4 months ago
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የአሥር ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በአልጄሪያ ጀመሩ
#ethiopia | የቫቲካኑ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በአራት የአፍሪካ አገራት የሚያደርጉትንና አሥር ቀናት የሚፈጀውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት በአልጄሪያ ጀምረዋል።
ቅዱስነታቸው በአልጄሪያ መዲና ሲደርሱ በፕሬዝዳንት አብደልማጅድ ተቡኔ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በመጀመሪያው ቀን ውሏቸውም አልጄሪያ ለነፃነቷና ለሉዓላዊነቷ ባደረገችው ተጋድሎ ለወደቁ ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ እውነተኛ ሰላም የፍትህና የክብር መገለጫ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ሊረጋገጥ የሚችለው በይቅርታ ብቻ እንደሆነ አሳስበዋል።
ቅዱስነታቸው በአልጄሪያ፣ በካሜሩን፣ በአንጎላና በኢኳቶሪያል ጊኒ የሚገኙ 11 ከተማዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቫቲካን ከፍተኛ ባለሥልጣን ካርዲናል ማይክል ቼርኒ እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ ከ20 በመቶ በላይ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በሚኖሩባት አፍሪካ ላይ የዓለምን ትኩረት ለማሳረፍ ያለመ ነው።
በጉዟቸው ወቅት ሰላም፣ ስደት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የወጣቶችና የቤተሰብ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚመክሩ ታውቋል።
ይህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት በአህጉሪቱ ካሉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመለማመድ ባለፈ፣ አፍሪካ አሁን ላይ ለምትገኝባቸው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የቫቲካንን አጋርነት ለማሳየት ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #channeltv #vatican #popeleoxiv #africatour #algeria #cameroon #angola #equatorialguinea #peace #catholicchurch #ርዕሰሊቃነጳጳሳት #አፍሪካ #ሰላም #ቫቲካን

Comments