24 days ago
እንግሊዝ ለግማሽ ፍፃሜው ደረሰች
*******************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ እንግሊዝ ኖርዌይን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜው ደርሳለች።
ከሌሊቱ 6 ሰዓት የተጀመረው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በደበኛው ሰዓት (በ90 ደቂቃ) 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
አንድሪያስ ሼልድረፕ ኖርዌይን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ በ36ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ጁድ ቤሊንግሃም እንግሊዝን 45+2 ደቂቃ ላይ አቻ አድርጓል።
መደበኛ ሰዓቱ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ያመሩ ሲሆን ጁድ ቤሊንግሃም እንግሊዝን አሸናፊ ያደረገችውን ግብ 93ኛ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በዓለም ዋንጫው ለሀገሩ የመጀመሪያ ተሳትፎ እያደረገ ያለው ጁድ ቤሊንግሃም እስካሁን ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ሲያስቆጥር አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
#ebc #ebcsport #worldcup #worldcup2026 #england

1 month ago
የማራካና ስታዲየሙ ልብ ሰባሪ ትዕይንት ለብራዚል
**************
ዓለም ዋንጫ አራት ዓመታቱን ጠብቆ በተመላለሰ ቁጥር ከሚታወሱ ክስተቶች አንዱ ይህ ነው። ብራዚልን ከ ኡራጓይ ያገናኘው የ1950 ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ።
በአንድ ስታዲየም ውስጥ ይህን ያህል ሰው ይታደማል ብሎ ለማሰብ የራቀ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ከብራዚላውያኑ የእግር ኳስ ታሪክ መቼቶች አንዱ የሆነው ማራካና የዚያን ዕለት ከ170,000 በላይ ሰዎችን ማስተናገዱ ይነገራል።
እንደውም ይህ ግምታዊ እንጂ ቁጥሩ ወደ 200,000 ሊያሻቅብ ይችላል ተብሎም ተፅፏል።
ያን ዕለት ሪዮ ዲጄኔሮ በማጀቷም በጎዳናዎቿም በተስፋ የጠበቀችውን የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ድሏን የጨበጠች ያህል በደስታ ተውጣለች። ተስፋን በቀላቀለ ደስታ። በዛ ጨዋታ ለ'ሴልሳኦዎ'ቹ ሻምፒዮን ለመሆን የአቻ ውጤት በቂያቸው ነበር።
በእርግጥም በሁለተኛው አጋማሽ ፍሪያካ ለብራዚል ያስቆጠራት ግብ ያን ሁሉ ጥበቃ ተጨባጭ፤ ተስፋዋንም አረጋጋጭ አስመስላ ነበር።
ሆኖም በደቂቃዎች ልዩነት ሁዋን አልቤርቶ ሺያፊኖ ያስቆጠራት የአቻነት ግብ የብራዚሎችን ሻምፒዮንነት የምታሳጣ ባትሆንም፣ የሰማያዊዎቹን ተስፋ አለምልማለች።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ 11 ደቂቃዎች ሲቀሩ አልሲደስ ጊጊያ ያስቆጠራት ግብ ሁሉንም ነገር ቀየረች። ማራካና ሰው የሌለበት ይመስል በጥልቅ ዝምታ ተዋጠ፤ ፀጥ ረጭ አለ።
ተጫዋቾች በሽንፈት ሜዳውን ለቀው ሲወጡ፤ ድፍን ሀገር ብዙ ጠብቆ ነበርና የሆነውን ባለማመን ሀዘኑን ይገልፅበት መንገድ ጠፋው። የሆነው ጉም የመዝገን ያክል የማይጨበጥ፤ አግኝቶ የማጣት ያክል መራራ ነበር።
ግዙፉ ማራካና ስታዲየም እግር ኳስ የተጠበቁት ብቻ ሳይሆኑ አንዳንዴ ከዓይን የማይገቡት፣ ግምትም የማይሰጣቸው ድል የሚነሱበት ስፖርት እንደሆነ እማኝ ሆነ። ከ76 ዓመታት በፊት የተከሰተው 'ማራካናዞ' የማራካናው ስብራት ዛሬም እየታወሰ ቀጥሏል።
