የትንሳኤ በዓል አስመልክቶ ወደ እየሩሳሌም ታቅዶ የነበረው መንፈሳዊ ጉዞ ተራዘመ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ሃይማኖታዊ ጉዞ አዘጋጅ ድርጅቶች ማህበር ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ወደ እየሩሳሌም ታቅዶ የነበረው መንፈሳዊ ጉዞ መራዘሙን ማህበሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ማህበሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ በታሪክ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባለቤትነት የሚመሩ ከስድስት በላይ ገዳማት የሚገኙባት ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም፣ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን የምታስተናግድ ታላቅ የሃይማኖት ስፍራ ብትሆንም አሁን ላይ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የጉዞ መርሃ ግብሩ ላይ ለውጥ ለማድረግ መገደዱን ገልጿል።
ለዘንድሮው የትንሳኤ በዓል ጉዞ በርካታ ምዕመናን አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀውና የቪዛ ሂደታቸውን ጨርሰው የነበረ ቢሆንም፣ በእስራኤልና በአካባቢው ባለው ወቅታዊ ግጭትና የሰላም እጥረት ምክንያት የአየር ክልል መዘጋትና የበረራዎች መስተጓጎል በመፈጠሩ ጉዞው ለምዕመናን ደህንነት ሲባል እንዲራዘም ተወስኗል።
ማህበሩ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ምዕመናን ያለ ምንም ስጋት ሃይማኖታዊ ስርአታቸውን መፈጸም የሚችሉበት አስተማማኝ ሁኔታ ባለመኖሩ መሆኑን ገልጾ፣ በቅርብ ክትትል ሁኔታዎችን እያጠና መሆኑንም ጠቁሟል።
በመሆኑም አሁን ያለው ስጋት ተወግዶና በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም መስፈኑ ሲረጋገጥ፣ በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ለሚከበረው በዓለ እርገት ጉዞው የሚከናወን መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
ምዕመናን በትግስትና በጸሎት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ እንዲጠባበቁ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ማህበሩም ቀጣይ ጉዞዎችን በተመለከተ መረጃዎችን ተከታትሎ ለተጓዦች እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#jerusalempilgrimage #ethiopianorthodox #pilgrimageupdate #faithjourney #holyland #ethiopia #spiritualtravel #newsupdate

4 months ago