10 days ago
የኢቢሲ የለውጥ ሥራዎች አገርን የሚጠቅሙና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጸባርቁ ናቸው፦ ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን
*****************************
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እያከናወናቸው ያሉ ሁለንተናዊ የለውጥ ሥራዎች ለሀገር የሚበጁና እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን ገለጹ።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ እና የሊቃውንት (ኡለማዎች) ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።
አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት የተቋሙን ታሪክ፣ የወቅታዊ ይዘት ዝግጅቶችን፣ የተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎችን እንዲሁም ተቋሙ ዘመኑን በዋጁ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች ራሱን እያደራጀ መሆኑን በአካል ተመልክተዋል።
ሼህ አብዱልከሪም በሰጡት አስተያየት፣ ኢቢሲ በውስጣዊ አደረጃጀቱም ሆነ በሚሠራቸው የሚዲያ ሥራዎች ኢትዮጵያዊነትን በተግባር የሚያንጸባርቅ ትልቅ ተቋም መሆኑን መታዘባቸውን ገልጸው፣ ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ እነዚህ የለውጥ ሥራዎቹ ተቋሙን "የኢትዮጵያ ራስ" አድርገውታል ብለዋል።
ምክር ቤቱ ለአዲሱ ትውልድ ጠቃሚ የሆኑ አገራዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅርበትና በትብብር ለመሥራት ሙሉ ፈቃደኛና ዝግጁ መሆኑንም ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን በዚህ አጋጣሚ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መላው ሕዝበ ሙስሊም መጪውን ታላቁን የዒድ አል-አድሐ (ዓረፋ) በዓል ሃይማኖታዊ አስተምህሮውን በጠበቀ መልኩና በተለመደው ውብ የኢትዮጵያዊ የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴት እንዲያከብረው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በዘሃራ መሀመድ
#ethiopia #ebc #islamicaffairs #mediareform #ethiopianism #eidaladha

18 days ago
የሰላም ድርድር መቋረጥ፣ የሆርሙዝ ሰርጥ አዳዲስ ክልከላዎች እና የባራካህ የኑክሌር ጣቢያ ጥቃት
**************
በመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ድርድር ጥረቶች፣ በሆርሙዝ ሰርጥ የባሕር ላይ መተላለፊያ ቁጥጥር እና በተመዘገቡ የጸጥታ ስጋቶች ዙሪያ አዳዲስ ክስተቶች ተመዝግበዋል።
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የነበረው ቀጥተኛ ድርድር መቋረጡን ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱ ያሻቀበ ሲሆን፣ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴን ለመቆጣጠርም አዳዲስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።
የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪ አስቀድሞ ያልተገለጸ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ቴህራን መግባታቸውን የፓኪስታኑ ‘ዶን’ ጋዜጣ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ይህ አስቸኳይ ጉብኝት የተደረገው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን የቅርብ ጊዜ የሰላም አማራጭ ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ የሰላም ድርድሩ ሙሉ በሙሉ እንዳይደናቀፍ ለማድረግ የተጀመረው የሽምግልና ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።
የኢራኑ ‘ተስኒም’ የዜና ወኪል በበኩሉ፣ ሚኒስትሩ ከኢራን አቻቸው ኤስካንዳር ሞሜኒ እና ከፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ባጌር ጋሊባፍ ጋር ተገናኝተው በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል ያለውን የሰላም ድርድር ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ጠቁሟል።
ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንዳስነበበው፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢራንን የሰላም ሃሳብ ውድቅ ቢያደርጉም፤ ኢራን የኑክሌር መርሐ ግብሯን ለ20 ዓመታት እንድታግድ የሚጠይቅ አማራጭ አቅርበዋል።
ይሁን እንጂ የኢራን ባለሥልጣናት በአሜሪካ ወገን ምንም ዓይነት ተጨባጭ የዲፕሎማሲ አካሄድ ለውጥ አልታየም ሲሉ መተቸታቸውን መህር የዜና ወኪል ዘግቧል።
የሆርሙዝ ሰርጥን በተመለከተ ኢራን የባሕር ላይ መተላለፊያውን ለመቆጣጠር አዲስ “ሙያዊ የአሠራር ሥርዓት” ያለችውን የቁጥጥር ሥርዓት ይፋ እንደምታደርግ አስታውቃለች።
የኢራን ፓርላማ የብሔራዊ ደኅንነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢብራሂም አዚዝን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ አዲሱ አሠራር ከኢራን ጋር ለሚተባበሩ የንግድ መርከቦች ብቻ ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፣ የአሜሪካ ደጋፊ ለሆኑ መርከቦች ግን ዝግ ይሆናል።
በተጨማሪም ኢራን በዲጂታል እና በቢትኮይን ክፍያ የሚሠራ “ሆርሙዝ ሴፍ” የተባለ አዲስ የባሕር ላይ መድን ይፋ ማድረጓን ፋርስ የዜና ወኪል አረጋግጧል።
በሆርሙዝ ሰርጥ ያለው የባሕር ላይ ትራፊክ አሁንም እንደቀዘቀዘ መሆኑን እና አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት መርከቦቻቸው በሰላም እንዲያልፉ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ጋር ድርድር መጀመራቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል።
በሌላ በኩል የቀጣናውን ሰላም ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርግ ክስተት ተመዝግቧል። በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች በሚገኘው የባራካህ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የድሮን ጥቃት ደርሷል።
‘አሶሺዬትድ ፕሬስ' እንደዘገበው ጥቃቱ ከኃይል ማመንጫው የውስጠኛው አጥር ውጭ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ጄነሬተር ላይ እሳት ቢያስነሳም፣ የኢምሬቶች ባለሥልጣናት እሳቱን በፍጥነት መቆጣጠር መቻሉን እና ምንም ዓይነት የጨረር ስጋትም ሆነ የሰው ጉዳት አለመድረሱን አረጋግጠዋል።
ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ጥቃቱን “ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ አውግዘውታል።
በመካከለኛው ምሥራቅ በአንድ በኩል ዲፕሎማሲያዊ የሰላም ጥረቶች ቢቀጥሉም፣ በሌላ በኩል እየተከሰቱ ያሉ የጸጥታ ስጋቶች ቀውሱ ወደ ከፋ ጦርነት እንዳያመራ ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ዓለም አቀፍ የጂኦፖለቲካ ተንታኞች በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።
በለሚ ታደሰ
#middleeastcrisis #peacetalks #straitofhormuz #diplomacy #globalenergy

