2 months ago
የሞተው ሕያው የሆነበት ማሩ ከዋሻ የሚፈስበት አስደናቂው ስፍራ
♦️ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
#ethiopia | በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ምስራቅ በለሳ ወረዳ፣ ጎጋ ቀበሌ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፤ የቀደመ ታሪኩን ፣ የተፈጥሮ ግርማውንና ታአምራት በአንድ ላይ የያዘ ድንቅ መንፈሳዊ ስፍራ ነው።
አባቶች እንደሚያስረዱት የስፍራው የቀደመ መጠሪያ "ዛጅር ማኤል" ይሰኝ ነበር። ይህ ስም "ዛጅር" ማለት ውሃ በደረቅ አለት ላይ ፈንጥቆ የሚወጣበትን አቅጣጫ ሲያመላክት፣ "ማ" ዋሻውን፣ "ኤል" ደግሞ የሰማይ አምላክን በመወከል እግዚአብሔር በድንቅ ሁኔታ በደረቅ አለት ላይ ውሃ የፈነጠቀበት ስፍራ መሆኑን ይናገራሉ።
የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የስብከተ ወንጌል ኃላፊ እና ጸኃፊ አባ ብርሃነ ሠላም እንደሚገልጹት፣ የቦታው ተአምራዊ ጉዞ በይፋ ጎልቶ መታየት የጀመረው በ2013 ዓ.ም የጸበል አገልግሎት ሲጀመር ነው።
በተለይም የስፍራውን ስም ከአዲሱ ስያሜ ጋር ያያዘው ታዓምር በዚሁ ዘመን ተከስቷል። ከገዳሙ 12 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በምትገኘው ዙ ሐሙሲት ከተማ አቅራቢያ የምትኖር አንዲት ሴት በጽኑ ታማ ወደ ህክምና ከተወሰደች በኋላ በቃሬዛ ላይ እያለች ህይወቷ ያልፋል።
በወቅቱ የጸበሉ አስተዳዳሪ የነበሩት አባት እና ሌሎች ካህናት አስከሬኑን ይዘው በመንገድ ላይ ሳሉ የእግዚአብሔርን ኃይል በማመን ቅዱስ ጸበሉን አፍሰው ረጩባት። በዚያው ቅጽበት የሞተችው ሴት ትንፋሽ ተመልሶላት ተነሳች፤ ሙሉ ፈውስ አግኝታም ድንቅ ምስክርነቷን ሰጠች።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጸበሉ "ሙት አንሳ" የሚለውን ስያሜ አገኘ። በኋላም ከዋሻው በላይ ከሚንጠበጠበው ማር ጋር ተያይዞ "ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም" ተብሎ መጠራት ጀመረ።
የገዳሙ መነኮሳት እንደሚናገሩት በዋሻው ጣሪያ ላይ ለዘመናት ሳይቆረጥ የቆየ ልዩ ማር ይገኛል። ይህ ማር በተለያዩ ጊዜያት በራዕይ "ተቆርጦ ለምእመናን ፈውስ ይሁን" የሚል መልእክት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም፣ የቦታው ገደላማና አስፈሪ አቀማመጥ ማንም እንዲደፍረው አላደረገም።
ቆየት ብሎ መነኮሳቱ በጸሎትና በምህላ ሲገቡ ንቡ ቦታውን ለቆ ይወጣል። ማሩ አሁን ላይ እየተቆረጠ ለበርካታ ድውያናትና ምእመናን ዘላቂ ፈውስን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ዛሬ ለቁጥር በርካታ የሆኑ መነኮሳት የሚኖሩበት ይህ ታላቅ ገዳም የተመሰረተው በአንድ አባት መንፈሳዊ ታዛዥነትና ጽናት ነው። አባ ብርሃነ ሠላም እንደሚያስረዱት፣ በ2009 ዓመተ ምህረት ግንቦት 21 ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ አባ ብርሃነ ማርያም ከድዊ አንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ በፊታቸው የተለየ ብርሃን እየመራቸው
ቦታው ይደርሳሉ።
ያን ብርሃን እየተከተሉ የሶስት ሰዓት መንገድ በእግር ተጉዘው አሁን ገዳሙ በሚገኝበት ስፍራ ሲደርሱ ብርሃኑ ተሰወረባቸው። በወቅቱ ምንም ዓይነት መኖሪያ ቤትና መጠለያ በሌለበት፣ የክረምቱ ዝናብና ቅዝቃዜ በበዛበት ወቅት አባታችን በእርጥብ ዋሻ ውስጥ ማደር ጀመሩ።
እግዚአብሔርም በቸርነቱ የሚያድሩበትን ስፍራ ደረቅ በማድረግ ጠበቃቸው፤ የዕለት ምግባቸውንም የአካባቢው ህዝብና ጸበልተኞች እያመጡ ያቀርቡላቸው ነበር።
የአባታችንን ትምህርትና ተአምራዊ ፈውሱን ያዩ በርካታ መንፈሳውያን ልጆች በየጊዜው ወደ ስፍራው በመምጣታቸው የምናኔ ሀሳብ በብዙዎች ህሊና ውስጥ ሰረፀ። አባ ብርሃነ ሠላም አያይዘው እንደሚገልጹት፣ በ2011 ዓመተ ምህረት በአካባቢው ሰበካ ጉባኤ ድጋፍ የተገዙ በሬዎችን በመጠቀም መሬት ማረስና የጋራ ኑሮ ተጀመረ። በ2013 ዓመተ ምህረት የመነኮሳቱ ቁጥር ከመቶ በላይ በመድረሱ የአካባቢው ህዝብና ካህናት ተመካክረው ቦታ በመስጠታቸው ትንሽ መቃኞ ተሠርቶ ታቦተ ሚካኤል ገባ።