ብራዚል በዚያ ልብ ሰባሪ ሽንፈት ወድቃ አልቀረችም። ስምንት ዓመታት ጠብቃ የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫዋን አነሳች። አምስት ጊዜም ደጋግማ አሸንፋ በምድር ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ የስኬት ምሳሌ ሆነች። እግር ኳስ በስማቸው ቢጠራ የማያንሱ እልፍ ክዋክብትን ለዓለም አበረከተች።
ዓለም ዋንጫ ከድል እና ሽንፈት ዜናዎች የሚሻገሩ ታሪኮችን ያጨቀ የትዝታ አውድማ፤ ወድቆ የመነሳትን ምሳሌ ገሀድ የሚያደርግ ትዕምርት ነው። በዘመን ሳይደበዝዝ፤ በጊዜ ርዝማኔ ሳያረጅ አሁንም ቀጥሏል።
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ #ebcsport #football #brasil

u126041 u12a0u1218u1271u121d u12a5u1305 u12ebu120du1230u1320u12c9 u12aeu12aeu1265
https://youtu.be/juVfrT8Fj... #worldcup #cr7 #ebcsport #u12a0u1208u121du12cbu1295u132b ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
በ41 አመቱም እጅ ያልሰጠዉ ኮኮብ
https://youtu.be/juVfrT8Fj... #worldcup #cr7 #ebcsport #አለምዋንጫ
2 months ago
ሊቨርፑል እና ፒኤስጂ ለማስፈረም የሚፎካከሩበት ተጫዋች አይቮሪኮስታዊው ኮከብ ያን ዲዮማንዴ
https://youtu.be/7VN4DsSwl... #ebcdotstream #ebcsport
Sponsored by
Surafel
2 months ago
የአለም ዋንጫ ሁለተኛ ጨዋታዎች ቀጥለዋል አንዶኒ ኢራዮላና ሚኬል አርቴታ በዝዉዉሩ ምን እያሰቡ ነዉ! #ebcsport #worldcup2026 #football #ebcdotstream #etv #sports
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
2 months ago
የኬፕ ቨርዴ የመከላከል ጥበብ
#ebcsport #worldcup2026 #football #sports
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
#ebcsport #worldcup2026 #football #sports
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
3 months ago
"የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ዘመን እየመጣ ነው" :- ጆን ሪጅን
#ethiopia | የዓለም አትሌቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆን ሪጅን እና የጨረታዎች፣ ውድድሮችና ሁነቶች ዳይሬክተር ማርክ ኸረስት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አከናውነዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ በቆይታቸው ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ግንባታው በመከናወን ላይ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ፣ ለስፖርቱ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸውን አስመልክተው መግለጫ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጆን ሪጅን፤ "ከ25 ዓመታት በፊት ለታላቁ ሩጫ አዲስ አበባ መጥቼ ነበር፤ አሁን ግን ከተማዋ እጅግ ተለውጣለች፣ በሚገርም ሁኔታም ዘምናለች" ብለዋል።