22 days ago
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ተሸኙ
#ethiopia | የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ሲያደርጉት የነበረውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በስኬት አጠናቀው ከሀገር መውጣታቸው ታውቋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ኩነቶችን ካከናወኑ በኋላ አመሻሹን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አማካኝነት አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
የፕሬዝዳንት ማክሮን ጉብኝት በርካታ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑበት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን የሳይንስ ሙዚየምን መጎብኘታቸው እንዲሁም በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የተካሄደው የሁለትዮሽ ውይይት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የኃይል እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስምምነቶች ተፈርመዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል ለታዳሽ ኃይል እና ለዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት እንዲሁም የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል ኃይል ልማት የመንገድ ካርታ ይገኙበታል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት በቆይታው የተደረጉት ውይይቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት ይበልጥ ያጠናከሩ ናቸው፡፡
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ለሚኖረው የወደፊት የሁለትዮሽ ግንኙነት ጠንካራ መሠረት ጥሎ ማለፉንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ፈረንሳይ #ዲፕሎማሲ #ኢኮኖሚ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

"የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ዘመን እየመጣ ነው" :- ጆን ሪጅን
#ethiopia | የዓለም አትሌቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆን ሪጅን እና የጨረታዎች፣ ውድድሮችና ሁነቶች ዳይሬክተር ማርክ ኸረስት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አከናውነዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በቆይታቸው ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ግንባታው በመከናወን ላይ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ፣ ለስፖርቱ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸውን አስመልክተው መግለጫ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጆን ሪጅን፤ "ከ25 ዓመታት በፊት ለታላቁ ሩጫ አዲስ አበባ መጥቼ ነበር፤ አሁን ግን ከተማዋ እጅግ ተለውጣለች፣ በሚገርም ሁኔታም ዘምናለች" ብለዋል።
በተመለከቷቸው መሠረተ ልማቶችና ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች እጅግ መደሰታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ "የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ቀን እየመጣ ነው" ሲሉ ያላቸውን ታላቅ ተስፋ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን በበኩላቸው፤ የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት እያሳዩ ላለው ድጋፍና ማበረታቻ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ የ2028 "አልቲሜት" ሻምፒዮንሽፕ እና የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ከግብ ለማድረስ፣ ፌዴሬሽኑ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በቅርበትና በትብብር እየሠራ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #ebcsport #ethiopia #ebc #ኢትዮጵያ #አትሌቲክስ #ፌዴሬሽን

23 days ago
ለምን ወደ ኢትዮጵያ...
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲፕሎማሲ የሀገር ህልውና እና ክብር መጠበቂያ መሳሪያ ነው።
ይህ የሚሆነው ግን የውጭ ግንኙነት እሳቤ እና አተያይ የጠራ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ''መደመር'' በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ ይህ ሐሳብ በጥልቅ ተተንትኗል።
''ሚዛናዊ ግንኙነት'' የሚለው ደግሞ ተጠቃሹ ነው። ኃያላን ሽኩቻ ውስጥ በገቡበት ዓለም የአንደኛው ወገን ከመሆን ይልቅ ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ባደረገ ሚዛናዊ ግንኙነት ከሁሉም ጋር በትብብር መስራት አዋጭ ነው።
ይህ ከቀደሙት ዓመታት የተለየ የኢትዮጵያ አዲስ የውጭ ግንኙነት እሳቤ እና አተያይ ዓለም ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሰራ አድርጓል።
የተለያየ ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ሀገራት እና መንግሥታት ወደ ፕራግማቲኳ ኢትዮጵያ እንዲተሙም ማድረግ ችሏል።
ከሕንድ እስከ ቱርክዬ፣ ከጣሊያን እስከ እስራኤል፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እስከ ኢንዶኔዢያ፣ ከጅቡቲ እስከ ጀርመን... ሶማሊያ ብዙ ብዙ... በአዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ስበት በርዕሳነ መንግሥታት የተመሙ ናቸው።
ፈረንሳይ ደግሞ በዚህ ረገድ ቀዳሚ ነች። ከ12 አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮ-ፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመደመር መንግሥት ዘመን የላቀውን ምዕራፍ ተቀዳጅቷል።
ለዚህም በመሪዎች ደረጃ የተደረገውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማየት ብቻ በቂ ነው።
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ይፋዊ ጉብኝታቸውን ያደረጉት በመጋቢት ወር 2011 ዓ.ም ነበር።
ፕሬዚዳንት ማክሮን በሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝታቸው ሀገራቱ በትብብር በሚሰሯቸው የመከላከያ፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በርካታ ስምምነቶች ተፈርመዋል።
ፈረንሳይ ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ቅርስ እድሳት በሙያና በገንዘብ ድጋፍ የምታደርግበት ማዕቀፍ ደግሞ ሌላው ተጠቃሹ ነው።
ፕሬዚዳንቱ በላሊበላ ተገኝተው ቅርሱን መጎብኘታቸውም የሚታወስ ነው።
ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ደግሞ ባሳለፍነው ዓመት ታሕሣሥ ወር 2017 ዓ.ም ነበር።
በወቅቱ መሪዎቹ በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ወደ ልዩ አጋርነት አድጎ ታይቷል።
በወቅቱም ፈረንሳይ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ እንደምትደግፍ ፕሬዚዳንቱ ይፋ አድርገዋል።
በአንድ ቀን ቆይታቸውም በመንግሥታቸው የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውን ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጎብኝተዋል።
አሁን ደግሞ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአዲስ አበባ ለሦስተኛ ጊዜ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው።
ይህም በሰባት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገ ይፋዊ ጉብኝት ሲሆን÷ የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ አዲስ አበባ ተደጋጋሚ መምጣት ሁለት ነገሮችን ይነግረናል፡፡
እድሜ ጠገቡ የኢትዮ-ፈረንሳይ ግንኙነት በሁሉም መስክ መጠናከርና ማደጉ ቀዳሚው ሲሆን÷ ከመደመር የውጭ ግንኙነት እሳቤዎች ውስጥ የሚዛናዊ ግንኙነት ዘውግ ግቡን መምታቱ ደግሞ ሁለተኛውና ዋነኛው ነው፡፡