በመጨረሻም በ2014 ዓመተ ምህረት መስከረም 29 ቀን በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቡጽዕ አቡነ ዮሐንስ አባታዊ ቡራኬና ውሳኔ ገዳም የመሆን ሙሉ ክብሩንና ስያሜውን አገኘ።
ይህን መንፈሳዊና ታሪካዊ ገዳም የሚገኘው ከአዲስ አበባ
በሰሜን አቅጣጫ 667 ኪሎ ሜትር፣ ከባህርዳር ከተማ 183 ኪሎ ሜትር፣ ከዞኑ ጎንደር ከተማ በአዲስ ዘመን - እብናት -ጎሃላ 192 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከጎንደር ማክሰኚት- አረባያ -ጎሃላ 119 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፤ በአባቶችና በእናቶች ጸሎትና በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ እስከ ዛሬ የቆየ፣ ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ መንፈሳዊ አደራ ነው።
ይህ ገዳም ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። ከሰሞኑን በገዳሙና በአካባቢው በመዘዋወር እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ሥራዎች ተመልክተናል፤ የተመለከትነውንም በተከታታይ ክፍሎች እናቀርብላችኋለን።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#mutansa #ethiopianmonastery #gondarethiopia #ethiopianorthodox #spiritualjourney

9 months ago
የንግሥተ አድባራት ደብረ ብርሃን ሥላሴ ዓመታዊ በዓል ተከበረ
📌 ቤተክርስቲያኑ ሁለገብ እድሳት እንዲደረግለት ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የሚገኘውና በኪነ-ህንፃ ጥበቡ የሚታወቀው የንግሥተ አድባራት ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል ዛሬ ጥር 7 ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አብነ ዮሐንስ፣ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በታላቁ ንጉሥ ዐፄ ኢያሱ (አድያም ሰገድ) የንግሥና ዘመን (1674-1698 ዓ.ም) የተገነባ መሆኑ ይታወቃል።
የኪነ-ህንፃ ባለሙያው፦ ቤተክርስቲያኑ በታዋቂው ባለሙያ ገብረ ሥላሴ አማካኝነት በኖኅ መርከብ ቅርፅ የተገነባ ነው።
በንጹህ ኖራና በተጠረቡ ድንጋዮች የተገነባ ሲሆን፣ የህንፃው ቅርፅ ምዕመናንን ከኃጢአት ማዕበል ጠብቃ ለሰማያዊ ክብር የምታበቃ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ተደርጎ ይወሰዳል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁትንና የቤተክርስቲያኑን ጣሪያና ግድግዳ ያጌጡትን ድንቅ ሥዕላት የሳሉት ባህታዊ አባ ኃይለ መስቀል ወልዱ እንደሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።
ቤተክርስቲያኑ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረና የኢትዮጵያ የጥበብና የሃይማኖት መታወቂያ ቢሆንም፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ምንም ዓይነት እድሳት ሳይደረግለት መቆየቱ ተገልጿል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት ብጹዕ አብነ ዮሐንስ እንደገለጹት፤ ይህንን ታሪካዊ ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና ከጉዳት ለመታደግ ሁለገብ እድሳት ማድረግ አሁን ላይ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ የአለም ቅርስ በሆነው ቤተክርስቲያን ጥገና ላይ በእውቀት በገንዘብ በጉልበት እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#ጌትነት ተመስገን
#debreberhanselassie #gondar #ethiopianorthodox #gondarethiopia #ደብረብርሃንሥላሴ #ጎንደር #ኢትዮጵያ #ተዋህዶ #ቅድስትሥላሴ

Comments