በተመለከቷቸው መሠረተ ልማቶችና ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች እጅግ መደሰታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ "የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ቀን እየመጣ ነው" ሲሉ ያላቸውን ታላቅ ተስፋ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን በበኩላቸው፤ የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት እያሳዩ ላለው ድጋፍና ማበረታቻ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ የ2028 "አልቲሜት" ሻምፒዮንሽፕ እና የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ከግብ ለማድረስ፣ ፌዴሬሽኑ ከዓለም አትሌቲክስ ጋር በቅርበትና በትብብር እየሠራ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #ebcsport #ethiopia #ebc #ኢትዮጵያ #አትሌቲክስ #ፌዴሬሽን

12 months ago
ይሄ ጠለፋ ሳይሆን የአንድ ሰው የፍቅር ታሪክ ነው::
ታሪክ የቀየረችው የኤዜ የስልክ ጥሪ
#ethiopia | አርሰናል ድምጹን አጥፍቶ ከፈጸማቸው ትልልቅ ዝውውሮች ምን አልባትም ይሄኛው ቀዳሚ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ኤቤሬቺ ኤዜ ከክሪስታል ፓላስ ወደ አርሰናል ያመራበት፡፡
እንግሊዛዊው ሁለ ገብ ተጫዋች በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ስሙ ከአርሰናል ጋር ሲያያዝ ቢቆይም በመድፈኞቹ በኩል ያለው ፍላጎት እየቀዘቀዘ መምጣቱን ተከትሎ ቶተንሀም ዝውውሩን ገፍቶበታል፡፡
እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ከሰኔ ወር ጀምሮ ከኤዜ ጋር በቅርበት በዝውውሩ ጉዳይ ሲያወራ ቆይቷል፡፡ የለንደን ተወላጁ ኤቤሪቺ ኤዜ እግር ኳስን የጀመረው በአርሰናል ቤት ነው፡፡ ለዚህ ክለብ የተለየ ፍቅር እንዳለው በተደጋጋሚ ሲናገር ይሰማል፡፡ ይሄንኑም ለክለቡ ያለውን ክብር ለሚካኤል አርቴታ ሲያስረዳም ቆይቷል፡፡
ኤቤሬቺ ኤዜ እግር ኳስን በአርሰናል አካዳሚ ቢጀምርም የ13 አመት ልጅ እያለ የአካዳሚው መልማዮች በወቅቱ ከእሱ የተሻሉ ታዳጊዎችን በማግኝታቸው እንዲቀነስ ሆነ፡፡ የለንደን ተወላጁ የያኔው ታዳጊ አርሰናልን እየወደደውም ቢሆን ለመለየት ተገደደ፡፡ በዚሁ ምክንያት ለተወሱኑ ቀናቶች ድብርት ውስጥ ገብቶ እንደነበርም ተዘግቧል፡፡
ከዚህ በኋላ ራሱን ለማግኝት ፉልሀም፣ ሪዲንግ፣ ሚልዋል፣ ኩይንስ ፓርክ ሬንጀርስ እና ወይኮምብ ወንድረስ ከቋሚነት እስከ ውሰት ያሳለፈባቸው ክለቦች ሆኑ፡፡ 2020 ላይ ግን ክሪስታል ፓላስ ኤዜን ከኪው ፒ አር በቋሚነት አስፈረመው፡፡ በሌላኛው የለንደን ክለብም ኤቤሬቺ ኤዜ ምርጥ መሆኑን አስመሰከረ፡፡
ሁለገቡ ተጫዋች በፓላስ ባሳየው ድንቅ ብቃት የበርካታ ክለቦች ትኩረት ሆነ፡፡ የእሱ ፍላጎት ግን በአውሮፓ ሻምፒንስ ሊግ የሚሳተፍ ከምንም በላይ ደግሞ ከእግር ኳስ ጋር የተዋወቀበት የልጅነት ክለቡ አርሰናል ነው፡፡ የአርሰናል ዝውውር ካልተሳካ የአርሰናል የምንጊዜም ተቀናቃኝ ወደ ሆነው ቶተንሀም ማምራት 2ኛ እቅዱም ሆነ፡፡
የቶተንሀሙ አማካይ ጄምስ ማዲሰን የጉልበት ጅማት መበጠስ ጉዳት ማስተናገዱ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ኤዜን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ወስደዋል፡፡