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ
#ethiopia | የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሦስተኛው ይፋዊ የሥራ ጉብኝትዎ በፈረንሳይና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጸና ወዳጅነት ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉም አመልክተዋል።
ወሳኝ እና ፍሬያማ በሆኑ ውይይቶች ላይ ትኩረት በምናደርግበት በዚህ ወቅት አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ እርሱም በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ያለው ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ብቻ የሚዘልቅ ነው ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ አዲስ አበባ ለገቡት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት “የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ወንድሜ ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራት እና ደስታ ነው” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሦስተኛው ይፋዊ የሥራ ጉብኝትዎ በፈረንሳይና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጸና ወዳጅነት ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል።
”ወሳኝ እና ፍሬያማ በሆኑ ውይይቶች ላይ ትኩረት በምናደርግበት በዚህ ወቅት አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ እርሱም በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ያለው ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ብቻ የሚዘልቅ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት።
#ebc

የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ ጋር ከ ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ አብረው ገብተዋል ::
በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሦስተኛው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በፈረንሳይና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጸና ወዳጅነት ጉልህ ማሳያ ነው።
seledadotio

Sponsored by
Surafel
30 days ago
ኢራን ቻይና ገባች
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ በመጣው ውጥረትና በዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያ ላይ የተደቀነውን ስጋት ተከትሎ፣ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ቤጂንግ ማቅናታቸው ተሰማ።
ሚኒስትሩ ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር የሚያደርጉት ይኸው ምክክር፣ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥምር ጥቃት ሳቢያ በነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ላይ ጉዳት ደርሶ፣ የዓለም የነዳጅ አቅርቦት መስመር ከፍተኛ መናጋት በገጠመው ወቅት የተደረገ በመሆኑ ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ትርጉም ተሰጥቶታል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ መሪዎች በዋናነት ቀጣላዊና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ አመልክቷል። ቻይና በበኩሏ ጉብኝቱ በነገው ዕለት እንደሚከናወን አረጋግጣለች።
ይህ ጉብኝት ኢራን ከምስራቁ ኃያል ሀገር ቻይና ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ ትብብር በማጠናከር፣ በምዕራባውያን የሚሰነዘርባትን ጫና ለመቋቋም እና በነዳጅ ገበያው ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት በጋራ ለመፍታት የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#iran #china #diplomacy #oilmarket #abbasaraghchi #middleeast #geopolitics #new

