5 months ago
የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወላጅ እናት እማሆይ አስካለ ማርያም የሥርዓተ ቀብር ሥነ ሥርዓት ተከናወነ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት እና የአፋን ኦሮሞ ቴሌቪዥን ጣቢያ የበላይ ኃላፊ እንዲሁም የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወላጅ እናት እማሆይ አስካለ ማርያም (ወይዘሮ አምሳለ ወርቅ ማሞ) በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
እማሆይ አስካለ ማርያም በ1933 ዓም በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መምህር አገር ቦሰቄ በተባለ ሥፍራ ከአባታቸው አቶ ማሞ ወልደየስና ከእናታቸው ወይዘሮ አጸደ በየነ ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በአካባቢያቸው በሚገኝ ትምህርት ቤት የመሠረተ ትምህርት እውቀትን ገብይተዋል።
በ1948 ዓም ከአባ ክንፈ ሚካኤል (አቶ ጌታነህ የኋላሸት) ጋር ትዳር በመመሥረት ስድስት ወንዶችና ሁለት ሴቶችን በድምሩ ስምንት ልጆችን ወልደው በሃይማኖትና በሥነ ምግባር ኮትኩተው አሳድገዋል።
ሟች እናት ለስምንት ልጆች እናት ከመሆናቸውም ባለፈ ለ38 የልጅ ልጆች፣ ለ20 የልጅ ልጆች ልጆች እንዲሁም ለ4 ቅም አያት ለመሆን የበቁ የልጅ ጸጋ የበዛላቸው እናት ነበሩ።
በሰው ዘንድ እጅግ የተወደዱ፣ ትሑት፣ እንግዳ ተቀባይና ለችግረኞች ሩኅሩኅ በመሆናቸው በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ነበራቸው።
የትዳር አጋራቸው ካረፉ በኋላ ቀሪ ሕይወታቸውን በጾም፣ በጸሎትና በትህርምት በመምራት አምላካቸውን ሲያገለግሉ ቆይተው ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓም በ85 ዓመታቸው አርፈዋል።
የሥርዓተ ቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በሉሜ ሞጆ ወረዳ ኤጀሬ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተሸኝተዋል።
#orthodoxtewahedo #eotc #abunemathewos #mojjo #ethiopianorthodox #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments