን ላይ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ የአለም ቅርስ በሆነው ቤተክርስቲያን ጥገና ላይ በእውቀት በገንዘብ በጉልበት እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#ጌትነት ተመስገን
#debreberhanselassie #gondar #ethiopianorthodox #gondarethiopia #ደብረብርሃንሥላሴ #ጎንደር #ኢትዮጵያ #ተዋህዶ #ቅድስትሥላሴ

7 months ago