1 month ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት ያከናወኗቸው ተግባራት
በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳይንሳዊ የምርምር ልህቀት፣ በከተማ ልማት፣ በኢኮኖሚ ሪፎርም እና በቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።
• የፕሮጀክቶች ምረቃ እና የሥራ ጅማሮ
የመጋቢት ወር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ውስጥ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀዋል። ይህ ማዕከል 40 የላብራቶሪ ክፍሎችን እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮ-ኢኩቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን ያካተተ ነው።
በከተማ ልማት ዘርፍ፣ የሚያዝያ ወር በአገልግሎት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ግንባታ ረገድ ጉልህ እመርታ የታየበት ወር ነበር። የአራዳ ፓርክ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ገጽታ ለውጥ የታየበት ሲሆን፤ ቀደም ሲል ችላ ተብለውና ለአደጋ ተጋልጠው የነበሩ ቤቶች የሚገኙበትን 40 ሄክታር መሬት ወደ ዘመናዊ ሁለገብ መዳረሻነት ቀይሮታል። ይህ የተቀናጀ የመሠረተ-ልማት እና የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት የታየበት ፕሮጀክት፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ700 በላይ ነባር ቤቶችን የማደስ ስራን አካቷል።
ከዚህም በተጨማሪ በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና የኦሊምፒክ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መሠረተ-ልማቶችን፣ የ15 የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዎችን ሃውልት እና ለተነሺ ነዋሪዎች ተብለው የተገነቡ 105 የንግድ ሱቆችን የያዘው የአዲስ ስፖርት ፓርክ በዚሁ ወር ተመርቋል።
የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት አቅም ለማሳደግ የ100 ሜጋ ዋት የአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተመርቋል። በተጨማሪም በሀዋሳ የቶዮ ምዕራፍ 2፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል። እነዚህ ፋብሪካዎች ከአዲሱ የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ፋብሪካ ጋር በመሆን በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹህ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቱሪዝም ዘርፍ፦ በገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር የተገነባው የሀሮ ደንዲ ሎጅ በይፋ ተመርቋል። በመጨረሻም፣ እንደ መታወቂያ ምዝገባ እና የሥራ ፈቃድ ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የታለመው የመሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት ስራ ጀምሯል።
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ ኅብረት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ጤና መሪ ሆነው የተሾሙት በያዝነው የሚያዝያ ነው።
ይህ ኃላፊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአካታች ዕድገት ቁልፍ መሣሪያ የሆኑትን የፈጠራ ሥራዎችን እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማሳደግ ረገድ እያሳዩት ያለውን የአመራር ጥበብ እውቅና የሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንቁ አመራር ሰጪነት በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ያስመዘገበችውን ጉልህ ስራ የሚያሳይ ነው።
• የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአፈጻጸም ግምገማ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሦስተኛውን የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም እና የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ግምገማ መርተዋል። በዚህም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት 9.2 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ወደ 10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል። ሪፖርቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ የተመዘገበውን ስኬታማ ሽግግር በዝርዝር ያሳየ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ያስመዘግቡ የነበሩ ተቋማት በአሁኑ ወቅት 2.1 ትሪሊዮን ብር ገቢ ወደ ማስገባት ተሸጋግረዋል። ለዚህ ውጤት መገኘት ቁልፍ የሆነው የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገቱ ዋና መሪ እንዲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው የሪፎርም አጀንዳ ነው።
ይህም እንደ ካፒታል ገበያ ባሉ አዳዲስ የፋይናንስ ሥርዓቶች እና እያደገ በመጣው የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት እየተደገፈ ይገኛል።
• የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማጠናከር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) እና ሮቦቲክስን በመጠቀም ወደ ቺፕስ እና ዳታ (ኢንዱስትሪ 4.0) መሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ የውጭ ምርቶችን መተካት የቻለው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የይዞታ መጠን ወደ 88 በመቶ ማድረሱን በስኬትነቱ ጠቅሰዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ሰላማዊ የባሕር በር ማግኘት የሀገር የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዳትሆን ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ እንደሚጨምርባት አስገንዝበዋል።
• ማህበራዊ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ አመራር፦
“ማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በተሰኘው እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክክር መድረክ ላይ፣ መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ19.8 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን እና ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ሥርዓተ-ትምህርት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።
በጤናው ዘርፍም በቅደመ መከላከል እና አክሞ ማዳን፤ መካከል የተሻለ ሚዛን ለመፍጠር ለ30 ዓመታት ያገለገለው ፖሊሲ እንዲሻሻል ተደርጓል። በአካባቢ ጥበቃ ረገድም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የኮፕ32 (COP32) ጉባኤን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት የጀመረች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዝግጅቱ ከሀገራዊው የአረንጓዴ ልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴውን ሰብስበው አቅጣጫ ተሰጥተዋል።
• ዲፕሎማሲ እና ቀጣናዊ ትስስር፦
ኢትዮጵያ የብሩንዲ፣ የላይቤሪያ፣ የደቡብ ሱዳን እና የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንቶችን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያስተናገደች ሲሆን፤ ይህም በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ በርካታ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አስችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር፣ ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት (Afrexim) ባንክ ፕሬዝዳንት፣ እንዲሁም ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጅቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትርን በመቀበል በሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፤ ከአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ጋር ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ጤና ረገድ የተሰጣቸውን ሚና ጨምሮ ሰፋ ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በሀገር ውስጥ ጉዳይ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በመገናኘት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ የፕሬዝዳንቱን የሥራ ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት በይፋ አራዝመዋል።
የሚያዝ ወር የትንሳኤ በዓል የተከበረበት በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በማዘጋጀትና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ በማጋራት ተጠናቋል።
#ethiopiadelivers #pmoethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ጋር ተወያዩ
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።
ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
እንደ መርሃ ግብሩ መግለጫ፣ የመሪዎቹ ምክክር ትኩረት የሚያደርገው በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር፣ በጸጥታ፣ በንግድ እና በጋራ የልማት መስኮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ነው።

''የኡጋዱጉ አዛዥ ኢብራሂም ትራኦሬ ሰላም አምጥቷል''ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ
#ethiopia | የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በኡጋዱጉ ባደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት፣ ከቡርኪና ፋሶው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ጋር በወቅታዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ይህ ስብሰባ በተለይ በሕብረቱ እና በታገዱት የሳሕል ቀጣና ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማደስ አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ ሆኗል።
ፕሬዝዳንት ንዳይሺሚዬ፣ መሪው ኢብራሂም ትራኦሬ ለሀገራዊ ሰላምና መረጋጋት እያሳዩት ያለውን "ጽኑ ቁርጠኝነት" በማድነቅ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሊቀመንበሩ ስለ ሳሕል ቀጣና እና ስለ ቡርኪና ፋሶ ህዝብ ነባራዊ ሁኔታ ካለባቸው የተዛባ ግንዛቤ ወጥተው፣ አሁን "ተጨባጭ እውነታውን" በተሻለ ሁኔታ መረዳታቸውን ገልጸዋል።
ወደ የጋራ መጻኢ እድል በጋራ ለመጓዝ የሚያስችል፣ ሀቀኛ እና በነባራዊ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሪፖርት ለአፍሪካ ሕብረት ለማቅረብ ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ጉብኝት በዋናነት በአሁኑ ወቅት ከአባልነታቸው የታገዱት የሳሕል ሀገራት ከሕብረቱ ጋር ዳግም የሚገናኙበትን "የትብብር ድልድይ" ለመገንባትና ለማጠናከር ያለመ ነው። የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ውይይቱ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት አካል ነው።
የስፑትኒክ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ይህ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ በቡርኪና ፋሶ እና በጎረቤቶቿ ላይ የሚታየውን ጫና ለማርገብ ትልቅ ፋይዳ ሊኖረው ይችላል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#አፍሪካ_ሕብረት #ቡርኪና_ፋሶ #ኢብራሂም_ትራኦሬ #ኤቫሪስቴ_ንዳይሺሚዬ #ሳሕል #አፍሪካ #ሰላም_እና_መረጋጋት

