Logo
YenetaTube
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ አዲስ አበባ ለገቡት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት “የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ወንድሜ ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራት እና ደስታ ነው” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሦስተኛው ይፋዊ የሥራ ጉብኝትዎ በፈረንሳይና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጸና ወዳጅነት ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል።

‎”ወሳኝ እና ፍሬያማ በሆኑ ውይይቶች ላይ ትኩረት በምናደርግበት በዚህ ወቅት አንድ ነገር እርግጥ ነው፤ እርሱም በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ያለው ትስስር ይበልጥ እየጠነከረ ብቻ የሚዘልቅ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት።
#ebc

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.