ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወጣቶች ቤተሰቦች የ4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከቱ
#ethiopia | በጥምቀት በዓል ዕለት ታቦት በሰረገላ ሲያጅቡ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ አራት ወጣቶች ቤተሰቦችና ለተረፈው አንድ ወጣት፣ ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ።
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ በኮዬ ፈጬ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናኛን ሰጥተዋል።
አደጋው በደረሰ ወቅት በሀገረ ስብከቱ በተዋቀረ የ10 አባላት ኮሚቴ አማካኝነት በንግድና በአቢሲኒያ ባንኮች በተሰበሰበው ገንዘብ መሠረት፦
* ለሦስት ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር፤
* በሕይወት ለተረፈው ወጣትና ለሌሎቹ ቤተሰቦች እንደየጉዳት መጠኑ ከ300 ሺህ እስከ 700 ሺህ ብር፤
* ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ ለተወሰኑት የሥራ ዕድልና የእህል ድጋፍ ተበርክቷል።
"ታማኝ አገልጋዮች ነበሩ"
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በዕለቱ ባስተላለፉት የማጽናኛ ትምህርት፣ ወጣቶቹ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የደረሰ አገልግሎት ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
ከሳምንቱ "ገብር ኄር" (ታማኝ አገልጋይ) ስያሜ ጋር በማያያዝም፣ ቤተሰቦቻቸው በእምነት እንዲጸኑና እንዳያዝኑ አበረታተዋል።
ለሟች ወጣቶች በደብሩ መታሰቢያ ሐውልት የቆመላቸው ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው ይህን የተቀናጀ የድጋፍ ሥራ ላከናወኑት ኮሚቴዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላት ምስጋና አቅርበው መርሐ ግብሩን በጸሎት አጠናቀዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያን #ብፁዕአቡነሳዊሮስ #ኮዬፈጬ #ሰብአዊድጋፍ #ተዋሕዶ #ethiopianorthodox

5 months ago