2 months ago
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአሥር ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በአልጄሪያ ጀመሩ
#ethiopia | የቫቲካኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአራት የአፍሪካ አገራት የሚያደርጉትንና አሥር ቀናት የሚፈጀውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት በአልጄሪያ ጀምረዋል።
ቅዱስነታቸው በአልጄሪያ መዲና ሲደርሱ በፕሬዝዳንት አብደልማጅድ ተቡኔ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በመጀመሪያው ቀን ውሏቸውም አልጄሪያ ለነፃነቷና ለሉዓላዊነቷ ባደረገችው ተጋድሎ ለወደቁ ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ እውነተኛ ሰላም የፍትህና የክብር መገለጫ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ሊረጋገጥ የሚችለው በይቅርታ ብቻ እንደሆነ አሳስበዋል።
ቅዱስነታቸው በአልጄሪያ፣ በካሜሩን፣ በአንጎላና በኢኳቶሪያል ጊኒ የሚገኙ 11 ከተማዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቫቲካን ከፍተኛ ባለሥልጣን ካርዲናል ማይክል ቼርኒ እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ ከ20 በመቶ በላይ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በሚኖሩባት አፍሪካ ላይ የዓለምን ትኩረት ለማሳረፍ ያለመ ነው።
በጉዟቸው ወቅት ሰላም፣ ስደት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የወጣቶችና የቤተሰብ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚመክሩ ታውቋል።
ይህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት በአህጉሪቱ ካሉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመለማመድ ባለፈ፣ አፍሪካ አሁን ላይ ለምትገኝባቸው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የቫቲካንን አጋርነት ለማሳየት ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #channeltv #vatican #popeleoxiv #africatour #algeria #cameroon #angola #equatorialguinea #peace #catholicchurch #ርዕሰሊቃነጳጳሳት #አፍሪካ #ሰላም #ቫቲካን

ከንቲባ አዳነች አበቤ ዶ/ር ዐቢይ የሚመሩትን የህክምና ማእከል ጎበኙ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ እና የከተማዋ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ በኢሊት የአንገት በላይ ቀዶ ህክምና ማእከል የሥራ ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱ ወቅት ክብርት ከንቲባዋና የጤና ቢሮ ሀላፊው በማእከሉ እየተከናወኑ ያሉ የህክምና አገልግሎቶችን ተመልክተዋል።
የማእከሉ መስራች ዶ/ር ዐቢይ ታደሰ ለከንቲባዋና ለልዑካን ቡድኑ ባደረጉት ገለጻ፣ ለተቋሙ ላሳዩት ድጋፍና ማበረታቻ በራሳቸውና በስራ ባልደረቦቻቸው ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ አይነቱ የከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ጉብኝት በጤናው ዘርፍ ለሚሰማሩ የግል የህክምና ተቋማት ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #addisababa #ethiopia #elitemedicalcenter #healthsector #adanechababe #dryohanneschala #medicalnews #healthcare #ethiopianhealth

3 months ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጋሞ ዞን የአደጋ ቀጠና ተገኝተው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገር ቤት እንደተመለሱ፣ በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለመግለጽና ድጋፎችን ለመከታተል በቀጥታ ወደ አርባ ምንጭ አቅንተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ እና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የዜጎች ሕይወት በማለፉና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት በመድረሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ወቅት በአርባ ምንጭ በመገኘት እየተከናወኑ ያሉ የነፍስ አድንና የድጋፍ ሥራዎችን በቅርበት እየገመገሙ ይገኛሉ።
መንግሥት ለተጎጂ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም ተግባራትን በቅንጅት እያከናወነ እንደሚቀጥልም በጉብኝታቸው ወቅት ገልፀዋል።
ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዝናብ ወቅት መሰል አደጋዎችን ለመከላከል ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
በአሁኑ ወቅት በመንግሥትና በበጎ ፈቃደኞች የተቀናጀ የድጋፍ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልፇል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታወቁ።
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የመከሩ ሲሆን፣ በተለይም በመተማመን ላይ የተመሠረተ የኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማስፈን ላይ ትኩረት አድርገዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት "የጸና ወዳጅነት" መሆኑን ገልጸዋል።
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የመከሩ ሲሆን፣ በተለይም በመተማመን ላይ የተመሠረተ የኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማስፈን ላይ ትኩረት አድርገዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት "የጸና ወዳጅነት" መሆኑን ገልጸዋል።
Sponsored by
Surafel
3 months ago
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስልታዊ ትብብራቸውን ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋገሩ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (UAE) መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጥበቅ የሚያስችል ከፍተኛ የሁለትዮሽ ውይይት በአቡ ዳቢ ተካሂዷል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሥራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን መሪ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ክቡር ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተገናኝተው መክረዋል። በውይይቱም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን "በመተማመን ላይ የተመሰረተ" ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ስልታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የውይይቱ ዋነኛ የትኩረት ነጥቦች፦
* ሁለንተናዊ ትብብር፦ በኢኮኖሚ፣ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ።
* የጋራ ተጠቃሚነት፦ የሁለቱን አገራት ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በጋራ መተግበር።
* ቀጣናዊ ሰላም፦ በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማስፈን በትብብር መስራት።
* አዲስ ምዕራፍ፦ ጉብኝቱ በሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።
ልዑካን ቡድኑ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ለፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ውይይቱ ለቀጣይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ጠንካራ መሰረት የጣለ መሆኑ ተነግሯል።
#ethiopia #uae #diplomacy #sheikhmohamedbinzayed #economicties #addisababa #abudhabi #strategicpartnership #regionalpeace