አርሰናል ኤዜ ላይ ያለው ፍላጎት በተጠበቀው ልክ አለመሄዱን ተከትሎ በክሪስታል ፓላስ እና በቶተንሀም መካከል ያለው ድርድር ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ፡፡ የተጫዋቹም ወደ ነጭ ለባሾቹ ቤት የማምራት ዕድሉ በዚያው ልክ የተቃረበ ሆኗል፡፡
ከክለቦቹ ስምምነት በኋላ የ27 አመቱ ኤቤሬቺ ኤዜ ባለፈው ረቡ ፊርማውን ለቶተንሀም ለማስቀመጥ ቀጠሮ የያዘበት ዕለት ሆነ፡፡
ከዚህ በኋላ አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡
ኤቤሬቺ ኤዜ ፊርማውን ለቶተንሀም ከማስቀመጡ በፊት የመጨረሻ እድሉን ለመሞከር ለአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ አንድ ስልክ ደወለ፡፡
“ለቶተንሀም ልፈርም ነው ወደ አርሰናል የምመጣበት ዕድል አብቅቷል ወይ የሚል መልዕክት ነበር”፡፡ ይቺ የመጨረሻ ስልክ ብዙ ነገሮችን የቀየረች እና ኤዜን ከልጅነት ክለቡ ጋር በድጋሜ እንዲገናኝ ትልቁን በር የከፈተች ሆነች፡፡
ሚካኤል አርቴታም የካይ ሀቨርዝን ጉዳት በተመለከተ ከቦርዱ ጋር ስብሰባ አድርጎ ስለበር በጀርመናዊው አጥቂ ቦታ ሌላ ሰው በማስፈለጉ ኤቤሬቺ ኤዜ በአርሰናል የሚፈለገው ሰው ሆነ፡፡
በሦስት ቦታ የሚጫወተው ኤዜም ለቶተንሀም የመፈረም ሃሳቡን በብርሀን ፍጥነት ቀይሮ ወደ አርሰናል ለማምራት ይሁንታውን ገለጸ፡፡ ረቡዕ ዕለት ለቶተንሀም ይፈርማል የተባለው ኤዜ የዚያኑ ቀን ሁሉንም ነገር ከአርሰናል ጋር ጨረሰ፡፡
ይሄ ዜና ከተሰማ በኋላ ወትሮም ከጎረቤታቸው አርሰናል ጋር በትልቅ ተቀናቃኝነት የሚተያዩት የቶተንሀም ደጋፊዎች እና የስራ ሃላፊዎች አስደንጋጩን ነገር ከመቀበል ውጭ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡
የ27 አመቱ ኤዜም በድጋሜ ወደ አርሰናል ለመመለስ የመድፈኞቹ ተጫዋቾችን ጭምር ለማሳመን ያደረገው ጥረት ተሳክቶለት ከ14 አመታት በኋላ ወደ ኢምሬትስ ተመለሰ፡፡
የቶተንሀም ሰዎችን ጨምሮ ብዙዎች አርሰናል ተጫዋቹን ከቶተንሀም ሆትስፐር እንደ ጠለፈው ሊያስቡ ይችላሉ ነገር ግን ይሄ ኤቤሬቺ ኤዜ ለአርሰናል መለያ ያለውን ፍቅር እስከ መጨረሻው ሰአት ያሳየበት እና ያሳካበት የፍቅር ታሪክም ሆነ፡፡
ምሽት አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 5 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ከደጋፊዎቹ ጋር ሲተዋወቅ ፊቱ ላይ የሚታየውም ደስታ የዚሁ ማሳያ ነበር፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#arsenal #eze #ebcsport

1 year ago
በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ ለፍጻሜ ደረሰች
#ethiopia | ለ13ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ሞሮኮ ጋናን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ ደረሰች፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛ 90 ደቂቃውን አንድ አቻ አጠናቀዋል፡፡ ኡዝራዎይ ለሞሮኮ ንያምክያ ደግሞ ለጋና ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተጨመረው 30 ደቂቃ ግብ ባለመቆጠሩ በተሰጠው መለያ ምት ሞሮኮ 4 ለ 2 አሸንፋለች፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ በተከታታይ ለፍጻሜ የደረሰችበትን ውጤት አስመዝግባለች፡፡
እሑድ በሚደረገው ፍጻሜ ሞሮኮ ከ9 ጊዜ ሻምፒዮኗ ናይጄርያ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡
በአንተነህ ሲሳይ
#africa #ebcsport #morroco

Comments