9 days ago
የኢቢሲ የለውጥ ሥራዎች አገርን የሚጠቅሙና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጸባርቁ ናቸው፦ ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን
*****************************
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እያከናወናቸው ያሉ ሁለንተናዊ የለውጥ ሥራዎች ለሀገር የሚበጁና እውነተኛውን ኢትዮጵያዊነት የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን ገለጹ።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ እና የሊቃውንት (ኡለማዎች) ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።
አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት የተቋሙን ታሪክ፣ የወቅታዊ ይዘት ዝግጅቶችን፣ የተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎችን እንዲሁም ተቋሙ ዘመኑን በዋጁ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች ራሱን እያደራጀ መሆኑን በአካል ተመልክተዋል።
ሼህ አብዱልከሪም በሰጡት አስተያየት፣ ኢቢሲ በውስጣዊ አደረጃጀቱም ሆነ በሚሠራቸው የሚዲያ ሥራዎች ኢትዮጵያዊነትን በተግባር የሚያንጸባርቅ ትልቅ ተቋም መሆኑን መታዘባቸውን ገልጸው፣ ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ እነዚህ የለውጥ ሥራዎቹ ተቋሙን "የኢትዮጵያ ራስ" አድርገውታል ብለዋል።
ምክር ቤቱ ለአዲሱ ትውልድ ጠቃሚ የሆኑ አገራዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቅርበትና በትብብር ለመሥራት ሙሉ ፈቃደኛና ዝግጁ መሆኑንም ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን በዚህ አጋጣሚ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መላው ሕዝበ ሙስሊም መጪውን ታላቁን የዒድ አል-አድሐ (ዓረፋ) በዓል ሃይማኖታዊ አስተምህሮውን በጠበቀ መልኩና በተለመደው ውብ የኢትዮጵያዊ የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴት እንዲያከብረው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በዘሃራ መሀመድ
#ethiopia #ebc #islamicaffairs #mediareform #ethiopianism #eidaladha