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት ዓረብ ኤሜሬቶች የሥራ ጉብኝት ጀመሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሥራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ ላይ አቡ ዳቢ፣ ዩናይትድ ዓረብ ኤሜሬቶች ገብተዋል።
በቆይታቸውም በሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ከኤሜሬቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በኤሜሬቶች ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

🇩🇰 የዴንማርክ አምባሳደር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያደረጉት ጉብኝት
#ethiopia | በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም (March 5, 2026) በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።
የጉብኝቱና የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
፩. የሪፎርም ሥራዎችና ዲጂታላይዜሽን
የአምባሳደሩ ዕይታ፦ አምባሳደር ሱን ክሮግስትረፕ ፍርድ ቤቱ እያከናወናቸው ያሉ የለውጥ ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም የዳኝነት ሥርዓቱን ግልጽነትና ተጠያቂነት ለማስፈን እየተሰራ ያለው የዲጂታላይዜሽን (Digitalization) ሥራ ለፍትሕ ሥርዓቱ መጠናከር ትልቅ እመርታ መሆኑን ጠቅሰዋል።
መሠረተ ልማት፦ አምባሳደሩ በፍርድ ቤቱ የተገነቡ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን በአካል ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
፪. የሁለትዮሽ ትብብርና ሥልጠና
የፕሬዝዳንቱ መልዕክት፦ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ በኢትዮጵያና በዴንማርክ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት በፍትሕ ዘርፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።
ምስጋና፦ በዴንማርክ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም (Danish Institute for Human Rights) አማካኝነት ለኢትዮጵያ ዳኞች ለተሰጠው የሙያ ሥልጠና ኤምባሲው ላደረገው አስተዋጽኦ ፕሬዝዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።
፫. የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ
ዴንማርክ በኢትዮጵያ በበርካታ ዘርፎች ላይ በጋራ እየሰራች መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ በቀጣይም ከፍርድ ቤቶች ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና በትብብር ለመሥራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ምንጭ፦
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
#ኢትዮጵያ #ዴንማርክ #ፍትሕ #ፌዴራልጠቅላይፍርድቤት #ዲጂታላይዜሽን #ethiopia #denmark #justicereform #digitaljudiciary #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዘርባጃን ገቡ
#ethiopia | በኢትዮጵያና በአዘርባጃን መካከል በየጊዜው እያደገ የመጣውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ የሚገኘው ሄዳር አሊዬቭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የጉብኝቱ ትኩረትና ፋይዳ
ይህ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያና በአዘርባጃን መካከል ያለው ቅርርብ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በዲፕሎማሲያዊ መድረኮች ጎልቶ የታየ ሲሆን፣ የዛሬው ጉብኝትም የዚሁ ስኬታማ ትብብር ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
በቆይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዘርባጃን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል አዳዲስ የኢኮኖሚና የቴክኒክ ትብብር መስኮችን ለመክፈት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርም ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች ይጠቁማሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #አዘርባጃን #ዲፕሎማሲ #ዐቢይ_አሕመድ #ባኩ #የሥራ_ጉብኝት #ethiopia #azerbaijan #diplomacy

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጋር ተወያዩ
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ፣ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር እንዲሁም ከ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጋር ፍሬያማ ውይይቶችን አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንቱን ተቀብለው ባደረጉት ውይይት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በጥልቀት መርምረዋል። ውይይቱ በዋናነት በጋራ ፍላጎቶች ላይ ተመስርቶ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ በበኩላቸው የእስራኤሉን ፕሬዚዳንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው ምክክር በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ታሪካዊ እንዲሁም ባህላዊ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
በአጠቃላይ የፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ የዛሬው የኢትዮጵያ ጉብኝት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት እና ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።
EBC

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ተወያዩ
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡትን የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግን በቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ምክክር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይቱን "ፍሬያማ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ትኩረቱም በሁለቱ አገራት የጋራ ፍላጎቶችና የትብብር መስኮች ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የሁለትዮሽ ግንኙነት፦ የኢትዮጵያና የእስራኤልን የቆየ ግንኙነት በዲፕሎማሲና በኢኮኖሚ መስኮች ይበልጥ ማጠናከር።
* የትብብር መስኮች፦ በሁለቱም አገራት የወል ፍላጎት ላይ ተመሥርቶ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
* ቀጣይነት፦ የፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።
ይህ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ትስስር ይበልጥ እንደሚያሳድገው ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #እስራኤል #ዲፕሎማሲ
#ዐቢይ_አሕመድ #አይዛክ_ሄርዞግ #ethiopia #israel #diplomacy

4 months ago
የቱርክዬው "ቶግ" (Togg) የኤሌክትሪክ መኪና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስጦታ ተበረከተ
የቱርክዬው ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በቱርክዬ የቴክኖሎጂ ዕድገት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውንና የሀገሪቱ ኩራት የሆነውን "ቶግ" (Togg) የኤሌክትሪክ መኪና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስጦታ አበርክተዋል።
ይህ ስጦታ ከመኪናነቱ ባለፈ በኢትዮጵያና በቱርክዬ መካከል ያለውን የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ቴክኖሎጂና ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ አጋርነት ማደጉን የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ተደርጎ ተወስዷል።
ስጦታ የተበረከተው መኪና ዝም ብሎ ተራ ተሽከርካሪ ሳይሆን ቱርክዬ በዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ያመረተችው የመጀመሪያው ሀገር በቀል ዘመናዊ መኪና ነው።
መኪናው ሙሉ በሙሉ በቱርክዬ መሐንዲሶች የተቀረጸና የተገነባ ሲሆን የቱርክዬን የኢንዱስትሪ ብቃት ለዓለም ያስተዋወቀ ፕሮጀክት ነው።
ቶግንከመኪናነት ባለፈ እንደ ተንቀሳቃሽ ስማርት መሣሪያ (Smart Device) ነው የሚታየው የላቀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂና የኢንተርኔት ግንኙነት ሥርዓት የተገጠመለት ነው።
ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ በመሆኑ ልክ እንደ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማትንና የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ለሚያበረታቱ ሀገራት ተመራጭ ያደርገዋል።
የመኪናው ውጫዊ ገጽታ የቱርክዬን ባሕላዊ ቅርሶች (ለምሳሌ የቱሊፕ አበባን) ከዘመናዊ ምቾት ጋር አጣምሮ የያዘ ውበት አለው።
ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ይህንን መኪና ለወዳጅ ሀገራት መሪዎች በስጦታ መስጠታቸው የቱርክዬን የቴክኖሎጂ አጋርነት ፍላጎት ያሳያል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን እንድታሳካ ወዳጅ ሀገራት ጫና እንዲያደርጉ ከፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ጋር ከመግባባት ደርሰናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*
130 ሚሊዮን ሕዝብ የባሕር በር አጥቶ መኖር ፍትሐዊ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ደባ የባሕር በር ተዘግቶባት መቆየቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሀገሪቱ የመልክዓ ምድር እስረኛ ሆና መቆየቷ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነም አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
እንደ ቱርክዬ ያሉ ወዳጅ ሀገራት አስፈላጊውን የዲፕሎማሲ ጫና በመፍጠር፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን በሰላማዊ መንገድ እንድታሳካ ድጋፍ እንዲያደርጉ ከፕሬዚዳንት ኤርዶዋን ጋር በጥልቀት መወያየታቸውን ጠቅሰዋል።
ሎጂስቲክስ እና የባሕር በር ለኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና ወሳኝ መሆናቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን በዚህ ረገድ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸው፤ ለተደረገው ውጤታማ ውይይትም ምስጋና አቅርበዋል።

የቱርክዬው ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለመጀመር አዲስ አበባ ገብተዋል። ለፕሬዝዳንቱና ለልዑካን ቡድናቸውም በኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት በቱርክዬ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ እና ታሪካዊ የአጋርነት ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል። በቆይታቸውም ከአንካራ እስከ አዲስ አበባ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ እና በሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት መካከል ዘላቂ ትስስርን የሚያረጋግጡ ውጤታማ ውይይቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ለፕሬዝዳንቱ ባደረገችው የእንኳን ደህና መጡ ጥሪ፣ ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ዳግም የሚያረጋግጥ መሆኑን አመልክታለች። በሁለቱ መሪዎች መካከል የሚደረገው ምክክር በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እና በቀጣናዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩርም ታውቋል።

የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ለታሪካዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
#ethiopia | ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየና የጠነከረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተጠቁሟል።
የመሪዎቹ መልዕክት እና የጉብኝቱ ፋይዳ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገጹ ባሰፈሩት መልዕክት፣ የፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን "ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ" የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
"በአንካራ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክሩ እና ዘላቂ ትስስርን የሚያረጋግጡ ውጤታማ ውይይቶች እንዲኖሩን እመኛለሁ።" — ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፦
* ኢኮኖሚያዊ ትስስር፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ልውውጥ ማሳደግ።
* ስትራቴጂካዊ አጋርነት፦ በምሥራቅ አፍሪካ እና በዩራሺያ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት።
* ፖለቲካዊ ውይይት፦ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያላቸውን መግባባት ማጠናከር።
ይህ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከአጋር ሀገራት ጋር የምታደርገውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያሰፋውና ለቀጣናው መረጋጋትም ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ቱርክዬ #ዐቢይአሕመድ #ረጀብጠይፕኤርዶዋን #ዲፕሎማሲ #አዲስአበባ #pmabiy #erdoğan #ethiopiaturkiye #diplomacy

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን አዲስ አበባ ገቡ
የቱርክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብዣ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብተዋል። ይህ ጉብኝት ፕሬዝዳንቱ ከአስር ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጀመሪያቸው ነው።
የጉብኝቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ታሪካዊ ምዕራፍ፦ ጉብኝቱ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 100ኛ ዓመትን ለማክበር የታለመ ነው። በ16ኛው ክፍለ ዘመን የጀመረው የታሪክ ግንኙነት አሁን ላይ ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማደጉ ተገልጿል።
የኢኮኖሚና የጸጥታ ትብብር፦ ቱርክ በኢትዮጵያ ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስትመንት ያላት ሲሆን፣ በዛሬው ውይይት በንግድ፣ በመሠረተ ልማት እና በጸጥታ ዘርፎች ላይ አዳዲስ ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቀጣናው መረጋጋት፦ ጉብኝቱ በአፍሪካ ቀንድ ካለው ወቅታዊ ውጥረት እና ቱርክ በቀጣናው ካላት የዲፕሎማሲያዊ ሽምግልና ሚና ጋር የተቆራኘ ነው የሚሉ ምሁራን አሉ።
የኢትዮጵያ መንግስታዊ መገናኛ ብዙኃን ፕሬዝዳንቱን "የአዲሷ ቱርክ መሐንዲስ" በማለት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ጥንካሬ ሲያጎሉ፤ ገለልተኛ ተንታኞች ግን ቱርክ በቀይ ባሕር እና በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ ለማስፋት የምታደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ይገልጹታል።
የመሪዎቹ መልእክት፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዝዳንቱ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጡ መልእክት፣ "ይህ የጉብኝት ልውውጥ በሁለቱ ጥንታዊ አገራት መካከል ያለውን የጸና አጋርነት የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
በቱርክ በኩልም ግንኙነቱ "ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት" በግልጽነት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ለሁለቱም ወገኖች ጠቃሚ እንደሆነ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያን የትምህርት ቴክኖሎጂ ለማጠናከር የሚያግዝ መድረክ ተካሄደ!
#fastmereja I ሪች ፎር ቼንጅ የተሰኘ ተቋም ያዘጋጀውና የሀገሪቱን የትምህርት ቴክኖሎጂ (EdTech) ሥነ-ምህዳር ለማጠናከር ያለመ ከፍተኛ የሥራ ጉብኝትና የፈጠራ ውጤቶች የቀረቡበት መድረክ በዛሬዉ እለት ተካሂዷል።
በመድረኩ ባለሀብቶችን እና የስነ-ምህዳር ተዋናዮችን በመሰብሰብ በዲጂታል ትምህርት፣ በፈጠራ መር ሥራ ፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ላይ በተመሰረቱ መፍትሄዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በዘርፉ የተመረጡ ኢትዮጵያውያን የትምህርት ቴክኖሎጂ (EdTech) ሥራ ፈጣሪዎች የትምህርትን ተደራሽነት፣ ጥራትና ፍትሃዊነት ለማሻሻል የቀረጹዋቸውን የፈጠራ መፍትሔዎች ለባለሀብቶችና ለፖሊሲ አውጭዎች አቅርበዋል።
እንዲሁም በዲጂታል ትምህርት፣ በኢኖቬሽንና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ዙሪያ በሚመለከታቸው አካላት መካከል ሰፊ የልምድ ልውውጥና የኔትወርክ ትስስር ተደርጓል።
መድረኩ የኢትዮጵያን የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የቴክኖሎጂና የዓለም አቀፍ አጋርነት ያለውን ሚና ያጎላ እንደሆነ ተገልጿል።
ከፍተኛ የስዊድን የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት መሠረት በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ፣ የሪች ፎር ቼንጅ ዓለም አቀፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሶፊያ ብሬትሆልትዝ፣ በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምባሲ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት መሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ሪች ፎር ቼንጅ (RFC) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱ በስቶክሆልም፣ ስዊድን ያቋቋመ ነው፡፡

❗️ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያና በግብፅ ወሳኝ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ከነገ ጥር 16 ጀምሮ ለሰባት ቀናት በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተቋማቸው አስታውቋል።
🔍 የጉብኝቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች፦
🇪🇹 በኢትዮጵያ (አዲስ አበባ)፦
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በመገናኘት በክልላዊ ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።
የአሜሪካ የግል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን የንግድ ተሳትፎ የሚያሳድጉበትን ዕድል ያመቻቻሉ።
ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በመሆን በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና በንግድ ትብብር ዙሪያ ይወያያሉ።
🇪🇬 በግብፅ (ካይሮ)፦
በካይሮ ከሚገኙ አሜሪካውያን ባለሀብቶች ጋር የሚመክሩ ሲሆን፣ የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ግንኙነት ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።
🇰🇪 በኬንያ (ናይሮቢ)፦
በጸረ-ሽብርተኝነት ትብብር፣ በንግድ እና ኬንያ በሄይቲ እያደረገችው ስላለው የሰላም ማስከበር ሚና ሰፊ ውይይት ይደረጋል።
🇩🇯 በጅቡቲ፦
በቀይ ባህር አካባቢ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ እና በሽብርተኝነት መከላከል ዙሪያ ከመሪዎች ጋር ይመክራሉ።
ልዑኩ መጀመሪያ ካይሮን መርገጡና በመቀጠል ወደ አዲስ አበባ ማቅናቱ፣ አሜሪካ በግድቡ ኢትዮጵያና ግብፅን በትራምፕ አማካኝነት ለማሸማገል የመጀመሪያው ሂደት ሊሆን ይችላል ተብሏል።

5 months ago
🇪🇹🇩🇯 ኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ቀጠናዊ ንግድን ልታሳድግ መሆኑን የጅቡቲው ባለሥልጣን ገለፁ
💱 ይህ እንቅስቃሴ ሀገሪቱ የውጭ ምርቶችን ከማስገባት ይልቅ ወደ ውጭ በመላክ ላይ ወደተመሰረተ የምጣኔ ሀብት ሞዴል ለማሸጋገር ያላትን ስትራቴጂያዊ እቅድ የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉ የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለሥልጣን ኃላፊ አብዲቃድር ኡመር ሀዲ ለጂቡቲ ሚዲያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አሳውቀዋል፡፡
"ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን በመቀነስ የምትልከውን ለመጨመር ትሻለች፡፡ አንድ ሀገር ከፍጆታዋ በላይ ስታመርት ኢኮኖሚዋ እየጠነከረ ይሄዳል" በማለት ጅቡቲ ለውጡን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አብዲቃድር ተናግረዋል።
🚢 ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 1.8 ሚሊየን ቶን የግብርና ማዳበሪያ ታስገባለች ያሉት ባለሥልጣኑ፣ አሁን ግን የነዳጅ ምርቶችን እና የግብርና ግብዓቶችን ወደ ውጭ ለመላክ አቅዳለች፤ ጅቡቲም ቀዳሚ የሎጂስቲክስ መተላለፊያ ሆና ታገለግላታለች ብለዋል።
ከሰሞኑ ወደ ጅቡቲ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶራሌህ ሁለገብ ወደብ እና የሆራይዘን ነዳጅ ተርሚናልን ጎብኝተዋል፡፡
Sputnik